abyssinialaw.com

abyssinialaw.com የኢትዮጵያ ሕጎችን፣ የፍርድ ውሳኔዎችን፣ የሕግ ጡመራዎችን፣ የሕግ ፎርሞችንና ጠቃሚ የሆኑ የሕግ መረጃዎችን ከአቢሲኒያ ሎው ይከታተሉ!

abyssinialaw.com is an open source for Ethiopian Lawyers, Students, Lecturers, Judges, Prosecutors, Advocates, Draft person and Researchers. It is dedicated not only to making Ethiopian Laws freely available in an electronic format but also to provide the status of the laws. This site is not affiliated in any way with any government entity; it is an independent, an effort to foster the learning of

Law and our Legal system. Laws here are made available through the private efforts of individuals who are donating their time and resources to provide quality information on our Laws and materials for policies, commentaries, blog entries, research papers for the betterment of our legal system.

17/10/2025

Legal analysis: “The Ethiopian Startup Proclamation No. 1396/2025: A Guide to Incentives and Legal Framework”. Insight from Liku Worku Law Office, a premier law f…

13/10/2025

በግልግል ዳኝነት የፍርድ ቤቶች ሚና

ጸሐፊ፡ ፍቃዱ አንዳርጌ መኮንን (ጠበቃ እና የሕግ አማካሪ)

ይህ ጽሑፍ፣ ከፍርድ ቤት ውጪ በግልግል ዳኝነት በሚፈቱ አለመግባባቶች ውስጥ መደበኛ ፍርድ ቤቶች ያላቸውን ወሳኝ ሚና ይተነትናል። የግልግል ዳኝነት ራሱን የቻለ ሥርዓት ቢሆንም፣ የግልግል ጉባዔን በማቋቋም፣ ጊዜያዊ ትዕዛዞችን በመስጠት፣ በማስረጃ አሰባሰብ ላይ ድጋፍ በማድረግ፣ እንዲሁም በግልግል የተሰጡ ውሳኔዎችን በማስፈጸምና በይግባኝ በመመርመር ረገድ የፍርድ ቤቶች ድጋፍ የግድ አስፈላጊ መሆኑን ጽሑፉ በዝርዝር ያስረዳል።

https://www.abyssinialaw.com/blog/the-role-of-courts-in-arbitration

ቅጽ 27 የሰበር ውሳኔዎች ታትሟልየፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ቅጽ 27 የሰበር ሰሚ ችሎት ውሳኔዎች አትሞ ለተጠቃሚዎች አውጥቷል፡፡ ውሳኔውን ከቴሌግራም ግሩፓችን ወይም ከዚህ በታች ባለው ሊን...
02/08/2025

ቅጽ 27 የሰበር ውሳኔዎች ታትሟል

የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ቅጽ 27 የሰበር ሰሚ ችሎት ውሳኔዎች አትሞ ለተጠቃሚዎች አውጥቷል፡፡
ውሳኔውን ከቴሌግራም ግሩፓችን ወይም ከዚህ በታች ባለው ሊንክ ማውረድ ይችላሉ

የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ቅጽ 27 የሰበር ሰሚ ችሎት ውሳኔዎች አትሞ ለተጠቃሚዎች አውጥቷል፡፡ ውሳኔውን ከዚህ ማግኘት ይችላሉ

08/07/2025

https://t.me/abyssinialaw/411

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ የ2017 ዓ.ም የግብር ዘመን ግብር አወሳሰንና አሰባሰብ አሠራር መላክን ይመለከታል በሚል ርዕስ ጠበቆች ለ2017 በጀት ዓመት ከግብር ዓመቱ አጠቃላይ ገቢ 35% እንደ ወጪ 65% ግብር የሚከፈልበት ገቢ ሆኖ በሠንጠረዥ "ሐ" መሠረት ግብሩን በማስላት ተሰውኖ ገቢውን እንዲሰበሰብ በማለት ትዕዛዝ ሰጥቷል። ውሳኔውን ከዚህ ያግኙ

