Yeka werda 09 Communication/የካ ወረዳ 09 ኮሙኒኬሽን

Yeka werda 09 Communication/የካ ወረዳ 09 ኮሙኒኬሽን ይህ የየካክ/ከተማ ወረዳ 09 ኮሙኒኬሽን የፌስቡክ ገጽ ነው።

ፔጃችንን ፎሎው በማድረግ አዳዲስና ትኩስ መረጃዎችን ያግኙ!!

ይህን ያውቁ ኖሯል?የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቅኝት
23/08/2026

ይህን ያውቁ ኖሯል?
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቅኝት

ዛሬ የኒው ሊፍ ሜዲካል ኮምፕሌክስን መርቀን ሥራ አስጀምረናል።  እንኳን ደስ አላችሁ! እንኳን ደስ አለን!ከተማችን አዲስ አበባ የጤና ቱሪዝም  ማዕከል እናደርጋታለን ስንል በመንግስት ብቻ የ...
23/08/2026

ዛሬ የኒው ሊፍ ሜዲካል ኮምፕሌክስን መርቀን ሥራ አስጀምረናል።

እንኳን ደስ አላችሁ! እንኳን ደስ አለን!
ከተማችን አዲስ አበባ የጤና ቱሪዝም ማዕከል እናደርጋታለን ስንል በመንግስት ብቻ የምናሳካው ሳይሆን በግሉ ዘርፍ የሚገነቡትንም ታሳቢ በማድረግ ስለሆነ፣ ዛሬ ያስመረቅነው የኒው ሊፍ ሜዲካል ሆስፒታልም የዚህ አንዱ ማሳያ ነው ።

ኒው ሊፍ ሜዲካል ኮምፕሌክስ በሃገራችን ከላፍቶ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ቀጥሎ ሁለተኛው PET-CT SCAN CAT LAB እና ሌሎች ዘመኑን የዋጁ ቴክኖሎጂዎች የተሟሉለት ትልቅ የጤና ማዕከል ነው። በጤናው ዘርፍ የምናደርገው ኢንቨስትመንት ክፍያው ከሁሉ የላቀ ስለሆነ እንደዚህ አይነት በጤናው ዘርፍ ለሚሰሩ የጤና ተቋማት እና ሆስፒታሎች ድጋፋችንን አጠናክረን እንቀጥላለን።

የኒው ሊፍ ሜዲካል ኮምፕሌክስ መስራችና ስራአስኪያጅ ዶ/ር ኢማን አብዱልራህማን እና ባለቤታቸው አቡበከር መሃመድ ሳላህን በራሴና በከተማው አስተዳደር ስም በጣም እናመሰግናለን።

ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ሕዝቦቿን ይባርክ!
ከንቲባ አዳነች አቤቤ

ኢትዮጵያ አሸንፋለች!
22/08/2026

ኢትዮጵያ አሸንፋለች!

22/08/2026
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ 6ኛ ዓመት 1ኛ መደበኛ ስብሰባ በዛሬው ዕለት አካሄደ። ካቢኔው በዛሬው ስብሰባው በቀረቡ  አጀንዳዎች ላይ ተወያይቶ  ውሳኔዎችን  አስተላልፏል፡፡በዚህ መ...
21/08/2026

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ 6ኛ ዓመት 1ኛ መደበኛ ስብሰባ በዛሬው ዕለት አካሄደ።

ካቢኔው በዛሬው ስብሰባው በቀረቡ አጀንዳዎች ላይ ተወያይቶ ውሳኔዎችን አስተላልፏል፡፡

በዚህ መሠረት፦

1- የማህበረሰብ ጤና አቀፍ መድህን ተጠቃሚዎች መዋጮን ለማሻሻል የቀረበ የውሳኔ ሀሳብ ተወያይቶ ተግባራዊ እንዲሆን አፅድቋል።

2- ሀገራዊ ፋይዳ ላላቸው ፕሮጀክቶች (ለሆቴል፣ ለሞልና አፓርትመንት፣ ኢንዱስትሪ፣ ለበጎ አድራጎት፣ መንግስታዊ ተቋማት እና የህክምና ተቋማት) የማስፋፍያና አዳዲስ የመሬት ጥያቄዎችን ለመመለስ የቀረበ የውሳኔ ሀሳብ ላይ ተወያይቶ ተፈፃሚ እንዲሆን አፅድቋል።

