Tewelde Haile Law Office

Tewelde Haile Law Office I have advocacy licences from SNNP regional state Attorney General and federal Attorney General . I'

12/09/2025
vacancy for lawyers .
12/07/2025

vacancy for lawyers .

07/07/2025

በወንጀል ድርጊት የተገኘ ገንዘብን ወይም ንብረት ሕጋዊ አስመስሎ ማቅረብንና ሽብርተኝነትን በገንዘብ መርዳትን ለመከላከልና ለመቆጣጠር ተሻሻሎ የወጣ አዋጅ ቁጥር 1387/2017 ላይ ለመርማሪዎች ( UnderCover investigators) ከግዲያ በስተቀር ማንኛውንም ድርጊት የሚፈቅደው አንቀፅ የተሰረዘ እና ከነባሩ አዋጅ አንቀፅ 26 ንዑስ አንቀፅ (3) ቀጥሎ አዲስ ንዑስ አንቀፅ (4) ማሻሻያ የተደረገበት መሆኑን ሰምተናል ። እንደ አንድ ህግ ባለ ሙያና ዜጋ ህግ አውጭው የህዝብ አስተየት ስምቶ አዋጁ በነጋሪት ጋዜጣ ከመታተሙ በፊት በቶሎ እርማት ማድረጉ በጣም ሊበረታታ ይገባል ባይ ነኝ።
የተሰረዘውን አንቀፅ justify ለማድረግ ሲሞክሩ የነበሩ የህግ ባለሙያዎች አሁን ምን ይሉን ይሆን ?

የቅጣት አወሳሰን መመሪያ ቍጥር 3/2017 ፀድቋል ። መመሪያው ከፀደቀበት ሰኔ 25 ቀን 2017 ዓ.ም . ጀምሮ 15 ቀን በኋላ ተፈጻሚ እንዲሆን ተወስኗልና እወቁት ብሏል የፌደራል ጠቅላይ ፍ...
04/07/2025

የቅጣት አወሳሰን መመሪያ ቍጥር 3/2017 ፀድቋል ። መመሪያው ከፀደቀበት ሰኔ 25 ቀን 2017 ዓ.ም . ጀምሮ 15 ቀን በኋላ ተፈጻሚ እንዲሆን ተወስኗልና እወቁት ብሏል የፌደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ።

18/06/2025

ማስታወቂያ

23/05/2025
22/05/2025

ቲክቶክን ጨምሮ በመሰል የማህበራዊ ሚዲያ መተግበሪያዎች ላይ የሙያውን ክብር እና ስነምግባርን የሚያጎድፉ ተግባራት ላይ የሚሳተፉ ባለሙያዎችን በተመለከተ ከኢትዮጵያ ፌደራል ጠበቆች ማህበር የተሰጠ ጥብቅ ማሳሰቢያ፤

=================

የፌደራል ጠበቆች ማህበር ቲክቶክን ጨምሮ በመሰል የማህበራዊ ሚዲያ መተግበሪያዎች የሚሠሩ የህግ ቪዲዮችን ይዘትና አቀራረብ በቅርበት ሲከታተል ቆይቷል:: በተመሳሳይ ጥቆማዎችንም ሲያሰባስብ ቆይቷል::

ሆኖም የሚሰሩ ተንቀሳቃሽ ምስሎች (Video) ዓላማ ለህዝብ ንቃተ- ህግ እና ግንዛቤን ለመፍጠር የሚያግዙ ይሆናሉ በሚል እና በተለይም ከሌሎች አቻ ሀገራት አንፃር በታሪክ አጋጣሚ ወደ ኃላ የቀረውን እና በቅርብ አመታት ከፍ ያለ መነቃቃት እያሳየ ያለውን የህግ አገልግሎት ዘርፍ ለማበረታታት ሲባል ጉዳዩን በትእግስት ለመከታተል ሞክሯል::

ይህ በእንዲህ እንዳለ ጉዳዩ እየተሻሻለ ከመምጣት ይልቅ የህግን ሙያ ክብር እና ጥብቅ ስነ-ምግባር በሚያጎድፍ መልኩ የቀጠለ ሆኖ ተገኝቷል::

ክትትል ሲደረግባቸው ቆይቶ በጥናት ከተለዩ ነጥቦች ውስጥ የሚከተሉት በማሳያነት ሊጠቀሱ የሚችሉ ናቸው::

1) አሁን በተግባር እየታየ ያለዉ አብዛኞቹ የሚሠሩት ቪዲዮች ማስረጃ ተመዝኖ ሊሰጥ የሚችል የህግ ምክር ላይ ትኩረት ያደረገ መሆኑ፡፡


2) አንዳንድ በዚህ ሂደት እየተሳተፉ ያሉ ጠበቆችና የህግ አማካሪዎች የሚያቀርቧቸው ፕሮግራሞች ይዘት እና ርዕስ ለአጠቃላይ ማህበረሰቡ የህግ ንቃተ- ህሊና የሚያሳድጉ ከመሆን ይልቅ በተጋነኑ መግቢያዎች ቀልብ ለመሳብ የሚሞክሩ፣