ደረጃ ሀ እና ለ የሒሳብ መዝገብ በለመያዛቸው ምክንያት የግብር ማስከፈያ የማትሪፈያ ህዳጉ እጥፍ ተወስዶ እና የታክስ ጉዳቱን 40 በመቶ እና የታክሱን እጥፍ በመቅጣት ሕጉን ተፈጻሚ እንዲደረግ ብሏል፤

04/07/2025

የወንጀል ቅጣት አወሳሰን መመሪያ ቁጥር 3/2017

የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የወንጀል ቅጣት አወሳሰን መመሪያ ቁጥር 3/2017 አውጥቷል።

ይህ መመሪያ ከጥቅምት 1 2006 ዓ.ም ጀምሮ ሥራ ላይ የነበረውን የወንጀል ቅጣት አወሳሰን መመሪያ በማሻሻል የወጣ ሲሆን ፍርድ ቤቱ መመሪያውን እና ማብራሪያውን ለተጠቃሚዎች ዛሬ አሰራጭቷል።

መመሪያው እና ማብራሪያውን ከዚህ ማግኘት ይችላሉ።

ከዚህ ቀደም አዲሱ የዳኝነት ክፍያ ስሌትን አስመልክቶ የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የዳኝነት ክፍያ ማስያ (calculator) የአሰላል ስህተት እንዳለው መጠቆማችን ይታወሳል። የፌዴራል ጠቅላይ...
09/06/2025

ከዚህ ቀደም አዲሱ የዳኝነት ክፍያ ስሌትን አስመልክቶ የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የዳኝነት ክፍያ ማስያ (calculator) የአሰላል ስህተት እንዳለው መጠቆማችን ይታወሳል። የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በጉዳዩ ላይ ማስተካክያ እሲያደርግ ድርስ Negari App ለተጠቃሚዎች ሳንለቅ ቆይተናል።

የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት አሁን አሰላሉን ያስተካከለ በመሆኑ (ምንም እንኳን አሁንም የተወሰነ ስህተት ቢኖረውም)፣ ከዚህ በታች ያለውን የNegari App ማሻሽያ ለቀናል።

የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የዳኝነት ክፍያ ስሌቱን ማስያ በትክክል እንደሚያደርግ ርግጠኞች ነን።

የNegari App መተግበሪያን ከቴሌግራም ገጻችን ዳውንሎድ ያድርጉ። telegram.me/abyssinialaw

የ iPhone ተጠቃሚዎች በአቢሲኒያሎው ድረገጽ በዚህ ሊንክ ማስያውን ማግኘት ይችላሉ፡
https://abyssinialaw.com/court-fee-calculator

የመድህን እና የማጓጓዣ ሕግ ይርጋበ፦ ካሴ መልካምየንግድ ሕግ ይርጋዎች ማለትም የንግድ ጉዳዮችን በሚመለከት የሚቀርቡ የይርጋ መቃዎሚያዎች ማለትም፡-1. በዳይሬክተሮች ቦርድ ላይ የሚቀርብ ክስ...
30/05/2025

የመድህን እና የማጓጓዣ ሕግ ይርጋ
በ፦ ካሴ መልካም

የንግድ ሕግ ይርጋዎች ማለትም የንግድ ጉዳዮችን በሚመለከት የሚቀርቡ የይርጋ መቃዎሚያዎች ማለትም፡-
1. በዳይሬክተሮች ቦርድ ላይ የሚቀርብ ክስ ይርጋ
2. የሚተላለፍ የገንዘብ ሰነድ (የሐዋላ ወረቀት እና የቼክ) 3 ዓይነት ይርጋዎች
3. በባለአክሲዮኖች ጉባዔ የተሰጠ ውሳኔን የማሰረዣ ክስ የማቅረቢያ የይርጋ ጊዜ
4. በአክሲዮን ማህበር አደራጆች ላይ የሚቀርብ ክስ ይርጋ
5. የንግድ ማህበራት የሀብትና ዕዳ መግለጫን የመቃወሚያ ክስ ማቅረቢያ የይርጋ ጊዜ
6. በዓይነት መዋጮ በተጋነነ ግምት ለደረሰ ጉዳት ክስን ለማቅረብ የይርጋ ጊዜ
7. ሀሰተኛ የትርፍ ክፍያን ለማስመለስ የሚቀርብ ክስ የይርጋ ጊዜ

