Free-Legal/ነፃ-ሕግ

Free-Legal/ነፃ-ሕግ Stay Legally Aware make a better decisions, and avoid unnecessary mistakes.
(1)

ማንኛውም የመንግሥት አካል የሚያወጣቸው ደንቦችና መመሪያዎች የትኛውም መሥሪያ ቤት ወይም የሥራ ሃላፊ በሠራተኞች ላይ የሚሰጠው የስንብት ውሳኔ በፍርድ ቤት ወይም በዳኝነት አካል እንዳይታይ መ...
26/07/2026

ማንኛውም የመንግሥት አካል የሚያወጣቸው ደንቦችና መመሪያዎች የትኛውም መሥሪያ ቤት ወይም የሥራ ሃላፊ በሠራተኞች ላይ የሚሰጠው የስንብት ውሳኔ በፍርድ ቤት ወይም በዳኝነት አካል እንዳይታይ መከልከል ኢ_ ሕገመንግስታዊ ስለመሆኑ ።በሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር 155/2000 አንቀጽ 37 ሥር የተደነገገው የመጨረሻ ውሳኔ የመስጠት ሥልጣን የዜጎችን እኩልነት እና ፍትሕ የማግኘት መብት የሚጥስ በመሆኑ ተፈጻሚነት የለውም በሚል የፌዴሬሽን ምክር ቤት በመስከረም 27/2018 ዓ.ም በመ/ቁ 142/2017 የሰጠው ውሳኔ.

"""""""""""""""""" #የመብት እኩልነት፦
26/07/2026

""""""""""""""""""
#የመብት እኩልነት፦

23/07/2026

ፍርድ ቤት ቀርበው ሳይጸድቁ የሕግ ውጤት የማይኖራቸው ጉዳዮች
1. የጉዲፈቻ (Adoption) ውል
የኢትዮጵያ የቤተሰብ ሕግ ቁጥር 194 የጉዲፈቻ ውል በፍርድ ቤት ካልጸደቀ የሕግ ውጤት አያስከትልም።
ምሳሌ፦ አቶ አበበ እና ወ/ሮ አልማዝ ልጅ ጉዲፈቻ ቢያደርጉም ፍርድ ቤት ካላጸደቀው ልጁ በሕግ ልጃቸው አይቆጠርም።
2. በጋብቻ ውስጥ የሚደረግ የስጦታ (Donation) ውል
የፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 2447–2448 በባልና ሚስት መካከል የሚደረግ አንዳንድ የስጦታ ውል በፍርድ ቤት መጽደቅ ያስፈልገዋል።
3. በጋብቻ ውስጥ የግል ንብረት ስምምነት
የተሻሻለው የቤተሰብ ሕግ አንቀጽ 57–60 ባልና ሚስት ንብረትን በተመለከተ የሚያደርጉት ስምምነት በፍርድ ቤት መጽደቅ አለበት።
ምሳሌ፦ ቤቱ የባል ብቻ ንብረት ነው ብለው ቢስማሙ ፍርድ ቤት ካላጸደቀው በሦስተኛ ወገን ላይ አይተገበርም።
4. የጋብቻ ውልን ማሻሻል
የቤተሰብ ሕግ አንቀጽ 61 የጋብቻ ውል ማሻሻያ በፍርድ ቤት ሳይጸድቅ ሕጋዊ ውጤት አያስከትልም።
5. ፍቺ (Divorce)
የተሻሻለው የቤተሰብ ሕግ አንቀጽ 76 እና ተከታዮቹ ባልና ሚስት በራሳቸው ስምምነት ብቻ ትዳርን ማፍረስ አይችሉም፤ የፍርድ ቤት ውሳኔ ያስፈልጋል።
6. የወራሽነት ማረጋገጫ
የፍትሐብሔር ሕግ ከአንቀጽ 947 በኋላ ያሉ ድንጋጌዎች የፍትሐብሔር ሥነ-ሥርዓት ሕግ የውርስ ማረጋገጫን የሚመለከቱ ሂደቶች ወራሽነት በፍርድ ቤት ተረጋግጦ የወራሽነት ማስረጃ እስኪሰጥ ድረስ በሕግ አይረጋገጥም።
7. ውል ማሻሻል
የፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 1675 እና ተከታዮቹ ሕጉ የፍርድ ቤት ፍቃድ እንዲያስፈልግ በግልጽ በደነገገባቸው ጉዳዮች ውስጥ ማሻሻያው ያለ ፍርድ ቤት ጸደቃ ውጤት አያስከትልም።
8. የግል ወይም የቤተሰብ ስም መቀየርየፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 32 እስከ 46 ሰዎችን የሚመለከቱ ድንጋጌዎችየፍትሐብሔር ሥነ-ሥርዓት ሕግ የፍርድ ቤት ማመልከቻ ሂደትየስም ለውጥ በፍርድ ቤት ከተፈቀደ በኋላ ብቻ በመንግስት መዝገቦች ይመዘገባል።
9. ውክልና (Agency)
የፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 2199 እና ተከታዮቹ በመሠረቱ ውክልና የፍርድ ቤት ጸደቃ አያስፈልገውም። ነገር ግን ሕጉ በልዩ ሁኔታ የፍርድ ቤት ፍቃድ ወይም ሹመት የሚጠይቅበት እንደ ሞግዚትነት ወይም አሳዳሪነት ያሉ ጉዳዮች ይለያሉ።
10. መክሰር (Bankruptcy)
የንግድ ሕግ የመክሰር ድንጋጌዎች አንድ ነጋዴ መክሰሩ የሚታወጅው በፍርድ ቤት ውሳኔ ነው።
11. የመጥፋት ውሳኔ (Declaration of Absence)
የፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 154 እሰከ 173 ሰዎችን የሚመለከቱ ድንጋጌዎች አንድ ሰው እንደጠፋ ወይም እንደሞተ በሕግ የሚታወቀው በፍርድ ቤት ውሳኔ ነው።
12. የልጅ ሞግዚት መሾም (Appointment of Guardian)
የቤተሰብ ሕግ ከአንቀጽ 255 ጀምሮ ያሉ የሞግዚትነት ድንጋጌዎች ለሕፃን ሞግዚት የሚሾመው በፍርድ ቤት ብቻ ነው።
ምሳሌ፦ የሕፃን ወላጆች ከሞቱ በኋላ አጎቱ ራሱን ሞግዚት ብሎ መቀጠል አይችልም፤ በፍርድ ቤት ሹመት ማግኘት አለበት ::

