The Law Office of Nesredin Abubeker/ ነስረዲን አቡበከር የህግ ቢሮ

The Law Office of Nesredin Abubeker/ ነስረዲን አቡበከር የህግ ቢሮ Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from The Law Office of Nesredin Abubeker/ ነስረዲን አቡበከር የህግ ቢሮ, Lawyer & Law Firm, Addis Ababa. Lideta Area, Addis Ababa.

Established:2015
The Law Office of Nesredin Abubeker
With a wealth of experience spanning nearly a decade, our office has built a reputation for providing comprehensive legal services across all sectors of law.

19/08/2025
17/08/2025

የገንዘብ ሚኒስቴር የቅድሚያ ግብር መክፈያ ጊዜ የሂሳብ ሪፖርት አቀራረብ ላይ የተመሰረተ መሆኑን አስታወቀ

የገንዘብ ሚኒስቴር፣ የደረጃ "ሀ" ግብር ከፋዮች የቅድሚያ ግብር ክፍያ ጊዜን አስመልክቶ አዲስ ማብራሪያ ሰጥቷል። ሚኒስቴሩ እንዳስታወቀው፣ የቅድሚያ ግብር የሚከፈለው በየሦስት ወሩ ሲሆን፣ የጊዜው ስሌት የሚጀምረው የሂሳብ ሪፖርት ከቀረበበት ወር ማብቂያ ጀምሮ ነው።

​ሚኒስትሩ ለገቢዎች ቢሮ የፃፈዉ ደብዳቤ ላይ ግብር ከፋዮች የየሦስት ወሩን የቅድሚያ ግብር ክፍያ፣ የሂሳብ ሪፖርት ካቀረቡበት ወር በኋላ ባሉት በየሦስት ወሩ መጨረሻ ባሉት 30 ቀናት ውስጥ መፈጸም ይጠበቅባቸዋል።

​በዚህ ማብራሪያዉ ላይ እንደጠቆመዉ የሂሳብ ሪፖርታቸውን በጥቅምት ወር የሚያቀርቡ ግብር ከፋዮች፣ የመጀመሪያውን ቅድሚያ ግብር በየካቲት ወር፣ ሁለተኛውን በግንቦት ወር፣ ሦስተኛውን ደግሞ በነሐሴ ወር ይከፍላሉ። በተጨማሪም፣ ዓመታዊ ግብራቸውን አጠቃለው እስከ ጥቅምት ወር መጨረሻ ድረስ መክፈል እንደሚኖርባቸው በዝርዝር አስቀምጧል።

ይህን ተከትሎ ​ የሂሳብ ሪፖርት የሚቀርብበት ወር የግብር ክፍያ ማጠናቀቂያ ወር እንደሚሆን የገለፀ ሲሆን በዚህም መሰረት፣ አንድ ግብር ከፋይ በየሦስት ወሩ የከፈለው ቅድሚያ ግብር ከጠቅላላ ዓመታዊ ግብሩ ያነሰ ከሆነ፣ የቀረውን ልዩነት መክፈል ግዴታ እንዳለበት አፅንኦት ሰጥቷል።

16/08/2025

የተጨማሪ እሴት ታክስ ምጣኔ ወደ 17 በመቶ እንዲያድግ ምክረ ሃሳብ ቀረበ

በኢትዮጵያ ዝቅተኛ የሆነውን የግብር ከጠቅላላ የሀገር ውስጥ ምርት ጥምርታን ለማሻሻል በሚደረገው ጥረት፣ የሀገሪቱ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ምጣኔን ከ15% ወደ 17.5% እንዲያድግ ምክረ ሃሳብ መቅረቡ ታወቀ።

