18/02/2025
በኢትዮጵያ ዉስጥ ያሉ ፅንፈኞች ለህዝቡ ግድ የማይሰጣቸዉ፣ በህዝቡ መገደል እና መሰቃየት የፖለቲካ ሸቀጣቸዉን የሚሸቅጡ ናቸዉ።
በጌራ እና በደራ ያየነዉም ድራማ ይሄዉ ነዉ። በግላጭ እነዚህ ፅንፈኞች እርስ በእርስ የሚጠላሉ፣ ለሞት የሚፈላለጉ ይመስላሉ። ዉስጥ ዉስጣቸዉን ግን እጅ ለእጅ ተያይዘዉ የሚንቀሳቀሱ ናቸዉ።
በጌራዉ ጉዳይ እነዚህ ፅንፈኞች አንድን ንጹህ ግለሰብ በአሰቃቂ ሁኔታ በማስገደል፤ በጅዋር መሀመድ የሚመራው የኦሮሞ ፅንፈኛ እና የአማራው ፅንፈኛ በመተባበር ለፖለቲካ ፍጆታቸው ሁለቱም መንግስትን በመወንጀል ላይ ተጠምዷል።
የአማራው ፅንፈኛ መንግስት ሸኔን አስታጥቆ የአማራን ህዝብ አስጨፈጨፈ፣ቤተክርስቲያንን አቃጠለ ብሎ ይጮኻል ሌላኛው ዋልታ ረገጡ የኦሮሞ ፅንፈኛ ደግሞ መንግስት በኦሮሚያ ዉስጥ ፋኖን አስታጥቆ የኦሮሞን ህዝብ እያስጨረሰ ነው ይላል።
ቆይ መንግስት እንዴት በአንድ ጊዜ ሁለት ነገር ማድረግ ይችላል?? ለህዝብ ያላቸው ንቀት ከፍተኛ በመሆኑ እንጂ እንዴትስ ህዝብ ይታዘባል እንዴት አይሉም?