Voice of Justice - የፍትህ ድምፅ

Voice of Justice - የፍትህ ድምፅ we are the voice of judges, prosecutors and victims of injustice in our justice system.

VOJ is established by different groups of prosecutors, judges, legal practitioners, and attornys for the aim of changing the problems incurred in our justice system specially in Amhara Region. we are also struggling the maladministration of the justice organs specially Courts and General Attorney organs. we are fighting for the creation of strong, independent and accountable justice organ.

®በዳኞች አስተዳደር አብይ ጉባዔ የሚወሰን የዳኞች የስንብት ዉሳኔ ምክር ቤት ቀርቦ ከመፅደቁ በፊት ፍርድ ቤት ቀርቦ የመታየቱ ጉዳይንም ይህ የህገ መንግስት ትርጉም ያካትተው ይሆን?® የዳኞች...
05/08/2026

®በዳኞች አስተዳደር አብይ ጉባዔ የሚወሰን የዳኞች የስንብት ዉሳኔ ምክር ቤት ቀርቦ ከመፅደቁ በፊት ፍርድ ቤት ቀርቦ የመታየቱ ጉዳይንም ይህ የህገ መንግስት ትርጉም ያካትተው ይሆን?

® የዳኞች የስንብት ውሳኔ ምክር ቤት ከመቅረቡ በፊት በይግባኝም ሆነ በሰበር ቀርቦ እንዳይመዘን የተደረገበት አመክንዬ ምንድን ነው?
~~~
የፌዴሬሽን ምክር ቤት 6ኛ የፓርላማ ዘመን፣ 5ኛ ዓመት የሥራ ጊዜ፣ 1ኛ መደበኛ ጉባዔ መስከረም 27 ቀን 2018 ዓ.ም መ/ቁ 142/17 በሰጠው ውሳኔ፣ ማንኛውም የመንግስት አካል የሚያወጣቸው ሕጎች የትኛውም መስሪያ ቤት ወይም የስራ ሃላፊ በሠራተኞች ላይ የሚሰጠው የስንብት ውሳኔ በፍርድ ቤት ወይም በዳኝነት አካላት ዘንድ ቀርበው እንዳይታዩና ውሳኔ እንዳያገኙ መከልከል ከሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 37(1) ጋር የሚቃረኑ በመሆናቸው ተፈጻሚነት እንዳይኖራቸው የሕገ መንግስት ትርጉም ውሳኔ አስተላልፏል፡፡

~~ከምክንያታዊ ጥርጣሬ በላይ~~"Beyond Reasonable Doubt"
04/08/2026

~~ከምክንያታዊ ጥርጣሬ በላይ~~
"Beyond Reasonable Doubt"

የኢ.ፌ.ዲ.ሪ የፌዴሬሽን ምክር ቤት ሰኔ 29 ቀን 2018 ዓ.ም በ6ኛው የፓርላማ ዘመን 5ኛ ዓመት 2ኛ መደበኛ ጉባኤ በመዝገብ ቁጥር 150 በመንግሥት አካል ሕጋዊ የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ የ...
04/08/2026

የኢ.ፌ.ዲ.ሪ የፌዴሬሽን ምክር ቤት ሰኔ 29 ቀን 2018 ዓ.ም በ6ኛው የፓርላማ ዘመን 5ኛ ዓመት 2ኛ መደበኛ ጉባኤ በመዝገብ ቁጥር 150 በመንግሥት አካል ሕጋዊ የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ የተሰጠው ሰው፣ የመሬቱ ሕጋዊ ባለይዞታ የመሆን እና በመሬቱ የመጠቀም ሕገ መንግሥታዊ መብቱ የተጠበቀ ነው።