08/07/2026

እነሆ የፌደራል የታክስ አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 983/2008ን ያሻሻለው አዋጅ ዋና ዋና ለውጦች በአጭሩ፦
የመስማማት (Settlement) ሥርዓት ተጨመረ
የታክስ ክርክሮች በፍርድ ቤት ወይም በይግባኝ ሳይቀጥሉ በስምምነት እንዲፈቱ አዲስ ሥርዓት ተዘርግቷል።
የታክስ ማጭበርበር በግልጽ ተተርጉሟል
እንደ ሐሰተኛ ደረሰኝ መጠቀም፣ ገቢ መደበቅ ያሉ ተግባራት በዝርዝር ተገልጸዋል።
አዲስ ማስረጃ ለማቅረብ ገደብ ተደርጓል
ከታክስ ውሳኔ በኋላ አዲስ ማስረጃ ማቅረብ የሚፈቀደው በልዩ ሁኔታ ብቻ ሲሆን፣ ከተቀበለም 20% ቅጣት ሊያስከትል ይችላል።
የታክስ ስሌት ይርጋ ጊዜ ተሻሽሏል
መደበኛው ይርጋ 5 ዓመት እንደነበረ ቀጥሏል።
የታክስ ማጭበርበር ከተረጋገጠ ግን እስከ 10 ዓመት ድረስ የታክስ ስሌት ሊሻሻል ይችላል።
በሁኔታ ላይ የተመሰረተ የታክስ ክሊራንስ ተጀምሯል
ክርክር ላይ ያሉ ወይም የክፍያ ስምምነት ያደረጉ ታክስ ከፋዮች የንግድ ፈቃድ ለማደስ፣ በጨረታ ለመሳተፍና ብድር ለማግኘት የሚያገለግል ልዩ የታክስ ክሊራንስ ማግኘት ይችላሉ።
የታክስ ከፋዮች ምደባ ዘመናዊ ሆኗል
ምዝገባና ምደባ በዓለም አቀፍ ISIC የኢንዱስትሪ ምደባ መሠረት ይከናወናል።
ቅጣቶች ተጠናክረዋል
ደረሰኝ አለመስጠት እስከ 100,000 ብር አስተዳደራዊ ቅጣት ሊያስከትል ይችላል።
የድርጅት ሥራ አስኪያጅና የፋይናንስ ኃላፊ የታክስ ወንጀልን ካወቁ፣ ካዘዙ ወይም ካስፈጸሙ በግል ተጠያቂ ይሆናሉ።
በአጠቃላይ የማሻሻያው ዓላማ የታክስ አስተዳደርን ዘመናዊ ማድረግ፣ ክርክሮችን በስምምነት እንዲፈቱ ማበረታታት፣ የታክስ ማጭበርበርን መከላከል፣ እና የታክስ ሕግን ማስፈጸም የበለጠ ጠንካራ ማድረግ ነው።

