05/09/2022
ህፃናቱን በአሰቃቂ ሁኔታ ህይወታቸው እንዲያልፍ ያደረገችው የቤት ሠራተኛ ፍርድ ቤት ቀረበች
(እለታዊ የኢትዩትዩብ መረጃዎች)
ፍርድ ቤቱ የህጻን ግዮናዊት መላኩ እና ህጻን ክርስቲና መላኩን በአሰቃቂ ሁኔታ ህይወታቸው እንዲያልፍ አድርጋለች የተባለችው ተጠርጣሪ ላይ ፖሊስ ተጨማሪ ምርመራ እንዲያደርግ የ14 ቀን ጊዜ ሰጠ።
ተጨማሪ ምርመራ እንዲደረግ የ14 ቀን ጊዜ የፈቀደው የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ 2ኛ ጊዜ ቀጠሮ ችሎት ነው።
ተጠርጣሪ ህይወት መኮንን ሀይሉ በነሃሴ 26 ቀን 2014 ዓ/ም ከጠኋቱ 3:30 ላይ በለሚኩራ ክ/ከ አራብሳ ኮንዶሚኒዬም ተቀጥራ በምትሰራበት መኖሪያ ቤት ውስጥ ምክንያቱ ባልታወቀ ሁኔታ የህጻን ግዮናዊት መላኩ አፏን በማፈን በቢላ በማረድ ህይወቷ እንዲያልፍ ማድረጓን እና ህጻን ክርስቲና መላኩን ደግሞ አፍፏን በማፈን በማነቅ በአጠቃላይ በአሰቃቂ ሁኔታ ህይወታቸው እንዲያልፍ ማድረጎን ፖሊስ ለችሎቱ አስረድቷል።
በዚህ መልኩ ተጠርጣሪዋን በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራ እያደረገ መሆኑን የገለጸው ፖሊስ የሰው ማስረጃ ለማሰባሰብና የግድያ ወንጀል የተፈጸመበትን ትክክለኛ ምክንያት በማስረጃ ለማረጋገጥ እንዲሁም በተጠርጣሪዋ ዙሪያ ያሉ ግለሰቦች ላይ ማስረጃ ለማሰባሰብና በወንጀሉ ስፍራ የተገኘ ስለታማ ቢላን በፎረንሲክ ለማስመርመር በተጨማሪም የአስከሬን ምርመራ ውጤት ለማምጣት በወ/መ/ስ/ህ /ቁ. 59/1 መሰረት የ14 ቀን ጊዜ እንዲሰጠው ጠይቋል።
በተጠርጣሪዋ በኩል ምንም አስተያየት ያልቀረበም።
የምርመራ መነሻ መዝገብን የተመለከተው የጊዜ ቀጠሮ ችሎቱ ተጠርጣሪዋ ላይ ፖሊስ ተጨማሪ ምርመራ እንዲያደርግ የ14 ቀን ጊዜ ፈቅዷል።
ምንጭ፦ ታሪኩ አዱኛ
አዝናኝና ቁም ነገር የሚያስጨብጡ ሃሳቦችን በሰፊውA wide range of fun and engaging ideas