ሕግ ቲዩብ Hig Tube

ሕግ ቲዩብ Hig Tube የሕግ ቢሮ - Law Office

03/02/2026

FANo !
!
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) ፥ የአማራ ሕዝብ መሪ ድርጅት ነው !!!

01/02/2026

የመግቢያ ቃል
===>
እንደዋርካ ጥላ ለአስሩ ደብር ወንድየ ሕዝብ መሰባሰቢያ የነበረው የመቶ አለቃ ጥሩነህ አባተ ጊዜ እና ትውልድ የጣሉበትን የታሪክ ቋጠሮ ተሸክሞ ሰው በሚፈለግበት ጊዜ ሁሉ ከፊት ኖሮ ሄዷል። 'ታምነህ የተሰጠኸውን አደራ እንደዐይንህ ብሌን ጠብቀው' የሚለውን አባታዊ አደራ ቆሜ ተቀብየዋለሁ። ለአገር እና ለሕዝብ ዋስትና የሚበቃ ሰው 'ታምኖ የተሰጠውን አደራ እንደውሀ ገድቦ፣ እንደጉም ሰብስቦ፣ እንደወተት አርግቶ፣ እንደጤፍ ጥሬ ደብቆ እና እንደፍትሕ በአደባባይ አሰምቶ በሚፈለግ ጊዜ መልሶ የሚሰጥ ነው' ይላል። የታመንሁበትን አደራ የትኛውም አይነት ይሁን ከነሙሉ ክብሩ መጠበቅ በትንሹ የሞከርሁት ወደፊት በሙላት የምኖረው የእደርስበት የሕይወት መሻቴ ነው።

እኔ 'ኢትኖግራፊክ ጸሐፊ ነኝ' ብየ አምናለሁ። ኢትኖግራፊ ከተገላጩ ማህበረሰብ ጋር አብሮ በመኖር በታዛቢነት እና በተሳታፊነት ሕይወቱን በመቅመስ የሚጣፍጠውንም ሆነ የሚመረውን እንደወረደ የመሰነድ ጉዳይ ነው። 'የእውቀት ምንጩ ማህበረሰቡ ነው' ማለት ነው። ማህበረሰቡ የኔ ብሎ የያዘውን የጋራ እምነት፣ እውቀት፣ እውነት፣ ባሕል፣ የኑሮ ፍልስፍና እና ማንነት በገላጭ ክዋኔያዊ ድርጊት፣ በሐተታ ተፈጥሮ፣ በትውፊት፣ በተረክ እና ታሪክ መልክ እያስተላለፈ ትውልድ ይመራበታል። የ'እንዲህ አድርግ እና እንዲህ አታድርግ' የልማድ ሕግ እያወጣ ስርአት ይጠብቅበታል። ማህበረሰብ ያጸናበታል። ስለሆነም እግሬ በደረሰበት ሁሉ ያገኘሁትን በኢትኖግራፈር አይን ሳነሳ ኖሬያለሁ። ይህ የ'አማራነት ጥቁር ሰው' መጽሐፍም በኑሮ ምልከታ፣ በስራ አጋጣሚ ተሳትፎ፣ በነገር አስረጂ ቃለመጠይቅ እና ውይይት እንዲሁም በማመሳከሪያ ንባብ ድምር እይታ ተጨምቆ የቀረበ ነው።

'አማራነት ጥቁር ሰው' ከ'ታሪክ እና ትውፊት' ቀጥሎ የአያቴን አደራ ለመወጣት የተሰጠኝን ለመስጠት የሞከርሁበት ሁለተኛ ስራየ ነው። በ'ታሪክ እና ትውፊት' መጽሐፍ ሁለተኛው ምእራፍ 'የአባቶቼ እርስት' በሚለው ንዑስ ርእስ ስር እንደተቀመጠው 'የሁላችንም የሕይወት መንገድ ዳዋ እንደመጣስ ያለ ነው፡፡ ሳናስተውል ከተጓዝንበት ጎዳና ቆም ብለን ካሰብነው ታሪካችን' ነው፡፡ ከዚህ አንጻር 'አማራነት ጥቁር ሰው' ሦሥት ትውፊታዊ የታሪክ እርከኖችን የሚዳስስ ነው። እነዚህ ትውፊታዊ የታሪክ እርከኖች የጥቁር ሰው ምሳሌ፣ ጥቁር ሰው እና አማራነት የሚሉ ናቸው። የጥቁር ሰው ምሳሌዎች ብሔራዊ አርበኞች ናቸው። ለሕዝብና ለአገራቸው የሚቆጠር፣ የሚጨበጥና የሚዳሰስ ሞያ የሰሩ ናቸው። ጥቁር ሰው ዓለምአቀፍ አርበኛ ነው። ስሙ ለራሱ ሕዝብ ብቻ ሳይሆን ለሌሎችም የሚተርፍ ነው። አማራነት ደግሞ የጥቁር ሰው ምሳሌ ነው።

