ጠበቃ ቴዎድሮስ አብዲሳ Lawyer Tewodros Abdisa

ጠበቃ ቴዎድሮስ አብዲሳ Lawyer Tewodros Abdisa ቴዎድሮስ አብዲሳ ሂርኮ
በማናቸውም የፌደራል ፍርድ ቤት ጠበቃና የሕግ አማካሪ
☎️0910616950
አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ🇪🇹

1⃣. ጋብቻው በየትኛውም ዓይነት የጋብቻ አፈጻጸም ሥርዓት ቢፈጸም በጋብቻ ላይ ፍቺ ለመወሰን ሥልጣን ያለው ፍርድ ቤት ብቻ ነው።2⃣. አንድ ወንድ እና አንዲት ሴት ለረጅም ጊዜያት ተለያይተው...
20/02/2026

1⃣. ጋብቻው በየትኛውም ዓይነት የጋብቻ አፈጻጸም ሥርዓት ቢፈጸም በጋብቻ ላይ ፍቺ ለመወሰን ሥልጣን ያለው ፍርድ ቤት ብቻ ነው።
2⃣. አንድ ወንድ እና አንዲት ሴት ለረጅም ጊዜያት ተለያይተው ቢኖሩም፤ ሌላ ትዳር ቢመሰርቱም ጋብቻቸው በፍርድ ቤት እስካልፈረሰ ድረስ በሕግ አግባብ ባልና ሚስት እንደሆኑ ይቆጠራሉ።
3⃣. ፍቺ ለመጠየቅ ጋብቻ መኖሩን ማስረዳት ቀዳሚ ግዴታ ነው። በአንድ ወንድና በአንዲት ሴት መካከል ጋብቻ አለ ለማለት የጋብቻ ምስክር ወረቀት በማቅረብ ማስረዳት ይቻላል። የጋብቻ ምስክር ወረቀት በሌለ ጊዜ የሰው ምስክሮችን በማቅረብ ማስረዳት ይቻላል።
4⃣በሕግ አግባብ 2 ዓይነት ፍቺ አለ። 1ኛው.የስምምምነት ፍቺ ሲሆን 2ኛው. አንደኛው ተጋቢ የፍቺ አቤቱታ አቅርቦ ውሳኔ የሚያሰጥበት ፍቺ ነው። ሁለቱም የግዴታ ለፍርድ ቤት የሚቀርቡ መሆን አለባቸው።
5⃣ጋብቻ በሁለቱ ተጋቢዎች ፍላጎት እና ነፃ ፈቃድ ላይ ብቻ የተመሰረተ በመሆኑ አንደኛው ተጋቢ ፍቺውን አልፈልግም ቢል ወይም ፍርድ ቤት ባይቀርብም ፍርድ ቤቶች የፍቺ ውሳኔ ከመስጠት የሚከለክላቸው አይደለም።
©ቴዎድሮስ አብዲሳ
በማናቸውም የፌደራል ፍርድ ቤት ጠበቃና የሕግ አማካሪ
☎️09 10 61 69 50
📍አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ🇪🇹

 #በመርህ ደረጃ ደመወዝ የሚከፈለው ሠራተኛው ለሠራበት የሥራ ጊዜ እና መጠን ነው። # በዚህም ረገድ በአሠሪና ሠራተኛ አዋጅ ሕጉ አዋጅ ቁጥር 1156/2011 ዓ.ም አንቀጽ 54 ንዑስ አንቀጽ...
13/02/2026

