Heni Lawyer

Heni Lawyer This page created to gives legal advice .

22/02/2022

“እግዚአብሔርን አሰብሁት ደስ አለኝም።” መዝ 77፥3

21/02/2022
20/02/2022

‼️ የውርስ ይርጋ ስንት ነው 🤔
🚨 ሙሉውን ከስር ያለዉን #ሊንክ በመጫን ማውረድ ይቻላል ⤵️
👉 t.me/joinchat/AAAAAExPP_EV3XyLKhhCpw
👉 t.me/joinchat/AAAAAExPP_EV3XyLKhhCpw
#አመለካከት 🇪🇹 #ሀበሻ

18/02/2022

📌 🚨 ጠቃሚ መፅሀፎችን ከስር ሊንኩን ተጭነው ማግኘት ይችላሉ ⤵️
👉 t.me/joinchat/TE8_8RXdfIsqGEKn
👉 t.me/joinchat/TE8_8RXdfIsqGEKn
👉 t.me/joinchat/TE8_8RXdfIsqGEKn
👉 t.me/joinchat/TE8_8RXdfIsqGEKn

🛡️ ተጨማሪ ማብራሪያ በቪዲዮ ለመከታተል ⤵️
➡️ https://bit.ly/3qO8YAP
➡️ https://bit.ly/3qO8YAP

ሳሙኤል ግርማ
የሕግ አማካሪና ጠበቃ
0911 190 299


#ጠበቃ #ሕግ #ሳሙኤልግርማ #ህግ #ጠበቃሳሙኤል
0911-190-299

#ሀበሻ

18/02/2022

❗በማናቸውም የኢትዮጵያ ከተሞች መሬት ላይ የተተከሉ ፍራፍሬ አቡካዶ ሙዝ ብርቱካን የመሳሰሉትን እና ለምግብነት የማይውሉ እንደ ዋንዛ ግራቪላ አይነት ተክሎች በአውራጎዳና መንገድ ማስፍፍት ወይም በማናቸውም የልማት ስራዎች ከቦታቸው ላይ ለሚነሱ ዜጐች የሚከፈል ካሳ ⤵️⤵️

📌 ሙሉ መመሪያውን ከስር ሊንኩን ተጭነው ማውረድ ይችላሉ ⤵️⤵️
👉 t.me/joinchat/AAAAAExPP_EV3XyLKhhCpw
👉 t.me/joinchat/AAAAAExPP_EV3XyLKhhCpw
👉 t.me/joinchat/AAAAAExPP_EV3XyLKhhCpw
👉 t.me/joinchat/AAAAAExPP_EV3XyLKhhCpw

📱 +251 911190299

#1 🇪🇹 Share Share Share

ሳሙኤል ግርማ
የሕግ አማካሪና ጠበቃ
0911 190299

🚨 #ከስር ተጭነው #በቴሌግራም ይቀላቀሉን 👇
t.me/joinchat/AAAAAExPP_EV3XyLKhhCpw
t.me/joinchat/AAAAAExPP_EV3XyLKhhCpw
t.me/joinchat/AAAAAExPP_EV3XyLKhhCpw
t.me/joinchat/AAAAAExPP_EV3XyLKhhCpw

