Kolfe keraniyo wereda 11 public service

Kolfe keraniyo wereda 11 public service Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Kolfe keraniyo wereda 11 public service, Legal, Addis Abeba, Addis Ababa.

09/07/2025
27/08/2024
እንኳን ለጌታችን ለመድሀኒታችን ለእየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በሰላም በጤና አደረሳቹ መልካም በዓል
07/01/2024

እንኳን ለጌታችን ለመድሀኒታችን ለእየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በሰላም በጤና አደረሳቹ መልካም በዓል

https://www.facebook.com/100067771711638/posts/683057817296603/?mibextid=Hn3EexMF1WhlYZLE
25/12/2023

https://www.facebook.com/100067771711638/posts/683057817296603/?mibextid=Hn3EexMF1WhlYZLE

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፐብሊክ ሰርቪስ እና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ ታህሳስ 12//04/2016 ዓ.ም ሊሰጥ ለነበረው የቴክኒክና ባህሪ ብቃት ፈተና ለመፈተን በስፍራው ለተገኛችሁ እና የከተማ አስተዳደሩን አቅጣጫ በፍፁም ኢትዮጵያዊ ጨዋነት በመቀበል ውሳኔውን ላከበራችሁ ሰራተኞች በሙሉ የላቀ ምስጋናውን እያቀረበ ለተፈጠረው ችግር ይቅርታ ይጠይቃል።

በቀጣይም በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ እና በኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ የተዘጋጀው ፈተና ቅዳሜ ታህሳስ 20/04/2016 ዓ.ም ከጠዋቱ 2:00 ጀምሮ የሚሰጥ መሆኑንም ቢሮው ያስታውቃል።
*******************
ፐብሊክ ሰርቪስ ቢሮ ታህሳስ 15 ቀን 2016 ዓ.ም

የከተማ አስተዳደሩ የቴክኒክና ባህሪ ብቃት ፈተና ለአመራሮች ፣ ለባለሙያዎች እና ለሰራተኞች ፈተና እንዲሰጡ ለአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ እና ለኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ ኃላፊነት በመስጠት ባሳለፍነው ሳምንት አርብ ቀን ማለትም በ 12/04/2016 ዓ.ም ፈተና ለመፈተን ሙሉ ዝግጅቱን ቢያጠናቅቅም ፈተናው የ አዲስ አበባ ዩንቨርስቲ ባጋጠመው ቴክኒካል ችግር ምከንያት ላልተወሰነ ጊዜ መራዘሙ አይዘነጋም።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ግን በእለቱ ከረፋዱ 5:00-11:30 በፍጹም ኢትዮጵያዊ ጨዋነት እና በትእግስት የፈተናውን መሰጠት ስትጠባበቁ ለነበራችሁ የ ከተማ አስተዳደሩ ሰራተኞች በሙሉ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፐብሊክ ሰርቪስ እና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ የላቀ ምስጋናውን እያቀረበ ነገር ግን በእለቱ በሰራተኛው ላይ ለደረሰው መጉላላት እና እንግልት ሁሉ ይቅርታ ይጠይቃል።

በተያያዘም ተፈታኞች በተረጋገጠ ሰላም አና በተረጋጋ ስሜት ፈተናውን እንዲወስዱ የተለመደ ኢትዮጵያዊ ጨዋነትን ላሳየው እና የሰላም አርበኛ ለሆነው የመንግስት ሰራተኛ በሙሉ ቢሮው ምስጋናን ይቸራል።

በተጨማሪም የከተማ አስተዳደሩን አቅጣጫ በመቀበል የትራንስፖርት አቅርቦት በማመቻቸት፣የትራንስፖርት ፍሰቱን በማሳለጥ እና ሰላም እና ፀጥታን በማስጠበቅ ሙሉ ድጋፍ ላደረጋቸው ባለድርሻ አካላት በሙሉ ቢሮ ከፍ ያለ ምስጋናውን ያቀርባል።

በቀጣይም በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ እና በኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ የተዘጋጀው ፈተና ቅዳሜ ታህሳስ 20/04/2016 ዓ.ም ከጠዋቱ 2:00 ጀምሮ የሚሰጥ መሆኑን እያስታወቀ ተፈታኞች ከዚህ ቀደም በ ኦረንቴሽን ወቅት የተቀመጡ መስፈርቶችን በሙሉ አሟልተው ለፈተና እንዲገኙ ቢሮው ጥሪ ያቀርባል።

በተመሳሳይም የተዘጋጀው ፈተና በቴክኒክ ችግር ምክንያት በመሰረዙ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ይቅርታ መጠየቁም አይዘነጋም።

21/11/2023
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፐብሊክ ሰርቪስ እና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ!***"ብቁ ንቁና ጤናማ አመራርና ሲቪል ሰርቫንት ለላቀ አገልግሎት"  #ለጥንቃቄበአዲስ አበባ በከተማ " ጉንፋን መ...
09/11/2023

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፐብሊክ ሰርቪስ እና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ!
***
"ብቁ ንቁና ጤናማ አመራርና ሲቪል ሰርቫንት ለላቀ አገልግሎት"

#ለጥንቃቄ

በአዲስ አበባ በከተማ " ጉንፋን መሰል " ህመም መከሰቱና ነዋሪዎች ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚገባቸው የጤና ባለሙያዎች እየመከሩ ናቸው።

