Legal talk with kidy

Legal talk with kidy ጠበቃ እና የሕግ አማካሪ ቅድስት ኤልያስ
0925122319

25/10/2025
የደቡብ ኢትዮጵያ ዐቃቢ ሕግ አዲሱ ደመወዝክልል ዐቃቢ ሕግ 31052የዞን ዐቃቢ ሕግ 25453የወረዳ ዐቃቢ ሕግ 21453@
15/10/2025

የደቡብ ኢትዮጵያ ዐቃቢ ሕግ አዲሱ ደመወዝ
ክልል ዐቃቢ ሕግ 31052
የዞን ዐቃቢ ሕግ 25453
የወረዳ ዐቃቢ ሕግ 21453@

28/05/2025

የወራሽነት ማስረጃ ፈልጋቹ የት መሄድ እንዳለባቹ ለማታቁ

በመቐለ ከተማ የሚገኙ ዳኞች፤ ከደህንነት ስጋት ጋር በተያያዘ ያቀረቧቸው ጥያቄዎች ካልተመለሱ የጀመሩትን የስራ ማቆም እንደሚቀጥሉ ገለጹበትግራይ ክልል መቐለ ከተማ የሚገኙ ዳኞች በትላንትናው ...
27/05/2025

በመቐለ ከተማ የሚገኙ ዳኞች፤ ከደህንነት ስጋት ጋር በተያያዘ ያቀረቧቸው ጥያቄዎች ካልተመለሱ የጀመሩትን የስራ ማቆም እንደሚቀጥሉ ገለጹ

በትግራይ ክልል መቐለ ከተማ የሚገኙ ዳኞች በትላንትናው ዕለት የጀመሩትን የስራ ማቆም ዛሬም በመቀጠላቸው በከተማይቱ የሚገኙ ፍርድ ቤቶች ተዘግተው ዋሉ። ዳኞቹ ለክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ያቀረቧቸው ጥያቄዎች እስኪፈቱ ድረስ የስራ ማቆማቸውን እንደሚቀጥሉ የትግራይ ዳኞች ማህበር ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ገልጿል።

በመቐለ ከተማ የሚገኙ ዳኞች ስራቸውን ለማቆማቸው በዋነኛነት የጠቀሱት ምክንያት “የደህንነት ችግር አለብን” የሚል ነው። የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር በትላንትናው ዕለት ባወጣው መግለጫም፤ በመቐለ ሰባት ክፍለ ከተሞች ባሉ ፍርድ ቤቶች እና በከተማይቱ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሚሰሩ ዳኞች “በደህንነት ስጋት” ምክንያት ስራ እንዳቆሙ ማሳወቃቸውን አረጋግጧል።

የትግራይ ዳኞች ማህበር ፕሬዝዳንት አቶ ዳዊት ሃይለስላሴ፤ ለክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ያቀረቧቸው አምስት ጥያቄዎች ከዳኞች ደህንነት ጋር የተያያዙ መሆናቸውን ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ተናግረዋል። የዳኞቹ የመጀመሪያ ጥያቄ በችሎት የሚመደቡ የጸጥታ አስከባሪዎችን የሚመለከት

ዜና በመቐለ ከተማ የሚገኙ ዳኞች፤ ከደህንነት ስጋት ጋር በተያያዘ ያቀረቧቸው ጥያቄዎች ካልተመለሱ የጀመሩትን የስራ ማቆም እንደሚቀጥሉ ገለጹ May 21, 2025 FacebookTwitterTelegramWhatsAppEmailCopy URL በትግ...

የፌዴራል ፍርድ ቤቶች የዳኝነት ክፍያን ለመወሰን የወጣው  ደንብ ቁጥር 1/2017  ታትሞ ወጥቷል***************************************በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት  በ...
26/05/2025

የፌዴራል ፍርድ ቤቶች የዳኝነት ክፍያን ለመወሰን የወጣው ደንብ ቁጥር 1/2017 ታትሞ ወጥቷል
***************************************
በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በቀን 19/03/2017 ዓ.ም የጸደቀው የፌዴራል ፍርድ ቤቶች የዳኝነት ክፍያን ለመወሰን የወጣው ደንብ ቁጥር 1/2017 በፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ታትሞ ወጥቷል፡፡

ደንቡን በብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት የሚያገኙት ሲሆን ስካን ኮፒውን በፍርድ ቤቱ ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fscethiopiaPR እንዲሁም በድረገጽ https://www.fsc.gov.et/ ማግኘት የሚችሉ መሆኑን በአክብሮት እንገልጻለን፡፡

የፌደራል ፍርድ ቤቶች ኮሚዩኒኬሽንና ስትራቴጂያዊ አጋርነት ዳይሬክቶሬት

በቤተሰብ ህግ መሰረት ባልና ሚስት ከጋብቻ በኋላ በውርስ ወይም በስጦታ በየግላቸው ያገኟቸው ንብረቶች የግል ንብረቶቻቸው ሆነው እንደሚቀሩ በተደነገገበት ሁኔታ በጋብቻ ወቅት ባልና ሚስት በፍ/...
26/05/2025