📱 +251 911190299

#1 🇪🇹 Share Share Share

18/02/2022

🛎️ የውርስ ንብረት ክፍፍል እንዴት ይፈጸማል ⁉️

ከውርስ ሐብት ጋር በተያያዘ በተለይም ደግሞ የክፍፍሉ ሂደት በሕግ እንዴት ይመራል ❓

የውርስ ጉዳይ በፍትሐብሔር የህጉ ዘርፍ ሰፊ ስፍራ ከሚሰጣቸው ዓበይት ጉዳዮች ውስጥ አንዱ ነው። ውርስ በውስጡ በርካታ ጽንሰ ሐሳቦችን ይዟል። ውርስ ከውርስ አከፋፈት ጀምሮ የውርስ መብቶችን እስከ ማስተላለፍ ድረስ ስለ ኑዛዜ፣ ስለ ወራሽነት ችሎታ፣ ከውርስ ስለመነቀል፣ ስለ ውርስ ማጣራት፣ ስለ ውርስ አስተዳደር፣ ስለ ውርስ እዳ አከፋፈል፤ ስለ ውርስ ንብረት ክፍፍል ወዘተ ስለሚመለከቱ ጉዳዮች በውስጡ አካቷል።
ስለ ውርስ ሲነሳ የውርስ ንብረት ጉዳይ ዋነኛ ማጠንጠኛ ነው። በጠቅላላ አነጋገር የውርስ ንብረት ሲባል ሟች በሕይወት ዘመኑ ያፈራውና በኑዛዜም ሆነ ያለኑዛዜ (በህግ) ወራሽ ለሆኑት ሰዎች የሚተላለፍ ሐብት ማለት ነው። ሟች ትቶት ያለፈው የሚንቀሳቀስም ሆነ የማይንቀሳቀስ፣ የሚዳሰስም ሆነ የማይዳሰስ፣ ከሦስተኛ ወገኖች ጋር ባደረገው የውል ስምምነት የሚያስገኝለት ሐብት እንዲሁም ከተመሰረተ የፍርድ ቤት እና የአስተዳደር ክርክር የሚያገኘው ጥቅም ሁሉ የውርስ ሐብት ነው። ይህ ሐብት ደግሞ ሟች በመሞቱ ምክንያት የሚቋርጥ መብትና ግዴታ ካልሆነ በቀር መብትን ብቻ ሳይሆን ግዴታንም ስለሚያጠቃልል ወራሾች ከአውራሻቸው የሚወርሱት እዳንም ጭምር ነው ማለት ነው።

በ1952 ዓ.ም ወጥቶ እስከአሁንም ድረስ በሥራ ላይ በሚገኘው የአገራችን የፍትሐብሔር ሕግ ስለ ውርስ በተመለከተው ክፍሉ ውስጥ ስለ ውርስ ንብረት ምንነት እና ስለሚያጠቃልላቸው ሐብቶች የሚያስቀ ምጠው ድንጋጌ የለም። ያም ሆኖ ከንብረት ሕግ መሰረታዊ ጽንሰ ሃሳብና ከውርስ መርሆ አንጻር ሲታይ ሟች ህይወቱ እስካለፈችበት ቀን ድረስ በባለቤትነት፣ በይዞታ፣ በአላባ ተጠቃሚነት ወይም በማናቸውም ሁኔታ የያዘው ንብረትም ሆነ ከዚሁ ንብረት ጋር የተያያዙ መብትና ግዴታዎች ሁሉ የውርስ ሀብት እንደሆኑ መገንዘብ ያስፈልጋል።

ይህ አጠቃላይ ግንዛቤ እንደተጠበቀ ሆኖ የውርስ ሕጉ ከሁሉም የውርስ ንብረቶች ለይቶ ለሕይወት ኢንሹራንስ ስለሚከፈል ገንዘብ፣ ስለ ጡረታና ካሣ በግልጽ አነጋገር ድንጋጌ አስቀምጦላቸዋል። ጡረታና ካሣን በተመለከተ ሕጉ በሞት ምክንያት ለሟቹ ዘመዶች ወይም ለባል ወይም ለሚስት የሚሰጡ ጡረታዎች ወይም ካሣዎች የውርሱ ሐብት አካል አይሆኑም በማለት በግልጽ አስቀምጧል።

