Zephaniah Alemu - ዘፋኒያህ ዓለሙ

Zephaniah Alemu - ዘፋኒያህ ዓለሙ አጣሁ ብየ የማላጎበድድ፣ አገኘሁ ብዬ የማልታበይ ፈጠሪ የመረጠኝ ዐማራ ነኝ‼

07/03/2026

ምርጥ እና ለየት ያሉ 13 የፌደሬሽን ምክር ቤት ዉሳኔዎች
(ጠበቃ አደም ሰይድ ከማል )
✅✅✅✅✅✅✅✅✅✅✅✅
1. በእምነት ማጉደል ወንጀል የተከሰሰ/የተጠረጠረ ሰው ሲጠየቅ በእጁ በገባ ንብረት መብት አለኝ በማለት ክርክር ካቀረበ ጉዳዩ በፍትሐ ብሔር ክርክር ከሚወሰን በስተቀር በእምነት ማጉደል ወንጀል አይከሰስም/አይቀጣም። የወንጀል ሕግ በጠባቡ መተርጎም አለበት በማለት የፌዴሬሽን ምክር ቤት መ/ቁ.73/11 ላይ የሰጠው አስገዳጅ የህግ ትርጉም ውሳኔ ነው።

2. ከዚህ ቀደም የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በሠ/መ/ቁ. 189707 እና በሠ/መ/ቁ. 228002 ጠቅለል ሲደረግ ቤትን ለረጅም ግዜ መያዝ ብቻውን የባለቤትነት መብት አያጎናጽፍም ሠ/መ/ቁጥር 228002፡፡ አንድን ቤት ለረጅም ግዜ መያዝ ብቻውን የባለቤትነት መብት የማያጎናጽፍ በመሆኑ እንዲሁም ቤቱ የቀበሌ / የመንግስት / ቤት መሆኑን የሚያሳይ ቅጽ 003 እና ቅጽ 004 በሌሉበትሁኔታ በተቋሙ የመረጃ ስርአት ቅጽ 008 በቀበሌ ቤትነት መመዝገቡ ብቻ ቤቱ በመንግስትየተወረሰ የቀበሌ /የመንግስት ቤት ነው ሊያስብለው አይችልም ብሎ ነበረ ሰበር ሰሚ ችሎቱ። በአዋጅ ቁጥር 47/67 ተወርሶ ለረጅም ግዜ በመንግስት እጅ የነበረ ቤትን በሚመለከት በስህተት አላግባብ ያለህጋዊ ምክንያት ተሰጥቷል የተባለው የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ የመከነና በመንግሰት ባለቤትነት የሚታወቅ ስለመሆኑ በተገለጸበት በአዋጅ ቁጥር 47/67 መሰረት መንግስት የወረሰው መሆኑን የሚያሳይ ቅጽ 003 እና ቅጽ 004 በሌለበት ቤቱን የመንግስት ንብረት አያሰኘውም የሚል ውሳኔ ወስኖ የነበረ ሲሆን ይህንን ውሳኔ የኢፌድሪ የፌደሬሽን ምክር ቤት መስከረም 29 ቀን 2016 ዓ.ም. ባደረገው 6ተኛ የፓርላማ ዘመን 3ተኛ አመት 1ኛ መደበኛ ጉባኤው በህገ መንግስት አጣሪው በቀረበለት መሰረት በመ/ቁጥር 108/15 የሠ/መ/ቁ .189707 ህገመንግስታዊነት አጣርቶ ውሳኔውን ሽሮታል።ስለሆነም የመንግስት ቤትን ለረጅም ጊዜ ከአዋጅ 47/67 በኋላ ይዞ ያስተዳድር የነበረ ሁለቱ ቅፃች ቅፅ 003 እና 004 ባይኖሩትም ባለይዞታነቱ ይቀጥላል።

3. የማይንቀሳቀስ ንብረትን በተመለከተ በፍ/ብ ሕጉ ዓንቀፅ 1195 መሰረት ንብረቱ በስሙ የተመዝገበለት ሰው ወይ ገለሰብ የንብረቱ ባለሃብት እንደሆነ የሕግ ግምት ሊወሰድለት ይገባል።እንዲሁም ሌላኛውወገን በክርክሩ ንብረቱ ከሕግ ወጭ የተሰጠው ስለ መሆኑ ማስረጃውን ባላስተባበለበት እና ማስረጃውን የሰጠው የከተማ መስተዳድር ካርታውን ባላመከነበት ሁኔታ ንብረቱን በስሙ በተመዝገበለት ሰው መብት በሚጥስ መልኩ የሚሰጥ ውሳኔ የሕገ መንግስቱ ድንጋጌዎች የሚጥስ ነው በማለት የፌዴሬሽን ምክር ቤት መስከረም 28 ቀን 2017 ዓ/ም በመ/ቁ.128/16 አስገዳጅ የሕገ መንግስት ትርጉም ተሰጥቷ

4. አመልካች አከራካሪውን ቤት ለመግዛት የራሱን የሀብት ምንጭ የተጠቀመ መሆኑ በስር ፍርድ ቤት አልተረጋገጠም፤ እንደዚሁም አንድ ሰው የንብረት ባለሀብት የሚሆነው በጉልበቱ በፈጠራ ችሎታው ወይም በገንዘቡ ንብረት ያፈራ ሲሆን እንጂ በስሙ ስለተመዘገበ ብቻ የግሉ ሊሆን አይችልም፡፡ቤት በገዛበት ወቅት ለአካለ መጠን ያልደረሰ መሆኑን በመጥቀስ በራሱ የሽያጭ ውሉን ሊዋዋል አይችልም ውሉ ከመሠረቱ ፈራሽ ነው በማለት የተሰጠ ዉሳኔ የሕገ መንግሥት አንቀጽ 36 (2) እና 40 የሚቃረን ነዉ፡፡ የፌዴሬሽን ምር ቤት ሚያዝያ 22 ቀን 2010 ዓ.ም የመ/ቁ. 41/10