05/07/2026

👉የመሬት ይዞታ መብት በይርጋ አይታገድም/ በይርጋም አይገኝም ሲልየፌዴሬሽን ምክር ቤት መስከረም 27 ቀን 2018 በመቁ 14//17 የሰጠዉ የህገ መንግስት ትርጉም።

የክርክሩ መነሻ :-
👉አመልካች መሬቱ በስማቸው የተመዘገበ ህጋዊ ይዞታቸው ሆኖ ሳለ፣ ተጠሪዎች በህገ-ወጥ መንገድ እንደያዙባቸው በመግለጽ እንዲለቀቅላቸው ጠይቀዋል።
👉የተጠሪዎች መከራከሪያ፡-መሬቱን ከ10 ዓመት በላይ ስለተጠቀምንበት ክሱ በ"ይርጋ" ሊታገድ ይገባል የሚል ነበር።
👉የፍርድ ቤቶች ውሳኔ
• የስር ፍርድ ቤት እና የፌዴራል ሰበር፡ ክሱ በ10 ዓመት የይርጋ ጊዜ ታግዷል በማለት የአመልካችን ጥያቄ ውድቅ አደረጉት።
✍️✍️✍️✍️የፌዴሬሽን ምክር ቤት ውሳኔ
👉👉ሕጋዊ መገኛ መንገዶች፦ የገጠር መሬት ይዞታ የሚገኘው ከመንግስት፣ በውርስ ወይም በስጦታ ብቻ እንጂ በይርጋ (ለረጅም ጊዜ በመያዝ) ሊገኝ የሚችልበት አራተኛ መንገድ የለም።
👉👉የሰበር ሰሚ ችሎቱ የሰጠው ትርጉም ግን በአዋጁ ያልተፈቀደውን እና አራተኛው የመሬት መገኛ መንገድ ተደርጎ የሚቆጠር አዲስ አሠራር የፈጠረ ነው በማለት ነቅፏል።
👉👉መሬት የመንግሥትና የሕዝብ የወል ሀብት በመሆኑ፣ መንግሥት በሕገ-ወጥ መንገድ በግለሰቦች የተያዘን መሬት ለማስለቀቅ ለፍርድ ቤት የሚያቀርበው ክስ በይርጋ ጊዜ ሊገደብ አይገባም።
👉👉ሕገ መንግሥታዊ ዋስትና፡ ምክር ቤቱ በኢ.ፌ.ዲ.ሪ ሕገ መንግሥት አንቀጽ 40 ንዑስ አንቀጽ 4 ሥር አርሶ አደሮች መሬት በነፃ የማግኘትና ከመሬታቸው ያለመነቀል መብት እንዳላቸው በግልጽ አስቀምጧል።
👉የመብቱ መጣስ፡ የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት የይርጋ ደንብን በመጠቀም የአመልካቹን ክስ ውድቅ ማድረጉ፣ አመልካቹ በሕጋዊ መንገድ ከያዙት መሬት እንዲፈናቀሉ የሚያደርግ በመሆኑ ይህ ውሳኔ ከመሬት ያለመነቀል መብትን የሚጥስ ነው ተብሏል።
👉የይዞታ መብት ጥበቃ፡ አንድ አርሶ አደር መሬቱን በሕጋዊ መንገድ ማግኘቱ ከተረጋገጠ፣ በሌላ ወገን "ለረጅም ጊዜ ይዤዋለሁ" የሚል የይርጋ መቃወሚያ ቢቀርብም፣ ይህ መቃወሚያ አርሶ አደሩን ከመሬቱ ለማፈናቀል ሕጋዊ መሠረት ሊሆን አይችልም።
👉የመንግሥት ድርሻ፡ የመሬት ባለቤትነት የመንግሥትና የሕዝብ በመሆኑ፣ ዜጎች ከመሬታቸው እንዳይፈናቀሉ የመጠበቅና በሕገ-ወጥ መንገድ የተያዘን መሬት የማስመለስ ግዴታ በመንግሥት ላይ እንደሚወድቅ ተገልጿል።
👉መሬት የመንግስትና የሕዝብ ነው፡ በሕገ-መንግሥቱ መሠረት መሬት የማይሸጥና የማይለወጥ በመሆኑ፣ አንድ ግለሰብ መሬትን በሕገ-ወጥ መንገድ ይዞ ስለቆየ ብቻ በይርጋ የባለቤትነት/የይዞታ መብት ሊያገኝ አይችልም።