3- በከፊል በኮሪደር ለምተው፣ በከፊል ሳይለሙ የቆዩ አካባቦዎችን በተሟላ ሁኔታ ለማልማት የቀረበ የውሳኔ ሀሳብ ላይ ተወያይቶ ተግባራዊ እንዲሆን አፅድቋል።

አዲስ አበባ፥ ከአፍሪካ ከተሞች ምርጥ የመንገድ መሰረተ-ልማት ባለቤት መሆኗን “ግሎባል ስታስቲክስ ዋየር” ገለፀ! ግሎባል ስታትስቲክስ በኤክስ ገፁ ይፋ ባደረገው መረጃ መሠረት፥ በአፍሪካ የተ...
20/08/2026

አዲስ አበባ፥ ከአፍሪካ ከተሞች ምርጥ የመንገድ መሰረተ-ልማት ባለቤት መሆኗን “ግሎባል ስታስቲክስ ዋየር” ገለፀ!

ግሎባል ስታትስቲክስ በኤክስ ገፁ ይፋ ባደረገው መረጃ መሠረት፥ በአፍሪካ የተሻለ እና ጥራት ያለው የከተማ መንገድ መሠረተ ልማት ያላቸው ከተሞች መዲናችን አዲስ አበባ በሁለተኛ ደረጃ አስቀምጧል።

መዲናችን አዲስ አበባ በአጭር ጊዜ ውስጥ ጥራት ያለው የመንገድ መሠረተ-ልማት እና ሰፊ የከተማ ትራምስፎርሜሽን ውጤት፣ ከተማዋ ዓለማቀፍ የስህበት ማዕከል እንድትሆን አድርጓታል።

በየካ ክፍለ ከተማ አስተዳደር “6400 A” የዲጂታል በጎነት ፕሮጀክት በይፋ ተጀመረነሐሴ 14/2018 ዓ•ም የካ ክ/ከተማ ወረዳ 11 ኮሙኒኬሽንበየካ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የበጎ ፈቃድ አገ...
20/08/2026

በየካ ክፍለ ከተማ አስተዳደር “6400 A” የዲጂታል በጎነት ፕሮጀክት በይፋ ተጀመረ

ነሐሴ 14/2018 ዓ•ም የካ ክ/ከተማ ወረዳ 11 ኮሙኒኬሽን

በየካ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ተሳትፎንና ተጠቃሚነትን ለማሳደግ “6400 A” የዲጂታል በጎነት ፕሮጀክት የማስተዋወቂያና በክፍለ ከተማ ደረጃ የማስጀመሪያ መርሃ ግብር ተካሂዷል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር በመተባበር ያስጀመረው ይህ የዲጂታል በጎነት ፕላትፎርም፣ የዜጎችን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች ከተረጅነት በዘላቂነት ለማቃለል የሁሉንም የማህበረሰብ ክፍል በቀላሉ በበጎ ፈቃድ ተግባራት ላይ ለማሳተፍ ያለመ ነው።

በማስጀመሪያ መርሃ ግብሩ ላይ የተገኙት የየካ ክፍለ ከተማ የብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ መገርሳ ገላና በክፍለ ከተማው በርካታ ሰው ተኮር የሆኑ የበጎ ፈቃድ ተግባራት መከናወናቸውን ገልፀው ሁሉም ሰው የበኩሉን አስተዋፅኦ ሲያደርግ የሰው ሰራሽና ተፈጥሮዊ አደጋን በእራሳችን አቅም ለመፍታት በጋራ መስራ ይገባል ሲሉ አሳስበዋል።

የየካ ክፍለ ከተማ የህብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ሀላፊ ወ/ሮ መሰለች አቡዬ በበኩላቸው የበጎ ፈቃድ ተግባር ለበርካታ አቅመ ደካማ ወገኖች፣ ለሀገር ባለውለታዎችና ለዝቅተኛ ገቢ ላላቸው የህብረተሰብ ክፍሎች ድጋፍ ማድረስ መቻሉን ያስረዱ ሲሆን የ“6400 A” ዲጂታል በጎነት ፕሮጀክትም በተለይ አቅመ ደካማና በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙ ዜጎችን ለመድረስ የሚያግዝ በመሆኑ የክፍለ ከተማው ነዋሪዎች በፕላትፎርሙ ላይ በመሳተፍ የበጎነት አሻራቸውን እንዲያሳርፉ ጥሪ አቅርበዋል።