#በመርህ ደረጃ ደመወዝ የሚከፈለው ሠራተኛው ለሠራበት የሥራ ጊዜ እና መጠን ነው።
# በዚህም ረገድ በአሠሪና ሠራተኛ አዋጅ ሕጉ አዋጅ ቁጥር 1156/2011 ዓ.ም አንቀጽ 54 ንዑስ አንቀጽ 1 ላይ “በዚህ አዋጅ ወይም አግባብ ባለው ሕግ በተለየ አኳኋን ካልተወሰነ በስተቀር ደመወዝ የሚከፈለው ለተሠራ ሥራ ብቻ ይሆናል።” በማለት ተደንግጓል።
#ስለዚህ አንድ ሠራተኛ በሥራ ገበታ ላይ ሳይገኝ የቀረበትን ሕጋዊ የሆነ ምክንያት ካላስረዳ በስተቀር ደመወዙ ሊከፈለው አይገባም።
ነገር ግን ሠራተኛው ለመሥራት እየቻለ እና እየፈለገ፣ በሥራ ገበታውም ላይ እየተገኘ ሥራ ያልሰጠውና እንዳይሰራ ያደረገው አሰሪው ወይም የአሰሪው ድርጊት ከሆነ ሥራ ባይሰራም ደመወዝ ሊከፈለው ይገባል።
#በዚህ ረገድ በአሠሪና ሠራተኛ አዋጅ ሕጉ አዋጅ ቁጥር 1156/2011 ዓ.ም አንቀጽ 54 ንዑስ አንቀጽ 2 ላይ “የዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ 1 ድንጋጌ ቢኖርም ሠራተኛው ለመሥራት ዝግጁ ሆኖ ሳለ ለሥራው የሚያስፈልገውን መሳሪያና ጥሬ ዕቃ ሳይቀርብለት በመቅረቱ ወይም የሠራተኛው ጉድለት ባለሆነ ምክንያት ሳይሰራ ቢውል ደመወዙን የማግኘት መብት ይኖረዋል።” በማለት ይደነግጋል።
#በመሆኑም አንድ ሠራተኛ ደመወዙ እንዲከፈለው ሲጠይቅ አሰሪው ሥራ ላልሰራበት ደመወዝ የመክፈል ግዴታ የለብኝም በማለት ቢከራከር ሠራተኛው ሥራውን ያልሰራው በራሱ ችግር ሳይሆን በአሰሪው ቸልተኝነት እና ሥራን ባለመስጠት መሆኑን ማስረዳት ከቻለ ያልሰራበትን ደመወዝም ቢሆን የማግኘት መብት ይኖረዋል።
ይግባኝ መብት ነው!!!
©ቴዎድሮስ አብዲሳ
በማናቸውም የፌደራል ፍርድ ቤት ጠበቃና የሕግ አማካሪ
☎️09 10 61 69 50
📍አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ🇪🇹

ውጤት ተለቋል።እስከ የካቲት 09 ቀን 2018 ዓ.ም ሪፖርት እንድታደርጉ ታዝዟል።ለፌደራል ፍርድ ቤቶች የሕግ ጉዳይ ጸሐፊ II ተወዳድራቹ የጽሑፍና የቃል ፈተና ተፈትናቹ ለነበረ ይህ ማስታወቂ...
12/02/2026

ውጤት ተለቋል።
እስከ የካቲት 09 ቀን 2018 ዓ.ም ሪፖርት እንድታደርጉ ታዝዟል።
ለፌደራል ፍርድ ቤቶች የሕግ ጉዳይ ጸሐፊ II ተወዳድራቹ የጽሑፍና የቃል ፈተና ተፈትናቹ ለነበረ ይህ ማስታወቂያ ወጥቷል።
ለሌሎች እንዲደርስ Share ያድርጉት።

የፌደራል ሰበር ሰሚ ችሎት ውሳኔዎች ቅጽ 28 ሙሉውን ከታች ያለውን ሊንክ በመጫን ያገኙታል።https://t.me/etonlinelegal
09/02/2026

የፌደራል ሰበር ሰሚ ችሎት ውሳኔዎች ቅጽ 28 ሙሉውን ከታች ያለውን ሊንክ በመጫን ያገኙታል።
https://t.me/etonlinelegal

መረጃው ለብዙዎች እንዲዳረስ Share ያድርጉት።የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ጥቅምት 27 ቀን 2018 ዓ.ም አውጥቶት ለነበሩት የሥራ መደቦች ለተመዘገባቹ በሙሉ።
21/01/2026