ይህንን የግብር ምጣኔ ማሳደግ፣ የሀገሪቱን የግብር ገቢ በከፍተኛ ሁኔታ ሊያሳድግ እንደሚችል ተነግሯል።

የገንዘብ ሚኒስቴር እና የፊስካል ጥናት ተቋም (IFS) በጋራ ባዘጋጁት አዲስ ጥናት፣ የኢትዮጵያ የ15% የተጨማሪ እሴት ታክስ ምጣኔ ከብዙ የምስራቅ አፍሪካ እና የደቡብ ሰሃራ አፍሪካ ሀገራት ምጣኔዎች ጋር ሲነጻጸር ዝቅተኛ ነው።

ለምሳሌ፣ የኬንያ የ ተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ምጣኔ 16% ሲሆን፣ የሩዋንዳና የዩጋንዳ ደግሞ 18% ነው። የደቡብ ሰሃራ አፍሪካ ሀገራት አማካይ ምጣኔም 17.5% መሆኑን አመልክቷል።

ጥናቱ አክሎም፣ የ ተጨማሪ እሴት ታክስ ምጣኔን ወደ 17.5% ማሳደግ ብቻ ከጠቅላላ የሀገር ውስጥ ምርት በተጨማሪ 0.4% ነጥቦችን ከ ተጨማሪ እሴት ታክስ ሊያስገኝ እንደሚችል ጠቁሟል።

ይህንንም ተግባራዊ ለማድረግ፣ ከዚህ በፊት ታክስ አልተሰበሰበባቸው የነበሩ እንደ ነዳጅ ያሉ ምርቶች ላይ ተጨማሪ እሴት ታክስ መሰብሰብ መጀመሩ ትልቅ አዎንታዊ እርምጃ ተደርጎ ተወስዷል።

"የኢትዮጵያ ታክስ-ለ-ጂ.ዲ.ፒ ምጣኔ፡ የማነፃፀሪያ ግምት እና የአፈጻጸም ትንተና" በሚል ርዕስ የተዘጋጀው ይህ ጥናት፣ የኢትዮጵያ የታክስ-ለ-ጂ.ዲ.ፒ ምጣኔ በ2022/23 በጀት ዓመት ወደ 7.5% ዝቅ ማለቱን ያሳያል።

ይህ ቁጥር በ2014/15 ከነበረው ከፍተኛው 12.4% ጋር ሲነፃፀር 4.9 በመቶ ነጥብ ቅናሽ አሳይቷል። ለዚህ ከፍተኛ የገቢ ቅናሽ ዋና ዋና ምክንያቶችም ዉስጥ ​መዋቅራዊ ለውጦች ፣​የፖሊሲ ልዩነቶች እና ​ዝቅተኛ የታክስ ተገዢነት መሆናቸውን በዝርዝር አስቀምጧል።

15/08/2025

Compare daily forex rates from major commercial banks, in one place.

The Addis Fortune Money Market Platform makes it easy.

No guesswork. No outdated info. Just real-time data to help you make smarter moves.

Download for Android https://ow.ly/42Mu50W7Jw5
Download for IOS https://ow.ly/8tYy50W7Jzf

25/07/2024

በግል አቤቱታ አቅራቢነት የሚያስቀጡ እና በወንጀል ክስ አቅራቢነት
የሚያስቀጡ ወንጀሎች ልዩነት

ወንጀሎች ክብደታቸውን እና የሚያስከትሉትን ጉዳት መነሻ በማድረግ በግል አቤቱታ አቅራቢነት የሚያስከስሱ እና በወንጀል ክስ አቅራቢነት የሚያስከስሱ (የግል አቤቱታ የማያስፈልጋቸው) ተብለው በሁለት ሊከፈሉ ይችላሉ፡፡ እነዚህ የወንጀል ዓይነቶች በክብደታቸው፣ በሚያስከትሉ ጉዳት መጠን እንዲሁም ከወንጀል ጥቆማ ጀምሮ እስከ ክርክር ሂደት ልዩነቶች አሏቸው፡፡ ይኸውም