ይህ ማለት በሕግ አግባብ የሟች ባሏን ጡረታ ወርሳ ስትጠቀም የነበረች ሴት ስትሞት ወይም የአባታቸውን ጡረታ ወርሰው ሲጠቀሙ የነበሩ ልጆች ሲሞቱ የጡረታው ገንዘብ ለወራሾች የማይተላለፍ በመሆኑ የውርስ ሀብት ክፍል አይሆንም። በተመሳሳይ በመኪና አደጋ ሕይወቱን ላጣ ሰው ልጆች ወይም ሚስት ወይም ዘመዶች ይከፈል የነበረ የካሣ ገንዘብ ተጠቃሚዎቹ ሲሞቱ ለወራሾቻቸው ሊተላለፍ ስለማይችል የውርስ ሀብት አካል አይሆንም።

ለህይወት ኢንሹራንስ የሚከፈልን ገንዘብ በተመለከተ ደግሞ በህጉ ለየት ያለ ድንጋጌ ተቀምጧል። የፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 827 ሟች ለሕይወት ኢንሹራንስ (መድን) የሚከፍለው ገንዘብ የውርስ ንብረት አካል ሊሆን እንደሚችል ያመለክታል። (በንግድ ሕጉ አንቀጽ 691 መሰረት የህይወት ኢንሹራንስ ማለት የኢንሹራንስ ኩባንያው ተዋዋዩ ስለኢንሹራንሱ የሚከፍለውን ገንዘብ በአንድ ጊዜ ወይም በተለያየ ጊዜ ተቀብሎ በተዋዋዩ ወይም ኢንሹራንስ በተገባለት ሦስተኛ ወገን ህይወት ወይም ሞት ጋር የተገናኙ ሁኔታዎች በደረሱ ጊዜ የተወሰነ ገንዘብ ለተዋዋዩ ወይም ለተጠቃሚው ለመክፈል የሚዋዋለው ውል ነው።)

ይህ የኢንሹራንስ ገንዘብ የውርስ ሀብት የሚሆነው ታዲያ በሁለት ሁኔታዎች ብቻ መሆኑን ሕጉ ያመለክታል። አንደኛ ሟች ለሕይወት በገባው ኢንሹራንስ ውስጥ የኢንሹራንሱን ተጠቃሚ በግልጽ በውሉ ውስጥ ያልወሰነ እንደሆነ ነው። ሁለተኛው ደግሞ ኢንሹራንሱ ለሟቹ ወራሾች ጥቅም ከተደረገ ነው። ከእነዚህ ሁኔታዎች ውጪ ግን (ለምሳሌ የኢንሹራንሱ ተጠቃሚ በግልጽ በውሉ ውስጥ ከተገለጸ) ለህይወት ኢንሹራንስ የሚደረግ ክፍያ የውርሱ ሐብት ክፍል አይሆንም። ይልቁንም ተጠቃሚው በኢንሹራንስ ውሉ ውስጥ የተገለጸው ሰው ብቻ ይሆናል።

ጉዳዩን በቀላሉ ለመረዳት እነዚህን አጭርና ግልጽ ምሳሌዎችን እንመልከት። አቶ ዓለማየሁ የተባሉ ሟች በሕይወት ሳሉ በአዋሽ ኢንሹራንስ ኩባንያ በገቡት የህይወት ኢንሹራንስ ውል ውስጥ የኢንሹራንሱን ተጠቃሚ በግልጽ ሳያመለክቱ ለአስር ዓመታት ለኩባንያው የኢንሹራንስ ክፍያ ፈጽመዋል። ወይዘሮ ማዘንጊያ የተባሉ ሟች ደግሞ በኩባንያው በገቡት የህይወት ኢንሹራንስ ውል ውስጥ ለእከሌ ለእከሌ ሳይሉ ለወራሾቼ ጥቅም በሚል ለአምስት ዓመታት ክፍያ ፈጽመዋል። በሁለቱም ምሳሌዎች ውስጥ የተከፈለው የኢንሹራንስ ክፍያ ገንዘብ የሟቾች የውርስ ሀብት አካል ይሆናል ማለት ነው።

የውርስ ንብረት ክፍፍል እንዴት ይፈጸማል?

