ናይ ለሚኩራ ወረዳ 04 ብልፅግና ፓርቲ ሚዲያ

ናይ ለሚኩራ ወረዳ 04 ብልፅግና ፓርቲ ሚዲያ Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from ናይ ለሚኩራ ወረዳ 04 ብልፅግና ፓርቲ ሚዲያ, Legal, Lemi kura woreda 04, Addis Ababa.

እንኳን ደስ አለን ፤ እንኴን ደስ አላችሁ!በፈረንሳይ ፓሪስ በመካሄድ ላይ በሚገኘው 33ኛው የኦሎምፒክ ውድድር ኢትዮጵያ ሁለተኛውን የብር ሜዳሊያ በአትሌት ፅጌ ዱጉማ በ800 ሜትር ሴቶች የፍ...
06/08/2024

እንኳን ደስ አለን ፤ እንኴን ደስ አላችሁ!

በፈረንሳይ ፓሪስ በመካሄድ ላይ በሚገኘው 33ኛው የኦሎምፒክ ውድድር ኢትዮጵያ ሁለተኛውን የብር ሜዳሊያ በአትሌት ፅጌ ዱጉማ በ800 ሜትር ሴቶች የፍፃሜ ውድድር አግኝታለች፡፡

የመደመር ዕሳቤ ኃይል በማሰባሰብ መርህ ያምናል።የመደመር አዲስ የለውጥ ቅኝት የአንድነትና የትብብር ሀገራዊ ወረትን አይቀሬና አስፈላጊ ለሆነው የለውጥ አጀንዳ እንደ ዋና እርሾ አድርጎ የወሰደ...
19/07/2024

የመደመር ዕሳቤ ኃይል በማሰባሰብ መርህ ያምናል።

የመደመር አዲስ የለውጥ ቅኝት የአንድነትና የትብብር ሀገራዊ ወረትን አይቀሬና አስፈላጊ ለሆነው የለውጥ አጀንዳ እንደ ዋና እርሾ አድርጎ የወሰደ አሰባሳቢ የፖለቲካ ዕሳቤ ነው።

ይህ የዕይታችን መነፅር በሀገራችን በተለይ ባላፉት 50 አመታት ተንሰራፍቶ የቆየው ባዕዳዊ የመጠፋፋት የፖለቲካ አስተሳሰብ የገታ በአዲስ መልክ የተቀነቀነ ሀገር በቀልና ጤናማ የፖለቲካ እሳቤና ፍኖት ነው።

መደመር የእያንዳንዱ ተናጥላዊ አቅምና ፀጋን የማስተባበር ፖለቲካዊ ፍኖተ ንቅናቄ ነው። ይህ ፍኖተ ንቅናቄ በትንሹ የመጣንበት የሽኩቻና የሴራ ፖለቲካ ከማስቀረት ጀምሮ እስከ በአለም ተወዳዳሪና የበለፀገች አገር የመፍጠር ራዕይ አስቀምጦ በተግባር እየሰራና ውጤት እያስመዘገበ ያለ ዕሳቤ ነው።

እነዚህንና መሰል ውጤቶችን ያስመዘገበው የመደመር ጉዟችን የሀገራችንን ቁስሎች በተሟላ ደረጃ ማከም እንዲቻል ለተቋም ግንባታ ትኩረት የሰጠ ለትብብርና ለዴሞክራሲ ባህል ግንባታ እጆቹን የሚዘረጋ፤ከርዕዮተ አለም ግትርነት ይልቅ በፕራግማቲዝም (ገቢር ነበብነት) አውድ ሁኔታዎችን የሚቃኝ፡ ከግራና ከቀኝ ዘመምነት ይልቅ መሀል ላይ ያለውን አሰባሳቢ መንገድ በፅኑ የሚሻ መዳረሻውን ሁለንተናዊ ብልጽግና ያደረገ ጉዞ ነው።

ይህ አዲስ የለውጥ ቅኝት የብቸኝነት ጉድለትን በመሙላት ከስግብግብነት ከመጠፋፋት ጉዞ ለለውጥ ዝግ ከመሆን ራሱን ያነፃ በመሆኑ የሀገራችን ፖለቲካ በታሪክ አጋጣሚዎች ያጋጠሙት ደዌዎች እንዲታከሙ የሚያስችል ነው።በተግባራዊነትም መንግስታዊ ካቢኔን ለተፎካካሪ ፓርቲዎች እስከ ማጋራት ድረስ ያደረሰ ውጤትን ያስመዘገበ በዘመናዊ የፖለቲካ ታሪካችን ውስጥ ተደፍረው የማያውቁ ውሳኔዎችን በድፍረት ወስኖ በመደመር ሰይፍ (ሰላም፣ይቅርታና ፍቅር) ሀገር መገንባት እንደሚቻል ያረጋገጠ ነው።

በተጨባጭ ካስመዘገብናቸው ውጤቶች መሀልም በጥቂቱ የፖለቲካና የዴሞክራሲ ምህዳርን ማስፋት፤ የህብረ ብሄራዊ አንጅነት ሚዛን መጠበቅ፤የተቋማት ግንባታ፤አገር በቀልና የብዝሀ አማራጭ ኢኮኖሚ ግንባታ፤የማህበራዊ እሴትና ትስስር ማጠናከር፤ የሀገር ክብር ያስቀደመና ዜጋ ተኮር የውጭ ግንኙነትን መትከል በዋናነት ይጠቀሳሉ።

Prosperity Party Lemi Kura Woreda 04 Branch

ከመደመር ጽንሰ ሀሳብ የተወሰደ

29/06/2024

ለምለሚቷ ለሚኩራ

28/06/2024

Address

Lemi Kura Woreda 04
Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ናይ ለሚኩራ ወረዳ 04 ብልፅግና ፓርቲ ሚዲያ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share

Category