በራስ ደስታ ዳምጠው መታሰቢያ ሆስፒታል የውስጥ ደዌ ስፔሻሊስት ሃኪም ዶ/ር ስንሻው አባይ ፤ በአዲስ አበባ በከተማ ለተከሰተው " ጉንፋን መሰል ህመም " ጥንቃቄ ማድረግ ይገባል ብለዋል።

ጉንፋን መሰል ህመሙ፦
- ከአፍንጫ ብዙ ፈሳሽ መውጣት፣
- ሳል፣
- ራስ ምታት፣
- ጉሮሮን የማቃጠል ስሜት፣
- ድካም፣ የምግብ ፍላጎት መቀነስ የመሳሰሉት እንደሆኑ ተናግረዋል፡፡

ዶክተሩ ፤ ሰሞኑን የተከሰተው ጉንፋን መሰል ህመም የላይኛውን የመተንፈሻ አካል ክፍል የሚያጠቃ ነው ብለዋል፡፡

ህመሙን ለመከላከል እና ለማስታገስ ፦
* ፈሳሽ መውሰድ፣
* ከቅዝቃዜ ራስን ማራቅ (ሙቀቱን የተመጣጠነ ማድረግ)፣
* መኖሪያ ቤትን አየር እንዲያገኝ ማድረግ፣
* በቂ የሆነ እረፍት መውሰድ እና የመሳሰሉትን ተግባራዊ ማድረግ አስፈላጊ መሆኑን መክረዋል።

በሌላ በኩል ፤ በቤት ውስጥ የእፅዋት ዝርያዎችን በፍም (እሳት) ላይ በማጨስ ጭሱን መታጠን ሳንባ እንዲያብጥ ወይም እንዲቆጣ በማድረግ ለጉዳት እንደሚዳርግ ተናግረዋል፡፡

ማህበረሰቡ ፦
° በህዝብ ማመላለሻ ትራንስፖርት ውስጥ መስኮቶችን በመክፈት፣
° በንግድ ቤቶች፣ ትምህርት ቤቶች እንዲሁም ሰው በተሰበሰበበት ቦታዎች የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭምብል በማድረግ፣
° የእጅን ንፅህና በአግባቡ በመጠበቅ እንዲሁም አስም ያለባቸው ምልክቶቹ እንደታዩባቸው ወደ ህክምና ተቋማት ሄደው መታየት እንዳለባቸው መክረዋል።

የጤና ሚኒስቴር ከህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ጋር በጋራ በመሆን በ2 ሺህ ያህል ናሙናዎች ላይ ምርመራ አድርጎ አዲስ አበባን ጨምሮ በተለያዩ አካባቢዎች የጉንፋንና ኢንፍሉዌንዛ በሽታ መከሰቱን ከሁለት ሳምንት በፊት ይፋ አድርጓል።

የዝናብ ወራት ማለፉን ተከትሎ በጥቅምትና ህዳር ወቅት ላይ አብዛኛውን ጊዜ የጉንፋንና ኢንፍሉዌንዛ በሽታ ይከሰታል፡፡

በጤና ሚኒስቴር የኮቪድ-19 ምላሽ ግብረ-ሃይል ዋና አስተባባሪ ዶክተር መብራቱ ማሴቦ ፤ ከጥቅምት ወር መጀመሪያ ጀምሮ በአንዳንድ የሀገሪቱ አካባቢዎች የጉንፋንና ኢንፍሉዌንዛ በሽታ መከሰቱን ተናግረዋል።

" እጅን በመታጠብ፣ አፍና አፍንጫን በመሸፈን በሽታውን በቀላሉ መከላከል ይቻላል " ያሉ ሲሆን በበሽታው የተያዙ ሰዎች በቂ እረፍት በመውሰድ፣ ፈሳሽና ትኩስ ነገሮች በመጠቀምና ተገቢውን ህክምና በማግኘት ስርጭቱ እንዳይስፋፋ ጥንቃቄ ማድረግ እንዳለባቸው አሳስበዋል።

የጤና ባለሙያዎች የሚሰጧቸውን ምክረ-ሀሳቦች በመተግበር፣ በርና መስኮቶችን በመክፈት፤ በቂ የአየር ዝውውር እንዲኖር በማድረግ መከላከል እንደሚቻልም ነው የገለፁት፡፡

መረጃው የአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ እና ኢዜአ ነው።

በኮልፌ ወረዳ 11 ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ፅ/ቤት አዘጋጅነት ለወረዳው ሰራተኞች በአዋጅ 56/2010 ፣ በዲሲፒሊን መመሪያ እና በቅሬታ አቀራረብና አፈታት ዙሪያ ስልጠና ተሰጠ።ጥ...
06/11/2023

በኮልፌ ወረዳ 11 ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ፅ/ቤት አዘጋጅነት ለወረዳው ሰራተኞች በአዋጅ 56/2010 ፣ በዲሲፒሊን መመሪያ እና በቅሬታ አቀራረብና አፈታት ዙሪያ ስልጠና ተሰጠ።
ጥቅምት 26/2016

Address

Addis Abeba
Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Kolfe keraniyo wereda 11 public service posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share

Category