ከዚህ አንጻር ከአያሌ የጥቁር ሰው ምሳሌዎች መካከል አርሶ ማደር የጋረዳቸው የመቶ አለቃ ጥሩነህ አባተን፣ ሐገር ጠባቂው ቀኝ አዝማች ባብል ደስታን፣ የወንዶች ቁና በላይ ዘለቀን እና ደንቢያ ላይ የልብ ሐውልት የቆመላቸውን የደጃዝማች ማሩ አካሉን ትውፊታዊ ታሪኮች ይዟል። የጥቁር ሰው ርዕይ መነሻ፣ መድረሻ ወይም ፍኖት እና መዳረሻ የሆኑትን እውነተኛውን ጥቁር ሰው ዳግማዊ አጼ ምኒልክን ደግሞ ጥቁር ሰው ከሸዋ እስከ አድዋ በሚል ታሪካዊ ሐተታ አካቷል። የጥቁር ሰው ሕልምና ትልም ማሰሪያ የሆነውን አማራነት ከውጭና ከውስጥ በሚነሳ የእይታ መነጸር በመዳሰስ በስብስቡ የመጨረሻው ምእራፍ ተቀምጧል።

ውጫዊ እይታው በስልጣኔ የሩቅ ህዝብ የሆነውን አማራን ያለ ስሙ ስም ሰጥተው፣ ያለ መልኩ መልክ አበጅተው ከገናና ማንነቱ አውርደውና አዋርደው የተጠላ፣ የሚጠቃና የሚጠፋ ወይም ጠቅላላ እጣፋንታው በሌሎች የሚወሰን ተቅበዝባዥ የሆነ ህዝብ ለመፍጠር የደከሙትንና የሚደክሙትን ስሁት ሐተታና የተፈጸመ የተግባር እቅድ የሚያመላክት ነው። በአንጻሩ ውስጣዊ እይታው ባለፈ የማህበረሰብ ስሪትና መንግስታዊ ልምምድ ስርአት የገባ የነበረው የአማራ ህዝብ በራሱ የውስጥ ጉድለት ያገኘውን የወል ማንነት መፍረስ እና የሌሎች መጠቀሚያ የመሆን ተጨባጭ አውድ ከእነመፍትሄው ለመጠቆም የተሞከረበት ነው። ከዚህ አይን በታሪክ አጋጣሚ የረገጥሁትን የሕይወት ዳና በተረዳሁት ልክ በመክተብ ለመጭው ትውልድ ምስክር እና ማመሳከሪያ ሆኖ እንዲያገለግል በማሰብ የተዘጋጀ መሆኑን እየገለጽሁ መልካም ንባብ እንዲሆንላችሁ እመኛለሁ።

ቃልኪዳን ግርማው ገበያው ( ጋዜጠኛ)

የቀድሞ የአሚኮ ም/ስራ አስኪያጅ የአሁን አርበኛ

31/01/2026

እንኳን ለ 86ኛው የአገው ፈረሰኞች ማህበር ክብረ በአል በሰላም አደረሳችሁ!!

27/01/2026

የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ የወታደራዊ ስልጠና መምሪያ ኃላፊ አርበኛ ሳሙኤል ባለእድል በድርጅታችን ምስረታ ሂደት እና ሌሎች ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ከFree Press ሚዲያ ጋ ያደረጉት ቃለ-ምልልስ ዛሬ ከቀኑ 8:30 ይለቀቃል።

Amhara Fano National Movement
https://x.com/afnm_official
https://t.me/Afnmnewschannel

