Legal and Justice Issue discussion Forum

Legal and Justice Issue discussion Forum Welcome to official page of Legal and Justice discussion forum. It is a page created and administer by interested lawyers. it is free from any politics.

this page is non profitable page created only to create additional space of discussion in any law areas. we try to create legal awareness .

Shout out to my newest followers! Excited to have you onboard! Sasi Kumar, Abdi Mohammed, Tadese Belaye, Alex Addis, Dëm...
11/10/2025

Shout out to my newest followers! Excited to have you onboard! Sasi Kumar, Abdi Mohammed, Tadese Belaye, Alex Addis, Dëmïs Jêmåw Ēw, Temesgen Kalasha, Mohammed Teha, Azeb Zewdu, Mencha Habib Suraji, Nesraddin Chole, Jihad Eb

09/08/2024

የፓስፖርት ማውጫና ማደሻ ወጋ ጭማሪ በሰዎች መንገድ እና በህገወጥ ሰዎች ዝውውር ላይ ያለው እንድምታ
(በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ)
የኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት ከነሐሴ 1 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ የተተገበረ የክፍያ ዋጋ ማሻሻያ ማድረጉን አስታውቀል፡፡ በሚኒስትሮች ምክር ቤት ደምብ ቁጥር 550/2024 መሠረት የዋጋ ማሻሻያ መደረጉን አሳውቀዋል፡፡
ኢትዮጵያ በሰፊው በሰዎች መነገድ እና ሰዎችን በህገወጥ መንገድ ድንበር ማሻገር ወንጀል በስፋት የሚስተዋለባት ሀገር ናት፡፡ የተለያዩ ጥናቶች እንደሚያሳዩት ለነዚህ ወንጀሎች በስፋት መስተዋል መነሻች ምክንያቶች ውስጥ አንዱ ዜጎች በህጋዊ መንገድ ወደ ወጭ ሀገራት ሂደው ለመስራት የሚያስችለው መንገድ በከባድ ብሮክራሲ የተተበተበ በመሆኑ ዜጎች በቀላሉ በህገወጥ መንግድ ለመጓዝ ስለሚመርጡ መሆኑን ያሳያል፡፡ ይህ በሆነበት ሁኔታ ላይ ይህን የወጋ ጭማሪ ማድረግ ውጤቱን የሚያከፋው እና በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ ሁኔታን የሚፈጥር ይመስለኛል፡።
በአብዛኛው በሰዎች መነገድ እና ሰዎችን በህገወጥ መንገድ ድንበር ማሻገር ወንጀል ሰለባ የሚሆኑ ወጣቶች በተለይም ሴቶች ሲሆኑ የኢኮኖሚ ሁኔታቸውንም ስንመለከት በአብዛኛው ስራ አጥ እና ዝቅተኛ የኑሮ ሁኔታ ላይ ያሉ ዜጎች ናቸው፡፡ ይህ የኢኮኖሚ ዝቅተኛ መሆን ለኢ-መደበኛ ስደት ገፊ መከንያቶች ውስጥ የሚጠቀስ ነው፡፡
በመሆኑም ባለዘመነ ብሮክራሲ ምክንያት እየተፈጠረያለውን ችግር ከድህነቱ ጋር ተደምሮ በከፋ ሁኔታ ላይ ባለበት በዚህ ወቅት ተጨማሪ የፓስፖርት ማውጫ ገንዘብ መጨመሩ በእሳት ላይ ቤዝን እንደመጨመር የሚታይ ነው፡።
ይህም የኢ-መደበኛ ስደት አንዱ እና ዋነኛው በሆነው የሰዎች መነገድ እና ሰዎችን በህገወጥ መንገድ ድንበር ማሻገር ወንጀል በስፋት እንዳያባብሰው እና በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ እንዳይሆንብን ከወዲሁ ቢታሰብብት እናለው፡፡
በእንዳልካቸው ወርቁ

29/04/2024

የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሽግግር ፍትሕ ፖሊሲ

https://www.youtube.com/watch?v=RfazI49uQCo
30/06/2022

https://www.youtube.com/watch?v=RfazI49uQCo

@ህጋዊ መከላከል /አልሞት ባይ ተጋዳይነት ምንነት@አንድ ድርጊት በአልሞት ባይ ተጋዳይነት የተፈፀመ ነው፡፡ የሚባለው ምን ምን ሁኔታዎች ተሟልተው ስገኙ እንደሆነ

17/06/2022
07/04/2022

ተወዳጅ ፊልሞችን መርጠን አቅርበንላችኃል፣ በተመቸዎት ቀን እና ሰአት በመረጡት ሀገርኛ ፊልም በሲኒማ ይዝናኑ!