የውርስ ንብረት ክፍፍል ጉዳይ በወራሾች መካከል የአለመግባባትና የክርክር መነሻ ነው። የሟች የቀብር ሥነ ስርዓት ከተፈጸመ ከቀናት በኋላ ወሬዎች ሁሉ የሚያተኩሩት ስለ ሟች ንብረትና ስለ ውርስ ጉዳይ ይሆናል። አንዳንዴም ድንኳን ሳይፈርስ እና እንባም ሳይደርቅ ቤተዘመዳሞችና ይገባናል ባዮች እሰጥ አገባ ውስጥ ሲገቡ የሚስተዋልባቸው አጋጣሚዎች ጥቂት አይደሉም።

ከዚያ ቀደም በጽኑ ፍቅር ይኖሩ የነበሩ እናትና ልጆች፤ እህትና ወንድሞች፣ አባትና ልጆች ወዘተ በውርስ ሀብት ክፍፍል ወቅት መስማማት እየተሳናቸው የፍርድ ቤቶችን ግቢ ሲያጨናንቁ ይውላሉ። ከበርካታ የክርክር መዛግብት ለመረዳት እንደሚቻለውም በውርስ ሀብት ምክንያት በርካታ ዘመዳሞች በባለጋራነት ተፈራርጀው ተከራክረዋል። ከውሳኔዎቹ ማግስት የዝምድና ገመዳቸው ተበጥሶ የተቆራረጡትን ቤት ይቁጠራቸው።

የሆነው ሆኖ የውርስ ሀብት ክፍፍል በአግባቡ እና ወራሾችን በሚያስማማ መልኩ እንዲከናወን የህጉን ድንጋጌዎች ማወቅ አስፈላጊ ነው። በዚህ መነሻ የውርስ ሀብት ክፍፍል የሚፈጸምበትን ሕጋዊ አካሄድ በዝርዝር እንመለከታለን። የውርስ ንብረት ከመከፋፈሉ አስቀድሞ የውርስ አጣሪ የሚባል አንድ ወይም ከዚያ በላይ የሆነ ሰው ይሾማል። የውርስ አጣሪ በህግ (ያለ ኑዛዜ ወራሽ የሆኑ ሰዎች)፣ በሟቹ ኑዛዜ የተመለከተ ወይም በፍርድ ቤት የተሾመ ሊሆን ይችላል።

የውርስ አጣሪውም ሟች ኑዛዜ ያለው መሆን ያለመሆኑን፣ ወራሾች የትኞች እንደሆኑ (በኑዛዜም ይሁን ያለኑዛዜ የሚወርሱትን)፤ ምን ዓይነት የውርስ ንብረት የት ቦታ እንደሚገኝ፤ ሟች የነበሩበትን እዳዎች ወዘተ በማጣራት ከነማስረጃዎች መዝግቦ ያስቀምጣል። ውርስ የማጣራት ጉዳይ በጣም መሰረታዊ ከመሆኑም በላይ በአግባቡ ካልተከናወነ ደግሞ የኋላ ኋላ በብዙ ሰዎች ላይ የማይተካ ጉዳት ሊያስከትል ይችላል።

የውርስ ንብረት በወራሾች መካከል ከመከፋፈሉ አስቀድሞ ታዲያ የውርስ እዳዎች በሚል በህግ የተመለከቱት ክፍያዎች ከውርሱ ንብረት ላይ መፈጸም አለባቸው። በዚሁ መሰረት በመጀመሪያ የሚከፈለው ለሟች ስርዓተ ቀብር ወጪ የሆነ ገንዘብ ነው። ቀጥሎ የሚከፈለው ደግሞ የውርሱን ንብረት ለማስተዳደርና ውርሱን ለማጣራት የወጣ ወጪ ነው። ሟች በመሞቱ ምክንያት የማይቋረጡ እዳዎች ለምሳሌ ብድር በሦስተኛ ደረጃ ይከፈላሉ። ለቀለብ ጠያቂዎች (የሟች ባል ወይም ሚስት፣ ልጆች ወይም ወንድምና እህት) እንዲሁም ሟቹ ያደረጋቸውን ልዩ ኑዛዜዎች በመጨረሻ ደረጃ ከውርሱ ንብረት ላይ እንዲከፈሉ ይደረጋል።

