29/08/2026
‹ሀላፊነት የማይሰማው ፍትሕ ሚኒስቴር እና
ባለቤት አልባው ዓቃቢያነ-ሕግ›
#የሰመራውን ጉባዔ ለዓቃቢያነ ህጎች የደመወዝ ጥያቄን መልስ ይሰጣል ተብሎ በጉጉት ቢጠበቅም ለባለሙያዎች እንደተቋም መልስ ሊሰጥ የማይችል ሆኖ ተጠናቋል። ሌሎች ተቋማት ከፌደራል እስከ ክልል የደምወዝና ጥቅማጥቅም መብት ቢያስከብሩም ፍትሕ ሚኒስቴር ግን ለክልል ፍትሕ ቢሮዎች እናት ተቋም መሆን የማይችል እንዲሁም የፍትሕ ስርዓት ማዕዘንነቱን አጥቷል። ዓቃቢያነ ሕጎችም ባለቤት አልባ የማይሰሙና የማይደመጡ ሆነዋል።
👉ዓ/ህጎች ስለቀጣይ በማህበራችሁና በሌሎች አማራጭ መንገዶች መብታችሁን ለማስከበር እራሳችሁን አዘጋጁ!