08/05/2023
ካመጣቸው ለውጦች ይልቅ ያልተሰሩ ቀሪ ስራዎችን ለመስራት የሚታትር ህዝባዊ ፓርቲ ብልፅግና !!
ፓርቲያችን ብልፅግና እየተገበረ በሚገኘው በመደመር እሳቤ የተቃኘ የብልፅግና ጉዞ የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች በሀገሪቱ በሚካሄደው ልማታዊ እንቅስቃሴዎች ንቁ ተሳታፊና ተጠቃሚ እንዲሆኑ አስችሏቸዋል፡፡
በአፈፃፀም ሂደት የሚያጋጥሙ መሰረታዊ ተግዳሮቶችን መፍታት እንዲቻልም ለመብቱና ለልማቱ ተጠቃሚነት የሚታገል ሞጋች ህብረተሰብ በመፍጠር ሂደት ላይ ቀጣይነት ያለው ስራ እየሰራ የሚገኝ አሳታፊ ፓርቲ ነው፡፡
በመላው ሀገራችን የህዝቡን ሁለንተናዊ የኑሮ ሁኔታ ለማሻሻል፣ ሁሉም የሀገሪቱ አካባቢዎች ፍትሀዊ የልማት ተጠቃሚ እንዲሆኑ ለማስቻል እንዲሁም በፖለቲካው መስክ ንቁ ተሳታፊ እና በኢኮኖሚውም ቢሆን የዳበረ ሀገር ለመፍጠር ተግቶ እየሰራ የሚገኝ ተራማጅና ፓርቲ ነው ብልፅግና፡፡
ፓርቲያችን ኢትዮጵያን በሀላፊነት ተረክቦ ማስተዳደር ከጀመረ ጊዜ አንስቶ ባስመዘገባቸው ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ፖለቲካዊና አካባቢያዊ ሁሉን ዓቀፍ ለውጦች የተነሳ በሀገሪቱ የታሪክ መዝገብ ውስጥ መስፈር የሚያስችል ዕውቅናን ከመላው የሀገራችን ህዝቦች፣ ከአፍሪካም ይሁን ከመላው ዓለም ማግኘት የቻለ ባለራዕይ ፓርቲ ነው፡፡
ብልፅግና በቂ ለውጥ አምጥቻለሁ በማለት ራሱን የጀግንነት ካባ የማያለብስ፤ ካመጣቸው ለውጦች ይልቅ ያልተሰሩ የቤት ስራዎችን ለመፈፀም ያካበተውን ህዝብን የማስተባበር ልምድ ተጠቅሞ ውጤት ለማምጣት ሌት ተቀን የሚጥር እና ለዚሁ ስራ እንቅፋት የሚሆኑ ውስጣዊ ድክመቶቹን በመፈተሽ ራሱን ማስተካከል የሚችል ከ12 ሚሊዮን በላይ አባላት ያሉት ግዙፍ ፓርቲ ነው፡፡
መልካም ሳምንት ይሁንልዎ !!