መረጃው ለብዙዎች እንዲዳረስ Share ያድርጉት።
የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ጥቅምት 27 ቀን 2018 ዓ.ም አውጥቶት ለነበሩት የሥራ መደቦች ለተመዘገባቹ በሙሉ።

🥺🥺🥺መርዶ በቀን አይነገርም ነበር እኮ🥺🥺🥺ነፍስህ ከደጋጎቹ ጋር ትረፍ🥺🙏🥺ለሁላችንም መጽናናቱን ይስጠን🥺🙏🥺
16/01/2026

🥺🥺🥺
መርዶ በቀን አይነገርም ነበር እኮ
🥺🥺🥺
ነፍስህ ከደጋጎቹ ጋር ትረፍ🥺🙏🥺
ለሁላችንም መጽናናቱን ይስጠን🥺🙏🥺

የDNA ምርመራ ወጪን ማን መክፈል አለበት?"እናትነት እውነት፤ አባትነት እምነት።"ታኅሳሥ 28 ቀን 2018 ዓ.ምአዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ #አንድን ወንድ ለአንድ ሕጻን አባቱ ነው ተብሎ ይወሰን...
06/01/2026

የDNA ምርመራ ወጪን ማን መክፈል አለበት?
"እናትነት እውነት፤ አባትነት እምነት።"
ታኅሳሥ 28 ቀን 2018 ዓ.ም
አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ
#አንድን ወንድ ለአንድ ሕጻን አባቱ ነው ተብሎ ይወሰንልኝ በማለት በፍርድ ቤት ውሳኔ ለማሰጠት በማያሻማ ሁኔታ ወንድየው ለሕጻኑ አባት መሆኑን ማረጋገጥ ያስፈልጋል።
#በትዳር ወይም ሳይጋቡ እንደባልና ሚስት በመኖር ግንኙነት ውስጥ ለሚወለዱ ልጆች ሕጉ ባልየው አባት ነው ተብሎ የሕግ ግምት እንደሚወሰድ ደንግጓል። የተሻሻለው የቤተሰብ ሕግ አንቀጽ 126 እና 130 /1/ን ይመለከቷል።
#የአባትነት ይረጋገጥልኝ ጥያቄ ብዙውን ጊዜ አከራካሪ የሚሆነው ከትዳር ወይም ሳይጋቡ እንደባልና ሚስት ከመኖር ግንኙነት ውጪ ለሚወለዱ ሕጻናት ነው።
የምርመራውን ወጪ ማን መሸፈን አለበት?
#በፍርድ ቤት ክርክር በየትኛውም አግባብ በፍርድ ቤት ትዕዛዝ እንዲቀርብለት የጠየቀውን ለማስረጃ ለማስቀረብ የጠየቀ ወገን ወጪን መሸፈን እንዳለበት ግልጽ ነው።
#በመሆኑም የDNA Test /የዘረመል ምርመራ/ እንዲደረግለት የጠየቀ ወገን ለምርመራው የሚያስፈልገውን ወጪ የመሸፈን ግዴታ ይኖርበታል።
ይግባኝ መብት ነው!!!
©ቴዎድሮስ አብዲሳ
በማናቸውም የፌደራል ፍርድ ቤት ጠበቃና የሕግ አማካሪ
☎️09 10 61 69 50
📍አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ🇪🇹

ነገር ግን እነዚህን የወራሹን ጥፋቶች ሟች ግልጽ በሆነ ጽሑፍ ይቅርታ ያደረለገት እንደሆነ ከውርስ መነቀሉ ይቀርልታል። #ሟች ተወላጅ ልጁን ከውርስ ለመንቀል የሚፈልግ ቢሆን በኑዛዜው ላይ በም...
29/12/2025

