Get Lawyer I ጌት ሎየር

Get Lawyer I ጌት ሎየር Get Lawyer is a social media banner created by Meseret Yenehun Law Office. Join & explore the legal🌍

ለመንገደኞች👇
06/04/2026

ለመንገደኞች
👇

ከውጭ የሚመጡ መንገደኞች እነዚህ እቃዎች ከቀረጥ ነፃ ወደ ኢትዮጵያ እንዲያስገቡ ይፈቀድላቸዋል። ምን ምን እቃዎቹ እንደሆኑና ብዛት ስንት ማስገባት እንደሚችሉ በዚህ አጭር ቪድዮ ምላ.....

ጠቃሚ መረጃ ለቤት ሻጭና ገዢ፡፡፡፡፡፡የቤት ሽያጭ ዋጋ ተመን አሰራርና የታክስ አገልግሎት ክፍያ ማንዋል ቁጥር 01/2016 ዓ.ም ማንዋሉን ቀጥሎ ባለው የጌት ሎየር የቴሌግራም ቻናል ላይ ያገ...
06/04/2024

ጠቃሚ መረጃ ለቤት ሻጭና ገዢ
፡፡፡፡፡፡
የቤት ሽያጭ ዋጋ ተመን አሰራርና የታክስ አገልግሎት ክፍያ ማንዋል ቁጥር 01/2016 ዓ.ም

ማንዋሉን ቀጥሎ ባለው የጌት ሎየር የቴሌግራም ቻናል ላይ ያገኙታል፡፡

04/04/2024

ገደብ ምንድነው?
በተለያዩ አጋጣሚዎች “ገደብ” የሚለው ቃል ሰምታችሁ ሊሆን ይችላል፡፡ ይህ ቃል በመዝገበ ቃላት የራሱ ትርጉም ቢኖረው በህግ ሙያ ያለው ትርጉም እንደሚከተለው ሊገለጽ ይችላል፡፡
በጠበቃ መሠረት የኔሁን
በወንጀል ተከስሶ የእስራት ቅጣት የተወሰነበት ሰው የተወሰነበትን የእስር ትዕዛዝ ሳይፈጽም ከእስር እንዲለቀቅ ማዘዝ ወይም የእስራት ቅጣቱ እንዳይፈፀም ማገድ በህጉ አገላለጽ ገደብ በመባል ይታወቃል፡፡
የወንጀል ህግ መሠረታዊ ዓላማው ጥፋተኞችን ከጥፋታቸው እንዲታረሙና እንዲማሩ ማድረግ መቻል ነው፡፡ ከዚህ ጋር ተያያዞ አንድ ጥፋተኛን ለማስተማር ወይም ከድርጊቱ እንዲታቀብ ለማድረግ ሁልጊዜ የእስራት ቅጣት ወስኖ የእስራት ቅጣቱን እንዲፈፀም ወደ ማረሚያ ቤት መላክ አስፈላጊ ላይሆን ይችላል፡፡ በዚህ ምክንያት ፍርድ ቤቶች አንድን ተከሳሽ በወንጀል ድርጊት ጥፋተኛ ተብሎ የእስራት ቅጣት ከተወሰነ በኋላ የእስራት ቅጣትን ሳይፈጽም ወይም ደግሞ ወደ ማረሚያ ቤት ሳይላክ ቢለቀቅ ተመሳሳይ ድርጊት ከመፈፀም የሚቆጠብ ስለመሆኑ የሚያሳዩ አካባቢያዊና ግላዊ ሁኔታዎች ካሉ የእስራት ቅጣቱ እንዳይፈፀም ማገድ ይችላሉ፡፡
ከዚህ ጋር ተያይዞ አብዛኛው ጊዜ በማስረጃ ተረጋግጠው ከሚቀርቡ ጉዳዮች መካከል፡
👉1. ተከሳሹ ከዚህ ቀደም የወንጀል ድርጊት ፈጽሞ የማያውቅ ሪከርድ የሌለበት ከሆነ አሁን በፈፀመውና ጥፋተኛ በተባለበት የወንጀል ድርጊትም ለፍርድ ቤት ቀርቦ የወንጀል ድርጊቱን መፈፀሙን አምኖ የገለፀ እንደሆነ፡፡
👉2. በፈፀመው የወንጀል ድርጊት የበደላቸው ወይም የጎዳቸው ግለሰቦች ካሉ ከእነሱ ጋር ታርቆ ካሳ የከፈለ ከሆነ፤ በተለያዩ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ የበጎ አድራጎት ተግባራት የሚሳተፍ ከሆነ
በእነዚህ ጥቅል ምክንያቶች ተከሳሹ የእስራት ቅጣቱን ባይፈፅም እንኳ የእስራት ቅጣ መወሰኑ በራሱ እንዲማር ያስችለዋል ተብሎ ግምት ስለሚወሰድ የተወሰነን የእስራት ቅጣት ማገድ እንዲችሉ ለፍርድ ቤቶች ስልጣን ተሰጥቷል፡፡
በአጠቃላይ በወንጀል ህጉ የተቀመጡ የገደብ ድንጋጌዎች አሉ፡፡
የህግ ግንዛቤዎን ለማሳደግ እንዲሁም ሀሳብና አስተያየት ለመስጠት የቴሌግራምና የቲክቶክ ቻናላችንን ይቀላቀሉ፡፡
Lawyer

