Medina Jibreel Law

Medina Jibreel Law Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Medina Jibreel Law, Lawyer & Law Firm, Addis Ababa, Addis Ababa.

23/02/2026
13/02/2026
With Sosi Grimay Arafayn – I just got recognized as one of their top fans! 🎉
17/10/2025

With Sosi Grimay Arafayn – I just got recognized as one of their top fans! 🎉

28/05/2025

የመንግስት እና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት ለሕዝብ አገልግሎት ዝግ የሚሆኑባቸው በሀገርአቀፍ ደረጃ ተከብረው የሚውሉ ብሔራዊ በዓላት ፡-

1. መስከረም 1 ቀን የዘመን መለወጫ (እንቁጣጣሽ) በዓል
2. የካቲት 23 ቀን የአድዋ ድል በዓል
3. ሚያዚያ 23 ቀን የዓለም የሠራተኞች (የላብአደሮች) ቀን
4. ሚያዚያ 27 ሰባት ቀን የአርበኞች (የድል) ቀን በዓል

የሚከተሉት በዓላት በሀገርአቀፍ ደረጃ ታስበው የሚውሉ ብሔራዊ በዓላት ናቸው ፡-
1. የካቲት 12 ቀን የሰማዕታት ቀን
2. ሕዳር 29 ቀን የኢትዮጵያ ህብረ-ብሄራዊነት (የብሔር ብሔረሰቦች) ቀን

በተጠቀሱት ብሔራዊ በዓላት የመንግስት እና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት ለሕዝብ አገልግሎት ክፍት ይሆናሉ፡፡

የሚከተሉት በዓላት በሀገርአቀፍ ደረጃ የሚከበሩ ሃይማኖታዊ በዓላት ናቸው ::

1. መስከረም 17 ቀን የመስቀል በዓል
2. በየአራት ዓመቱ የሚመጣው ልዩነት እንደተጠበቀ ሆኖ ታህሳስ 29 ቀን የሚውለው የገና ወይም የኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል
3. ጥር 11 ቀን የጥምቀት በዓል
4. የስቅለት በዓል
5. የትንሳኤ (ፋሲካ) በዓል
6. የኢድ-አልአድሃ (አረፋ) በዓል
7. የመውሊድ በዓል
8. የኢድ አልፈጥር በዓል

በተጠቀሱት ሃይማኖታዊ በዓላት የመንግስት እና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት ለሕዝብ አገልግሎት ዝግ ይሆናሉ። ግንቦት 20 ግን የሕዝብ በዓላትን እና የበዓላትን አከባበር ለመወሰን በወጣው አዋጅ ውስጥ አልተካተተም።

ይሄ አያድርስ እንጂ ምን ይባላል አሁን
10/04/2025

ይሄ አያድርስ እንጂ ምን ይባላል አሁን

የደስታው ተካፋይ ለመሆን በሰርጉ ላይ የተገኙ 3 ታዳሚዎችን ገድሎ 4ቱ ላይ የመግደል ሙከራ ያረገው ሙሽራ በ22 ዓመት እስር ተቀጣ!

👉🏽 ዐቃቤ ህግ በፍርድ ቤቱ ውሳኔ ቅር በመሰኘቱ ይግባኝ ጠይቋል!
******
አስገራሚ የሆነውን ዜና ያጋራው የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ፖሊስ ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነትና ኮሚንኬሽን ስለ ወንጀሉ ዝርዝር ሲያስረዳ የወንጀል ድርጊቱ የተፈፀመው በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል በካፋ ዞን ጌሻ ወረዳ ውስጥ ሲሆን ሙሽራውበሰርጉ ዕለት የደስታው ተካፋይ የሆኑትን ሶስት ሰዎች ገሎ በአራት ሰዎች ላይ የመግደል ሙከራ ወንጀል መፈፀሙንና አንድ መኖሪያ ቤት ማቃጠሉ በዐቃቤ ህግ የክስ ዝርዝር ተመላክቷል ይላል።