• ሙሉ የዉሳኔዉ ይዘት
በ358 የገባዉ የአሁን አመልካች አከራካሪውን ቤት ለመግዛት የራሱን የሀብት ምንጭ የተጠቀመ መሆኑ በስር ፍርድ ቤት አልተረጋገጠም፤ እንደዚሁም አንድ ሰው የንብረት ባለሀብት የሚሆነው በጉልበቱ በፈጠራ ችሎታው ወይም በገንዘቡ ንብረት ያፈራ ሲሆን እንጂ በስሙ ስለተመዘገበ ብቻ የግሉ ሊሆን አይችልም በማለት የፌደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት የሰጠዉ ዉሳኔ በሕገ መንግሥቱ ያለኝን የንብረት መብት ይጥሳል ሲሉ ቅሬታቸውን አቅርበዉ ምክር ቤቱ ጉዳዩን እንደሚከተለዉ መርምሯል፡፡
በተያዘው ጉዳይ በፍ/ቤቶች በነበረ ክርክር ተጠሪ አከራካሪውን ቤት በተመለከተ ቤቱ በባንክ ዕዳ ምክንያት ሲሸጥ ወጪው ከቀድሞ ባለቤታቸው ቄስ ታየ ምሕረቴ ጋር ከነበራቸዉ የጋብቻ ሀብት ወጪ በማድረግ በአመልካች ስም ቤቱ የተገዛ መሆኑን እንደዚሁም በተመሳሳይ አከራካሪዎቹ የቀንድ ከብቶችም ከተጠቀሰው የጋብቻ የጋራ ሀብት ወጪ ተደርጎ የተገዙ መሆናቸውን በመጥቀስ ንብረቶቹን በጋብቻ ውስጥ የተፈሩ ስለሆነ የጋራ ይባሉልኝ የሚል ክርክር አቅርበዋል፡፡
ፍ/ቤቶችም ግራ ቀኙን አከራክረው በዋናነት አመልካች አከራካሪዎቹን ንብረቶች ከራሱ የሀብት ምንጭ ወጪ አድርጎ ስለመግዛቱ አላስረዳም በሚል ምክንያት ላይ በመመሥረት ንብረቶቹን የተጠሪና የቀድሞ ባለቤታቸው ቄስ ታየ ምሕረቴ በጋብቻ ውስጥ የተፈሩ የጋራ ሀብት ናቸው በማለት መወሰናቸውን መረዳት ይቻላል፡፡ ሆኖም ግን ፍ/ቤቶች ተጠሪ የቀድሞ ባለቤታቸው ቄስ ታየ ምሕረቴ በአንድ በኩል የሚፈለግባቸውን የባንክ ዕዳ መክፈል አቅቷቸው አከራካሪው ቤት በጨረታ ሊሸጥ የቻለ መሆኑን አረጋግጠው በሌላ በኩል አከራካሪውን ቤት ለመግዛት የሚያስችል ገንዘብ አቅም ኖሯቸው ከጋራ ሀብታቸዉ ወጪ አድርገው አከራካሪውን ቤት ገዝተዋል ሲሉ መደምደማቸውን ስንመለከት የተጠቀሰው ምክንያትና ድምዳሜ አብረው የሚሄዱ አለመሆናቸውን መረዳት የሚቻል ሲሆን ይልቁንም ፍርድ ቤት የተጠቀሱት አከራካሪው ቤት ከተጠቃሹ የጋብቻ ሀብት ወጪ ተደርጎ ያልተገዛ መሆኑን ያስረዳል ለሚል ድምዳሜ የቀረበ ነው፡፡
በተጨማሪም ፍ/ቤቶች በተለይ አከራካሪው ቤት ከተጠቃሹ ጋብቻ የጋራ ሀብት ወጪ ተደርጎ የተገዛ ነው ብለው እንደወሰዱት ግምት እንኳ ቢሆን ዕዳውን ቀድሞውኑ በቀጥታ መክፈል እየቻሉ ባለመክፈል ንብረታቸውን እንዲሸጥ በመፍቀድ በተዘዋዋሪ በአመልካች ስም ቤቱን የመግዛታቸው ድርጊት ተጠሪ ከቀድሞ ባለቤታቸው ጋር በመሆን ሕግን በተቃረነ መልኩ አንዳች ኃላፊነት ለመሸሽ ወይም ለሕገ ወጥ ዓላማ ሲሉ የከወኑት ተግባር ነው፡፡ በመሆኑም ተጠሪ ከቀድሞ ባለቤታቸው ጋር በመሆን በፈጸሙት ሕግን የተቃረነ ተግባራቸው ተጠቃሚ ሊሆኑ የሚገባ አይደለም፡፡ ተጠሪና የቀድሞ ባለቤታቸው ሕግን ባልተቃረነ መንገድ አከራካሪዎቹን ንብረቶች በፈቃዳቸው ከጋራ ንብረታቸው ወጪ በማድረግ አካለመጠን ባልደረሰ በአመልካች ስም ገዝተዋል ብሎ መነሳት ከምክንያታዊነት እና ሕገ መንግሥታዊ መሠረት ካለው የሕጻናትን ጥቅም በቀደምትነት ከማክበር መርህ ጋር የሚቃረን ይሆናል፡፡ በሌላ በኩል አመልካች በተለይ አከራካሪውን ቤት ስመ ሀብቱን በስሙ አድርጎ ማስረጃውን ይዞ የሚገኝ ሆኖ እያለ በዚህም በፍ/ሕ/ቁ 1195 መሠረት አንድ የማይንቀሳቀስ ንብረትን ስመ ሀብቱን በስሙ በማድረግ ማስረጃውን በእጁ ያደረገ ሰው የንብረቱ ባለቤት እንደሆነ የሚገመት ስለመሆኑ ተደንግጎ እያለ፣ እንደዚሁም ይህንኑ ድንጋጌ ተከትሎ በሚገኘው አንቀጽ 1196 መሠረት የቀረበ ግምቱን ሊያስተባብል የሚችል ክርክርም ሆነ ማስረጃ በሌለበት አልያም ሌላ ሕጋዊ ምክንያት በሌለበት ሁኔታ ፍ/ቤቶች አከራካሪዎቹ ንብረቶች አንድ አካለ መጠን ያልደረሰ ልጅ ንብረት ከሚያፈራባቸው መንገዶች በአንዱ የተገኙ ንብረቶች ስለመሆናቸው መነሻ ግምት በመያዝ በተቃራኒው ሕግ በሚፈቅደው አግባብ ተጠሪ ማስተባበያ ማቅረብ አለማቅረባቸውን መመርመር ጉዳዩን መመልከት እየተገባቸው በተቃራኒው አመልካች ስለመብታቸው እንዲያስረዱ ግዴታን በመጣል መወሰናቸው የሕጻናት የተሻለ ጥቅም ለማስጠበቅ በሚረዳ መልኩ ውሳኔ የሰጡ አለመሆናቸውን የሚያረጋግጥ ስለመሆኑ ውሳኔው በኢፌዲሪ ሕገ መንግሥት አንቀጽ 36 (2) ሕጻናትን የሚመለከቱ እርምጃዎች በሚወስዱበት ጊዜ መንግሥታዊ ወይም በግል የበጎ አድራጊነት ተቋሞች፣ በፍርድ ቤቶች፣ በአስተዳደር ባለሥልጣኖች ወይም በሕግ አውጪ አካላት የሕጻናት ደኅንነት በቀደምትነት መታሰብ አለበት በሚል የሰፈረው ሕገ መንግሥታዊ ድንጋጌ እንደዚሁም በሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 4ዐ የሰፈረውን የንብረት መብት ድንጋጌ የሚቃረን በመሆኑ በሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 9/1/ መሠረት ተፈጻሚነት የለውም በማለት ምክር ቤቱ በሙሉ ድምጽ ወስኗል፡፡
5. .ከጋብቻ በፊት የነበረ የግል ቤት በትዳር ዉስጥ ከፍተኛ ወጪ ወጥቶ ማሻሻያ እና ማስፋፊያ ቢደረግለትም የጋራ ንብረት ሊሆን አይገባም፡፡ ቀደም ሲል ከጋብቻ በፊት የግል የነበረ ቤት በትዳር ዉስጥ መሰረታዊ በሚባል ደረጃ እድሳት ከተደረገለት ወይም ከፍተኛ ወጪ ወጥቶ ማሻሻያ ከተደረገለት ቤቱ የባልና ሚስት የጋራ ይሆናል በማለት በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ዉሳኔ ተሰጥቶ ነበር፡፡ይህ የሰበር ሰሚ ችሎቱ ዉሳኔ ሕገ-መንግስቱን ይቃረናል በሚል የሕገ-መንግስት ትርጉም ለፌደሬሽን ምክር ቤት ቀርቦት የነበር ሲሆን የፌዴሬሽን ምክር ቤቱ መስከረም 28-2017 ዓ.ም በሰጠዉ ዉሳኔ የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት የሰጠዉን ዉሳኔ በመሻር ተፈጻሚነት የለዉም ብሏል፡፡
ፌደሬሽን ምክር ቤት ዉሳኔ ከጋብቻ በፊት የግል የነበር ቤት በጋብቻ ዉስጥ ማሻሻያ እና ማስፋፊያ መደረጉ ቤቱን የጋራ ንብረት አያደርገዉም፡፡ ቤቱን ለማሻሻል እና ለማስፋፋት የወጣ ወጪ ተጣርቶ ወጪዉ በድርሻ እንዲወስዱ ከሚደረግ በስተቀር ቤቱ የጋራ አይሆንም፡፡
መዝገብ ቁጥር,130/2016
መስከረም 28-2017 ዓ.ም
6. ህፃናት በስማቸው የተመዘገበ የማይንቀሳቀስ ንብረት ባለቤት የመሆን ሕገ መንግስታዊ መብት ያላቸው ስለመሆኑ፤ ስለዚህ በፍቺ ወቅት የባልና ሚስት የጋራ ንብረት ነው ሊባል የማይችል መሆኑና፤ ባል ወይም ሚስት የፍርድ ባለዕዳ በሚሆንበት ጊዜ ፍ/ቤቱ የፍርድ ማስፈፀሚያ ሊውል የማይችል መሆኑ።የፌዴራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ሰመቁ 210433፤ ሰመቁ 55081 ቅፅ 11፥ 94489 እና 210483 ያልታተሙ የሰበር ሰሚ ችሎቱ የተንፀባረቀው አቋም “ አካለ መጠን ያልደረሰ ልጅ የማይንቀሳቀስ ንብረት በስሙ የተመዘገበ ቢሆንም ንብረቱ በእውቀቱ፤ በጉልበቱ ወይም በገንዘቡ ያፈራው መሆኑ ማስረዳት አለበት ካለስረዳ ግን የንብረቱ ባለቤት መሆን አይችልም የሚል ነው። የሰበሮቹ ትንታኔ ህፃናት ንብረት ሊያፈሩ አይችሉም፤ ካፈሩም ምንጩ መታወቅ አለበት የሚል ነው። የሰበር ውሳኔዎቹ መነሻ ያደረጉት የህገ መንግስቱ አንቀፅ 40(2) አንድ ሰው የንብረት ባለቤት መሆን የሚችለው በጉልበቱ፤ በመፍጠር ችሎታው ወይም በካፒታሉ ያፈራው ሲሆን ነው የሚለውን ነው። ነገር ግን የፌዴሬሽን ምክር ቤት የማይንቀሳቀስ ንብረት በስሙ የተመዘገበለት ሰው ህፃናትን ጨምሮ በንብረቱ ላይ የባለሀብትነት መብት ይኖራቸዋል። ንብረቱም በጉልበታው ወይም በመፍጥር ችሎታቸው ወይም በካፒታላቸው እንዳፈሩት ይቆጠራል።ፍ/ቤቶች የማይንቀሳቀስ ንብረት ባለቤትንት ማስረጃን ወይም ሰነድን በፍ/ብ/ህ/ጉ አንቀፅ 1195 ሲተረጉሙ በሕጉ አንቀፅ 1196 ስር ከተዘረዘሩ መስፈርት ውጪ በሌላ ማናቸውም መስፈርት የሰነድ ማስረጃ ውድቅ ማድረግ የለባቸውም። ይህ በሰነድ የተረጋገጠው ባለሀብትንት በሰው ምስክር አይስተባበልም።ስለሆነም የሰበር ውሳኔዎቹ ተፈፃምንት የላቸውም ማለት ነው።የፌዴሬሽን ምክር ቤት ውሳኔ መ/ቁ 116/16
7. አንድ ሰው በሕገ ወጥ መንገድ ባገኘው ወይም የራሱ የመጠቀም መብት በሌለው ይዞታ ላይ በጉልበቱ፣ በገንዘቡ፥ ወይም በፈጠራ ችሎታው ንብረት ቢያፈራ በቤቱ ላይ የባለሃብትነት መብት እስከምን ድረስ ነዉ?(የመ/ቁጥር 106/15 ላይ ሰኔ 28 ቀን 2015 ዓ.ም)
አንድ ሰው በሌላ ሰው ይዞታ ላይ ንብረት ሊያፈራ እና በተፈራው ንብረት ላይም ሕገ መንግስታዊ እና ሕገዊ መብት ከባለይዞታው ጋር በሚደረገው ስምምነት መሰረት ነው፡፡በኢፌዲሪ ሕገ መንግስት አንቀጽ 40(1) መሰረት ንብረት የሚፈራው በጥረት እና በገንዘብ ቢሆንም ጥረቱ መደረግ ያለበት በሕጋዊ መንገድ ነው፡፡በሕገ መንግስቱ መሰረት መሬት የመንግስት እና የሕዝብ ሲሆን ዜጎች ደግሞ በመሬት የመጠቀም ሕገ መንግስታዊ መብት አላቸው፡፣ በመሬት የመጠቀም መብት ያለው ሰው በቅድሚያ መሬቱን በሕጋዊ መንገድ ያገኘ ስለመሆኑ ለዚህም ማረጋገጫ ከአስተዳደር አካል የባለይዞታነት ማረጋገጫ ሰነድ ሊኖረው ይገባል:: በዚህ ሁኔታ ባገኘው እና በተመዘገበው መሬት ላይ በጉልበት፣ በመፍጠር ችሎታ እና በካፒታል የሚፈራ ማናቸውም ንብረትም ሕገ መንግስታዊ እና ሕጋዊ ጥበቃ ይደረግለታል፡፡አንድ ሰው በሕገ ወጥ መንገድ ባገኘው ወይም የራሱ የመጠቀም መብት በሌለው ይዞታ ላይ ንብረት ቢያፈራ፣ ንብረቱ የተፈራው በጉልበቱ፣ በገንዘቡ፥ ወይም በፈጠራ ችሎታው ቢሆንም በቤቱ ላይ ሙሉ የባለሃብትነት ሕገ መንግስታዊ መብት እና ጥበቃ የሚያገኘው ቀድሞ በመሬቱ የመጠቀም መብት ከመንግስት ወይም ከባለይዞታው ሲያገኝ ነው፡፡አንድ ሰው በራሱ ባል ሆነ ይዞታ ላይ ቤት አፍርቶ ከተገኘም ከባለይዞታው ጋር ባለው ሀጋዊ መሰረት ጉዳዩ መፍትሄ የሚያገኝ እና ያወጣውን ገንዘብ ከሚጠይቅ በቀር የቤቱ ባለሃብት ሊሆን አይችልም::
ጠበቃ አደም ሰይድ ከማል, [12/26/2025 9:37 PM]
⓱ለእርሻ የተመደበ ይዞታ ላይ ያለ አትክልት እና ቤት የሚደረግ የሽያጭም ሆነ የመያዣ ውል መሬቱን ከመሸጥ ወይም ከማስያዝ የተለየ ውጤት አይኖረውም :