03/04/2024

ውድ የጌት ሎየር ቤተሰቦች!
በቅርቡ የወጣው “የመኖሪያ ቤት ኪራይ ቁጥጥር እና አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 1320/2016” በቴሌግራም ቻናላችን ያገኙታል፡፡
👇

https://t.me/Meseretlawoffice/40

02/04/2024

ጋብቻ በሚፈርስበት ወቅት የሚነሱ የህግ ክርክሮች
ክፍል 1

05/03/2024
ወደ ኢትዮጵያ ይዞ መግባት የሚቻለው፤ ከሀገር ሲወጣ ለመያዝ የሚፈቀድለው የጥሬ ገንዘብ መጠንበተመለከተ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ መመሪያ በቴሌግራም ቻናላችን ያገኙታል፡፡👇
04/03/2024

ወደ ኢትዮጵያ ይዞ መግባት የሚቻለው፤ ከሀገር ሲወጣ ለመያዝ የሚፈቀድለው የጥሬ ገንዘብ መጠን
በተመለከተ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ መመሪያ በቴሌግራም ቻናላችን ያገኙታል፡፡
👇

የሥራ ውል ስለማቋረጥሠላም የጌት ሎየር ቤተሰቦች! በዚህ ጽሑፍ አንድ ሠራተኛ የስራ ውል ማቋረጥ ቢፈልግ እንዴት ማቋረጥ እንዳለበት ማብራሪያ ይዘንላችሁ ቀርበናል፡፡ዕድሜው ለስራ የደረሰ ሰው ...
22/02/2024

የሥራ ውል ስለማቋረጥ

ሠላም የጌት ሎየር ቤተሰቦች! በዚህ ጽሑፍ አንድ ሠራተኛ የስራ ውል ማቋረጥ ቢፈልግ እንዴት ማቋረጥ እንዳለበት ማብራሪያ ይዘንላችሁ ቀርበናል፡፡

ዕድሜው ለስራ የደረሰ ሰው ኑሮውን ለመምራት ሰዎችን ቀጥሮ በሚያሰራ ግለሰብ ወይም ድርጅት ውስጥ ለመስራት ይስማማል፡፡ አሰሪና ሠራተኛ የስራ ውል ስምምነት ሲመሰርቱ በመካከላቸው ስለሚኖረው የሥራ ግንኙነት እንዲሁም መብትና ግዴታቸው በውል ስምምነታቸው እና በአሰሪና ስራተኛ አዋጅ ቁጥር 1156/2012 የሚተዳደር ይሆናል።

ለመንደርደሪያነት አሰሪ እና ሠራተኛ ማለት ምን ማለት ነው ሚለውን በቅድሚያ እንመልከት፡፡ ከላይ በተጠቀሰው አዋጅ አንቀጽ 4 መሠረት አሰሪ ማለት አንድ ወይም ከአንድ በላይ ሰዎችን ቀጥሮ የሚያሰራ ግለሰብ ወይም ድርጅት ሲሆን ሠራተኛ ማለት ከአሠሪ ጋር በቅጥር ላይ የተመሠረተ የስራ ግንኙነት ያለው ግለሰብ ነው፡፡