06/01/2026

እንኳን ለጌታችን ለመድኀኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ በዓለ ልደት አደረሳችሁ፤ አደረሰን!!!
************************************
ልደቱ ከልደታት ይበልጣል። የተወለደውም ከተወለዱት ይልቃል። መወለዱም ለሌሎች ነጻነትን፣ ሕይወትን እና ክብርን ይሰጣቸው ዘንድ ነው እንጂ ለራሱ በመወለዱ የሚጠቀም ሆኖ አይደለም። ልደቱም ከአእምሮ በላይ ነው። ንጉሠ ሰማይ ወምድር ሲሆን በከብቶች በረት ተወለደ። መላእክት በፊቱ በመንቀጥቀጥ የሚያመሰግኑት ሲሆን አህያ እና ላም በፊቱ ቆመው እስትንፋሳቸውን ገበሩለት። ለቅዱሳን የብርሃን ልብስን የሚያለብስ ሲሆን በእራፊ ጨርቅ ተጠቀለለ። በሁሉ የመላ፣ የማይወሰን ሲሆን በግርግም ተጠቀልሎ ተኛ.......። ይህ ሁሉ ስለትሕትና የተደረገ ነው። ይህ ሁሉ ስለ ሰው ልጆች የተከፈለ ነው። ይህ ሁሉ ስለ ነጻነት፣ ክብር እና ሕይወት(ድኅነት) የተከፈለ ነው።

ምንም እንኳን ልደታችን ከልደቱ፣ ባሕርያችን ከባሕርይዉ፣ ሥራችን ከአምላካዊ ሥራው ባይተካከል በልደቱ አንጻር ግን የምንማረው አለ። የተወለድንበት ሰዋዊ ዓላማ ቢኖረንም ስለሌሎች መኖርን፣ ለሌሎች ዋጋ መክፈልን፣ ስለ ሎሎች ተወልዶ ስለ ሌሎች ተላልፎ መሰጠትን እንማራለን። ክርስቶስ ስለሰው ልጆች ተወልዶ ብቻ አልቀረም፤ ስለሰው መከራ ተቀበለ፣ ሞተ፣ ተነሣም እንጂ። እኛም ዛሬ ለነጻነት፣ ለሰብአዊ ክብር፣ ለእውነት መከራ እንቀበላለን፤ እንሞታለን። ክብር እና ነጻነት ያለ ሞት(መሥዋዕትነት) የተገኙበት ጊዜ የለም። በነጻነት እና በክብር ላይ የሚደረግ ውስልትና ግን ነውርም ኃጢአትም ነው።

ስለነጻነት እና ክብር ብላችሁ በዱር በገደሉ የምትዋደቁ የሠራዊታችን አባላትና አመራሮች፣ ለተከበርከው የአማራ ሕዝብ እና በዓሉን ለምታክብሩ ሁሉ መልካም በዓለ ልደት እንዲሆንላችሁ እንመኛለን።

በድጋሚ እንኳን ለበዓለ ልደቱ አደረሳችሁ!!!

አዲስ ትውልድ፣ አዲስ አስተሳሰብ፣ አዲስ ተስፋ!!!

በአፋብኃ ቴዎድሮስ ዕዝ የ102ኛ ኮር ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ
ታኅሣሥ ፳፰/ ፳፻፲፰ ዓ.ም

ማይክልነት ይለምልም ፥ ቲባግነት ይውደም !!
19/12/2025

ማይክልነት ይለምልም ፥ ቲባግነት ይውደም !!