የ“6400 A” ፕላትፎርም የበጎነት ባህልን በበለጠ ለማስፋፋት፣ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮችን ለመቅረፍ እንዲሁም ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው ዜጎች ዘላቂ ጠቀሜታ ለመፍጠር አስተዋጽኦው ከፍተኛ መሆኑን ገልጸዋል።

ህብረተሰቡ ወደ 6400 “A” የጽሑፍ መልዕክት (SMS) በመላክና በቀን 1 ብር በመለገስ የበጎ ፈቃድ አገልግሎቱን በመደገፍ በጎነትን ማስፋፋትና ፕሮጀክቱ የተቀመጠለትን ዓላማ እንዲያሳካ የበኩሉን አስተዋጽኦ እንዲያበረክት ጥሪ ቀርቧል።

በየካ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የ8ኛ ዙር የማካካሻ ኮርስ እጩ ምልምል የሰላም ሠራዊት አባላት ተመረቁ14/12/2018 ዓ.ም | የካ ኮሙኒኬሽንየየካ ክፍለ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ጽ/ቤ...
20/08/2026

በየካ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የ8ኛ ዙር የማካካሻ ኮርስ እጩ ምልምል የሰላም ሠራዊት አባላት ተመረቁ

14/12/2018 ዓ.ም | የካ ኮሙኒኬሽን

የየካ ክፍለ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ጽ/ቤት በ8ኛ ዙር የማካካሻ ኮርስ ለ1,000 እጩ ምልምል የሰላም ሠራዊት አባላት የንድፈ ሐሳብና የተግባር ሥልጠና በመስጠት አስመርቋል።

በምርቃት ሥነ-ሥርዓቱ ላይ የተገኙት የየካ ክፍለ ከተማ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ፍፁም ኃይሌ እንደገለጹት የሰላም ሠራዊት አባላት ከጸጥታ መዋቅሩ ጋር በመቀናጀት የከተማችንን ሰላምና ጸጥታ በማስጠበቅ፣ ሀገራዊ፣ ከተማዊና ሃይማኖታዊ የአደባባይ ክንውኖች በሰላም እንዲከናወኑ ከፍተኛ አስተዋጽኦ አድርገዋል።

አዲስ የሰላም ሠራዊት ምልምሎችም በሥልጠናው ያገኙትን እውቀትና ክህሎት በተግባር በመተርጎም ለአካባቢያቸውና ለክፍለ ከተማው ሰላምና ጸጥታ መጠበቅ የድርሻቸውን እንዲወጡ ጥሪ አቅርበዋል።

ዋና ሥራ አስፈጻሚው አክለውም፣ የሰላም ሠራዊቱ የሰላም አምባሳደርነቱን በተግባር እያረጋገጠ የውስጥና የውጭ ግጭቶችን በመከላከል ረገድ የሚያበረክተው አስተዋጽኦ ከፍተኛ መሆኑን በመጠቆም ዛሬ የተመረቁት አዲስ ምልምል የሰላም ሠራዊት አባላት የአካባቢያቸውንና የክፍለ ከተማውን ሰላምና ጸጥታ ከሚያውኩ ኃይሎች ለመጠበቅ የተሰጣቸውን ኃላፊነት በብቃት መወጣት እንዳለባቸው አስገንዝበዋል።

የየካ ክፍለ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሀብታሙ ደረጀ በበኩላቸው የሰላም ሠራዊት አባላት በሥልጠናው ያገኙትን የንድፈ ሐሳብና የተግባር እውቀት ወደ ተጨባጭ ውጤት በመቀየር የአካባቢያቸውንና የከተማዋን ሰላም በተጠናከረ መልኩ ማስቀጠል እንዳለባቸው ገልጸዋል።

