ጠበቃ ይልቃል/Attorney Yelkal Yizengaw

ጠበቃ ይልቃል/Attorney Yelkal  Yizengaw Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from ጠበቃ ይልቃል/Attorney Yelkal Yizengaw, Lawyer & Law Firm, Belay Zeleke Street, Addis Ababa.

ወቅታዊ የተሻሻሉ፣አዲስ የወጡ ህጎች፣የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ውሳኔወች፣ጠቃሚ የህግመረጃወች በዚህ ገጽ ለተከታዮቻችን እናደርሳለን።
በማናቸውም ጉዳይ ጥብቅና ለማቆም
ለህግ ምክር አገልግሎት።
(+251) 0975121866
or(+251)0941696748
https://t.me/yilkalyizengaw

 #እንድታውቁት የሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ አገልግሎት የውክልና አገልግሎቱን በአምስት ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች ከወረቀት ነጻ በሆነ ሲስተም ተደራሽ ማድረግ መጀመሩን አሳውቋል።ሜክሲኮ በሚገኘው ቅር...
17/08/2026

#እንድታውቁት

የሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ አገልግሎት የውክልና አገልግሎቱን በአምስት ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች ከወረቀት ነጻ በሆነ ሲስተም ተደራሽ ማድረግ መጀመሩን አሳውቋል።

ሜክሲኮ በሚገኘው ቅርንጫፍ አስር ልዩ እና መደበኛው ቅርንጫፍ ፣አያት አደባባይ ሎሚያድ ሱፐርማርኬት በሚገኘው ቅርንጫፍ አስራአንድ እንዲሁም ካዛንቺስ እናት ታወር ላይ በሚገኘው ቅርንጫፍ ስምንት እና ቦሌ በሚገኘው ቅርንጫፍ አስራሁለት ጽ/ቤቶች ነው አገልግሎቱን መስጠት የተጀመረው።

በቅርቡም በሁሉም ቅርጫፎች ተግባራዊ ለማድረግ እየሰራሁ እገኛለሁ ሲል የሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ አገልግሎት አስታውቋል።

ከተገልጋዮች ምን ይጠበቃል ?

⚫በ https://dars.gov.et:5102 ሊንክ በመጫን መግባት፤

⚫ ብሄራዊ መታወቂያን በመጠቀም አስፈላጊ ዶክመንቶችን መጫን

⚫ ወደተጠቀሱት ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች ማቅናት

⚫ የተጫነውን መረጃ መያዝ የሚያስፈልግ ሲሆን ዶክመንቱ ተመሳክሮ ትክክለኛነቱ ሲረጋገጥ የኤሌክትሮኒክ ፊርማ (signature pad) በመፈረም የውክልና ሰነዱ በኦንላየን ይላካል።

⚫ በሰነዱ መገልገል ሲፈልጉ የሰነዱን ትክክለኛነት በQR Code ማረጋገጥ ይችላሉ።

የሰነዶች ማረጋገጫ እና ምዝገባ አገልግሎት ከወረቀትአልባ አገልግሎት በተጨማሪ በቴሌሳይን መተግበሪያ አማካይነት የቤተሰብ የጠበቃ እና የአስተዳደር ውክልና አገልግሎት ወደተቋም መምጣት ሳይጠበቅባቸው ካሉበት ሆነው ማግኘት የሚያስችላቸው አሰራር መተግበሩን አስታውሷል።

https://t.me/yilkalyizengaw

10/08/2026

👉ማንኛውም ተቋማት፤ ትምህርት ቤቶች ሕፃናት አስተማሪዎችም ሆነ ቤተሰቦቻቸው ወይም ሞጋዚዎቻቸው ፈቃድ ሳይሰጡበት የሕፃናቱን ፎቶግራፍ በበይነ-መረብ ወይም ኢንተርኔት ላይ በመልቀቅ ማስታወቂያ በመሥራት ገንዘብ ሰብሰብ ማስታወቂያ መሥራት በየትኛውም ክፍለ-አህጉራት ያለ ሰው ሊመለከተው የሚችል በመሆኑ ባለቤቶቹ ፈቃድ በአደባባይ ሊለጠፍ ሆነ ሊባዛ ወይም ሊሸጥ የማይችል በመሆኑ የተለጠፈ ማስታወቂያ እንዲነሳ እና በፎቶግራፉ የተገኘው ጥቅም ጋር ተመጣጣኝ የሆነ ካሣ ሊከፈል የሚገባ ነው።በፍ/ሕ/ቁ. 27፤ 29(1)(2)መ/ቁ 168527
ጥቅምት 26/ 2012 ዓ.ም