ሸገር ታይምስ ሚዲያ ከኮሚሽኑ መረጃ ለመመልከት እንደቻለው የዞኑ ፍትህ መምሪያ የልዩ ልዩ ወንጀሎች ዐቃቤ ህግ ብርሃኑ ወ/ሚካኤል እንደገለፁት ተከሳሽ አስራት መንገሻ መሸሻ የተባለው ግለሰብ በካፋ ዞን በጌሻ ወረዳ ጋዊቲ ቀበሌ ነሐሴ 19 ቀን 2016 ዓ.ም ከምሽቱ 2፡00 ሰዓት በተከሳሹ በሰርጉ ደስታ ላይ የታደሙትን ሶስት ሰዎችን በመግደልና አራት ሰዎች ላይ የመግደል ሙከራ ወንጀልና ንብረት በማቃጠል ወንጀል በመፈፀሙ ዐቃቤ ህግ በግለሰቡ ላይ ስምንት የወንጀል ክሶችን መመስረቱን ተናግረዋል፡፡

ዐቃቤ ህግ በክስ አንድ ላይ እንዳመላከተው ሙሽራው ከሰርጉ ታዳሚዎች መካከል የግል ተበዳይን በያዘው ጩቤ ግራ ደረቱ ላይ በመውጋት ህይወቱ እንዲያልፍ በማድረጉ በኢ.ፌ.ዲ.ሪ የወንጀል ህግ አንቀፅ 539 ንዑስ አንቀፅ 1 ሀ ላይ ያለውን ተላልፎ በመገኘቱ በፈፀመው ከባድ ሰው መግደል ወንጀል ክስ መስርቶበታል፡፡

በክስ 2 በክስ አንድ ላይ የተጠቀሰው የግል ተበዳይ የሆነው ልጇ መወጋቱን ሰምታ ሩጣ የደረሰችውን የሟች እናትን በያዘው ጦር ጎኗ ላይ በመውጋት ህይወቷ እንዲያልፍ በማድረጉ በኢ.ፌ.ዲ.ሪ የወንጀል ህግ አንቀፅ 539 ንዑስ አንቀፅ 1 ሀ ላይ ያለውን ተላልፎ በመገኘቱ በፈፀመው ከባድ ሰው መግደል ወንጀል ክስ መስርቶበታል፡፡

ዐቃቤ ህግ በክስ 3 የወንጀል ዝርዝር እንደተጠቀሰው የግል ተበዳይ መኖሪያ ቤት በእሳት ሲያቃጥል የድረሱልኝ ጩኸት ሰምቶ የመጣውን ግለሰብ በያዘው ጦር ቀኝ የእግሩ ጭኑ ላይ በመወጋቱ በድንጋጤ በመሸሹ በሁለተኛው ቀን አስክሬኑ ከጫካ ውስጥ መገኘቱን ተከትሎ ዐቃቤ ህግ በኢ.ፌ.ዲ.ሪ የወንጀል ህግ አንቀፅ 540 ላይ ያለው ህግ ተላልፎ በመገኘቱ ተከሳሹ በፈፀመው ሰው መግደል ወንጀል ክስ ቀርቦበታል፡፡

በክስ 4 ተከሳሹ 1ኛ በየነች ሻታቾን እና ልጇን ቡዛየሁ አድማሱን ወግቶ ሁለቱን ከገደለ በኃላ መኖሪያ ቤታቸውን ከነሙሉ ቁሳቁስ ሲያቃጥል የጩኸት ድምፅ ሰምቶ የመጣውን የግል ተበዳይን በያዘው ጦር ግራ የእጅ ክርኑ ላይ አንድ ጊዜ በመውጋት ተከሻሹ በኢ.ፌ.ዲ.ሪ የወንጀል ህግ አንቀፅ 27 ንዑስ 1 እና የወንጀል ግጉ አንቀፅ 539 ንዑስ አንቀፅ 1 ሀ ላይ ያለውን ተላልፎ በመገኘቱ በፈፀመው ከባድ ሰው መግደል ሙከራ ወንጀል ክስ ተመስርቶበታል፡፡