በህጉ የውርስ እዳዎች በሚል የተሰየ ሙት ከላይ የተዘረዘሩት አምስት ዓይነት እዳዎች እንደቅደም ተከተላቸው በየተራ ተከፍለው ከተጠናቀቁ በኋላ ወሳኙ ጉዳይ የውርሱን ሐብት ክፍፍል መፈጸም ነው። በፍትሐብሔር ሕጉ ቁጥር 1079 በግልጽ ተደንግጎ እንደምናነበው የውርስ ንብረት ክፍፍል የሚፈጸመው በወራሾች መካከል በሚደረግ ስምምነት ነው። ወራሾች ያልተስማሙ ከሆነ ግን ከመካከላቸው አንዱ በትጋት ያሰናዳው የውርስ ሐብት ክፍፍል ለፍርድ ቤት ቀርቦ እንዲጸድቅ በማድረግ ነው።

በዚሁ መሰረት ህጉ የመከፋፈሉን አፈጻጸም ደንብም ያስቀመጠ ሲሆን፤ የንብረት ክፍፍል የሚፈጸመውም ሟቹ በጻፈው የኑዛዜ ቃል መሰረት ስለመሆኑ ሕጉ ይደነግጋል። ስለክፍፍሉ የተጻፈ የኑዛዜ ቃል የሌለ ከሆነ ግን ህጉ የራሱን የክፍፍል ድንጋጌዎች አስቀምጧል። ንብረቶቹን ለመከፋፈል ደግሞ ግምታቸው መቀመጥ አለበት። ንብረቶቹ ክፍፍሉ በሚደረግበት ቀን እንደሚገመቱና የሚገምቱትም ራሳቸው ወራሾቹ መሆናቸውን ሕጉ አስቀምጧል። ወራሾች ካልተስማሙ ደግሞ በመረጧቸው ወይም በፍርድ ቤት በተመረጡ ሽማግሌዎች ንብረቶች ይገመታሉ። የማይንቀሳቀሱ ንብረቶች ደግሞ በአዋቂዎች ለምሳሌ በመሀንዲስ ግምት ይወጣላቸዋል። ንብረቶች ግምት ከወጣላቸው በኋላ በወራሾች ወይም በፍርድ ቤት የተመረጠ ሰው ወይም አዋቂ ንብረቶቹን ለወራሾች ያደላድላል ማለት ነው።

የውርስ ንብረት ከሚከፋፈልባቸው መርሆዎች ውስጥ አንዱ ታዲያ የውርስ ንብረት በዓይነት የሚከፋፈልበት አሠራር ነው። ይኸውም እያንዳንዱ ወራሽ ከውርሱ ንብረት ውስጥ በዓይነት እየተሰጠው ክፍፍሉ የሚፈጸምበት ሂደት ነው። ወራሾች ንብረቶችን በዓይነት ሲከፋፈሉ ደግሞ ዋጋቸው የተለያየ ሊሆን ስለሚችል እኩል ድርሻ ላይኖር ይችላል። እንዲህ ያለው ሁኔታ ሲያጋጥም ደግሞ አብላጫ ዋጋ ያለውን ንብረት የወሰደ ሰው አነስተኛ ዋጋ የተቆረጠለትን ንብረት ለወሰደው ወራሽ ተጨማሪ ገንዘብ እንዲሰጠው በማድረግ ድርሻቸውን ማስተካከል እንዲችሉ ነው ህጉ መፍትሔ ያስቀመጠው።