02/04/2022

ከመጋቢት 30 ጀምሮ በሁሉም ሲኒማ ቤቶች

24/03/2022
14/03/2022

ማስታወቂያ
የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት የጥብቅና ፈቃድ በፈተና ለማግኘት ከዚህ በታች የተመለከቱትን መስፈርቶች የሚያሟላ ኢትዮጵያዊ ወይም ትውልደ ኢትዮጵያዊ መመዝገብ የሚችል መሆኑን እንገልፃለን፡፡

1. እውቅና ካለው የኢትዮጵያ ከፍተኛ የትምህርት ተቋም በሕግ የመጀመሪያ ዲግሪ የተመረቀ እና በህግ ሙያ ቢያንስ ሶስት ዓመት ወይም በሕግ ዲኘሎማ የተመረቀና በሕግ ሙያ አምስት ዓመት የሥራ ልምድ ያለው፣
2. ከኢትዮጵያ ውጪ ካለ ከፍተኛ የትምህርት ተቋም በሕግ የመጀመሪያ ዲግሪ ያለውና በኢትዮጵያ ውስጥ በሕግ ሙያ ለአምስት ዓመት የሰራ፣
3. ከሚሰራበት ተቋም የመልካም ስነ-ምግባር ማስረጃ ማቅረብ የሚችል፣
4. በመጨረሻ ጊዜ ይሰራበት ከነበረበት ተቋም ተቋሙን ከለቀቀበት ጊዜ በፊት ባሉት 2 አመታት ውስጥ በከባድ የዲስፕሊን ጥፋት ያልተቀጣ፣
5. የመመዝገቢያ 200.00 ብር /ሁለት መቶ ብር/
6. የታደሰ መታወቂያ ፎቶ ኮፒ፣
7. የትምህርትና የሥራ ልምድ ማስረጃ ኦርጅናል እና ፎቶ ኮፒ፣
8. ከግል መ/ቤት የሚቀርብ የሥራ ልምድ ግብር የተከፈለበት ስለመሆኑ፣
9. በአማርኛ ያልተፃፉ ማንኛውም የሚቀርቡ ማስረጃዎች በአማርኛ ተተርጉመው አንድ ላይ ማቅረብ፣
10. በአዲሱ የትምህርት ፖሊሲ በሕግ ዲኘሎማ የተመረቀ ከሆነ የብቃት ማረጋገጫ ምዘና /COC/ተፈትኖ ያለፈበትን ውጤት ማቅረብ አለበት፡፡
ማሳሰቢያ፡-
 የመመዝገቢያ ቀን፡-ከመጋቢት 5 ቀን 2014 ዓ.ም እስከ መጋቢት 16 ቀን 2014 ዓ.ም ባሉት የሥራ ቀናት፣
 የመመዝገቢያ ቦታ፡- ባንቢስ/ኡሬኤል ቤተክርስቲያን አካባቢ ፍትሕ ሚኒስቴር ሕንፃ ጠበቆች አስተዳደር ቢሮ 2ኛ ፎቅ፣
 የፈተና ኮድ የሚሰጥብት ቀን፡-ከመጋቢት 15 እስከ 16 ቀን 2014 ዓ.ም ጠበቆች አስተዳደር ቢሮ 2ኛ ፎቅ፣
 ፈተና የሚሰጥበት ቀንና ቦታ፡-መጋቢት 17 ቀን 2014 ዓ.ም ከጥዋቱ 3.00 ሰአት ፒያሳ ከጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ከፍ ብሎ በሚገኘው የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ህንፃ አዳራሽ ውስጥ ይሆናል፡፡
የኢፌዲሪ ፍትሕ ሚኒስቴር

Address

Addis Ababa
1370

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Legal and Justice Issue discussion Forum posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share

Category