3) ተከታዮችን የሚያመጣ በሚል አሳሳች ርዕሶችንና ርዕሰ ጉዳዮችን ይመርጣሉ፡፡ በዚህም አግባብ የተሰሩ ቪዲዮች ብዙ ተከታዮች እና ተመልካቾችን ያገኛሉ፡፡ ሆኖም ህብረተሰብን የሚያሳስቱ በመሆናቸው ከአስተማሪነታቸው ይልቅ አደናጋሪ ይዘት ተላብሰዋል::


4) ሌላዉ እነዚሁ ባለሙያዎች (ጠበቆች) የሚመርጡት ይዘት መሠረታዊ የህግ ግንዛቤን የሚጨምሩ ተጨባጭ ጉዳዮች ከመሆን ይልቅ ቀልብ ይስባሉ ያሏቸውን እጅግ አከራካሪ፣ በሰበር ሰሚ ችሎት የተለያየ ትርጉም የተሰጠበት፣ በእያንዳንዱ ጉዳይ በተለየ ማስረጃና የክርክር ይዘት ታይቶ ሊወሰን የሚገባ አወዛጋቢ ይዘቶች ላይ አንዱን ክርክር ብቻ ይዞ የመስራት ሁኔታ በስፋት ተስተውሏል፡፡


5) ከዚሁ ጋር በተያያዘ በጉዳዩ ላይ በቂ ጥናት እና ንባብ ሳይደረግ የተሳሳተ የህግ ድምዳሜ ተይዞ በቲክቶክ ቪዲዮ ላይ እየተሰራ ይገኛል፡፡ ለምሳሌ፡ " ፖሊስ ያለ መጥሪያ ተጠሪጣሪን ይዞ ሊያስር አይችልም" በሚል የተሰራዉ ቪዲዮ ላይ በአንድ የፖሊስ አባል ምላሽ ተሰጥቶበታል፡፡


6) አንዳንድ ቲክቶከር የህግ ባለሙያዎች ከቪዲዮአቸዉ ሥር የሚሰጡ አስተያየቶች ላይ የሙያዉን ክብር በማይመጥን መልኩ የመሰዳደብ ሁኔታ ይስተዋላል፡፡ እንዲሁም በተወሰነ መልኩ አንዱ ባለሙ የሌላኛውን ይዘት ወይም ቪዲዮ የጠበቃዉንም ሆነ የሙያዉን ክብር በማይመጥን ሁኔታ ስህተቱን ተገቢነት በጎደላቸው ንግግሮች ማጣጣል ይገኝበታል፣


7) በጠበቆች የስነምግባር ደንብ ቁ. 57/1999 ከተፈቀዱ ተግባራት በዘለለ ማለትም ከሚሰጡት አገልግሎት፣ አገልግሎቱን ከሚሰጡበት ቦታ ባለፈ ግልጽ የሆነ ማስታወቂያ የመስራት ሁኔታ እየተደጋገመ ተስተውሏል፡፡

8)ባለሙያውንና የሙያውን ክብር ዝቅ በሚያደርግ መልኩ አካለዊ እንቅስቃሴ የታጀበባቸው ዳንስን የመሰሉ ተግባራትን ማሳየት፤ የቀን ዉሎዉን የሚያሣይ የይዘት ያለው ባለሙያዎች ከመኖሪያ ቤታቸዉ ጀምሮ ያለዉን ሂደት፣ የፍርድቤት ምስል፣ ሰዎችን ሲያነጋግሩ የሚያሳዩ ይዘቶች በመቅረጽ ማስተላለፍ ይገኙበታል፡፡

ከላይ በዝርዝር የተመለከተው ቢኖርም በቲክቶክ እና መሰል የሶሻል ሚዲያ ዘርፎች መሠረታዊ የንቃተ ህግ ጉዳዮች ላይ በሀላፊነት ስሜት የሚሰሩ፣ ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ የህብረተሰቡን ብዥታ እና ግርታን የሚቀርፉ በርካታ ባለሙያዎች መኖራቸውም ግንዛቤ ተወስዶበታል፡፡

በመሆኑም በዚህ ተግባር ላይ ተሰማርታችሁ ያላችሁ የፌደራል ጠበቆች ማህበር አባላትና የህግ ባለሙያዎች ማህበሩ በቅርበት ሲከታተላቸው የቆዩ ጉዳዮች እንደተጠበቁ ሆነው ከዚህም በኃላ የህግን ሙያና የባለሙያውን ክብር የማያስጠብቁ፤ ከአስተማሪነታቸው ይልቅ ብዝታን የሚፈጥሩ እና መሰል ከላይ በዝርዝር የተጠቀሱ ተግባራትን መፈጸም ከአዋጅ ቁ. 1249/13 እንዲሁም ከደንብ ቁ. 57/1992 ተፈጻሚነት ያላቸው ድንጋጌዎች በሚያዙት አግባብ ከድርጊታቸው በማይቆጠቡት ላይ አግባብነት ያለው የዲሲፕሊን እርምጃ የሚወሰድ መሆኑን በጥብቅ ያሳውቃል፡፡

የኢትየጵያ ፌደራል ጠበቆች ማህበር፡፡

ግንቦት 13 ቀን 2017ዓ.ም

Address

Lebu And Lideta
Addis Ababa

Opening Hours

Monday 09:00 - 17:00
Tuesday 09:00 - 17:00
Wednesday 09:00 - 17:00
Thursday 09:00 - 17:00
Friday 09:00 - 17:00

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Tewelde Haile Law Office posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Tewelde Haile Law Office:

Share