እዚህ ላይ ሳይጠቀስ የማይታለፍ መሰረታዊ ጉዳይ የንብረት አመዳደብ በሚደረግበት ወቅት ንብረቶቹ የሚመደቡት ለእያንዳንዱ ወራሽ የሚሰጡት ጠቀሜታ ታሳቢ ተደርጎ መሆን አለበት የሚለው ነው። ለምሳሌ የእንጨት መሰንጠቂያና ጣውላ ማዘጋጃ ፋብሪካ በውርሱ ንብረት ውስጥ ቢኖር በቤትና የቢሮ ዕቃዎች ምርት ላይ ለተሰማራ ወራሽ ሊደለደል ያስፈልጋል ማለት ነው። ከዚህ ሌላ ኢትዮጵያውያንና የውጭ አገር ዜጎች ወራሾች በሆኑበት የንብረት ክፍፍል ሂደት ውስጥ የማይንቀሳቀሱ ንብረቶች ካሉ ለኢትዮጵያውያን እንዲደለ ደሉም ሕጉ ደንግጓል።

ከወራሾች አንዱ ለውርሱ የሚከፍለው እዳ ያለበት እንደሆነ (ለምሳሌ ከሟች አባቱ ገንዘብ የተበደረ ልጅ) እዳው በድርሻው ውስጥ እንደሚታሰብበትም ልብ ማለት ያስፈልጋል። በተጨማሪም የቤተዘመድ መታሰቢያ ዕቃዎች በሚል ህጉ የገለጻቸው ጽሑፎችና የመታሰቢያ ዕቃዎች ለሽያጭ እንዳይቀርቡ ከወራሾች አንዱ የመቃወም መብት እንዳለውና በወራሾች መካከል ስምምነት ከጠፋ ዕቃዎቹ ከቤተዘመድ እጅ እንዳይወጡ አስፈላጊውን ጥንቃቄ በማድረግ ለአንዱ ወራሽ እንዲሰጡ ወይም እንዲሸጡ ፍርድ ቤት ሊወስን እንደሚችል ግንዛቤ መያዝም ያስፈልጋል።

ወራሾች የውርስ ሀብትን በዓይነት መከፋፈል ካልቻሉ ወይም በዓይነት ለመከፋፈል የማይቻል ንብረት ካለ ወይም በዓይነት ለመከፋፈል አስቸጋሪ ሁኔታዎች ሲገጥማቸው ከመካከላቸው አንዱ ንብረቱን እንዲወስድ እና የድርሻውን ቀንሶ ዋጋውን እንዲሰጣቸው መስማማት ይችላሉ። የውርስ ንብረት ተሸጦ ገንዘቡን ሳይሆን በዓይነት እንዲከፋፈል ህጉ የፈለገበት ዓይነተኛ ምክንያት ህብረተሰቡ ለውርስ የሚሰጠውን የተለየ ቦታ ከግምት ውስጥ በማስገባት ከሚሸጥ ይልቅ በወራሾች እጅ እንዲቆይ ለማድረግ ነው።

የሆነው ሆነ በዓይነት ለመከፋፈል ካልተስማሙ ግን ንብረቱ ይሸጣል ማለት ነው። የመጀመሪያው የሽያጭ ሂደት በራሳቸው በወራሾቹ መካከል የሚደረግ የሐራጅ ሽያጭ ስለመሆኑ ከፍትሐብሄር ሕግ ቁጥር 1093 (1) መንፈስ ለመረዳት ይቻላል። በወራሾቹ መካከል የሐራጁን ጨረታ ለማድረግ ስምምነት የታጣ ከሆነ ግን ባዕድ የሆነ ሰው የሚሳተፍበት የሐራጅ ጨረታ ተካሂዶ ንብረቱ እንደሚሸጥና ገንዘቡን እንደሚከፋፈሉ ህጉ ያመለክታል።