በክስ 5 ተከሳሹ በክስ አንድ እና በክስ ሁለት ላይ እናት እና ልጅን ወግቶ ሲገድል የጩኸት ድምፅ ሰምቶ ለማጣራት በመምጣት ላይ የነበረውን ተከሳሹ መንገድ ላይ አስቁሞ ወዴት እንደሚሄድ ሲጠይቀው የጩኸት ድምፅ ሰምቶ ለማጣራት እየሄደ መሆኑን ሲገልፅለት ፀያፍ ስድብ ሰድቦት እያባረረው በያዘው ጩቤ ግራ ጡንቻውን ሲወጋው በድንጋጤ ተንከባሎ እንሰት ውስጥ በመግባቱ የሞተ መስሎት ጥሎት መሄዱን የጠቀሰው ዐቃቤ ህግ ግለሰቡን በኢ.ፌ.ዲ.ሪ የወንጀል ህግ አንቀፅ 27 ንዑስ 1 እና የወንጀል ግጉ አንቀፅ 539 ንዑስ አንቀፅ 1 ሀ ላይ ያለውን ተላልፎ በመገኘቱ በፈፀመው ከባድ ሰው መግደል ሙከራ ወንጀል ክስ ተመስርቶበታል፡፡

ዐቃቤ ህግ በክስ 6 ላይ እንዳተተው ተከሳሹ የሰው መኖሪያ ቤት ሲያቃጥል የጩኸት ድምፅ ሰምቶ እሳቱን ለማጥፋት የሞከረውን የግል ተበዳይ ለምን እሳቱን ታጠፋለህ በሚል በያዘው ጦር በመውጋት ከባድ ጉዳት አድርሶበት በሰዎች እርዳት ወደ በህክም ተወስዶ ከሞት መትረፉን ጠቅሶ ተከሳሹ በኢ.ፌ.ዲ.ሪ የወንጀል ህግ አንቀፅ 27 ንዑስ 1 እና የወንጀል ግጉ አንቀፅ 540 ላይ ያለውን ተላልፎ በመገኘቱ በፈፀመው ከባድ ሰው መግደል ሙከራ ወንጀል ክስ ተመስርቶበታል፡፡

ዐቃቤ ህግ በክስ 7 ላይ በዝርዝር እንዳስቀመጠው ተከሳሹ የሰው መኖሪያ ቤት ሲያቃጥል የጩኸት ድምፅ ሰምቶ እሳቱን ለማጥፋት የሞከረውን የግል ተበዳይ ለምን እሳቱን ታጠፋለህ በሚል በያዘው ጦር በመውጋት ከባድ ጉዳት በማድረሱ ዐቃቤ ህግ ተከሳሹን በኢ.ፌ.ዲ.ሪ የወንጀል ህግ አንቀፅ 27 ንዑስ 1 እና የወንጀል ግጉ አንቀፅ 540 ላይ ያለውን ተላልፎ በመገኘቱ በፈፀመው ከባድ ሰው መግደል ሙከራ ወንጀል ክስ መስርቷል፡፡

ዐቃቤ ህግ በክስ 8 ላይ ተከሳሹ ንብረት ላይ ጉዳት ለማድረስ በማሰብ የግል ተበዳዮች መኖሪያ ቤት ከነሙሉ ቅሳቁሱ በማቃጠሉና የአከባቢ ነዋሪዎች እሳቱን ለማጥፋት ያሉትን ጉዳት አድርሶባቸው የንብረት ዋጋ ግምቱ 130 ሺህ ብር የሚያወጣ ንብረት በእሳት በማቃጠሉ በኢ.ፌ.ዲ.ሪ የወንጀል ህግ አንቀፅ 494 ንዑስ 1 ላይ ያለውን ተላልፎ በመገኘቱ በፈፀመው የሰው ንብረት በእሳት በማቃጠል ከባድ ጉዳት የማድረሰ ወንጀል መከሰሱን ነው ዐቃቤ ህግ ብርሃኑ ወ/ሚካኤል የወንጀል ድርጊቱን በስካር መንፈስ ሆኖ መፈፀሙን ጨምረዉ ተናግረዋል።

የካፋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ከዞኑ ዐቃቤ ህግ የቀረበለት የክስ መዝገብ ግራ ቀኙን ሲያከራክር ቆይቶ የዐቃቤ ህግ የሰው ምስክሮችን አስቀርቦ ካዳመጠ በኃላ ተከሳሹን ላይ የጥፋተኝነት ብይን ሰጥቷል፡፡

በዚሁ መሰረት የካፋ ዞን ከፍተኛ ፍርደ ቤት መጋቢት 30 ቀን 2017 ዓ.ም በዋለው የወንጀል ችሎት ተከሳሽ አስራት መንገሻ መሸሻ በ22 አመት ፅኑ እስራት እንዲቀጣ መወሰኑን ዐቃቤ ህግ ብርሃኑ ወ/ሚካኤል ገልፀው የዞኑ ዐቃቤ ህግ በፍርድ ቤቱ ውሳኔ ቅር በመሰኘቱ ህጉን ተከትሎ ይግባኝ መጠየቁን ማስረዳታቸውን ነው ዘገባው ያመላከተው።
https://www.youtube.com/c/ShegerTimesMedia

28/02/2025

በባል እና ሚስት መካከል የተፈጠረን ግጭት ለመገላገል የገቡት ጎረቤት ለምን ገላገልከን በማለት የገደሉት እናት እና ልጅ በእስራተ ተቀጡ

በቦረና ዞን ተልተሌ ወረዳ ሐዶ ቀበሌ ውስጥ የባልና ሚስትን ፀብ ለመገላገል ግልግል የገቡ ጐረቤትን የገደሉ እናትና ልጅ በእስራት መቀጣታቸው የቦረና ዞን ፖሊስ መምርያ አስታዉቋል።

* 1ኛ ተከሣሽ ኡንጋ ዱለቻ ልጅ
* 2ኛ ተከሣሽ ገልገልቱ ኡርቤ እናት ሲሆኑ

ታሕሣስ 28 ቀን 2017 ዓ. ም የገና በዓል ዋዜማ ላይ ሑለተኛ ተከሣሽ ገልገልቱ ከባለቤታቸው ጋር በተፈጠረ አለመግባባት ግጭት መፈጠሩ ተገልጿል።

ባለቤታቸውን እየደበደቡ እያለ ለግልግል የገቡት አቶ ጫና ቱቶ የተባሉ ጐረቤት ሑለተኛ ተከሣሽ ገልገልቱ ለምን ትገላግለናለህ በማለት ባለቤትዋን ስትመታበት በነበረ ፍልጥ እንጨት ኩላሊታቸው ላይ በመምታት ጉዳት ስታደርስባቸው አንደኛ ተከሣሽ ኡንጋ ዱለቻም እናቴን ለምን ትገላግላታለሕ በማለት ለግልግል የመጡትት አቶ ጫና ቱቶን በቀኝ እግሩ ሁለት ግዜ ፊኛቸው ላይ በመርገጥ ጉዳት ያደረሠባቸው መሆኑን በማስረጃ ተረጋግጧል ።

ተጐጂው አቶ ጫና ቱቶ በእናት እና ልጅ በደረሠባቸው ጉዳት ኩላሊታቸው እና ፊኛቸው ላይ ጉዳት በመድረሱ የገና በዓል እለት በአካባቢ ሠዎች እርዳታ ወደ ሆስፒታል እየሄዱ እዳለ ሕክምና ሣያገኙ መንገድ ላይ ሕይወታቸው እንዳለፈ ተረጋግጧል።

ፖሊስ ከአካባቢ ሠዎች በደረሠው መረጃ መሰረት የሟችን አስክሬን በሆስፒታል በማስመርመር የድርጊቱ ፈፃሚዎች እናትና ልጅን በቁጥጥር ስር በማዋል የምርመራ መዝገቡን በሠውና በአስክሬን የምርመራ ውጤት በማጠናከር ለዓቃቢ ሕግ ልኳል።

ዓቃቢ ሕግም ከፖሊስ የደረሠውን የምርመራ መዝገብ ተመልክቶ በወንጀል ሕግ ቁጥር 540 ቀላል ባልሆነ ሁኔታ አስበው ሠውን በመግደል ወንጀል ክስ መስርቷል፡፡ የተመሰረተውን ክስ ሲከታተል የቆየው የቦረና ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት የካቲት 17 ቀን 2017 ዓ.ም በዋለው ችሎት