የፌደሬሽን /ም/መ/ቁ.08/08 መጋቢት 3 ቀን 2008 ዓ.ም የተሰጠ ውሳኔ፣
የአማራ ክልል የገጠር መሬት አስተዳደር እና አጠቃቀም አዋጅ ቁ.133/98 በአንቀጽ 19 ላይ በግልጽ እንደተመለከተው የገጠር መሬት ይዞታን የመጠቀም መብት በዋስትና ማስያዝ የተፈቀደው የገጠር መሬት ይዞታን ለማልማት በሊዝ የያዘን ሰው የሚመለከት ነው፡፡
በመሆኑም በወረዳው አካባቢ ጥበቃ፣ መሬት አጠቃቀም እና አስተዳደር ጽሕፈት ቤት በተሰጠው የይዞታ ማረጋገጫ ደብተር እንደተጠቀሰው አከራካሪው ይዞታ ለእርሻ የሚውል (የተመደበ) ሲሆን በዚህ ዓይነት ይዞታ ላይ አትክልት እና ቤት አለው በሚል ምክንያት የሚደረግ የሽያጭም ሆነ የመያዣ ውል መሬቱን ከመሸጥ ወይም ከማስያዝ የተለየ ውጤት አይኖረውም፡፡

ከላይ በተጠቀሰው የክልሉ የገጠር መሬት አስተዳደር እና አጠቃቀም አዋጅ ድንጋጌ መሠረት ደግሞ በአከራካሪው የመሬት ይዞታ ላይ ያለን የመጠቀም መብት በመያዣነት ማስያዝ ለአመልካች የሚፈቀድ አይደለም፡፡

ይህ የአዋጁ ድንጋጌ መሬት በመያዣ ሰበብ እንዳይሸጥ ወይም በተዘዋዋሪ መንገድ መሬት እንዳይሸጥ እንዳይለወጥ፣ አርሶ አደሩ ከይዞታው እንዳይፈናቀል የሚከለክል እና ሕገ
መንግሥቱ በአንቀጽ 40(3) ላይ መሬት እንዳይሸጥ እንዳይለወጥ ያስቀመጠውን ዓላማ የሚያሳካ ነው፡፡ በመሆኑም አከራካሪውን መሬት መሸጥ በግልጽ የተቀመጠውን ሕገ መንግሥታዊ ድንጋጌ የሚፃረር ሲሆን በመያዣ ውል መስጠትም ቢሆን በአዋጁ ያልተፈቀደ እና በተዘዋዋሪ መንገድ የሚደረግ ሽያጭ በመሆኑ በውጤቱ የሕገ መንግሥት ጥሰት ያለው ነው፡፡