የጀግና መንገድ አንድ ብቻ ነው
=================
አርበኛ Chalachew Tafere እንደከተበው

የጀግና መንገድ ምርጫ የማይፈለግበት አንድ ብቻ ነው። መንገዱን ግን በዓላማቸው ያልቆረቡ ከእፋቸው ያልፀዱ ፣ እንጥፍጣፊ የሞራልም፣ የህሊናም፣ የፍትሕም፣ የርትዕም ተጠየቅ ያልፈጠረባቸው ራሳቸውንም ማንነታቸውን ሃገራቸውንም ባህልና ሃይማኖታቸውን ሁሉ የረሱ ሃጣን ደፍረው አይሞክሩትም።
ዓለምን ያልናቁትም በፍፁም አያስቡትም። የወላዋዮችም የእግራቸው ጫፍ አይነካውም። ሳያስቡ በድንገት ዘው ብለው ከገቡበትም አንድ ጋት እርቀት ሳይጓዙበት የመንገዱ ደብዛ ይጠፋባቸዋል። እነሱም ይጠፋሉ።
የጀግኖች መንገድ ሞትን እንደ ተራ ነገር የናቁ፣ አስፈሪውን መላዕከሞት በእጃቼው ጨብጠው አርበድብደው መዳፋቸው ላይ እንደ ጨው አሟሙተው ጉሮሮውን ሲጥ አድርገው ገድለው አስረው፣ ገንዘው እንዳይነሳ አድርገው የረገጡ ህያው ጀግኖች፤ በፍፁም የአርበኝነት ተጋድሎ በሚያፈሱት የደም ፍሳሽ የሚፀና ሳይኮሰኩሳቸው ስለሰነቁት ትልቅ አላማ ሲሉ እንደ ቅዱስ ጊወርጊስ መሰንጠቅን ፣ መቃጠልን፣ መቀላትን በቃ ምንም አይነት ምድራዊ ግፍና ሰቆቃን ከቁብ ሳይቆጥሩት አጥንታቸውን እንደ ዋርካ ፍልጥ ሰንጥቀው ፥ እንደ አሳ ሾህ ከስክሰው ፥ እንደ ጃርት ወስፌ መሬት ላይ ተክለው ፥ በሰረገላ ላይ በግርማ እንደ ተሞሸረ ሙሽራ በእልፍኝ ውስጥ እንደተጋበዘ የክብር እንግዳ ትክ የሌላትን አንድያ ሕይወታቸውን ፍፁም ደስ እያላቸው በክብር ሰጠው እንደ ሰልስቱ ደቂቅ በእሳት እቶን ውስጥ በክብር አልፈው የቆረቡለትን ዓላማ ቅንጣት ሳያዛንፉ የክብር አክሊልን የሚቀዳጁበት ፣ መንታ አልባ ፣መስቀለኛም አማራጭም የሌለው ፥ እንደፈለጉ የማይንሸራሸሩበት ፣ ደስታም መከራም እንደ ሁኔታው የሚፈራረቁበት ፥ ሽንፈት አንጎልን በመርፌ የተወጋ ያክል ጥልቅ ህመም እየተሰማህ ለድል የምትፀናበት ተሰውተህ የምታስመዘግበውን ድል እስከ መጨረሻው ድረስ አይነኬ አድርገህ ጠላቶችህ የማይደርሱበት ቦታ አርቀህ ለመስቀል የከፈልከውን ዋጋ ወደ ደስታ ቀይረህ ወደ ተሻለ የሞራል ልዕልና የምትሸጋገርበት ከጭራ የቀጠነ ወደ ኋላ የማይመለሱበት ሽንፈትን የማያስተናግድ የድል መንገድ ነው።
የጀግና መንገድ ምርጫ የሌለው በከበሩ ዋጋወች የሚገነባ እጅግ በጣም ውድ የሆነ ምርጫ የሌለው አንድ ቀጭን መንገድ ብቻ ነው።
ለቆረብንለት ታላቁን የአማራ ህዝብ ህልውና የማረጋገጥ አላማ ዳር ሳናደርስ ላንመለስ እጅግ ክብር እና ውድ የሆነውን የጀግኖችን ቀጭኗን መንገድ ብቻ ተከትለን ወደፊት እንራመዳለን።
ድል ለታላቁ የየአማራ ህዝብ !!
ድል ለጀግናው አማራ ፋኖ !!
አዲስ ትውልድ፣ አዲስ አስተሳሰብ ፣ አዲስ ተስፋ !!

ሕግ ቲዩብ Hig Tube
23/09/2025

ሕግ ቲዩብ Hig Tube

በአማራነት- ለአማራነት እንሰለጥናለን- እንታጠቃለን❗️
-
አፋብኃ ም/አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ
9ኛ ሳሙኤል አወቀ ክፍለጦር
ሶማ ብርጌድ ምሩቃን የተላለፈ መልዕክት ፤
-
በቅድሚያ በዚህ የአማራ ትግል ክስተት ለሆነው ውጤት የሆነው ምረቃ ላይ ለተገኛችሁ ታዳሚያን በሙሉ እንኳን ደስ ያላችሁ ለማለት እወዳለሁ።

ይህ ቁጭት የወለደው ሰልጣኝ ነው !!
ይህ ንዝረት የሆነ ትውልድ ነው !!

የዛሬ ሰልጠኞች አማራ ከሰብአዊ እና ብሔራዊ ክብሩ ከመዋረድ አልፎ ጥፋት ሲታወጅበት ይህን አዋጅ ለመቀልበስ ህልውናችሁን በክንዳችሁ ለማስከበር የወጣችሁ የአማራነት ሰልፈኞች ናችሁ።

እናንተ ሰልጣኞች አማራን ከዘመናት አክሳሪ የጦርነት ውርስ ብሎም የስልጣኔ ጸርነት ከወለደው ጠላትነት ለማዳን በዚህ ወሳኝ ወቅት የተገኛችሁ በመሆናችሁ የዘመኑን ትውልድ ዕዳ ተሸክማችኋል። በዚህም አማራ በስስት የሚጠብቃችሁ የአማራነት ክንድ ናችሁ።