ከሕጉ እና ከሰበር አስገዳጅ የሕግ ትርጉም አንጻር ተዳሰዋል። የእነዚህ ጉዳዮች የይርጋ ጊዜ ሰፊ ትንታኔ ከፈለጉ መጽሐፉን እንዲያነቡ እነሆ ጀባ ብለናል።

መልካም ንባብ

ይህ ጽሑፍ በቀጥታ የተወሰደው በፍትሐብሔር ሥነ-ሥርዓት ሕግ የመጀመሪያ ደረጃ መቃዎሚያዎች ከሚለው ተሻሽሎ ከታተመው መጽሐፍ ላይ ነው። ሆኖም ለዚህ የበየነ-መረብ ጽሑፍ ለንባብ እንዲመ....

ይድረስ ለፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት - የፌደራል ፍርድ ቤቶች የዳኝነት ክፍያን ለመወሰን የወጣ ደንብ ቁጥር 1/2017 መሰረት የተሰራው ማስሊያ (calculator) ስህተት ያለበት ስለመሆኑ ...
29/05/2025

ይድረስ ለፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት - የፌደራል ፍርድ ቤቶች የዳኝነት ክፍያን ለመወሰን የወጣ ደንብ ቁጥር 1/2017 መሰረት የተሰራው ማስሊያ (calculator) ስህተት ያለበት ስለመሆኑ
ካልኩሌተሩ የዳኝነት ክፍያ ጣሪያን ግምት ሳያስገባ በፐርሰንት/በመቶኛ ብቻ በማስላቱ የሚከተለው ዓይነት ስህተት አለው፤
ለምሳሌ

ለ20ሺ ብር የዳኝነት ጥያቄ የዳኝነት ክፍያው 2ሺ ሲሆን ለ21ሺ ብር ደግሞ 1,890.00 ነው። ለ20 ሺ ብር ዳኝነት 2ሺ የሚከፈል ከሆነ እንዴት ለ21ሺ ብር ዳኝነት 1,890.00 ይከፈላል። ይህ ግልጽ ስህተት ነው። ይህ ስህተት የተገኘው በግልጽ አሰላሉን ደንቡ ስለማያሳይ ነው።
በእኛ አረዳድ
እስከ ብር 20 ሺ ላለ የዳኝነት ጥያቄ ጣሪያው 10 በመቶ ማለትም 2ሺ ብር ተይዞ ከ20ሺ ብር በላይ ላለው ደግሞ ቀጣይ ያለው 9 በመቶ ይሰላል ማለት ነው። በመሆኑም፡
ለ20,000.00 ብር ዳኝነት ጥያቄ የዳኝነት ክፍያ 2,000.00 ብር ሲሆን
ለ21,000.00 ብር ደግሞ ብር 2,089.91 ይሆናል።

ተክክለኛውን አሰላል ከዚህ ይመልከቱ
https://www.abyssinialaw.com/court-fee-calculator

በቀጣይ የነጋሪ አፕን ማሻሻያ እንለቃለን። ይጠብቁን ይህንን ለጠቅላይ ፍርድ ቤት ያድርሱልን።

በመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያዎች ላይ ትኩረት የሚሹ አወዛጋቢ ነጥቦችና መፍትሔዎቻቸውበ፡ ካሴ መልካምይህ ጽሑፍ የተወሰደው በፍትሐብሔር ሥነ-ሥርዓት ሕግ የመጀመሪያ ደረጃ መቃዎሚያዎች በሚል ከታተ...
11/04/2025

በመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያዎች ላይ ትኩረት የሚሹ አወዛጋቢ ነጥቦችና መፍትሔዎቻቸው
በ፡ ካሴ መልካም