የሥልጠናው ተሳታፊ አዲስ ምልምል የሰላም ሠራዊት አባላትም ከጸጥታ አካላት ጋር በቅንጅት በመሥራት የአካባቢያቸውን ሰላም ለማስፈን፣ ወንጀልን ለመከላከልና የሰላም አምባሳደርነታቸውን በተግባር ለማረጋገጥ ቁርጠኛ መሆናቸውን ገልጸዋል።

በምርቃት ሥነ-ሥርዓቱ የሥልጠና ማጠናቀቂያ ለአሰልጣኞችና ለምልምል የሰላም ሠራዊት አባላት የእውቅና ምስክር ወረቀት ተሰጥቷል።

ይምጡና በአዲስ መሶብ የአንድ ማዕከል ድጂታል የመንግስት አገልግሎት የካ ቅርንጫፍ ይገልገሉ!በአዲስ መሶብ የአንድ ማዕከል ድጂታል የመንግስት አገልግሎት የካ ቅርንጫፍ የሚሰጡ አገልግሎቶች #1...
19/08/2026

ይምጡና በአዲስ መሶብ የአንድ ማዕከል ድጂታል የመንግስት አገልግሎት የካ ቅርንጫፍ ይገልገሉ!

በአዲስ መሶብ የአንድ ማዕከል ድጂታል የመንግስት አገልግሎት የካ ቅርንጫፍ የሚሰጡ አገልግሎቶች

#1 መሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ

የባለቤትነት ስመ ንብረት ዝውውር አገልግሎት
የሊዝ ይዞታ መብት ማስተላለፍ
ዋስትና ዕዳና ዕገዳ ምዝገባ አገልግሎት
የዋስት ዕዳ እገዳ የመሰረዝ አገልግሎት
የሊዝ ውል አገልግሎት

#2. ቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ

1. የአከራይ ተከራይ የምዝገባ አገልግሎት
2. የአከራይ ተከራይ ውል ማደስ ወይም ማቋረጥ
3. በኪራይ ቤት አዲስ ውል የማዋዋል አገልግሎት
4. የቤት ቅይይር ጥያቄን ምሊሽ የመስጠት
5. . ተነሺዎች ምትክ ቤት የመመደብ
6. አምስት አመት የሞሊቸዉ የጋራ መኖሪያ ቤቶች ማስረጃ
7. የዉሃና የመብራት ማስገባት የፍቃድ
8. የመንግስት ቤት የኪራይ ውሌ ማደስ ወይም ማቋረጥ
9. የስም ዝውውር አገልግሎት
10 የቤት እድሳትና ጥገና ጥያቄ
11. የመንግስት ቤት አገልግሎት ለውጥ

#3. የመሬት ይዞታና ምዝገባ መረጃ ኤጀንሲ

1. የቋሚ ንብረት እዳ መያዣ ዋስትና ምዝገባ
2. የሪል ስቴት የጋራ ህንጻ ንብረት እዳ ስረዛ
3. የቁራሽ መሬት ይዞታ የፍርድ ቤት ዕግድ ምዝገባ
4. የቋሚ ንብረት እዳ ምዝገባ ዕድሳት
5. የሪል እስቴት የተናጠል ሰርተፍኬት ካርታ
6. የሪል እስቴት የስም ዝውውር

#4. ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን

1. የጋራ መኖሪያ ቤቶችን ተጠቃሚዎች የማስተላለፍ ስራ
2. የጋራ መኖሪያና ቤቶችን በሸያጭ በጨረታ ማስተላለፍ

#5. የሲቪል ምዝገባና ነዋሪዎች አገልግሎት ኤጀንሲ

1. የልደት ምዝገባና ማስረጃ
2. የጉዲፈቻ ምዝገባና ማስረጃ
3. የፍቺ ምዝገባና ማስረጃ
4. የሞት ምዝገባና ማስረጃ
5. የጋብቻ ምዝገባ ማስረጃ እድሳት
6. የነዋሪነት መታወቂያ አገልግሎት
7. የዲጂታል መታወቂያ

#6. የሥራና ክህሎት ቢሮ

1. የመረጃ ምክርና ግንዛቤ አገልግሎት
2. ስራ ፈላጊዎችን እና ኢንተርፕራይዞችን መመዝገብ
3. በኢንተርፕራይዝ ማደራጀት
4. የአገር ውስጥ ሥራና ሠራተኛ ማገናኘት
5. የፋይናንስ ድጋፍ ማመቻቸት