ስልጠናችሁ የስነ ልቦና፣ የአካል፣ የስልት ብቻ ሳይሆን የአላማም ነው። የምንዋጋው ፖለቲካዊ አላማን በወታደራዊ እና ሌሎች አቅሞች ለማሸነፍ ነውና። ይህ አይነቱ ትግል ደግሞ የጠራ አላማን መታጠቅ ይሻል።
ራዕያችን ነው። ይህ ራዕይ እንዲሳካ በቅድሚያ ከፊታችን የህልውና አደጋ የጋረጠውን የአረመኔው አብይ አገዛዝ ማስወገድ የሁላችን ግዳጅ ነው።

የዛሬ ተመራቂዎች እውነት እና ቅንነት ላለበት ትግል የሚያስፈልገውን ሁለንተናዊ ብቃት ታጥቃችሁ በመገኘታችሁ ባለ ዕዳ ብቻም ሳይሆን ዕድለኞችም ናችሁ። የአዲሱ ትውልድ አካል ናችሁና ዕድለኞች ናችሁ።

ይህ ትግል አማራነትን የመረጡ፣ አማራ ሊጠፋ አይገባውም የሚሉ ነው፤ አማራ መንግስት እና ሀገር አልባ ሆኖ አይቀጥልም በሚል ጽኑ እምነት ለአማራነት የቆረበው ትውልድ ትግል ነው። ይህ የአዲሱ ትውልድ ትግል ነው፤ እናንተ ዘመነኞቻችሁ፣ አባቶች ብሎም የአያቶች ዘመን ሳይቀር የተፈጸመውን ስህተት የምታርሙ ናችሁ።

እኛ አማራነትን ከሚሸሽገው እና ከአማራነት ከሚደበቀው ትውልድ፣ አማራን ሁለተኛ አድርጌ ልኑር ከሚለው ትውልድ፣ ከጠላት ጋር ተባብሮ ሽልማት ከሚቀበለው ትውልድ፣ አማራን በሚያስከብረው ሀገር አቅኝነቱ ጥፋተኛ አድርጎ ሲያጠቃ ከነበረው ትውልድ የተላቀቅን፣ የተፋታን አዲስ ትውልድ ነን፤ ናችሁ።።

ዘመኑ የሚጠይቀውን የአስተሳሰብ፣ የአሰላለፍ እና የመሻት አዲስነት የተቀበልን ትውልድ ነን።የአዲሱ ትውልድ ትግል፣ የአማራ መጠቃት ከወለደው ቁጭት ባሻገር የአባቶቹን አማራን የሀገር ባለቤት የማድረግ ንቃት የተላበሰም ትውልድ ነው።

📌 ቀደምት የብሔራዊ ንቃት ጀማሪ ከሆኑት አንዱ፣ ለአማራነት ካሳ የሆነው ዳግማዊ ቲዎድሮስ ብሔራዊ ቁጭት እና ንቃት የትውልዱ ርዕዮታዊ ጮራ ነው። ቀጠናችነ በዚህ አብዮታዊ ጮራ ፈንጣቂ ስም መሰየሙ ትግላችንን የበለጠ ያጸናዋል።
📌 የበላይ ዘለቀ ዘመን ተሻጋሪ ራስ በቅ ጸረ ፋሽስታዊ ትግል ለትውልዱ የትግል መስመር ታማኝነት እና ጠባቂነት ቋሚ የህሊና ድምጽ ነው።

የእኒህ ቀደምት ዋኖቻችንን ብሔራዊ ንቃት በማሰብ የዛሬን ርሀብ፣ ችግር፣ የጓድ መሰዋዕትነት መቀበል፣ አድካሚ ጉዞ፣ ከዳተኛውን እና ደመኛውን ጠላት በመታገል ታግሰን በቁርጠኝነት የምንሻገርበት ስንቅ ልንይዝ ይገባል።
ይህ ቁጭትን ያዘለ ንቃት ነገን ለአማራ ብሎም ለመላው ሀገር ፍትሀዊ መንግስት የምናቆምበት ነው። ከዚያም ባሻገር በአማራነት ብሔራዊ ንቃት ያቆምነውን ፍትሐዊ መንግስት የምናጸናው ይህንኑ ስንቅ ጠብቀን በማቆየት ይሆናል።