​አንድ ሰው የሌላ ሕጋዊ ባለይዞታ በሆነ መሬት ላይ (ባለይዞታው ሳይቃወመው እንኳን ቢሆን) ቤት ቢሠራ፣ የመሬቱ ባለይዞታነት ወይም የቤቱ ሙሉ ባለሃብትነት ወደ ቤቱ ሠሪ አይተላለፍም።

​የሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 40(7) "በመሬት ላይ ንብረት ያፈራ ሰው የንብረቱ ባለቤት ይሆናል" የሚለው ድንጋጌ የሚሠራው የመሬት ባለይዞታነት መብት ላለው ሰው እንጂ፣ በሌላ ሰው ይዞታ ላይ ያለ ሕጋዊ መሠረት ንብረት ለገነባ ሰው የቤት ባለቤትነት መብት ለመስጠት አይደለም።

​ባለይዞታው ሳይቃወም በይዞታው ላይ ቤት የሠራ ሰው የሚኖረው ሕገ መንግሥታዊ መብት ለቤቱ/ለግንባታው ያወጣውን ወጪ (ግምት) ከመሬቱ ባለይዞታ የመጠየቅ መብት ብቻ ነው።

​በመሆኑም የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት "በሌላ ሰው መሬት ላይ ቤት የሠራ ሰው የቤቱ ባለቤት ይሆናል" በማለት የሰጣቸውን የቀደሙ አስገዳጅ ውሳኔዎች ኢ-ሕገ መንግሥታዊ ናቸው በማለት የሕገ መንግስት ትርጉም ውሳኔ ሰጥቷል።

የአማራ ክልል ፍ/ቤቶች በክረምት
03/08/2026

የአማራ ክልል ፍ/ቤቶች በክረምት

በወንጀል የተከሰሰ ማንኛውም ሰው ድርጊቱን ስለመፈጸሙ በዐቃቤ ሕግ በኩል "ከምክንያታዊ ጥርጣሬ በላይ" (beyond reasonable doubt) ካልተረጋገጠ በቀር ጥፋተኛ ተብሎ የቅጣት ውሳኔ...
30/07/2026

በወንጀል የተከሰሰ ማንኛውም ሰው ድርጊቱን ስለመፈጸሙ በዐቃቤ ሕግ በኩል "ከምክንያታዊ ጥርጣሬ በላይ" (beyond reasonable doubt) ካልተረጋገጠ በቀር ጥፋተኛ ተብሎ የቅጣት ውሳኔ ሊሰጥበት የማይገባ መሆኑን እና ይህ ሳይረጋገጥ የሚሰጥ የጥፋተኝነትና የቅጣት ውሳኔ ሕገ-መንግሥታዊ እንዳልሆነ በኢ.ፌ.ዲ.ሪ ሕገ-መንግሥት አንቀጽ 20 (3) ሥር ከተረጋገጠው "ንጹህ ሆኖ የመገመት መብት" አንጻር የፌዴሬሽን ምክር ቤት አስገዳጅ የሕገ-መንግሥት ትርጉም ውሳኔ ሰጥቷል። በተጨማሪም ተከሳሽ ጥፋተኛ አለመሆኑን በተራው ለማስረዳት በዐቃቤ ሕግ ማስረጃ ላይ ምክንያታዊ ጥርጣሬን (reasonable doubt) መፍጠር በቂው እንደሆነ ተወስኗል።

የፌዴሬሽን ምክር ቤት ውሳኔ፣
መዝገብ ቁጥር 151፣
ሰኔ 29 ቀን 2018 ዓ.ም

⚖️⚖️⚖️በአዋጅ ቁጥር 813/2006 መሠረት አንድን ሸቀጥ ማከማቸት ወይም ማጓጓዝ ወንጀል የሚሆነው ሸቀጡ እጥረት ያለበት መሆኑ በሚኒስቴሩ በወጣ የሕዝብ ማስታወቂያ ሲገለጽ ብቻ ነው ሰመቁ ...
26/04/2026

⚖️⚖️⚖️በአዋጅ ቁጥር 813/2006 መሠረት አንድን ሸቀጥ ማከማቸት ወይም ማጓጓዝ ወንጀል የሚሆነው ሸቀጡ እጥረት ያለበት መሆኑ በሚኒስቴሩ በወጣ የሕዝብ ማስታወቂያ ሲገለጽ ብቻ ነው ሰመቁ 266087

የክርክሩ መነሻ 👉🏿አመልካች በመኪና የፓልም የምግብ ዘይት ጭነው ሲጓጓዙ በፖሊስ ተያዙ። ዓቃቤ ሕግ አመልካቹን በሁለት ወንጀሎች ከሰሰ፦