27/06/2026

የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 358 መሠረት የሚቀርብ የፍርድ መቃወሚያ አቤቱታ ዓላማ በቅን ልቦና ሆነው ሳይሰሙ መብታቸው የተነካ ወገኖችን ለመጠበቅ በመሆኑ፣ አንድ ወገን ክርክር መኖሩን አስቀድሞ እያወቀ ጣልቃ ገብቶ ሳይከራከር የፍርዱን ውጤት ጠብቆ የሚያቀርበው መቃወሚያ ተቀባይነት የለውም
የሰበር ሰሚ ችሎት መዝገብ ቁጥር=210964
✅✅✅✅✅✅✅✅✅✅✅✅✅
👉የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 358 በክርክሩ ውስጥ ተካፋይ መሆን የሚገባው ወይም በክርክሩ ውስጥ ተካፋይ ለመሆን የሚችል እና እንዲሁም ተካፋይ ባልሆነበት ክርክር የተሰጠው ፍርድ መብቱ የሚነካበት ማናቸውም ሰው ተካፋይ ባልሆነበት ክርክር የተሰጠው ፍርድ ከመፈጸሙ በፊት መቃወሚያ ማቅረብ እንደሚችል ይደነግጋል፡፡ የፌዴራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በሰ.መ.ቁ 56795፤118947 እናበሌሎችም መዛግብት በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 358 መሠረት የተዘረጋው ሥርዓት አስቀድሞ በተሰጠው ውሣኔ መብቱ የሚነካበት ወገን ባለበት ውሣኔ እንዳልተሰጠበት ተቆጥሮ እንደገና ክርክር የሚጀምርበት ሥርዓት መሆኑን፤መሰረታዊ አላማምውም ቅን ልቦና ያላቸው ወገኖች በመሰረታዊ ሕግ የተጠበቀላቸውን የመከራከር መብት ባለመከራከር ዋጋ እንዳያጣ ማድረግ መሆኑን፤ ድንጋጌው በክርክሩ ውስጥ ለመግባት የሚችልና ተካፋይ ባልሆነበት ክርክር የተሰጠው ፍርድ መብቱን የሚነካበት ማናቸውም ወገን አቤቱታውን ለማቅረብ መብት እንዳለውበመለኪያነትያስቀመጠውን መሆኑን እና ይዘቱም የተቃውሞ አቤቱታውን ለማቅረብ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 39፣40 እና 41 አግባብ የክርክሩ ተካፍይ ሊሆን ይገባው የነበረውንና በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 33 አግባብ ደግሞ በጉዳዩ መብትና ጥቅም ያለው ወገን መሆን እንደሚገባ የሚያስገነዝብ መሆኑን፤ በድንጋጌው የተቀመጠው የሕጉ ሀሳብ በተቃውሞ አቤቱታ አቀራረብ ሥርዓት መብቱ ሊከበርለት የሚገባው ወገን ክርክር ባስነሳው ንብረት ላይ ያለው የመሟገት መብት የተጠበቀ ነው ለማለት እንጂ በማንኛውም ጉዳይ ቢሆን በአንድ ጉዳይ ላይ ክርክር መጀመሩን ያወቀ ወገን የክርክሩን ውጤት ጠብቆ መብቱን የሚነካበት ሆኖ ባገኘው ጊዜ ከውሣኔ በኋላ የመሟገት መብት እንዲኖረው ማድረግ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 358 ድንጋጌ አላማ ውጤት አልባ የሚያደርግ መሆኑን በመግለጽ አስገዳጅ የሆነ የሕግ ትርጉም ሰጥቶበታል፡፡ በተያዘው ጉዳይ በተጠሪዎች መካከል በአከራካሪው ቤት ሊይ ክርክር ሲደረግ አመልካች አስቀድመው ያውቁ እንደነበር ፍሬነገርን የማጣራት እና ማስረጃን የመመዘን ስልጣን ባላቸው የስር ፍርድ ቤቶች ተረጋግጧል፡፡ ስለሆነም አመልካች በጉዳዩ ላይ የሚደረገው ክርክር መብታቸውን የሚነካ ከሆነ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 41 መሠረት ጣልቃ በመግባት መብታቸውን ማስከበር ሲችል የክርክሩን ውጤት ጠብቀው በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 358 መሠረት ያቀረቡት አቤቱታ ተቀባይነት የለውም።
👉 የሰ.መ.ቁ. 210964 መጋቢት 28 ቀን 2014 ዓ.ም