በመሆኑም ጉዳዩን የተመለከተው ፍርድ ቤት ሕገ መንግሥቱን የሚፃረር ስምምነት በመቀበል የሰጠው ውሳኔ መሬት እንዳይሸጥ እንዳይለወጥ በሚል የተደነገገውን ሕገ መንግሥታዊ ክልከላ የጣሰ እና አመልካችን ከይዞታቸው ያፈናቀለ በመሆኑ የሕገ መንግሥቱን አንቀጽ 40(3እና4) የጣሰ ነው፡፡

በመሆኑም ጉዳዩ የሕገ መንግሥት ትርጉም የሚያስፈልገው ነው በማለት ጉባኤው በሙሉ ድምጽ ተስማምቶ ይኸው ጉዳይ ለመጨረሻ ውሳኔ ለፌዴሬሽን ምክር ቤት እንዲተላለፍ በማለት የውሳኔ ሃሳቡን አቅርቧል የሚል ነው፡፡

ምክር ቤቱም የአጣሪ ጉባኤውን የውሳኔ ሀሳብ መሠረት በማድረግ በጉዳዩ ላይ የምክር ቤቱ የሕገ መንግሥት ትርጉምና የማንነት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ያቀረበውን የውሳኔ ሃሳብ ተመልክቷል፡፡በዚህም መሠረት ምክር ቤቱ እንደተረዳው በዚህ ጉዳይ የደቡብ ጎንደር ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በአሁኗ አመልካች ከሳሽነት እና በአሁኑ ተጠሪ ተከሳሽነት መነሻነት ለቀረበለት የሁከት ይወገድልኝ (የመሬት ይዞታዬን ይለቀቅልኝ) እና የመሬት አላባ ይከፈለኝ ክስ ፍርድ ቤቱ በተከሳሹ በኩል የቀረበለትን በአመልካችና ተጠሪ መካከል በቀን 04/06/89 ዓ.ም ተደርጓል ተብሎ የቀረበውን የሽያጭ ውልና ሐምሌ 18 ቀን 1990 ዓ.ም ተፈጽሟል ተብሎ የቀረበውን የዕርቅ ስምምነት ተቀብሎ በማጽደቅ ከሳሽ (የአሁኗ አመልካች) ቤቱንና የአትክልቱን ቦታ አስይዤ ብር 900 (ዘጠኝ መቶ ብር) ገንዘብ ተበድሬ ሄድኩኝ ትበል እንጂ ቤቱንና አትክልቱን ለመሸጧ የቀረበው የጽሑፍ ማስረጃ አረጋግጧል፤ ከዚያም በኋላ በመያዣነት ነው የሰጠሁት በማለት በእርቅ እንዲፈፀም ድርድር ገብታ በሽማግሌዎች እርቅ ተፈጽሞ በዕርቁ መሠረትም በተወሰነው ጊዜ ገንዘቡን ለተከሳሽ (የአሁኑ ተጠሪ)
መልሳ ቤቱንና አትክልቱን መረከብ ስላልቻለች በእርቁ መሠረት እንዲፈፀም በማለት የሰጠው ውሳኔ ከኢፌዴሪ ሕገ መንግሥት አንቀጽ 40(3እና4) ድንጋጌዎች ጋር የሚቃረን በመሆኑ በሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 9(1) ድንጋጌ መሠረት ተፈፃሚነት ሊኖረው አይገባም፡፡
በመሆኑም በደቡብ ጎንደር ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሕገ መንግሥቱን አንቀጽ 40(3እና4) ድንጋጌዎችን በሚቃረን መልኩ የሰጠው ውሳኔ ሕገ መንግሥታዊ ጥሰት ያለብት በመሆኑ በሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 9(1) ድንጋጌ መሠረት ተፈጻሚነት ሊኖረው አይገባም በማለት ምክር ቤቱ በሙሉ ድምጽ ወስኗል፡፡

8. በይርጋ ፤በሞግዚት ስህተትና በሥነ ሥርዓታዊ ጉዳይ የሕፃናትን ሕገ መንግሥታዊ መብት የሚጥስ ውሳኔ መሰጠት የለበትም፡-
የፌ/ም/መ/ቁ. 896/05
መጋቢት 3 ቀን 2008 ዓ.ም
የአመልካች ቅሬታም የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ጉዳዩን በይግባኝ በሚያይበት ጊዜ ተጠሪው በሀሰት አመልካች በአካባቢው የለችም በማለት እኔ በሌለሁበት ጉዳዩ እንዲታይ አድርጎ ማስወሰኑን፣ ተጠሪ በከፍተኛ ፍርድ ቤት መልስ ሲሰጥ የዘረመል (DNA) ምርመራ እንዲደረግ ሲያመለከት እኔም ተስማምቼ እያለሁ ፍርድ ቤቱ አላግባብ ይህን ጥያቄ ማለፉን፣ የይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤትም ይህንን ሳያጣራ የስር ፍርድ ቤት ውሳኔን መሻሩን፣ እንዲሁም የተሰጠው ውሳኔ ‹‹In the best interest of the child” የሕፃኑን መሰረታዊ መብትና ጥቅም የሚለውን ዓለም አቀፋዊ መርህ›› የሚቃረንና ሕፃኑ ወላጆቹን የማወቅና ከእነሱም እንክብካቤ የማግኘት መብት በሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 36(1) /ሐ/ እና (2) የተመለከተውን የሚፃረር ነው የሚል ነው፡፡
ፍሬ ሃሳቡ ከዚህ በላይ እንደተዘረዘረው ሲሆን ‹‹ተጠሪ አገባሻለሁ ብሎኝ የግብረ ሥጋ ግንኙነት አድርገን ከዚሁ የተነሳ ሕፃን ሱራፌል ስለተወለደ የልጁ አባትነት ይታወቅልኝ›› ስትል አመልካች ክስ የመሠረተች ሲሆን ተጠሪ በበኩሉ ይህን ክዷል፡፡
ጠበቃ አደም ሰይድ ከማል(0910214108)
ሆኖም “አመልካች ከወለደች በኋላ ተጠሪው ብር 1000 በቅንነት ሰጥቻታለሁ፤ የእኔና የልጁ ደም ተወስዶ የዘረመል ምርመራ እንዲደረግልኝ” ሲል በከፍተኛ ፍርድ ቤትም ሆነ በይግባኝ ሰሚው ጠቅላይ ፍርድ ቤት ቅሬታውን አቅርቧል፡፡
በመጀመሪያ ደረጃ ጉዳዩን የተመለከተው የአማራ ክልል የሰሜን ጎንደር ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በአመልካች በኩል የቀረበው የሰው ምስክር በቂ ነው በማለት የዘረመል ምርመራውን ሳያዝ የልጁ አባት ነው ብሎ ወስኗል፡፡ ይግባኝ ሰሚው ጠቅላይ ፍርድ ቤትም በመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የቀረበውን ማስረጃ በቂ አይደለም ብሎ ውሳኔውን ሙሉ በሙሉ ውድቅ በማድረግ ተጠሪ በቅሬታው ባመለከተው መሠረት የዘረመል (DNA) ምርመራ እንዲደረግ ትዕዛዝ ሳይሰጥ ቀርቷል፡፡
ውሳኔው በሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 36(2) ላይ የተመለከተውን እርምጃዎች ሲወስዱ በመንግሥታዊ ወይም በግል በጎ አድራት ተቋሞች፣ በፍርድ ቤቶች፣ በአስተዳደር ባለሥልጣኖች ወይም በሕግ አውጭው አካላት የሕፃናት ደኅንነት በቀደምትነት መታሰብ አለበት የሚለውን ድንጋጌ እንዲሁም ኢትዮጵያ ባጸደቀችው የተባበሩት መንግሥታት የሕፃናት መብቶች ስምምነት አንቀጽ 4 መሠረት በስምምነቱ ዕውቅና ያገኙትን የሕፃናት መብቶች ተግባራዊ ለማድረግ አስፈላጊ የሆኑ የሕግ የአስተዳደርና ሌሎች ዕርምጃዎችን ሁሉ ተዋዋይ ሀገራት መውሰድ አለባቸው የሚለውን በሚቃረን መልክ የተሰጠ ውሳኔ ነው፡፡
የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚም የአመልካች አቤቱታ ማቅረቢያ ጊዜ አልፎበታል ብሎ አቤቱታውን ውድቅ ማድረጉ በሞግዚቷ ስህተትና በሥነ ሥርዓታዊ ጉዳይ የሕፃኑን ሕገ መንግሥታዊ መብት የሚጥስ ውሳኔ መስጠቱ የሕፃኑን መሰረታዊ መብትና ጥቅም የሚጎዱና በሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 36(1)/ሐ/እና(2) የተደነገገውን ሕፃናት ወላጆቻቸውን የማወቅና ከእነሱም እንክብካቤ የማግኘት መብት የሚጥስ ስለሆነ ጉዳዩ የልጁን ሕገ መንግሥታዊ መብት በሚያስጠብቅ መልኩ ታይቶ ውሳኔ ሊሰጥበት ስለሚገባ የሕገ