ነገር ግን እነዚህን የወራሹን ጥፋቶች ሟች ግልጽ በሆነ ጽሑፍ ይቅርታ ያደረለገት እንደሆነ ከውርስ መነቀሉ ይቀርልታል።
#ሟች ተወላጅ ልጁን ከውርስ ለመንቀል የሚፈልግ ቢሆን በኑዛዜው ላይ በምን ምክንያት እንደነቀለው በግልጽ ማመላከት እንዳለበት በፍትሐ ብሔር ሕጉ ቁጥር 938 /1/ ላይ ላይ “ተናዛዡ ከርስት ከውርስ ለመንቀል የደረሰበትን ምክንያት በኑዛዜው ውስጥ ካልገለጸ በቀር ልጁን ወይም ወደ ታች የሚቈጠር ተወላጁን ከውርስ ቢነቅል አይጸናም።” በማለት ይደነግጋል።
#ሟች ተወልጃ ልጁን ከውርስ ለመንቀል የሚችልባቸው ምክንያቶች ምን ምን እንደሆኑ በፍትሐ ብሔር ሕግ ቁጥር 838 ላይ በግልጽ ተመልክተዋል። እነሱም፦
የፍትሐ ብሔር ሕግ ቁጥር 838 ያልተገባ ስለ መሆን (1) ወንጀሎች ወይም ቅጣቶች
#ሟቹን ለመውረስ የማይገባ ነው ተብሎ የወራሽነትን መብት የሚያጣው
1️⃣ሟቹን ወይም የሟቹን ወደ ታች የሚቆጠሩ ተወላጅ ወይም ወደ ላይ የሚቆጠሩ ወላጆች አንዱን ወይም የሟቹን ባል ወይም ሚስት አስቦ በመግደል የተፈረደበት።
2️⃣ከነዚሁ ሰዎች መካከል አንደኛውን ለመግደል በመሞከር የተቀጣ።
3️⃣በሐሰት በወንጀል ወይም በሐሰት ምስክርነት ይህ በሐሰት መወንጀል በሐሰት መመስከር ከነዚሁ ሰዎች መካከል በአንደኛው ላይ የሞት ፍርድ ወይም ከአስር ዓመት የበለጠ የጽኑ እስራት ቅጣትን ለማስተካከል የሚያሰጋ ሁኖ የተቀጣ ማኛውም ሰው ነው።
በሁሉም ምክንያቶች ወራሹ በወንጀል ተከሶ ቅጣት የተጣለበት መሆን አለበት።
የፍትሐ ብሔር ሕግ ቁጥር 840 (3) ሌሎች ምክንያቶች
#በተለይ ሟቹን ለመውረስ የማይገባ ነው ተብሎ
ሀ. የሟቹን ሰውነት ሁኔታ ምክንያት በማድረግ አውራሹ ከመሞቱ በፊት በአሉት በሦስት ወር ውስጥ ኑዛዜ እንዲያደርግ እንዳይለውጥ ወይም እንዳይሽር የከለከለ።
ለ. አስቦ ያለሟቹ ፈቃድ የሟቹን የመጨረሻ ኑዛዜ ያበላሸ እንይገኝ ያደረገ ያጠፋ ወይም ጉዳዩን በማወቅ በሐሰት ኑዛዜ የተጠቀመ የወራሽነት መብት ያጣል።
ይግባኝ መብት ነው!!!
©ቴዎድሮስ አብዲሳ
በማናቸውም የፌደራል ፍርድ ቤት ጠበቃና የሕግ አማካሪ
☎️09 10 61 69 50
📍አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ🇪🇹

የታኅሳሥ ወር 2018 ዓ.ም የሐራጅ ማስታወቂያ ሙሉውን ለመመልከት ይህንን link https://t.me/etonlinelegal ይጫኑ።
06/12/2025

የታኅሳሥ ወር 2018 ዓ.ም የሐራጅ ማስታወቂያ ሙሉውን ለመመልከት ይህንን link https://t.me/etonlinelegal ይጫኑ።

Address

Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ጠበቃ ቴዎድሮስ አብዲሳ Lawyer Tewodros Abdisa posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share

Category