26/06/2026

TikTok | Make Your Day

24/06/2026

የባሕል ፍርድ ቤቶች የዳኝነት ስልጣን

የባህል ፍርድ ቤቶችን ለማቋቋም እና እውቅና ለመስጠት በወጣው አዋጅ ቁጥር 298/2017 መሰረት እውቅና ተሰጧቸው ወደ ስራ እንዲገቡ የሚደረጉ የባሕል ፍርድ ቤቶች በሚከተሉት ጉዳዮች ላይ የዳኝነት ሥልጣን ይኖራቸዋል።

የሥረ ነገር ሥልጣን

የባሕል ፍርድ ቤቶች ክርክሮችን ማየት የሚችሉት ተከራካሪ ወገኖች ጉዳያቸው በባሕላዊ ፍርድ ቤት እንዲታይ ፍቃድ ከሰጡ በኃላ ሲሆን በሚከተሉት ጉዳዮች ላይ የዳኝነት የሥረ ነገር ሥልጣን አላቸው👇

👉 የፍትሐብሔር ጉዳዮች (በገንዘብ መጠን፣ በንብረቱ እና በጉዳዩ አይነት ገደብ ሳይደረግበት)፤

👉 በግል አቤቱታ አቅራቢነት የሚታዩ የወንጀል ጉዳዮችን (አነስተኛ የወንጀል አይነቶች) እና የደንብ መተላለፍ ድርጊቶች፤

👉 በሌሎች በዐቃቢ ሕግ ክስ አቅራቢነት በሚታዩ የወንጀል ጉዳዮች ላይ የወንጀል ጉዳዩን የማየት ሥልጣን ባይኖራቸውም👇
👉 በክርክሩ ውስጥ ያሉ ወገኖችን ማስታረቅ
👉 ካሳ መወሰን እና ማስፈጸም
👉 ወጪ እና ኪሳራ የማስከፈል ሥልጣን ተሰጥቷቸዋል፡፡

👉 ከዚህ ህግ ውጪ በሌሎች ህጎች በግልጽ ተለይቶ የመወሰን ስልጣን በተሰጣቸው ጉዳዮች ላይ የዳኝነት ሥልጣን አላቸው፡፡

የግዛት ወይም አካባቢያዊ ሥልጣን

ከላይ የተመለከተው የባሕል ፍርድ ቤቶች የስረ ነገር ሥልጣን እንደተጠበቀ ሆኖ፣ የባሕል ፍርድ ቤቶች የቀረበላቸውን ጉዳይ ለማየት ከስር ከተመለከቱት መስፈርቶች መካከል ቢያንስ አንዱ የተሟላ መሆን ይጠበቅበታል 👇

👉 ከተከራካሪ ወገኖች መካከል ቢያንስ አንዱ የባሕል ፍርድ ቤቱ የሥልጣን ወሰን ስር በሚገኝ ቀበሌ ውስጥ ነዋሪ ወይም ተወላጅ ከሆነ፤

👉 ለክርክር ምክንያት የሆነው ቋሚ ንብረት የባሕል ፍርድ ቤቱ የሥልጣን ወሰን ስር በሚገኝ ቀበሌ ውስጥ የሚገኝ ከሆነ፤

👉 ለክርክር መነሻ የሆነው ጉዳይ የተጀመረው ወይም ፍፃሜ ያገኘው የባሕል ፍርድ ቤቱ የሥልጣን ወሰን ውስጥ ከሆነ ነው፡፡

👉 ከላይ አካባቢያዊ የዳኝነት ሥልጣን በሚመለከት ከተቀመጡ ማሳያዎች በተለየ መልኩ የሚያስቀምጥ የባህል ህግ በሚኖርበት ጊዜ የባሕል ሕጉ ተፈፃሚነት የሚኖረው ይሆናል፡፡

የመንግስት ተቋማት ሠራተኞቻቸውን የመቆጣጠር እና የመከታተል ግዴታቸውን ሳይፈፅሙ ቀርተው በተገልጋዮች ላይ ጉዳት በደረሰ ጊዜ ጉዳዩ አይመለከተንም ማለት የሚያቀርቡት ክርክር ተቀባይነት የሌለው...
16/06/2026