የዛሬ ሰልጣኞች በከፍተኛ መስዋዕት ተጀምሮ በተጠናቀቀው ስልጠና ከሌሎች ሰልጣኞቻችን በተለዬ ልዩ የሞራል ዕዳ አለባችሁ።
ይህ እንዳለ ሆኖ ትግሉ እና ድርጅታችን በደረሰበት ወሳኝ ምዕራፍ ወቅት በመገኘት የተጣለባችሁን ዕዳ እና የተሰጣችሁን ዕድል በቁጭት እና በንቃት ትግሉ የድሎች ድምር ለሆነው አሸናፊነት እንዲበቃ በጽናት እንደምትታገሉ በማመን አንኳን ደስ አላችሁ ለማለት እወዳለሁ።

አሰልጣኞች ይህን የአማራ ሠራዊት ለማብቃት ላሳያችሁት ትጋት እና ለከፈላችሁት መስዋዕትነት እያንዳንዳችን እናከብራችኋለን።
የስልጠና ሂደቱን ላስተባበራችሁ እና ለመራችሁ አመራሮች የተሰጣችሁን ድርጅታዊ ግዳጅ በመፈጸም ድርጅታችሁን አኩርታችኋልና በትጋታችሁ በርቱ።

ስልጠናውን በአይነት እና በገንዘብ የደገፋችሁ ክንዶቻችን፣ የሰልጣኝ ቤተሰብ እና የአከባቢው ነዋሪ የትግሉ ባለቤት በመሆን በምትጠየቁት ሁሉ የአቅማችሁን ብቻ ሳይሆን ከዚያም በላይ በመደገፍ ላሳያችሁት ቅንነት በሰልጣኙ እና በድርጅታችን አማራ ፋኖ ብሔራዊ ሀይል ምዕራብ አማራ ቀጠና ስም እናመሰግናችኋለን።

ስልጠናው ይቀጥላል!!
ስልጠና የስርአት መሠረት ነውና ስርአት የገባ ፖለቲካዊ ማህበር ለማንበር ብሎም በዘላቂነት የአማራነት ዘብ የሚሆን ሠራዊት ለመፍጠር እንሰለጥናለን፣ እናሰለጥናለን።

አማራነት ያሸንፋል !!
አዲስ ትውልድ! አዲስ አስተሳሰብ! አዲስ ተስፋ!
Dawit Mehari Adanene

እናሰለጥናለን ፥ እናደራጃለን ! አማራዊ ግስጋሴን ፥ አማራዊ ንቃት እና አስተውሎትን ከፍ እናደርጋለን!በድል ጀምረናል ፥ እናሸንፋለን !! ወደፊት ብቻ !!ምንያምር አዲስ - Minyamir A...
22/09/2025

እናሰለጥናለን ፥ እናደራጃለን !
አማራዊ ግስጋሴን ፥ አማራዊ ንቃት እና አስተውሎትን ከፍ እናደርጋለን!
በድል ጀምረናል ፥ እናሸንፋለን !!
ወደፊት ብቻ !!
ምንያምር አዲስ - Minyamir Addis

