25/05/2024
የኮንዶሚንየም ቤት ሽያጭ
==============
የኮንዶሚንየም ቤት የደረሰው ሰው ለ3ኛ ወገን በሽያጭ ወይም በስጦታ ሊያስተላልፍ የሚችለው ቤቱን ከገዛ 5 አመት ሲሞላው ብቻ ስለመሆኑ በአዋጅ ቁጥር 19/97 ተደንግጓል። ይሁንና ይህ ጊዜ መቆጠር የሚጀምረው እጣው ከወጣ በኃላ ነው ወይስ እጣውን ተከትሎ ከሚመለከተው የአስተዳደር አካል ጋር ውል ከተደረገበት ጊዜ ጀምሮ ነው የሚለው ሲያከራክር የነበረ ሲሆን በአዋጁ ላይ በግልፅ ባይቀመጥም ከጠቅላላ ድንጋጌዎቹ ይዘት የምንረዳው የኮንዶሚንየም ቤት እጣ ከከተማው አስተዳደር ጋር የቤት ግዢ ውል ለማድረግ መብት የሚሰጥ እንጂ እራሱ የቤት ግዢ ውል አይደለም፡፡ ስለዚህም የኮንዲሚንየሙ ባለቤት ለ3ኛ ወገን በሽያጭ ወይም በስጦታ ማስተላለፍ የሚችለው ቤቱን በገዛ 5 አመት ሲሞላው ነው የሚለው ጊዜ የሚቆጠረው እጣ ከደረሰበት ቀን ጀምሮ ሳይሆን የሚቆጠረው የቤት ሽያጭ ውል ከሚመለከተው የመንግስት አካል ጋር ከተፈፀመበት ቀን ጀምሮ ነው፡፡
/የሰበር መ/ቁ 158899/
=======
Join us on Telegram👇👇
https://t.me/ET_Legalhub
👉 Tiktok 👇
https://vm.tiktok.com/ZMMEL5E2W/