ጠበቃ አደም ሰይድ ከማል, [12/26/2025 9:37 PM]
መንግሥት ትርጉም የሚያስፈልገው ነው በማለት ጉባኤው በሙሉ ድምጽ ተስማምቶ ጉዳዩ ለመጨረሻ ውሳኔ ለፈዴሬሽን ምክር ቤት እንዲተላለፍ በማለት የውሳኔ ሃሳቡን አቅርቧል የሚል ነው።
ምክር ቤቱም የአጣሪ ጉባኤውን የውሳኔ ሃሳብ መሠረት በማድርግ በጉዳዩ ላይ የምክር ቤቱ የሕገ መንግሥት ትርጉምና የማንነት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ያቀረበውን የውሳኔ ሀሳብ ተመልክቷል፡፡
በዚህም መሠረት ምክር ቤቱ እንደተረዳው የሕጻን ሱራፌል ወላጅ እናት ሕጻኑ ከአቶ ዘውዱ የተወለደ በመሆኑ አባትነቱ እንዲረጋገጥለት በሰሜን ጎንደር ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ክስ ካቀረበች በኋላ ፍርድ ቤቱ በአመልካች በኩል የቀረበው የሰው ምስክር በቂ ነው በማለት ተከሳሹ የልጁ አባት ነው ብሎ ቢወስንም ይግባኝ ሰሚው የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት በከፍተኛው ፍርድ ቤት የቀረበው ማስረጃ በቂ አይደለም ብሎ ውሳኔውን ሙሉ በሙሉ ውድቅ በማድረግ ተጠሪ በቅሬታው ባመለከተው መሠረት የዘረመል(DNA) ምርመራ እንዲደረግ ትዕዛዝ ሳይሰጥ ቀርቷል፡፡ አመልካቿም ለክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት አቤቱታ ብታቀርብም በተቀመጠው የጊዜ ገደብ ቅሪታዋን አላቀረበችም በማለት አቤቱታውን አልተቀበለውም፡፡
ይሁን እንጂ የሕጻናትን ጉዳይ በተመለከተ በሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 36 ድንጋጌዎች መሠረት ፍርድ ቤቶችም ሆነ ሌሎች የመንግሥት አካላት ሕጻናትን የሚመለከቱ እርምጃዎች በሚወስዱበት ጊዜ የሕጻናት ደህንነት በቀደምትነት መታሰብ እንዳለበት በአስገዳጅ ሁኔታ ተመልክቶ እያለ የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ተጠሪ የሕጻኑ አባት አይደለም በማለት ሲወስንና የሰበር ችሎቱም የአመልካችን አቤቱታ በጊዜ ገደብ ምክንያት ውድቅ ማድረጉ የሕፃኑን ሕገ መንግሥታዊ መብት የሚጥስ እና የሕፃኑን መሰረታዊ መብትና ጥቅም የሚጎዳ ሆኖ ተገኝቷል፡፡
በመሆኑም በሕጻን ሱራፊል ጉዳይ ላይ በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ጠቅላይ ፍርድ ቤት የተሰጠው ውሳኔ በሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 36(1)/ሐ/እና(2) የተደነገገውን ሕፃናት ወላጆቻቸውን የማወቅና ከእነሱም እንክብካቤ የማግኘት መብት አላቸው የሚለውን የሚቃረን ስለሆነ በሕገመንግሥቱ አንቀጽ 9(1) ድንጋጌ መሠረት ተፈፃሚነት ሊኖረው አይገባም በማት ምክር ቤቱ በሙሉ ድምጽ ወስኗል ።
ጠበቃ አደም ሰይድ ከማል