የመንግስት ተቋማት ሠራተኞቻቸውን የመቆጣጠር እና የመከታተል ግዴታቸውን ሳይፈፅሙ ቀርተው በተገልጋዮች ላይ ጉዳት በደረሰ ጊዜ ጉዳዩ አይመለከተንም ማለት የሚያቀርቡት ክርክር ተቀባይነት የሌለው ስለመሆኑ
ሰ.መ.ቁ 137589 ቅፅ 22

14/06/2026

‎በሌሉበት የተሰጠ ፍርድን ስለማንሳት ✍️
‎( Setting Aside an Ex _ Parte Judgment )

‎⚫️ አንድ ሰው መጥሪያ ሳይደርሰዉ ወይም በበቂ ምክንያት ሳይቀርብ ቀርቶ ዉሳኔ ከተላለፈበት ፣ ፍርዱ ተነስቶ ክርክሩ ከዜሮ እንዲጀምር የመጠየቅ መብቱ " የመሰማት መብት " ( Right to be Heard ) አካል ነው ።

‎⚫️ ፍርዱ እንዲነሳ የሚጠየቅባቸው ምክንያቶች ✍️

‎ፍርድ ቤቱ ፍርዱን አንስቶ ክርክሩን እንደገና እንዲጀምር ለማድረግ ተከሳሹ ከሚከተሉት ምክንያቶች አንዱን ማሳየት አለበት ፦

‎👉 መጥሪያው በአግባቡ አለመድረሱን ፦ ለተከሳሹ መጥሪያ በሕግ በተደነገገው መሠረት ( በአካል ፣ በቤተሰብ ወይም በጋዜጣ ) ሳይደርሰዉ ቀርቶ ከሆነ ።

‎👉 በበቂ ምክንያት መቅረት ፦ መጥሪያው ደርሶት ቢሆንም ፣ በፍርድ ቤት ቀን ለመቅረብ የሚያግድ " በቂ ምከንያት " ካጋጠመዉ ለምሳሌ ከባድ ሕመም ፣ ድንገተኛ አደጋ ወይም ከቁጥጥር ዉጪ የሆነ ምክንያት ።

‎⚫️ ሂደቱና የጊዜ ገደቡ ✍️

‎👉 ማመልከቻ ማቅረብ ፦ ተከሳሹ ፍርዱን የሠጠው ፍርድ ቤት ድረስ በመሄድ " በሌለሁበት የተሰጠው ፍርድ ተነስቶልኝ መከላከያዬን ላቅርብ " የሚል ማመልከቻ ማቅረብ አለበት ።

‎👉 የጊዜ ገደብ ፦ የፍትሐብሔር ጉዳይ ከሆነ ፣ ፍርድ መኖሩን ካወቀበት ቀን ጀምሮ በ 30 ቀናት ዉስጥ ማመልከቻቸውን ማቅረብ ይኖርበታል ።

‎⚫️ በአጋጣሚ በቁጥጥር ሥር ከዋለ ( በወንጀል ጉዳይ )

‎ግለሰቡ በሌለበት ተፈርዶበት በኋላ በፓሊስ የተያዘ ከሆነ ፣ ግለሰቡ ለፍርድ ቤቱ በመቅረብ " መጥሪያ አልደረሰኝም ወይም የቀረሁት በበቂ ምክንያት ነው " የሚል ማመልከቻ ያቀርባል ።

‎⚫️ ፍርድ ቤቱ ምክንያቱን ካመነበት ፣ ቀደም ሲል የሰጠውን ዉሳኔ በማንሳት ክርክሩ ገና ከጅምሩ ( ከክስ ንባብ ጀምሮ ) በድጋሚ እንዲሰማ ያዛል ።

‎⚫️ በዚህ ጊዜ መከላከያውን የማቅረብ ፣ ምስክሮችን የማሰማት እና ጥያቄ የመጠየቅ ዕድል ያገኛል ።

‎⚫️ ዓላማው ፦ የፍትህ መጓደልን መከላከል ✍️

‎ሕጉ ይህን ዕድል የሰጠው ፣ አንድ ሰው ሳይሰማና ሳይከላከል በመፈረዱ የሚደርሰውን የፍትህ መጓደል ለማስቀረት ነው።

Address

Addis Ababa

Telephone

+251992731165

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Free-Legal/ነፃ-ሕግ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Free-Legal/ነፃ-ሕግ:

Shortcuts

Share

Category