ማንኛውም ግለሰብ ደመወዝ እየተከፈለው ለአሠሪው ሥራ ለመስራት ከአሰሪው ጋር የሥራ ውል ስምምነት ይመሰርታል፡፡ ነገር ግን ከሁለቱ ወገኖች አንደኛው የሥራ ውል ማቋረጥ ቢፈልግ የሥራ ውልን በሕግ ወይም በስምምነት ማቋረጥ ይችላል፡፡

የሥራ ውል በአሠሪው ወይም በሠራተኛው አነሳሽነት ሊቋረጥ ይችላል፡፡ በሠራተኛው አነሳሽነት የስራ ውል በሚቋረጥበት ጊዜ ለአሰሪው ቅድሚያ ማስጠንቀቂያ መስጠት ይኖርበታል፡፡ በአዋጁ የተገለፁ በቂ ምክንያቶች ሲኖሩ ያለማስጠንቀቂያ የስራ ውል ማቋረጥ ይቻላል፡፡

በቅድሚያ ማስጠንቀቂያ የሥራ ውል ለማቋረጥ

ደመወዝ እየተከፈለው ለአሰሪው ሥራ ለመስራት የተስማማ ሠራተኛ በተለያየ ምክንያት በሥራው መቀጠል ካልፈለገ በማስጠንቀቂያ የሥራ ውል የማቋረጥ መብት አለው፡፡

በዚህም መሠረት የሙከራ ጊዜውን የጨረሰ ማንኛውም ሰራተኛ ለአሠሪው የ30 ቀናት ቅድሚያ ማስጠንቀቂያ በመስጠት በማናቸውም ምክንያት የሥራ ውሉን ማቋረጥ ይችላል፡፡

ያለማስጠንቀቂያ የሥራ ውል ለማቋረጥ

በአሠሪና ሠራተኛ ጉዳይ አዋጅ ቁጥር 1156/2011 አንቀጽ 32 መሠረት የሚከተሉት የሥራ ውልን ያለማስጠንቀቂያ ለማቋረጥ በቂ ምክንያቶች ይሆናሉ፡፡

ሀ.አሠሪው ወይም የሥራ መሪው የሠራተኛውን ሰብዓዊ ክብርና ሞራል የሚነካ ወይም በወንጀል ሕጉ መሠረት የሚያስቀጣ ሌላ አድራጎት የፈፀመበት እንደሆነ፤

ለ.ሠራተኛው በአሰሪው ወይም በሥራ መሪው ወሲባዊ ትንኮሳ ወይም ጥቃት የተፈፀመበት እንደሆነ፤

ሐ.ለሠራተኛው ደኀንነት ወይም ጤንነት የሚያሰጋና ሊደርስ የተቃረበ አደጋ መኖሩን አሠሪው እያወቀ ወይም አደጋውን ለመከላከል የሚያስፈልጉ እርምጃዎችን እንዲወስድ በተሰጠው ባለስልጣን ቀደም ሲል በተሰጠው ትዕዛዝ ወይም አግባብ ያለው የሠራተኞች ማህበር ወይም ሰራተኛው ራሱ አስቀድሞ በሰጠው ማስጠንቀቂያ መሠረት በተወሰነው የጊዜ ገደብ ውስጥ እርምጃዎችን ያልወሰደ እንደሆነ፤

መ.አግባብ ባላቸው ሕጎች በተወሰነው መሠረት አሰሪው ለሠራተኛው መፈፀም ያለበትን ግዴታዎችን በተደጋጋሚ ያልፈፀመ እንደሆነ

# # #

ዉድ የጌት ሎየር ቤተሰቦች በዚህ ጽሑፉ ዙሪያ አስተያየት ካላችሁ ወይም ተጨማሪ ማብራሪያ ከፈለጋችሁ በአስተያየት መስጫው ላይ ማስቀመጥ ትችላላቸሁ፡፡ መረጃው ለሌሎች እንዲደርስ ሼር ማድረግን እንዳትረሱ ልናስታውሳችሁ እንወዳለን፡፡
https://t.me/Meseretlawoffice

Address

Yeka Sub City
Addis Ababa

Opening Hours

Monday 08:30 - 16:30

Telephone

+251912503651

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Get Lawyer I ጌት ሎየር posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Get Lawyer I ጌት ሎየር:

Share