👉የመጀመሪያ ክስ፦ በገበያ ላይ እጥረት ያለበትንና በመንግሥት ድጎማ የሚቀርብን ዘይት ከመደበኛው የንግድ አሠራር ውጪ ማጓጓዝ።
👉ሁለተኛ ክስ፦ ድርጊቱን ሕጋዊ ለማስመስል የሐሰት ደረሰኝ መጠቀም።
👉የሥር ፍርድ ቤቶች የሰጡት ቅጣት
• አመልካቹ ጥፋተኛ ነው ተብሎ 4,500.00 ብር መቀጮ እንዲከፍል።
👉ዘይቱን ሲያጓጉዝበት የነበረው መኪና በአዋጅ ቁጥር 813/2006 መሠረት ለመንግሥት እንዲወረስ።
✅✅✅✅✅የሰበር ሰሚ ችሎት ትንተና እና ውሳኔ
👉ሕጋዊነት (Principle of Legality)፦ አንድ ድርጊት ወንጀል ሊባል የሚችለው በሕግ በግልጽ "ወንጀል" ተብሎ ሲደነገግ ብቻ ነው።
👉የመንግሥት መመሪያ፦ በወቅቱ የነበረው የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር እንዲሁም የገንዘብ ሚኒስቴር የምግብ ዘይት እንደማንኛውም ሸቀጥ በነፃነት እንዲዘዋወር እና ሽያጩ እንዳይስተጓጎል መመሪያ አውጥተው ነበር።
👉እጥረት አለመታወጁ፦ በሕጉ መሠረት አንድን ዕቃ ማጓጓዝ ወንጀል የሚሆነው "እጥረት ያለበት መሆኑ በሕዝብ ማስታወቂያ ሲገለጽ" ነው፤ በዚህ ጉዳይ ላይ ግን እንዲህ ያለ ማስታወቂያ አልወጣም።
👉የመኪና መወረስ፦ መኪና ሊወረስ የሚችለው ዕቃ ለመደበቅ ተሻሽሎ ከተሠራ ወይም ባለቤቱ ወንጀል መሆኑን እያወቀ እንዲፈጸም ከፈቀደ ብቻ ነው። በዚህ ጉዳይ ግን ድርጊቱ ራሱ ወንጀል ሆኖ አልተገኘም==

24/04/2026

ተሽከርካሪዎ እንዳይወረስ በሰበር የተሰጠ ውሳኔ
~~
የፌዴራል ሰበር/መዝ/ቁ 204922
~~
በጉምሩክ አዋጅ ቁጥር 859/2006 አንቀጽ 147 (3) ላይ የተመሰረተ ሲሆን፣ ሕጉ ኮንትሮባንድ የጫነ ተሽከርካሪ እንዲወረስ የሚያዝዘው በተሽከርካሪው አካል ላይ የዕቃ መደበቂያ ተሰርቶበት መገኘቱ ሲረጋገጥ ብቻ መሆኑ የተወሰነበት የህግ ትርጉም
~~
አንድ ተሽከርካሪ የኮንትሮባንድ ዕቃዎችን ለመደበቅ እንዲያስችል ተደርጎ አካሉ ተለውጦ (ሻግ ተበጅቶለት) ከተገኘ፣ ባለንብረቱ ድርጊቱን "አላውቅም" ቢል እንኳ ተሽከርካሪው ተወርሶ ለመንግስት ገቢ እንደሚሆን አጽንቷል።

በዚህ ረገድ ባለንብረቱ ስለ ድርጊቱ አስቀድሞ ማወቁ ወይም አለማወቁ በሕጉ ፊት ዋጋ የማይሰጠው በመሆኑ፣ ተሽከርካሪው የመንግስት ንብረት ሆኖ እንዲመዘገብ የተሰጠውን ውሳኔ ሰበር ሰሚ ችሎቱ አጽንቶታል።

ይህ ውሳኔ የመኪና ባለንብረቶች ለተሽከርካሪዎቻቸው ጥንቃቄና ክትትል እንዲያደርጉ የሚያሳስብ ጠንካራ የሕግ መልዕክት ያስተላልፋል።

በ7 (ሰባት) ዳኞች የተሰጠ የሰበር ውሳኔ፤ መዝገብ ቁጥር 246230መጋቢት 25/2018ከዚህ ቀደም በሰ/መ/ቁ 186946 የተሰጠው ውሳኔ ‘‘በአንድ ቦታ ላይ ሁለት የተለያዩ ሰዎች የይዞታ ማ...
10/04/2026

በ7 (ሰባት) ዳኞች የተሰጠ የሰበር ውሳኔ፤
መዝገብ ቁጥር 246230
መጋቢት 25/2018

ከዚህ ቀደም በሰ/መ/ቁ 186946 የተሰጠው ውሳኔ ‘‘በአንድ ቦታ ላይ ሁለት የተለያዩ ሰዎች የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ ቢኖራቸው አንደኛው ቤት ቢሰራ ሌላኛው ወገን በይዞታዬ ላይ እየተቃወምኩኝ ቤት ስለሰራ ያፍርስልኝ በማለት መጠየቅ የማይችል መሆኑን’’ የሚገልጸው ውሳኔ ተለውጧል፡፡