• በግል አቤቱታ የሚያስቀጡ ወንጀሎች በባህሪያቸው ቀላልና
ጉዳታቸው በግለሰቦች ላይ ተወስኖ የሚቀር ሲሆን በወንጀል ክስ አቅራቢነት የሚያስጠይቁት ግን ከባድ፣ ውስብስብና ከግለሰብ አልፈው በሕዝብና በሀገር ላይ ጉዳት የሚያስከትሉ ናቸው፡፡ ለምሳሌ ስድብ፣ ዛቻ፣ ስም ማጥፋትና የመሳሰሉት በተበዳይ የግል አቤቱታ አቅራቢነት የሚያስከስሱ ወንጀሎች ሲሆኑ ውንብድና፣ ሽብርተኝነት፣ ሙስና፣ ግድያና የመሳሰሉት ወንጀሎች ደግሞ በወንጀል ክስ አቅራቢነት (በማንኛውም ሰው ጠቋሚነት) የሚያስከስሱ ወንጀሎች ናቸው፡፡

• በግል አቤቱታ አቅራቢነት ብቻ የሚያስቀጣ መሆኑ በወንጀል ሕጉ ልዩ ክፍል ወይም በሌላ ማሟያ የወንጀል ሕግ ተደንግጎ በተገኘ ጊዜ በግል ተበዳይ ወይም በሕጋዊ ወኪሉ አቤቱታ ካልቀረበ በቀር የወንጀል ክስ ማቅረብ እንደማይቻል በወንጀል ሕጉ አንቀፅ 212 ስር ተደንግጓል፡፡

በሌላ በኩል በባህሪያቸው ከግላዊ ይልቅ ህብረተሰባዊ ጉዳቶችን የሚያስከትሉ፣ የህብረተሰቡን ሰላምና ደህንነት አደጋ ላይ የሚጥሉ ወንጀሎችን በሚመለከት ጥቆማዎችንና መረጃዎችን ለሚመለከተው አካል መስጠት የሁሉም ዜጎች መብትም ኃላፊነትም ነው፡፡ ሆኖም ከባድ ወንጀሎችን ለሚመለከተው አካል ማሳወቅ ግዴታ ሆኖ የሚደነገግባቸው ሁኔታዎችም አለ፡፡ ለአብነትም የሽብር ወንጀልን በተመለከተ ያወቀውን ለሚመለከተው አካል ማሳወቅ ግዴታ ሲሆን ይህን ግዴታ አለመወጣት የሽብር ወንጀልን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር በወጣው አዋጅ ቁጥር 1176/2012 አንቀፅ 15 መሰረት የወንጀል ተጠያቂነት የሚስከትል ነው፡፡

• ሌላው ልዩነት በግል አቤቱታ የሚያስቀጡ ወንጀሎች በዕርቅ
ሊቋረጡ የሚችሉ ሲሆን በማንኛውም ሰው በሚቀርቡ ጥቆማዎች መሰረት በተመሰረተ ክስ ግን የበዳይና ተበዳይ መታረቅ ቅጣት ሲጣል በማቅለያነት ከሚያዝ በስተቀር ክስ ሊያቋርጥ አይችልም፡፡ ከዚህም በተጨማሪ በግል አቤቱታ የሚያስቀጡ ወንጀሎች ክስ ቀጣይነት በተበዳይ ፍላጎት ላይ የተንጠለጠለ ሲሆን በወንጀል ክስ አቅራቢነት የሚያስጠይቁት ግን የተበዳይ ፍላጎት ተፅኖ አያሳድርባቸውም፡፡

በንቃተ ህግ ትምህርትና ስልጠና ዳይሬክቶሬት

የፍትህ ሚኒስቴርን የማህበራዊ ትስስር ገፆችን ይቀላቀሉ
Facebook
https://www.facebook.com/MOJEthiopia/
(x) Twitter
https://x.com/MOJEthiopia
YouTube channel
https://youtube.com/...3701...

