Konjit Legal Clinic

Konjit Legal Clinic በሕግ ዙሪያ ያለንን ግንዛቤ ለማስፋት እንዲሁም ሀሳቦችን ለመለዋወጥ

16/01/2026

የፌደራል የገቢ ግብር አዋጅ ማሻሻያ አዋጅ ቁጥር 1395/2017 አስመልክቶ አጭር ማብራርያ

 ማሻሻያ አዋጁ ከሐምሌ 1 ቀን 2017ዓም ስራ ላይ ዉሏል።
በአዋጁ በግብር ስርዓቱ ላይ በርካታ ማሻሻያዎች እንዲሁም አዳዲስ የታክስ አሰባሰብ ስርዓቶችን ያካተተ ነዉ። ለአብነት ያህልም፡-
 አዲስ የግብር ከፋይ ደረጃዎች
በቀድሞ ሶስት የግብር ከፋይ ደረጃዎች ሀ፣ ለ ፣ሐ ቀርቶ ሁለት ደረጃዎች
ሀ እና ለ ብቻ እንዲሆን ተደርጓል።
ደረጃ 'ሀ' ግብር ከፋይ ድርጅቶች እና ጠቅላላ ዓመታዊ ገቢዉ ብር 2 ሚሊዮን ወይም ከዚያ በይ የሆነ ማንኛዉም ሰዉ እንዲሁም ደረጃ 'ለ' ግብር ከፋይ ድርጅትን ሳይጨምር መታዊ ገቢዉ ከብር 2 ሚሊዮን የሚያንስ ሰዉ ሲሆን ሌላዉ አዋጁ ያካተተዉ ግብር የተጣለበት ገቢ
 ከዲጂታል አገልግሎትና ዲጂታል ይዘት ፈጠራ የሚገኝ ገቢ ሲሆን ከዲጂታል አገልግሎት (የሳተላይት ቴሌቭዥን፣የሶፍት ዌር አቅርቦት ወዘተ..)በመስጠት የሚገኝ ገቢ 5% ግብር የሚከፍልበት እና ከዲጅታል ይዘት ፈጠራ ( ከዩቲዩብ፤ከቪዲዮ ማጋርያ መድረኮች ፣ከፖድካስትና መሰል የማህበራዊ መድረኮች) የሚገኝ ገቢ በመደበኛ የንግድ እንቅስቃሴ አካል ከሆነ የንግድ ገቢ ግብር የተጣለበት ሲሆን ከዚህ ዉጭ ከሆነ ሌሎች ገቢዎች በሚል ተካቶ 15%ግብር ይከፈልበታል።
 በጥሬ ገንዘብ ግብይት ላይ ገደብ መጣል
ማንኛዉም ግብር ከፋይ በአንድ ግብይት ከብር 50,000 በላይ በጥሬ ገንዘብ መቀበል ወይም መክፈል እንደማይችል ተደንግጓል።
ይቀጥላል........

https://youtube.com/shorts/Xolv0zjIfMw?feature=share
01/01/2026

https://youtube.com/shorts/Xolv0zjIfMw?feature=share

ጠቃሚ የታክስ ህግ መረጃዎች እና ማብራሪያዎች በሙያዉ የዳበረ እዉቀትና ልምድ ባላቸዉ ባለሙያዎች የሚቀርብበት መድረክ ነዉ፡፡

Address

Addis Ababa
ET2121

Telephone

251 927424162

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Konjit Legal Clinic posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share

Category