9. የአመልካችን አቤቱታ በፍሬ ነገር ላይ በጥልቀት ሳይመረምርና ሳያጣራ ጠቅላላ የይርጋ ሕግን መሠረት በማድረግ የተሰጠ ውሳኔ የመሰማት እና ትክክለኛ ውሳኔ የማገኘት ሕገመንግስታዊ መብት ጥሰት ነው፤የውክልና የጥቅ ግጭት እና የፍታብሔር ሕጉ አንቀጽ 1845 የ10 አመት ይርጋ ትርጓሜ (የፌዴሬሽን ምክር ቤት ሰኔ 3 ቀን 2012 ዓ.ም የመ/ቁ.67/11)
(ጠበቃ አደም ሰይድ ከማል)
• ክርክሩ በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ በመኖሪያ ቤት ሕብረት ሥራ ማኅበር የተገኘ ቤት በውክልና ተሽጧል የተባለበት ውል የጥቅም ግጭት አለበት የሚል ክስ በይርጋ ቀሪ ሆኗል መባልን የሚመለከት ነው፡፡ አመልካች በከ2ኛ ተጠሪ ጋር ሚያዝያ 17 ቀን 1989 ዓ.ም ተፈፀመ የተባለው ውል በሌለሁበትና ፈቃዴን ሳልሰጥ ስለተደረገ፣ የቤት ሽያጭ ውል መኖሩን ያወቅሁት በ2005 ዓ.ም በመሆኑ ይፍረስልኝ የሚል ዳኝነት ጠይቀዋል፡፡
ተጠሪዎች ክሱ በይርጋ የሚታገድ በመሆኑ ውድቅ እንዲደረግላቸው መቃወሚያ አቅርበዋል፡፡ ፍ/ቤቱም ውል መኖሩን ያወቅኩት በ2005 ዓ.ም ነው የሚለው ክርክራቸው በማስረጃ ስላልተደገፈ በፍ/ብ/ህ/ቁ 1845 መሠረት በ10 ዓመት ይርጋ ታግዷል ብሏል
ይሕ ውሳኔ እስከ ፌደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ጸንቷል።በዚሕ ምክንያት ጉዳዩ ፌደሬሽን ምክር ቤት ቀረበ
• በዚሁ መሠረት አመልካች ቅሬታ ያቀረቡበት የፍርድ ቤት ውሳኔ የሕገ መንግሥት ጥሰት የተፈፀመበት መሆን አለመሆኑን,ምክር ቤቱ መርምሯል፡፡
አመልካች የውክልና ሥልጣን በቀን 08/03/87 ዓ.ም ለ1ኛ ተጠሪ ሰጥቼ ንብረቱን እንዲያስተዳድርልኝ ወከልኩት እንጂ በቀጥታ ለ2ኛ ተጠሪ ያደረግሁት ሽያጭ የለም፡፡ ተጠሪዎች ባልና ሚስት በመሆናቸው ውክልናውን ሰበብ በማድረግ ቤቱን ከመያዛቸው በቀር አመልካች ውክልና እንደሰጠሁ ወደ ኤርትራ በመሄዴ እና የኢትዮ-ኤርትራ ግጭት በመፈጠሩ ወደ ኢትዮጵያ ባለመመለሴ ምክንያት 1ኛ ተጠሪ በውክልና ሥልጣኑ እንደ መልካም አባት ማስተዳደር ሲገባው በሕገ ወጥ ተግባር ለባለቤቱ በመሸጥና እንደእማኝ በመፈረም ያለአግባብ ለመበልጸግና የንብረት ባለቤት ለመሆን ያደረገው ጥረት ነው፡፡
በሌላ በኩል የሕብረት ሥራ ማኅበሩን በመክሰስ በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ቁ/ 130494 በቀረበ ክስ ዝውውር ለማድረግ ሲንቀሳቀሱ የካቲት 25 ቀን 2005 ዓ.ም ማወቄ፣ 2ኛ ተጠሪ ባለቤቷን መወከሌንና ኤርትራ መሄዴን እያወቀች አሰጥታብኝ የነበረው የመጥፋት ውሳኔ መሻሩን፣ የሽያጭ ውሉ ሀሰተኛ ሰነድ እንጂ በአመልካች የተፈፀመ እንዳልሆነ ለማረጋገጥ የፎረንሲክ ምርመራ ቢታዘዝም በዳኛ መቀየር ምክንያት ውጤቱ ሳይታወቅ ሂደቱ ተቋርጦ መወሰኑ፣ ከሕብረት ሥራ ማኅበሩ ማስረጃ ሳይጠየቅ እና ምስክሮች ሳይደመጡ በቀረበ መቃወሚያ ብቻ የተሰጠው ውሳኔ ተገቢነት እንደሌለው እና ክሱ በይርጋ እንደማይታገድ እንዲሁም የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ በመ/ቁ 43600 በማይንቀሳቀስ ንብረት ላይ የሚደረግ ክርክር ይርጋ የለውም ሲል ከሰጠው ውሳኔ ጋር ስለሚቃረን በጉዳዩ ላይ የሕገ መንግሥት ትርጉም እንዲሰጥበት የሚል ዝርዝር ቅሬታ አቅርበዋል፡፡
• የማይንቀሳቀስ ንብረት ላይ የመፋለም ክስ በይርጋ የማይታገድ መሆኑን የፌዴራል ሰበር ሰሚ ችሎት በመዝገብ ቁጥር 43600 አስገዳጅ ውሳኔ መስጠቱ ይታወቃል፡፡ ይህ አስገዳጅ ውሳኔ ተሰጥቶ እያለ ፍ/ቤቱ የአመልካችን ሁኔታና ማስረጃ ሳይመረምር በጠቅላላ ሕግ የተደነገገውን የፍ/ብ/ህ/ቁ/ 1845 በመጥቀስ በይርጋ በብይን መዝጋቱ ተገቢነት የለውም፡፡
• ተወካይ በተወከለበት ጉዳይ ላይ የወካዩን ጥቅምና ፍላጎት ማስከበር ያለበት መሆኑን የእንደራሴነት ሕግ ይደነግጋል፡፡ በዚህም ላይ ተወካይ የጥቅም ግጭት የሚያስነሱ ሁኔታዎችን ማስወገድ ያለበት መሆኑን የፌዴራል ሰበር ሰሚ ችሎት በመ.ቁ. 32241 ቅጽ 5 ላይ አስገዳጅ ውሳኔ ሰጥቷል፡፡
1ኛ ተጠሪ የአመልካች ተወካይ ሲሆኑ፤ ለ2ኛ ተጠሪ ደግሞ ባል በመሆናቸው ተወካይ ከቤተሰቡ ጋር የሚያደርጋቸው ውሎች እና ሌሎች ተግባሮች የወካዩን ጥቅም ስለሚጎዳና የጥቅም ግጭት ስለሚኖርበት ይህንንም ለወካዩ ማሳወቅ ሲኖርበት ባለማሳወቁ ከቤተሰቡ ጋር የሚያደርገው ተግባር ተቀባይነት የለውም፡፡ ይህንንም ፍ/ቤቱ ማጣራት ሲገባው ማለፉ ፍትሐዊነትን ያዛባል፡፡
አመልካች ከኢትዮጵያ ወደ ኤርትራ የሄዱት ሁለቱ ሀገሮች መልካም ግንኙነት እያላቸው እንጂ በጦርነቱ ወቅት ወይም ከጦርነቱ በኋላ አይደለም፡፡
በኢፌዲሪ ሕገ መንግሥት አንቀጽ 40 /2/ መሠረት ማንኛውም ሰው በጉልበቱ፣ በዕውቀቱ ወይም በገንዘቡ የግል ንብረት የማፍራት መብት እንዳለው ተመልክቷል፡፡ በዚህ አግባብ ንብረት ያፈራ ሰው ደግሞ በሕግ አግባብ በንብረቱ የመጠቀም እና የማስተላለፍ መብት እንዳለው በዚህ ድንጋጌ ንዑስ አንቀጽ 1 ስር ተደንግጎ ይገኛል፡፡ አንድ ሰው በሕግ አግባብ ያፈራው የግል ንብረት መብቱን ሊያጣ የሚችለው ሕግ በዘረጋው ሥርዓት ብቻ መሆን እንዳለበት የሚያከራክር ጉዳይ አይሆንም፡፡ በፍርድ ቤት ደረጃ በሚደረገው ክርክር ደግሞ አንድ ሰው የንብረት መብቱን ሊያጣ የሚችለው በኢፌዲሪ ሕገ መንግሥት አንቀጽ 37 ሥር የተመለከተው ፍትሕ የማግኘት መብቱን ባስከበረ ሁኔታና በሕግ በተዘረጋው ሥርዓት መከላከያ እና ተገቢ ክርክር በማቅረብ መሆን እንዳለበት ግልጽ ነው፡፡ከዚህ ሁሉ ሕጋዊ ሂደት ውጪ ግን አንድ ሰው የንብረት መብቱን ያጣ እንደሆነ በሕገ መንግሥቱም ሆነ በዝርዝር ሕጎች የተመለከተውን የሚጥስና ሕግን ያልተከተለ ድርጊት በመሆኑ ተቀባይነት ሊኖረው አይገባም፡፡
ይህ የፍርድ ቤት ብይን የአመልካችን አቤቱታ በፍሬ ነገር ላይ በጥልቀት ሳይመረምርና ሳያጣራ ጠቅላላ የይርጋ ሕግን መሠረት በማድረግ የተሰጠ ነው፡፡ በዚህ መልኩ የተሰጠ ፍርድ የአመልካችን በሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 37 ንዑስ አንቀጽ 1 ላይ የተደነገገውን የመሰማትና ትክክለኛ ውሳኔ የማግኘት እና በሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 40 ንዑስ አንቀጽ 1 እና 2 ላይ የተደነገገውን የንብረት መብት በመቃረን የተወሰነ ነው፡፡