7 (ሰባት) ዳኞች በተሰየሙበት ችሎት መዝገብ ቁጥር 246230
“በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በመ/ቁ186946 በሚያዝያ 26/2013 ዓ.ም የተሰጠው አስገዳጅ ትርጉም እና ሌሎች መዝገቦች ላይ የተያዘዉ ተመሳሳይ አቋም ተለውጦ፤ በአንድ ባለይዞታ ሊመዘገብ የሚገባን የከተማ ይዞታ ከአንድ በላይ የሆነ የይዞታ ማረጋገጫ ወይም ካርታ ለተለያዩ ሰዎች ተደርቦ ተሰጥቶ ሲገኝ ለቦታው ባለመብትነት ቅድሚያ የሚሰጠው መጀመሪያ ያስመዘገበው ሰው ነው’’ በሚል ተተርጉመዋል፡፡

የተሽከርካሪ ሽያጭ ውል ህጋዊነት እና ማስረጃ አቀራረብ ~~~በሰበር መ/ቁ 283524 በቀን 27/05/2018 ዓ.ም ~መኪና ሲገዙ ወይም ሲሸጥ በውልና ማስረጃ በኩል ሳያረጋግጡ በመንደር ውል ...
08/04/2026

የተሽከርካሪ ሽያጭ ውል ህጋዊነት እና
ማስረጃ አቀራረብ
~~~
በሰበር መ/ቁ 283524
በቀን 27/05/2018 ዓ.ም
~
መኪና ሲገዙ ወይም ሲሸጥ በውልና ማስረጃ በኩል ሳያረጋግጡ በመንደር ውል መደረጉ ያለው እጣ ፈንታ በተለይም ግለሰቡ (ተጠሪ) ከአንድ ሻጭ (አመልካች) ጋር የመኪና ሽያጭ ውል ተፈራርመው፣ ከፊል ክፍያ ፈጽመውና መኪናውን ተረክበው ለዓመት ያህል ሲጠቀሙ ይቆያሉ ። ነገር ግን ሻጭ መኪናውን በሌላ ቁልፍ ከፍተው በመውሰድ "አልሸጥኩም፣ እንዲያስተዳድሩልኝ ውክልና ነው የሰጠኋቸው" በማለት በመካድ ተከራክረዋል ። በሰበር ሰሚ ችሎትም መኪና እንደ ተራ ንብረት ሳይሆን እንደ "ልዩ ተንቀሳቃሽ ንብረት" የሚቆጠር በመሆኑ፣ ዝውውሩ በህግ ፊት እንዲጸና በሚመለከተው የመንግስት አካል ዘንድ መመዝገብና መረጋገጥ አለበት ። በተጨማሪም የመኪና ሽያጭ መኖሩን ለማረጋገጥ በሚመለከተው አካል የተረጋገጠ የሽያጭ ሰነድ ማቅረብ እንጂ በሰው ምስክር ብቻ ማረጋገጥ የማይቻል ስለመሆኑ።

≈≈ሰ/መ/ቁ.224265 ≈≈(ሕዳር 30 ቀን 2015 ዓ.ም)---ከሳሽ የሆነ ወገን አስቀድሞ የሚመጣውን የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ አውቆ በክሱ ጊዜ ማስረጃ ማያያዝ ነበረበት ማለት የማይቻል እ...
25/03/2026

≈≈ሰ/መ/ቁ.224265 ≈≈
(ሕዳር 30 ቀን 2015 ዓ.ም)
---
ከሳሽ የሆነ ወገን አስቀድሞ የሚመጣውን የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ አውቆ በክሱ ጊዜ ማስረጃ ማያያዝ ነበረበት ማለት የማይቻል እና ለቀረበበት የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ማስተባበያ እንዲሆነው ከሳሽ የሆነ ወገን አስቀድሞ በክሱ ካቀረበው ማስረጃ በተጨማሪ ሌላ ማስረጃ ማቅረብ እንደሚችል የተሰጠ የህግ ትርጉም።

Address

Justice
Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Voice of Justice - የፍትህ ድምፅ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share

Category