ይህ ጽሑፍ የተወሰደው በፍትሐብሔር ሥነ-ሥርዓት ሕግ የመጀመሪያ ደረጃ መቃዎሚያዎች በሚል ከታተመው በ2017 ዓ.ም ተሻሻሎ በቀረበው መጽሐፌ ላይ ሲሆን የግርጌ ማስታዎሻዎቹ እና ማጣቀሻዎቹ ለዚህ ጽሑፍ ሲባል ለንባብ በሚመች አግባብ እንደገና ተቀናጅተው ተሰርተዋል፡፡ በዚህ ጽሑፍ የተካተቱት አብዛኛዎቹ ነጥቦች አወዛጋቢ ሆኖም በሕግ ባለሙያው ብዥታ እና ልዩነት የሚፈጥሩ ነጥቦች በመጽሐፉ የመጀመሪያ ዕትም ያልነበሩ አሁን ላይ በችሎት በሚገጥሙ ክርክሮች ሰበር ጭምር መፍትሔ የሰጣቸውን እና ሰበር መፍትሔ ያልሰጠባቸውን ደግሞ የመጽሐፉ አዘጋጅም የራሱን ምልከታ እና መፍትሔ የሚላቸውን ሃሳቦች ያሰቀመጠባቸው ጉዳዮች ናቸው፡፡

በዚህ በተሻሻለው ዕትም ከ400 በላይ የመጀመሪያ ደረጃ መቃዎሚያን የሚመለከቱ በ5 እና በ7 ዳኞች የተሰጠ የሰበር ችሎቱ አስገዳጅ የሕግ ትርጉ እና በርካታ የፌዴራሽን ምክር ቤቶች የተካተቱበት ነው፡፡ ከዚህም በተጨማሪ በመጀመሪያ ደረጃ እና በከፍተኛ ፍርድ ቤት በችሎት አከራካሪ የሆኑ ጉዳዮች እና ፍ/ቤቶቹ የሰጡት ፍርድን መነሻ በማድረግ መፍትሔ የሚሆኑ ነጥቦችን ለማስቀመጥ ተሞክሯል፡፡

በዚህ ጽሑፍ የሚከተሉትን ያገኛሉ።
1. በጽሑፍ ያልቀረበን የመጀመሪያ ደረጃ መቃዎሚያን ከሳሹ በቃል ክርክር የማቅረብ መብት ያለው ስለመሆኑ
2. በመቃወሚያ ላይ ማስረጃ የመስማት አስፈላጊነት
3. በብዙ መቃወሚያዎች ላይ የውሳኔ አሰጣጥ ስነ-ስርዓት
4. በመቃወሚያዎች ላይ ከሳሽ በክሱ ያልዘረዘራቸውን ማስረጃዎች የማቅረብ መብት
5. በተጣመሩ ተከሳሾች አንዱ በሌላኛው ላይ መቃዎሚያዎችን የሚያነሱበት አግባብ
6. በመቃዎሚያዎች ላይ ይግባኝ የሚባልበት አግባብ
7. በመጀመሪያ ደረጃ መቃዎሚያ ላይ ውሳኔ ከተሰጠ በኋላ የክስ መሻሻል ውጤት
8. የመጀመሪያ ደረጃ መቃዎሚያና እሱን ለመወሰን መሰረት የሚሆነው ሕግ
9. በፍርድ ቤት በራሱ እና በተከራከሪዎች ብቻ የሚነሱ መቃዎሚያዎችን
10. በተከራካሪዎች ብቻ የሚነሱ የመጀመሪያ ደረጃ መቃዎሚያዎች
11. ፍርድ ቤቱ በራሱ ሊያነሳቸው የሚችሉ የመጀመሪያ ደረጃ መቃዎሚያዎች
https://www.abyssinialaw.com/blog/controversial-points-and-their-solutions-for-preliminary-objections
መልካም ንባብ!

Address

Bole, Gulf Aziz Building
Addis Ababa
23113

Opening Hours

Monday 09:00 - 17:00
Tuesday 09:00 - 17:00
Wednesday 09:00 - 17:00
Thursday 09:00 - 17:00
Friday 09:00 - 17:00

Telephone

251912168579

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when abyssinialaw.com posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to abyssinialaw.com:

Share