13/09/2025

መስከረም 03 ቀን 2018 ዓ.ም
ከአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል የተሰጠ መግለጫ
```````````````````````````````````````````````````
አረመኔው የአብይ አህመድ አገዛዝ በአማራ ህዝብ ላይ የዘር ማጥፋት ጦርነት ከከፈተ ድፍን ሁለት ዓመታትን አስቆጥሯል። በእነዚህ ሁለት ዓመታት ግዜ ውስጥ አገዛዙ ያልተጠቀመው የዘር ማጥፋት እና የጦርነት ስልት የለም። አማራው ራሱን የሚከላከልበትን ጦር መሳሪያ እንዳይኖረው በማድረግ መዋቅራዊ ዘር ማጥፋት ወንጀል ለመፈፀም አስቦ በከፈተው ሁሉንተናዊ ጦርነት ህፃናትን ጨፍጭፏል። ንፁሃንን በመግደል የሽብር ተግባር አከናውኗል። ሁለንተናዊ ጦርነትን ካስፈፀመባቸው መካከል የህዝብ መገልገያ ተቋማትን አገልግሎት በማይሰጡበት ማውደም አንደኛው ነው።

ይህ ውድመት ከደረሰባቸው ማህበራዊ ተቋማት መካከል ትምህርት ቤቶች እና ኮሌጆች ቀዳሚዉን ድርሻ ይይዛሉ። የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ባደረገው የዳሰሳ ጥናት ከ6000 በላይ 1ኛ እና 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች፣ የቴክኒክ እና ሙያ ተቋማት እና የዩኒቨርሲቲ ካምፓሶች አገልግሎት በማይሰጡበት ደረጃ ወድመዋል። ለፋኖ መረጃ ትሰጣላችሁ የተባሉ መምህራን ተገድለዋል፣ በአስር ሺወች የሚቆጠሩ ታዳጊ ሴት ተማሪወች በአረመኔው ሰራዊት በጅምላ ተደፍረዋል። ይህ ሁሉ ውድመት የደረሰው የአገዛዙ ሰራዊት ትምህርት ቤቶችን በድሮን፣ በጀት፣ በመድፍ እና በሌሎች ከባድ መሳሪወች በቀጥታ በመደብደቡ፣ ተቋማቱን በቀጥታ በማፍረስ እና በማቃጠሉ እንዲሁም ሁሉም የጠላት ሰራዊት እነኝህን የትምህርት ተቋማት በካምፕነት በመጠቀሙ ነው።

ይህ ወንጀል ላለፉት ለሁለት ዓመታት በአማራ ህዝብ ላይ ሲፈፀም መዋቅሩ የፈራረሰው አገዛዝ መፍትሔ መስጠት አልቻለም። ይልቁንም ሰራዊቱ ይህንን ወንጀል እንዲፈፅም ስልታዊ እና ይፋዊ ድጋፍ እና ፈቃድ በመስጠት ላይ ይገኛል።

ይህንን እና ተመሳሳይ የጠላት ተልዕኮወችን በመከላከል ታሪካዊ ኃላፊነቱን እየተወጣ ያለው የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል በበኩሉ በማህበራዊ ተቋማት ላይ ውድመት የማይደርስባቸውን ወታደራዊ ስልቶችን በመጠቀም እና ሰራዊታችንም ተቋማቱ እንዳይወድሙ በመጠበቅ ታሪካዊ ኃላፊነቱን ሲወጣ ቆይቷል።

የብልፅግና ካሪኩለም ለአማራ ህዝብ ትርጉም ያለው ፋይዳ ያመጣል ተብሎ ባይታመንም በእነኝህ የአገዛዙ የጥፋት ተልዕኮወች ምክንያት ሚሊየኖች ከትምህርት ገበታ ተገልለው መሰረታዊ ዕውቀት የማይገበዩበት ሁኔታ መፈጠሩ ድርጅታችንን በእጅጉ ያሳስበዋል።

በተለይም የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ማእከላዊ ኮማንድ ለቀናት ባደረገው ስብሰባ በአጀንዳነት ከተነጋገረባቸው ጉዳዮች መካከል የትምህርት ሁኔታ አንደኛው ነበር። በዚህ መሰረት በአጀንዳው ላይ መፍትሔ የሚያመጣ ግብረ ኃይል ስምሪት ወስዶ ጥናት አድርጎ ባመጣው የመፍትሔ ሃሳብ መሰረት ብሔራዊ ኃይሉ በዚህ ጉዳይ ላይ ከዚህ በፊት ያወጣውን መግለጫ ገቢራዊነት በሚያረጋግጥ መልኩ ማሻሻል እንዳለበት አምኖበታል።

በመሆኑም ግብረ ኃይሉ የዳሰሳ ጥናቱን መሰረት አድርጎ ባቀረበው የውሳኔ ሐሳብ ላይ ማዕከላዊ ኮማንዱ ሰፊ ውይይት ካደረገ በኋላ ለሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ተከታዩን ጥሪ ያቀርባል።

1) በትምህርት ጉዳይ ለሚሰሩ ዓለም አቀፍ ግብረ ሰናይ ድርጅቶች