25/07/2024

“Lighting the way forward” navigating the complexities of currency Swaps: NBE’s recent move

The national bank of Ethiopia (NBE) and its counterpart central bank in the United Arab Emirates (CBUAE) have inked a swap and memorandum of understanding, according to a public announcement made last Tuesday. According to the NBE announcement, cross-border transaction settlement in local currencies would be possible up to a nominal value of 3 billion AED and 46 billion ETB ($795.8) at the current exchange rate.

In order to set an example and spur development for sustained foreign exchange surges in the nation, NBE is adopting a proactive and forward-thinking strategy. Its action is an illustration of brilliant strategy that, despite modest beginnings, may catalyze change and act as a ray of hope for a brighter future.

Read More (https://www.capitalethiopia.com/2024/07/22/lighting-the-way-forward-navigating-the-complexities-of-currency-swaps-nbes-recent-move/)

Website (https://bit.ly/capital_site) | Facebook (https://bit.ly/capital_fb) | X (https://bit.ly/capital_X) | TikTok (https://bit.ly/Capital_tiktok) | Instagram (https://bit.ly/Capital_Insta) | Linkedin (https://bit.ly/Capital_In) | Youtube (https://bit.ly/capital_yt)

25/07/2024

#ፋና #ኢትዮጵያ

25/06/2024

ለፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ተገልጋዮች በሙሉ

ወደ ፍርድ ቤቱ አቤቱታ፣ መልስ እና የመልስ መልስ በሰነድ ከሚቀርበው በተጨማሪ በሶፍት ኮፒ በሲዲ መቅረብ እና ከመዝገቡ ጋር መያያዝ ያለበት መሆኑ ይታወቃል

ሆኖም ፍርድ ቤቱ የአገልግሎት አሰጣጡን ተደራሽ ለማድረግ ቀድሞ በሲዲ ብቻ ሲቀርብ ከነበረው በሌሎች አማራጮች ከቀን 18/10/2016 ዓ.ም ጀምሮ በፍላሽ ወይም በሌሎች በማንኛውም ሊገለበጡ በሚችሉ የኤሌክትሮኒክስ መሳሪያዎች አማካኝነት ሬጅስትራር ጋር በመቅረብ የሶፍት ኮፒ ቅጅዎችን ማስገባት የምትችሉ መሆኑን በአክብሮት እንገልፃለን

የፌደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት

21/06/2024

Ethiopia to allow up to 49% foreign ownership in banks

The draft proclamation for Banking Business in Ethiopia will allow foreign investors to take up to 49 percent share in Ethiopian financial firms.

The highly anticipated proclamation includes provisions for foreign players to establish partially or fully owned foreign bank subsidiaries, open foreign bank branches, establish representative offices, or acquire shares of a bank.

It also states that foreign nationals, other than foreign banks and foreign-owned Ethiopian organizations, may acquire shares in banks. However, direct shareholding by a strategic investor in an existing or new domestic bank is limited to 40 percent of the total subscribed shares of a bank.

This is a revision of the previous proposal mentioned in the policy document.

Non-strategic foreign national investors and foreign juridical persons are limited to seven percent and ten percent of subscribed shares of a bank, respectively.

Regardless of the above provisions, the aggregate shareholding by foreign nationals and foreign-owned Ethiopian organizations in a bank is limited to 49 percent of the total subscribed shares of a bank.

The draft proclamation also adds that, "for the purpose of attracting strategic investments that would benefit the economy and/or as a way of resolving a distressed bank and preserving financial stability, the National Bank may, on an exceptional basis and subject to fulfillment of other preconditions, allow well-established, reputable, and financially sound foreign banks to partially or fully acquire existing domestic banks through acquisition."

Address

Addis Ababa. Lideta Area
Addis Ababa

Opening Hours

Monday 09:00 - 17:00
Tuesday 09:00 - 17:00
Wednesday 09:00 - 17:00
Thursday 09:00 - 17:00
Friday 09:00 - 17:00
Saturday 09:00 - 17:00

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when The Law Office of Nesredin Abubeker/ ነስረዲን አቡበከር የህግ ቢሮ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share