18/02/2025
የቀጠለው የፅንፈኞች ድራማ እና የንፁሀን ሞት
ፅንፈኞች የህዝብ ሞት እና ስቃይ ግድ አይሰጣቸውም ይልቁኑ በንፁሃን ሞት ላይ የደም ንግድ በመስራት ለፖለቲካ ፍጆታ ይጠቀሙበታል። አለፍ ሲል ደግሞ የዩቲዩብ ዶላር መሸቀያ ያደርጉታል። ተላላኪዎች ገንዘብ እስካስገኘላቸው ድረስ ሀገር ፍርስርሷ ቢወጣ ጉዳያቸው አይደለም።
ከሰሞኑም በጅማ ጌራ በጅዋር መሀመድ የሚመራው የኦሮሞ ፅንፈኛ እና የአማራው ፅንፈኛ በመተባበር አንድን የኦሮሞ ባለሀብት በአሰቃቂ ሁኔታ ከአስገደሉ በኋላ ለፖለቲካ ፍጆታቸው ሁለቱም መንግስትን በመወንጀል ላይ ተጠምዷል። የአማራው ፅንፈኛ መንግስት ሸኔን አስታጥቆ የአማራን ህዝብ አስጨፈጨፈ፣ቤተክርስቲያንን አቃጠለ ብሎ ጮኽ ብሎ ስለፍፍ ስውል በሌላኛው ዋልታ ረገጡ የኦሮሞ ፅንፈኛ ደግሞ መንግስት የአማራ ገበሬዎችን አስታጥቆ የኦሮሞን ህዝብ እያስጨረሰ ነው ይላሉ። ቆይ መንግስት እንዴት በአንድ ጊዜ ሁለት ነገር ማድረግ ይችላል?? ለህዝብ ያላቸው ንቀት ከፍተኛ በመሆኑ እንጂ እንዴትስ ህዝብ ይታዘባል እንዴት አይሉም?
ለማንኛውም አሁን ላይ የፅንፈኞች ሴራ ራቁቱን እየቀረ ነው። ህዝብ እየዞረባቸው ነው ሴራቸው በአደባባይ እየተጋለጠ ነው። የጊዜ ጉዳይ ነው እንጂ ፅንፈኞች ከምድራችን ተጠራርጎ ይጠፋሉ!!!