ጠበቃ አደም ሰይድ ከማል(0910214108)
በመሆኑም የፍ/ቤቶች ውሳኔ የሕገ መንግሥቱን አንቀጽ 37 ንዑስ አንቀጽ 1 እና አንቀጽ 40 ንዑስ አንቀጽ 1 እና 2 የሚቃረን ስለሆነ በሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 9(1) መሠረት ተፈጻሚነት የለውም በማለት ምክር ቤቱ በሙሉ ድምጽ ወስኗል፡፡
10. ይዞታው ለእርሻ የሚውል (የተመደበ) ሲሆን በዚህ አይነት ይዞታ ላይ አተክልትና ቤት አለው በሚል ምክንያት የሚደረግ ሺያጭ ሆነ የመያዣ ውል መሬቱን ከመሸጥ ወይም ከማስያዜ የተለየ ውጤት አይኖረውም በማለት የፌደሬሽን ምክር ቤት ውሳኔ ሰጠ=መጋቢት 3/2008
11. ግራ ቀኙ ጉዳዩን በግልግል ዳኝነት ለመጨረስ ተስማምተዉ ፍ/ቤቱ አልተስማሙም በማለት የቀረበዉን መቃዎሚያ ዉድቅ አድርጎ ጉዳዩን ተቀብሎ ማየቱ የህገ መንግስቱን አንቀጽ 37(1) መሰረት የዳኝነት ስልጣኑ ለሌላ አካል ተሰጥቶ ባለበት ሁኔታ ስልጣን ሳይኖረዉ ጉዳዩን ተቀብሎ መመልከቱ ህገ መንግስታዊ ጥሰት ነዉ(የፌደሬሽን ምክር ቤት መ/ቁ 125/2016 መስከረም 28/2017 ዓ/ም)
12. የገጠር መሬት ይዞታን ሲጠቀም በቆየ ሰው ላይ ይርጋን ተፈጻሚነት የለዉም፡-
️በመሠረቱ የይርጋ ደንብ ተፈጻሚ የሚሆነው ከፈቃድ፡ ከውል ወይም ከሕግ ውጭ ንብረት ተይዞ በሚቆይበት ጊዜ እንጂ የንብረቱ ባለቤት በንብረቱ እየተጠቀመ ከቆየና ፍቃዱ ባለበት ሁኔታ አይደለም፡፡
️ አንድ ሰው በይርጋ ምክንያት መብቱን የሚያጣው በንብረት መብቱ መጠቀም ሲያቆም እንጂ በንብረቱ እየተጠቀመ የቆየን ባለመብት ይርጋ የሚያግደው አይሆንም፡፡ ይህ መርህ ለሁሉም ንብረቶች ተፈጻሚነት ያለው ሲሆን ለመሬት ይዞታ የውርስ ክርክርም ተፈጻሚነት የሚያጣበት ምክንያት አይኖርም፡፡
️በመሆኑም በመሬት ይዞታ መብቱ ይጠቀም የነበረ ግለሰብ በይርጋ ምክንያት መብቱን ሊያጣ የሚችለው በይዞታው መጠቀም ሲያቆም እንጂ በመሬቱ እየተጠቀመ የቆየን ባለመብት ይርጋ የሚያግደው አይሆንም በማለት የኢፌዲሪ የፌዴሬሽን ምክር ቤት
5ኛ የፓርላማ ዘመን፣ 4ኛ ዓመት፣ 2ኛ መደበኛ ጉባዔ ሰኔ 02 ቀን 2011 ዓ.ም አስገዳጅ ውሳኔ ሰጥቷል።
13. ባልና ሚስት በሕግ የሚፀና ፍቺ መፈጸማቸውን የሚያስረዳ ማስረጃ ባይኖርም በአካል ተለያይተው ከኖሩና ሁለቱ በየፊናቸው የየራሳቸው ሕይወት መሥርተው መኖር መጀመራቸው ከተረጋገጠ ጋብቻቸው ከ10 ዓመት በኋላ እንደፈረሰ ይቆጠራል እንድሑም በጋብቻ ውስጥ የተፈራው የባልና ሚስት የጋራ ንብረት ጥያቄ ደግሞ በይርጋ በ10 ዓመት ጊዜ ውስጥ ቀሪ ሆኗል በማለት የተሰጠው ውሳኔ ሕገመንግስታዊ ድንጋጌዎችን ይቃረናልና ተፈጻሚነት የለውም(ፌዴሬሽን ም/ቤት 3/10/ 2012 ዓ.ም ፤መ/ቁ. 77/12)
ጠበቃ አደም ሰይድ ከማል(0910214108)
https://t.me/adem2141

30/11/2025

We are Back!

ሁለቱ የዐማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (ዐብን) መሥራችና ጠንካራ አመራር የነበሩት ተሰማ ካሣሁን እና በቀለ ምንአለ በቃን ብለው ከፓርቲው ለቀዋል‼
01/04/2023

ሁለቱ የዐማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (ዐብን) መሥራችና ጠንካራ አመራር የነበሩት ተሰማ ካሣሁን እና በቀለ ምንአለ በቃን ብለው ከፓርቲው ለቀዋል‼

አሁን ሥራ ላይ ባለውና የሀገር ማፍረሻ በሆነው የሀገረ ኢትዮጵያ ሕገ መንግሥት መሠረት የአንድ ክልል ፖሊስ ሠራዊት በሦስት ዓይነት ምድብ ይደራጃል፤ ይኸውም መደበኛ ፖሊስ፣ አድማ በታኝ ፖሊስ...
01/04/2023

አሁን ሥራ ላይ ባለውና የሀገር ማፍረሻ በሆነው የሀገረ ኢትዮጵያ ሕገ መንግሥት መሠረት የአንድ ክልል ፖሊስ ሠራዊት በሦስት ዓይነት ምድብ ይደራጃል፤ ይኸውም መደበኛ ፖሊስ፣ አድማ በታኝ ፖሊስ፣ ፈጥኖ ደራሽ ፖሊስ እና ልዩ ኃይል ፖሊስ በመሆን የሚደራጅ ነው።
ይህም በመሆኑ አሁን ልዩ ኃይል ትጥቅ ፈቶ ወደ ፖሊስ ይቀላቀል ወይም ይበተን የሚል ወሳኔ እንደተላሉፈ የሚነገረው ነገር ሁሉ ሕገ ወጥና ሌላ ዓላማ ያለው በተለይም ደግሞ ዐማራን ፖሊስ እንዳይኖረው ለማድረግ ሲባል የተሸረበ ሴራ ነው።
ስለሆነም ጉዳዩ እንዲህ በቀላሉ የአንድ ሰሞን ጫጫታ ብቻ ሆኖ እንዳይቀር፣ ትጥቅ የሚፈታ አንዳች የልዩ ኃይል አባል የማይኖር መሆኑ እንደተጠበቀ ሆኖ፣ ጉዳዩን ወደ ፌዴሬሽን ምክር ቤት በመውሰድ የዚችን ወለፈንዲ ሀገር የምንፈትሽበት የመጨረሻ ዕድል ይሆናል።
ዐባት ሀገር ዐማራ ወይም ሞት‼

01/04/2023

ምንም አያደርግም ተብለህ ስትናቅ የሚጠላህ የጎረቤትህ ውሻ በርህ ላይ መጥቶ ይሸናል‼

30/03/2023

መብረቅ ሁለቴ አይመታም!!

30/03/2023

In the end, Amhara shall prevail‼

ዐማራ ማደንዘዣው ይበቃሓል። ከለውጥ ተብዬው ድራማ በኋላ ታግለው ያታግሉኛል ያልካቸው ብአዴንም ዐብንም ከዚያ በፊት በጅምላ ቀርቶ በተናጠል በየቀኑ ያለማሰለስ ከማትገደልበት ወደ በየቀኑ ያለማ...
29/03/2023

ዐማራ ማደንዘዣው ይበቃሓል።

ከለውጥ ተብዬው ድራማ በኋላ ታግለው ያታግሉኛል ያልካቸው ብአዴንም ዐብንም ከዚያ በፊት በጅምላ ቀርቶ በተናጠል በየቀኑ ያለማሰለስ ከማትገደልበት ወደ በየቀኑ ያለማሰለስ በጅምላ የምትገደልበትና የምትፈናቀልበት አድርሰውሓል - የጀመርከውን አብዮት አጨናግፈው።

ያኔ በእነሱ መተማመንህ ተቀባይነት ነበረው ብለን ብንወስድ ዛሬ ከዚህ ሁሉ በኋላ ግን ሞኝነት ነው። በእነሱ እየተመራህ የምታተርፈው ከነበረው የየቀን እልቂትና መፈናቀል እጅግ የገዘፈ ነው የሚሆነው። ሌላ የሚታመን ቢሆንም እንኳ በፓርቲ የፖለቲካ ትግል መዳን ፈጽሞ አይቻልም - #ረፍዷል።