ጉዳዩን ይበልጥ ግልጽ ለማድረግ አንድ በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት እልባት ያገኘን የውርስ ክርክር በወፍ በረር እንመልከት። ሟች ስድስት ልጆችን አፍርተው ነበር ይህን ዓለም የተሰናበቱት። ለልጆቻቸው ያቆዩትን አንድ ቤት ደግሞ አንዷ ልጃቸው በይዞታዋ አድርጋ ትቆያለች። የኋላ ኋላ አንደኛው ወንድሟ ቤቱ የውርስ ንብረት ስለሆነ ስድስት ወራሾች ስለሆንን ቤቱ በጨረታ ተሸጦ ድርሻዬን ትስጠኝ ሲል ክስ ይመሰርታል። እህት በበኩሏ ሟች አባቷ በህይወት እያሉ ከዓመታት በፊት በስጦታ ያስተላለፉላት መሆኑንና መብራትና ውሃ በስሟ አስገብታ ስትጠቀምበት የቆየች የግል ንብረቷ መሆኑን ጠቅሳ ተከራከረች።

ጉዳዩን በመጀመሪያ ደረጃ የዳኝነት ስልጣኑ የተመለከተው የወረዳ ፍርድ ቤት እና በይግባኝ ክርክሩን ያደመጠው የዞን ፍርድ ቤት እና የክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎትም ንብረቱ የውርስ ሐብት ነው በሚል ለስድስት ወራሾች እንዲከፋፈል ከወሰኑ በኋላ ክፍፍልን በተመለከተ ደግሞ ቤቱ በሐራጅ ተሸጦ ወንድም (ከሳሽ) የድርሻውን እንዲወስድ ይወስኑለታል። ይሁንና እህት በውሳኔው ቅር በመሰኘት በአገሪቱ የመጨረሻ የዳኝነት ስልጣን ላለው ለፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ዶሴዋን አቀረበች። ችሎቱም የሥር ፍርድ ቤቶች በክፍፍል ረገድ የሰጡትን ውሳኔ በመሻር የቤቱ የገበያ ዋጋ ተገምቶ ባለይዞታዋ እህት ለአምስቱ ወራሾች ድርሻ በመክፈል ቤቱን በዓይነት እንድታስቀር ወስኖላታል። ይህንን ማድረግ ካልቻሉ ግን ቤቱ በጨረታ ተሸጦ ሁሉም ወራሾች ድርሻቸውን እንዲ ወስዱ ሲል ነው የወሰነው።

ከዚህ ክርክርና ውሳኔ የምንረዳው መሰረታዊ ጉዳይ የውርስ ሐብትን ሸጦ ገንዘቡን መከፋፈል የመጀመሪያ ሕጋዊ ሂደት አለመሆኑን ነው። ከሁሉም በላይ አንዱ ወራሽ ንብረቱ ተሸጦ የድርሻ ገንዘቤ ይሰጠኝ በማለቱ ብቻ የውርስን ንብረት ለሽያጭ ማቅረብ ሕጋዊ አካሄድ አለመሆኑን መገንዘብ ይቻላል። በመሆኑም የውርስ ሐብት ክፍፍል በቅድሚያ በዓይነት በሚደረግ ድልድል መሆን እንዳለበት እንዲሁም በዓይነት ለመከፋፈል በወራሾች መካከል ስምምነት ከሌለ ደግሞ ንብረቱን በመሸጥ መከፋፈል እንደሚቻል ህጉ አስቀምጧል። በዚህ የውርስ ንብረት ሽያጭ አማራጭ ሂደት ታዲያ ንብረቱን በገበያ ዋጋው የማስቀረት ፍላጎት ያላቸው ወራሾች መብት ጥበቃ የተደረገለት ነው ማለት ነው።

ሳሙኤል ግርማ
የሕግ አማካሪና ጠበቃ

🛑 👇👇

👉 t.me/joinchat/AAAAAExPP_EV3XyLKhhCpw
👉 t.me/joinchat/AAAAAExPP_EV3XyLKhhCpw


📱 0911-190-299

18/02/2022
18/02/2022

በቴሌግራም የሕግ ቻናላችንን ይቀላቀሉ ➘
telegram.me/ethiolawblog
Telegram.me/ethiolawblog

18/02/2022

Address

Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Heni Lawyer posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share