* 1ኛ ተከሣሽ ኡንጋ ዱለቻ ልጅ ጥፋተኛ ሆኖ
በመገኘቱ በ12 ዓመት እስራት

* 2ኛ ተከሣሽ ገልገልቱ ኡርቤ እናት በ
11 ዓመት እስራት

እንዲቀጡ የተወሠነባቸው መሆኑን ከቦረና ዞን ፖሊስ መምርያ ወንጀል ምርመራ ዋና ክፍል ብስራት ሬዲዮ እና ቴሌቪዥን ያገኘው መረጃ ያሳያል።

~እንኳንም ዩንቨርስቲ አልገባሁ~ከዱባ ወጥ ቀጥሎ ኢቶጲስ ውስጥ የማይወደድ ነገር ቢኖር ትምህርት ነው ። አለመማር አንድ ነገር ሁኖ ሳለ የተማሩት ላይ መሳለቅ ደግሞ የሚገርም ነው።ትምህርት አ...
26/02/2025

~እንኳንም ዩንቨርስቲ አልገባሁ~

ከዱባ ወጥ ቀጥሎ ኢቶጲስ ውስጥ የማይወደድ ነገር ቢኖር ትምህርት ነው ። አለመማር አንድ ነገር ሁኖ ሳለ የተማሩት ላይ መሳለቅ ደግሞ የሚገርም ነው።

ትምህርት አያስፈልግም ብለው የሚናገሩ ሰዎች በኩራት የሚያነሷት ነጥብ "የተማሩ ሰዎች የት ደረሱ" የምትለዋ ቀሽም የማሸማቀቂያ ምክንያት ስትሆን፤ የተማሩት የት እንደደረሱ አብረን እንመልከት።

ከመሰረታዊ ጥናቶች እንጀምር።

1. ወንጀል

በ2021 Institute for Securities Studies (ISS) ባሳተመው ጥናት መሰረት 92.7% ገደማ ከባድ ወንጀሎች የሚፈፀሙት ዩንቨርስቲ ባልቀመሱ ግለሰቦች ሲሆን፤ 6.5% ወንጀሎች ዲግሪ ባላቸው እና ቀሪው 0.8% ብቻ ደግሞ ማስተርስ እና ከዛ በላይ ባላቸው ግለሰቦች የሚፈፀሙ ናቸው ይላል።

ይሄ ጥናት ኢቶጲስ ውስጥም የሚሰራ መሆኑን ለማወቅ፤ ስልክ ለመስረቅ ብሎ አንገት በጩቤ የሚወጉትን እና ወጡ ላይ ጨው አበዛሽ ብለው ሚስታቸውን በዘነዘና ከሚገሉት ሰዎች ጀምሮ መመልከት በቂ ነው።

እዚህ ጋር የተማረ ሰው ምን አተረፈ ካልክ? "ህሊና" የሚባል ነገር እልሀለሁ።

2. ገንዘብ

ሌላኛው የተማሩ ልጆች ላይ የመዘባበቻ ነጥብ፤ ስራ እና ገንዘብ የማጣታቸው ጉዳይ ነው። በመጀመሪያ ደረጃ ይሄ የነሱ ድክመት ሳይሆን የሀገሪቱ ድክመት ነው፤ እሱን ትተን ወደ ንግድ እንኳ ብንመለስ፤ ንግድ ላይም የተማረ እና ያልተማረ ሰው ቢሳተፍ የተማረው ሰው የተሻለ successful የመሆን እድል እንዳለው የሚያሳዩ ብዙ ዳታዎች አሉ።

ለምሳሌ አለማችን ላይ ካሉ ቢሊየነሮች መሀል 71 ፐርሰንቱ ከዩንቨርስቲ ዲግሪ እስከ PhD የጨረሱ ጎበዝ ተማሪዎች ናቸው። Bill Gates ወይም ማርቆስ Zuckerበርግ አይነት በጣም ጥቂት ባለሀብቶች በእርግጥ ከኮሌጅ ት/ት አቁመዋል፤ ነገርግን እነዚህ ግለሰቦች ት/ት ያቆሙት ከ Harvard እና Yale እንጂ ማትሪክ ወድቀው አይደለም።