መዳኛህ ልክ እንደ ጽዮናዊያን የጸነፈ ብሔርተኝነትና የነፍጥ ትግል ነው። መዳኛህ ፋኖነት ብቻ ነው። በጠንካራ ክንድኽ ጠላትን ከደቆስክ በኋላ በፖለቲካውም አሸናፊ ትሆናለህ። ዓለም የኃያላን ናት። ከዐባት ሀገር ሩሲያም ትምህርት ውሰድ።

ጽንፈዓለሙ የዐማርኛ ቋንቋ በዐባት ሀገር ሩሲያ‼_______________ የፑቲን ሀገር ሩሲያ የአማርኛን ቋንቋ በሩሲያ ትምህርት ቤቶች ማስተማር ልትጀምር መሆኗን አስታውቃለች። በሞስኮ ስቴት ...
29/03/2023

ጽንፈዓለሙ የዐማርኛ ቋንቋ በዐባት ሀገር ሩሲያ‼
_______________

የፑቲን ሀገር ሩሲያ የአማርኛን ቋንቋ በሩሲያ ትምህርት ቤቶች ማስተማር ልትጀምር መሆኗን አስታውቃለች። በሞስኮ ስቴት ዩኒቨርሲቲ የእስያ እና የአፍሪካ ሀገራት ኢንስቲትዩት ዳይሬክተር አሌክሲ ማስሎቭ እሁድ እለት በሩሲያ-አፍሪካ አለም አቀፍ የፓርላማ ጉባኤ ላይ እንደተናገሩት ሩሲያ የአፍሪካ ቋንቋዎችን አማርኛንና ስዋሂሊን በሩሲያ ትምህርት ቤቶች ለማስተማር እየተዘጋጀን ነው ብለዋል።

እንደሚታወቀው ቻይና አማርኛ ቋንቋን በመጀመሪያ ዲግሪ እያስተማረች ነው። ትምህርቱ በቤጂንግ የውጭ ጥናት ዩኒቨርስቲ (BFSU) መሰጠት ጀምሯል። ከጀርመን ታዋቂ ከሆኑት ዩኒቨርስቲዎች አንዱ የሆነው ሀምቡርግ ዩንበርሲቲ የአማርኛ ት/ ት ማስተማር ከጀመረ መቶ ዓመት አልፎታል።

አማርኛ ቋንቋን በ2007 ዓ.ም.የአፕል የቴክኖሎጂ ማዕከል አማርኛን ከዓለም ግዙፍ ቋንቋዎች ተርታ መድቦ የቴክኖሎጂ ቋንቋ አድርጎታል። በ2008 ዓ.ም. የጎግል የቴክኖሎጂ ማዕከል የመተርጎሚያ ቋንቋ አድርጎታል። Dstv'ም የአለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና፣የኦሊምፒክ ውድድሮችን ጨምሮ የእንግሊዝ ኘሪሚየር ሊግ ፣ የስፔን ላሊጋ ፣ የጣሊያን ሴ ሪ ኤ እንዲሁም ቻምፒየንስ ሊግ ጨዋታዎችን በአማርኛ ቋንቋ እንዲተላለፉ ከወሰነ አመት አስቆጥሯል።

አማርኛ በUS አሜሪካ የመንግስት ቋንቋም ነው። እንዲያውም በአሜሪካዋ ቨርጂኒያ ግዛት አሌክሳንድሪያ ዳሽ የሚባለው የከተማ አውቶቢስ ላይ "እንኳን ወደ በደህና መጣችሁ!" የሚል ጽሁፍ ማየትም የተለመደ ነው።
ዐባት ሀገር ዐምሓራ ወይም ሞት‼

የዲሞክራሲ ምድረ በዳ በሆነች ሀገር፣ ዐብን መንግሥ ት ሥልጣኑን በምርጫም ይሁን በልመና እንደማይለቅ እስካሁን ድረስ አያውቅም እንዴ? ባያውቁ እንኳ አስረግጠን እየነገርናቸው ነው ምርጫ የተሳ...
28/03/2023

የዲሞክራሲ ምድረ በዳ በሆነች ሀገር፣ ዐብን መንግሥ ት ሥልጣኑን በምርጫም ይሁን በልመና እንደማይለቅ እስካሁን ድረስ አያውቅም እንዴ?

ባያውቁ እንኳ አስረግጠን እየነገርናቸው ነው ምርጫ የተሳተፉትና ከዚያም ባለፈ ጦርነቱን ጨምሮ በብዙ ጉዳዮች ከጎኑ የተሰለፉት።

#በግልፅ "... ምርጫ በመሳተፍ ገዳዩንና ሕገ- ወጡን ቡድን መንግሥታዊ ቅርጽ እንዲኖረውና ሕጋዊ እንዲመስል እውቅና መስጠት ነው፤ ይኸንን ማድረግ ከምርጫ በኋላ በእርግጠኝነት ለሚፈፀመው እልቂት ገዳይን መተባበር ነው... ያኔ ?..." ብለናችኋል። በተያያዥ የዐማራን ትግል ያለ ዐብን ብአዴን ለምን ማጨናገፍና ማሳት እንደማይችልም አብራርተናል - ባይሰወርባቸውም።

አሁን የዐማራ ትግል ላይ ውኃ ቸልሰው፣ ሕዝቡን አሳስተውና አስተኝተው እንደተፈራው አስጨርሰው፣ እልቂት እንዲፈጸምበትና እንዲፈናቀል ተባብረው ሳለ " " ወይም " " ብሎ መጠየቅ ምን ለመፈየድ ነው?? መልሱ ቀድሞ የታወቀ ነው - የነገርናችሁ። በዚህ መንገድ ሥልጣን አይለቅም። ሥልጣን እንዲለቅማ "ምርጫ በመሳተፍ" የትግል ሥልትና መንገድ እንዲሳት አታድርጉ ተብላችኋል። ደጋግሜ አስታውሳችኋለሁ - ማንም ቢሰለችም፤ ምክንያቱም አሁንም ከልባቸው ሥልጣን እንዲለቅ ቢፈልጉ ዐብይን ሥልጣን እንዲለቅ ከመጠየቅ ይልቅ ወልቃይትና ራያን በተመለከተ፣ መከላከያ የፈፀመውን ደባ፣ የታሰሩ ፋኖዎች፣ እየተሳደዱ ያሉ ፋኖዎች፣ በወለጋ የተፈፀመው ሁሉ በመንግሥት እንጂ በሌላ በማንም አለመሆኑን (ባይሆን ኑሮ ማስቆም ቀላል መሆኑን)... ወዘተ አስታውሶ ለ ዐማራ፣ ፋኖ፣ ሌሎች ብሔሮች ወዘተ የባሰ ነገር ከመፈጠሩ በፊት በአንድነት ለትግል ተነስ ብሎ ጥሪ ማድረግ ነበር። ፓርላማ ውስጥ በጠነከረ መልኩ መጥራት ባይቻል እንኳ ይኸ ሁሉ እልቂትና መፈናቀል እንዲሁም ወረራ ባለበት ጥፋቱን ቅንጣት እንኳ ለመቀበል ፈቃደኛ ስላልሆነ ከእንግዲህ በዚህ መልኩ በፓርላማም በሌላም አብሮ መቆዬት አብሮ አገር ማፍረስና ሕዝብ ማስጨረስ ነው በሚል ረግጦ በመውጣት ትክክለኛውን መንገድ ማመላከትም ይቻል ነበር። ረግጦ ከወጡ በኋላ ደግሞ በፓርቲ/ፓርቲዎች (በተናጠልም በጋራም) ሕዝባዊ እምቢተኝነት መጥራት ይቻል ነበር። በፊት እንኳ ይደረግ ነበር።

ስለዚህ የምርና ከልብ አይደለም፤ ማስመሰል ነው።

Address

GAMBIA
Addis Ababa
251

Opening Hours

Monday 00:00 - 23:59
Tuesday 00:00 - 23:59
Wednesday 00:00 - 23:59
Thursday 00:00 - 23:59
Friday 00:00 - 23:59
Saturday 00:00 - 23:59
Sunday 00:00 - 23:59

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Zephaniah Alemu - ዘፋኒያህ ዓለሙ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Zephaniah Alemu - ዘፋኒያህ ዓለሙ:

Share