ኢትዮጵያ ውስጥ የትምህርትን ጉዳይ በመደገፍ የሚታወቁት ሴቭ ዘ ችልድረን፣ ዩኒሴፍ፣ ዩኔስኮ እና መሰል ተቋማት ለትምህርት ማስፈፀሚያ በሚል ለአገዛዙ የሚበጅቱት በርካታ ሚሊዬን ዶላር ቢኖርም ይኸው በጀት በአገዛዙ በኩል ለጦርነት ግብዓት እየዋለ ይገኛል። ስለሆነም ግብረ- ሰናይ ድርጅቶቹ ይህንን ጉዳይ እንዲያጤኑት እና ክትትል እንዲያደርጉበት ጥሪ እናቀርባለን።

2) ለመላው የአማራ ህዝብ

አገዛዙ ባገኘው አጋጣሚ ሁሉ እየፈፀመ ያለው በአማራ ላይ የጀመረውን የዘር ማጥፋት ጦርነት ማስቀጠል መሆኑ በተግባር ተረጋግጧል። በትምህርት ተቋማት ላይ በአረመኔው ሰራዊት የደረሰው ውድመትም የዚህ አካል መሆኑ ይታወቃል። ስለሆነም የአገዛዙ ሰራዊት የህዝብ አንጡራ ሀብት የሆኑትን ተቋማት በማውደም፣ ሴት ልጆቹን በመድፈር፣ ህዝቡንም በመዝረፍ እና ጨለማ ውስጥ ለማስገባት የሚያደርገውን የወንጀል ተግባር ያቆም ዘንድ የመከላከያ ሰራዊት ነኝ የሚለው የአገዛዙ ጠባቂ ክልሉን ለቆ እንዲወጣ እና የመማር ማስተማር ተግባሩ እንዲከናወን ህዝቡ ተገቢውን ትግል እንዲያደርግ ጥሪ እናቀርባለን።

3) ለተማሪ ወላጆች እና ለተማሪወች

ከላይ የጠቀስናቸው ጥቃቶች በተለይ በተማሪወች እና በወላጆቻቸው ላይ ከፍተኛ ስነ-ልቦናዊ እና ማህበራዊ ቀውስን ያስከተሉ በመሆናቸው አገዛዙን በማንኛውም መንገድ ለመታገል የቀዳሚነቱን ሚና መውሰድ ይገባቸዋል። ስለሆነም የትውልድ ክፍተት እንዲፈጠር የችግሩ ምንጭ የሆነው የአገዛዙ ሰራዊት የፈፀመው የጥፋት ወረራ በመሆኑ የአገዛዙ ወራሪ ሰራዊት ወደ መደበኛው ተልዕኮው እንዲመለስ እና ክልሉን ለቆ እንዲወጣ በየደረጃው ባለ የአገዛዙ መዋቅር በኩል ግፊት እንድታደርጉ እናሳስባለን።

4) በቀጣይ ትምህርት የሚቀጥልበትን ሁኔታ በተመለከተ

ከላይ ባቀረብነው ጥሪ መሰረት የአገዛዙ ሰራዊት ክልሉን ለቆ እንዲወጣ የሚደረገውን ሰላማዊ የህዝብ ትግል እንደተለመደው በኃይል የሚያፍን ከሆነ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ተቋማት፣ የአፍሪካ ሕብረት፣ የአውሮፓ ሕብረት እና ሌሎች የሚመለከታቸው ተቋማት በታዛቢነት የሚያስፈፅሙት የትምህርት ተቋማትን ከወታደራዊ እና ፖለቲካዊ እንቅስቃሴዎች ነፃ የማድረግ የትምህርት የሰላም ስምምነት መደረግ ይኖርበታል።

ይህ ኮሎምቢያ፣ ኔፓል፣ ኮንጎ እና ፊሊፒንስን ጨምሮ በበርካታ ሀገራት በነበሩ የእርስ በእርስ ጦርነቶች ወቅት ተግባራዊ ተደርጎ ተጨባጭ ውጤት የተገኘበት ነው።

በመሆኑም ዓለም አቀፍ ተሞክሮወችን እና መመዘኛወችን ከሀገራችን ነባራዊ ሁኔታ ጋር በማዋደድ ወደ ፊት በዝርዝር በምናስቀምጣቸው መርሆወች መሰረት የሚፈፀም ስለሆነ አገዛዙ ለዚህ ጉዳይ አወንታዊ ምላሽ እንዲሰጥ እና የወደሙ ተቋማት ተጠግነው ከፖለቲካዊ እና ወታደራዊ ተግባራት ነፃ ሆነው ህፃናት ወደ ትምህርት ገበታ የሚመለሱበትን ሁኔታ እንዲመቻች ለሚመለከታቸው አካላት ሁሉ ጥሪ እናቀርባለን።

አዲስ ትውልድ! አዲስ አስተሳሰብ! አዲስ ተስፋ!

13/09/2025

Address

Https://t. Me/Higtube
Addis Ababa

Opening Hours

Monday 09:00 - 17:00
Tuesday 09:00 - 17:00
Wednesday 09:00 - 17:00
Thursday 09:00 - 17:00
Friday 09:00 - 17:00
Saturday 09:00 - 17:00
Sunday 09:00 - 17:00

Telephone

+251911289071

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ሕግ ቲዩብ Hig Tube posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to ሕግ ቲዩብ Hig Tube:

Share