በቤተሰብ ህግ መሰረት ባልና ሚስት ከጋብቻ በኋላ በውርስ ወይም በስጦታ በየግላቸው ያገኟቸው ንብረቶች የግል ንብረቶቻቸው ሆነው እንደሚቀሩ በተደነገገበት ሁኔታ በጋብቻ ወቅት ባልና ሚስት በፍ/ቤት ወይም ስልጣን ባለው አካል ባልፀደቀ ውል ከውርስ የሚገኝ ንብረት የጋራ ነው በሚል ቢዋዋሉም ውሉ በፍርድ ቤት ካልተረጋገጠ በቀር ውጤት ስለሌለው በጋብቻ ወቅት በውርስ የተገኘ ንብረት የአንደኛው ተጋቢ የግል ንብረት ሆኖ የሚቀጥል ስለመሆኑ

ሰ.መ.ቁ.198277 volume 26

26/05/2025

#ንግድ Kidist Elias

በጋብቻ ውስጥ የተፈራ ንብረት የክፍፍል ጥያቄ ጋብቻው ከፈረሰበት ቀን ጀምሮ በ10 ዓመት ውስጥ ካልቀረበ በይርጋ ይታገዳል የሚል ትርጉም መስጠት የተፋቾችን ሕገ መንግሥታዊ የንብረት መብት የሚ...
23/05/2025

በጋብቻ ውስጥ የተፈራ ንብረት የክፍፍል ጥያቄ ጋብቻው ከፈረሰበት ቀን ጀምሮ በ10 ዓመት ውስጥ ካልቀረበ በይርጋ ይታገዳል የሚል ትርጉም መስጠት የተፋቾችን ሕገ መንግሥታዊ የንብረት መብት የሚጥስ ስለሆነ በሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 40(1፣ 7)፣ 50(5)፣ 55፣ 79(1)፣ እና 9(1) መሠረት ተፈጻሚነት የለውም::
ፌደሬሽን ም/ቤት መ/ቁ. 77/12 (ሰኔ 3/2012 ዓ.ም.)

Celebrating my 4th year on Facebook. Thank you for your continuing support. I could never have made it without you. 🙏🤗🎉
23/05/2025

Celebrating my 4th year on Facebook. Thank you for your continuing support. I could never have made it without you. 🙏🤗🎉

የወለደቻትን የ11 አመት ታዳጊ ልጅ ከእንጀራ አባቷ ጋር በማበር በአሰቃቂ ሀኔታ የግድያ ወንጀል የፈፀሙት የቅጣት ውሳኔ ተላለፈባቸው ።ተከሳሽ ወላጅ እናት አና እንጀራ አባት በሞት እንዲቀጡ ...
23/05/2025

የወለደቻትን የ11 አመት ታዳጊ ልጅ ከእንጀራ አባቷ ጋር በማበር በአሰቃቂ ሀኔታ የግድያ ወንጀል የፈፀሙት የቅጣት ውሳኔ ተላለፈባቸው ።

ተከሳሽ ወላጅ እናት አና እንጀራ አባት በሞት እንዲቀጡ ነው የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በዛሬው ዕለት በዋለው ችሎት ውሳኔ አስተላልፏል ።

የወንጀል ድርጊቱ የተፈፀመው ጥቅምት 30 ቀን 2015 ዓ/ም በግምት ከምሽቱ 3 ሰአት በሚሆንበት ግዜ ወረዳ 04 በልዩ ስሙ ካባ ሰፈር እየተባለ በሚጠራው ስፍራ የግድያ ወንጀል መፈፀሙን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል

የድሬዳዋ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ ወንጀል ምርመራ ዘርፍ ከፌዴራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ ጋር በመናበብ በተሰራው ስራ 1ኛ ተከሳሽ ሀና በየነ የተባለች የሟች ታዳጊ ወላጅ እናት እና 2 ተኛ ተከሳሽ ብሩክ አለሙ የተባለው የሟች ታዳጊ እንጀራ አባት ፍቅር እና እንክብካቤ የምትሻውን የ11 አመት ታዳጊ ከወላጅ አባቷ ጋር እንዳትገናኝ ብሎም የመማር መብቷን በመንፈግ በአሰቃቂ ሁኔታ በማፈን በከባድ ሁኔታ በመደብደብ ከባድ የግድያ ወንጀል ሊፈፅሙባ ችለዋል።

በዚህም ፖሊስ አጣርቶ አቃቤ ህግ የመሰረተውን ክስ መዝገብ የተመለከተው የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ድሬዳዋ ምድብ አራተኛ ችሎት ግንቦት 15 ቀን 2017 ዓ/ም በዋለው ችሎት 1ኛ ተከሳሽ ሀና በየነ እና 2ኛ ተከሳሽ ብሩክ አለሙን ጥፋተኛ ሆነው ስለገኛቸው በሞት እንዲቀጡ ውሳኔ አስተላልፏል ።

Address

Lideta
Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Legal talk with kidy posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share