#7. ገቢዎች ቢሮ

1. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር መስጠት
2. የኢ ፋይሊንግ እና ኢ ፔይመንት አገልግሎ

#8. ፕላንና ልማት ቢሮ

1. የፕላን ማብራሪያ አስተያየት
2. የውስጥ ለውስጥ መንገድ ጥናት
3. የፕላን መረጃዎችን ማሰራጨት

#9. ብሔራዊ መታወቂያ

1. የፋይዳ መታወቂያ ምዝገባ
2. የፋይዳ መታወቂያ ማስተካከያ

#10. የሰነዶች ማረጋገጫ አገልግሎት

1. የሚንቀሳቀስ እና የማይንቀሳቀስ ንብረቶች ማስተላለፍ ዉል
2. ብድር ውል
3. የሽርክና ማህበር ቃለ-ጉባኤ
4. የሽርክና ማህበር ቃለ-ጉባኤ ማረጋገጥ
5. የትርጉም ሰነዶች ማረጋገጥ
6. የውጭ ጉዳይ ሰነዶች
7. ውል ማፍረሻ
8. ውል ማሻሻያ
9. ውክልና መሻሪያ
10. ቃለ መሀላ
11. ኑዛዜ
12. ድርሻ መልቀቅ
13. ዲክላሬሽን(ማረጋገጫ)
14. ልዩ ልዩ ዉሎች
15. የኪራይ ውል
16. ማህበራት መመስረቻ
17. ውክልና

#11. የኢትዮጵያ ፖስታ

1. የፋይዳ መታወቂያ ቀጠሮ ማስያዝ
2. የፋይዳ መታወቂያ ህትመት
3. የፋይዳ መታወቂያ ምዝገባ
4. የፋይዳ መታወቂያ እደላ
5.የፋይዳ መታወቂያ ማስተካከያ
6. የመንገድ ፈንድ አገልግሎት
7. የጽፈት አገልግሎት

#12. ኢትዮ ቴሌኮም

1. በቴሌብር ለመክፈል
2. ቴሌብር ለመክፈት
3. ሲም ለማውጣት

#13. የትራፊክ ማኔጅመንት ባለስልጣን

1.

በየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 09 አስተዳደር የተቀናጀ የሞዴል ብሎክ ልማት ሥራ አወንታዊ ለውጥ እያመጣ ይገኛል።በየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 09 አስተዳደር የአካባቢን ውበት ለመጠበቅ፣ ለነዋሪዎች ም...
18/08/2026

በየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 09 አስተዳደር የተቀናጀ የሞዴል ብሎክ ልማት ሥራ አወንታዊ ለውጥ እያመጣ ይገኛል።

በየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 09 አስተዳደር የአካባቢን ውበት ለመጠበቅ፣ ለነዋሪዎች ምቹ የመኖሪያና የሥራ አካባቢን ለመፍጠር እንዲሁም የተቀናጀ የአገልግሎት አሰጣጥን ለማጠናከር ያለመው የተቀናጀ የሞዴል ብሎክ ልማት ሥራ በተሳካ ሁኔታ እየተከናወነ ይገኛል።

የሞዴል ብሎክ ልማት ሥራው በዋናነት የአካባቢ ጽዳትና አረንጓዴ ልማትን፣ የከተማ ግብርናን፣ የጸጥታና ደህንነት ሥራዎችን እንዲሁም ህገ-ወጥነትን የመከላከል ተግባራትን በቅንጅት ያካተተ ነው። የብሎኩ ነዋሪዎችና ህብረተሰብ ክፍሎች በልማት ሥራው ላይ በንቃትና በባለቤትነት ስሜት በመሳተፍ ላይ ሲሆኑ፣ ይህም የአካባቢውን ገጽታ በመቀየር ረገድ ከፍተኛ አስተዋጽኦ አበርክቷል።

የካ ወረዳ 09 ኮሙኒኬሽን፣ነሀሴ 12/2018

Address

Addis Ababa
Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Yeka werda 09 Communication/የካ ወረዳ 09 ኮሙኒኬሽን posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share