ታዲያ ኢትዮጵያ ውስጥ ለምን ሀብታሞቹ ደንቆሮ ሆኑ ብለህ ልትጠይቅ ትችላለህ፤ አግባብም ነው። ለዚህ ቀላሉ መልስ "ቁጥር 1ን" ተመልከት ነው፤ የኛ ሀገር ሀብታም በአመዛኙ ደፋር፣ ወንበዴ፣ አጭቤ፣ አምታች ነው። ይሄንን ውንብድና ደፍሮ እንዲሰራ የሚያደርገው ደግሞ አለመማሩ ነው።

ኢትዮጲስ ውስጥ ለምን generational wealth እንደሌለ ታውቃለህ? አባት ሀብታም ሲሆን ልጆቹን ጥሩ ቦታ ያስተምራል፤ ከዛ ልጆች ህሊና ይኖራቸዋል፤ ከዛ የአባታቸውን የወንበዴ ቢዝነስ ማስቀጠል ይከብዳቸዋል፤ አለቀ።

የተማረ ሰው ቁጥር ማነስ ከPolitical Stability፣ ከPoverty Alleviation፣ ከInnovation & ከEntrepreneurship እና አጅግ ብዙ አሁን ላለንበት አዘቅት ምክንያቶች ጋር በብዙ ጥናቶች አስደግፎ ማስረዳት ይቻላል።

በአጭሩ ት/ት ምን ያደርጋል የሚልህ ነጋዴ ሂሳቡን የሚያሰራው በተማረ Accountant ነው፣ ሲከሰስ ተከራክሮ ንብረቱን የሚያስመልስለት የተማረ ጠበቃ ነው፣ ህንፆውን የሚያስገነባው በተማረ ኢንጂነር ነው፣ ሲያመው የሚሄደው የተማረው ዶክተር ጋር ነው፤ ከዛ አልፎ ልጁን አጥና እያለ የሚጨቀጭቀው እና ፅድት ያለ international school ልኮ የሚያስተምረው ይሄው ራሱ ሰውዬ ነው።

እና ምን ልልህ ነው፤
አለመማር አያኮራም።
እንኳንም ዩንቨርስቲ አልገባሁ አይባልም፤ ነውር ነው።

@ Natnael Afework

12/02/2025

ኢትዮጵያ የከፋ ሙስና ከሚታይባቸው ሀገራት ተርታ ተሰለፈች

💥 ከ180 አገራት 99ኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች

በዓለም ላይ በሕዝባዊ አገልግሎቶች ዘርፍ ያለውን የሙስና ሁኔታ እየተከታተለ ዓመታዊ ሪፖርት የሚያወጣው ትራንስፓረንሲ ኢንተርናሽናል በተጠናቀቀው የአውሮፓውያኑ 2024 ዓመት የአገራትን የሙስና ደረጃን ይፋ አድርጓል።

ሪፖርቱ የ180 የዓለም አገራትን የሙስና ደረጃ ያወጣ ሲሆን ከፍተኛውን ነጥብ በማግኘት ሙስና በጣም በዝቅተኛ ደረጃ የሚገኝባቸው ፖለቲካዊ አለመረጋጋት እና ግጭት የሌለባቸው አገራት ሲሆኑ፣ ሙስና ሥር የሰደደባቸው ደግሞ ግጭት እና ቀውስ ያለባቸው አገራት መሆናቸውን አመልክቷል።
በአገራቱ ዝርዝሩ ውስጥ ያደጉ የሚባሉት አገራት ከፍተኛውን ነጥብ በማግኘት ዝቅተኛ ሙስና የተመዘገባባቸው በመሆን ከፊት ያሉትን ደረጃዎች ይዘዋል።

በአገራት ውስጥ ያለውን የሙስና ደረጃ ለመመዘን ከሚሰጠው ከፍተኛ የሙስና ነጥብ ከሆነው 100 ውስጥ 37 በማግኘት ኢትዮጵያ ከ180 አገራት 99ኛ ደረጃ ላይ እንደምትገኝ ሪፖርቱ አስፍሯል።

ይህ የአገራት የሙስና ሁኔታን አመላካች የሆነው ዝርዝር በዓለም አቀፍ ደረጃ በስፋት የሚጠቀስ ሲሆን፣ ባለሙያዎች እና የንግድ ሰዎች በዋናነት ከሙስና አንጻር የሚገመገሙት የአገራት ሕዝባዊ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ናቸው።

በዚህ ምዘናም በአገራት ውስጥ ያለው የሙስና ሁኔታን ዜሮ (በከፍተኛ ሁኔታ ሙስና የተንሰራፋበት) እስከ 100 (ሙስና አስከ ሌለበት) ድረስ ነጥብ በመስጠት ነው የአገራት ደረጃ የሚወሰነው።

በዓለም ዙሪያ የፀረ ሙስና እንቅስቃሴን በማራመድ በሚታወቅ በትራንስፓረንሲ ኢንተርናሽናል አማካኝነት በየዓመቱ የሚወጣው ይህ የአገራት የሙስና ደረጃ ጠቋሚ ሪፖርት ውስጥ አብዛኞቹ የዓለም አገራት ተካተዋል።

ያለፈው ዓመትን በሸፈነው በዚህ ሪፖርት ኢትዮጵያ ከ180 አገራት በሕዝብ አገልግሎት ዘርፍ ባለ ሙስና 99ኛ ደረጃ ላይ የተቀመጠች ሲሆን፣ ይህም ቀደም ባለው የአውሮፓውያን ዓመትም በተመሳሳይ ደረጃ ላይ እንደነበረች ሪፖርቱ አመለክቷል።
በሪፖርቱ መሠረት ከሙስና አንጻር ከአጎራባች አገሮች አንጻር ኢትዮጵያ በተሻለ ደረጃ ላይ የምትገኝ ሲሆን፣ በዙሪያዋ ያሉ አገራት በሙሉ ከኢትዮጵያ ከፍ ባለሁኔታ ሙስና እንዳለባቸው ሪፖርቱ ይፋ አድርጓል።

በዚህም መሠረት ኬንያ 32 ነጥብ በማግኘት 121ኛ፣ ጂቡቲ በ31 ነጥብ 127ኛ፣ በእርስ በርስ ጦርነት ውስጥ የምትገኘው ሱዳን በ15 ነጥብ 170ኛ፣ ኤርትራ በ13 ነጥብ 173ኛ፣ ሶማሊያ በ9 ነጥብ 179ኛ እና ደቡብ ሱዳን በ8 ነጥብ 180ኛ ደረጃ ላይ ይገኛሉ።
የአገራትን የሙስና ሁኔታን በሚያሳየው ደረጃ ላይ ከሚሰጠው 100 አጠቃላይ ነጥብ ከግማሽ በላይ የሚያስመዘግቡ አገራት በጥሩ ሁኔታ ላይ ያሉ የሚባሉ ናቸው።
ከዚህ አንጻር በአጠቃላይ በአፍሪካ በተሻለ ደረጃ ላይ የሚገኙት አገራት ሲሸልስ (በ72 ነጥብ 18ኛ)፣ ኬፕ ቬርዲ (በ62 ነጥብ 35ኛ) ቦትስዋና (በ57 ነጥብ 43ኛ) እና ሞሪሺየስ (በ51 ነጥብ 56ኛ) ደረጃ ላይ ይገኛሉ።
በምዘናው ውስጥ ከተካተቱት 180 አገራት መካከል ሙስና በጣም በዝቅተኛ ደረጃ ላይ የሚገኝባቸው ቀዳሚ አስር አገራት የአውሮፓው እና የእስካንዴኔቪያን አገራት ናቸው።....
(BBC Amharic)

Address

Addis Ababa
Addis Ababa

Telephone

+251911016600

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Medina Jibreel Law posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Medina Jibreel Law:

Share