https://t.me/yilkalyizengaw

https://t.me/yilkalyizengaw
08/08/2026

https://t.me/yilkalyizengaw

ይልቃልይዘንጋው ስፈርህ (LLB,LLM in international law) በማናቸውም የፌደራል ፍርድ ቤቶች ጠበቃና የህግ አማካሪ። 0941696748/0975121866 Email yilkalyizengaw@gmail .com

04/08/2026
በወንጀል የተከሰሰ ማንኛውም ሰው ድርጊቱን ስለመፈጸሙ በዐቃቤ ሕግ በኩል "ከምክንያታዊ ጥርጣሬ በላይ" (beyond reasonable doubt) ካልተረጋገጠ በቀር ጥፋተኛ ተብሎ የቅጣት ውሳኔ...
29/07/2026

በወንጀል የተከሰሰ ማንኛውም ሰው ድርጊቱን ስለመፈጸሙ በዐቃቤ ሕግ በኩል "ከምክንያታዊ ጥርጣሬ በላይ" (beyond reasonable doubt) ካልተረጋገጠ በቀር ጥፋተኛ ተብሎ የቅጣት ውሳኔ ሊሰጥበት የማይገባ መሆኑን እና ይህ ሳይረጋገጥ የሚሰጥ የጥፋተኝነትና የቅጣት ውሳኔ ሕገ-መንግሥታዊ እንዳልሆነ በኢ.ፌ.ዲ.ሪ ሕገ-መንግሥት አንቀጽ 20 (3) ሥር ከተረጋገጠው "ንጹህ ሆኖ የመገመት መብት" አንጻር የፌዴሬሽን ምክር ቤት አስገዳጅ የሕገ-መንግሥት ትርጉም ውሳኔ ሰጥቷል። በተጨማሪም ተከሳሽ ጥፋተኛ አለመሆኑን በተራው ለማስረዳት በዐቃቤ ሕግ ማስረጃ ላይ ምክንያታዊ ጥርጣሬን (reasonable doubt) መፍጠር በቂው እንደሆነ ተወስኗል።

የፌዴሬሽን ምክር ቤት ውሳኔ፣ መዝገብ ቁጥር 151፣ ሰኔ 29 ቀን 2018 ዓ.ም
join my telegrbm channel
https://t.me/yilkalyizengaw

29/07/2026

" ጠበቃ ባለሙያ እንጂ አስማተኛ አይደለም ",,,,, ከ social media መንደር ,,,,,,
ዛሬ በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሆነ ምድብ ይግባኝ ችሎት ኮሪደር ላይ ቁጭ ብዬ እስክጠራ እጠብቃለሁ ።

ቀይ ፊቶ በንዴት በርበሬ የመሰለ ሴትዮ በስልክ በቁጣ ስትሳደብ ከቆየች በኋላ አጠገቤ ተቀመጠች።

" ጠበቃ ነሽ ? " አለችኝ የታቀፍኩትን ጋወን እያየች ።
" አዎ ነኝ " አልኳት ።
" አንድ የማይረባ ጠበቃ ገዝቼ ተጫወተብኝ ።
የት ነው ጠበቃ የሚከሰሰው ? " አለችኝ ።

" የማይረባ " እና " ጠበቃ ገዝቼ " የሚሉት ቃላት የጠበቃ ስስ ጎኔን ነክተዉት ብስጭት አልኩ።
" ምን አድርጎሽ ነው ? " አልኳት ንዴቴን ዉጬ።
" ኧረ የማይረባ ነው ፣ እሱን ጠበቃ ብዬ መግዛቴ በ1966 ዓ.ም የአያቴን መሬት አባቴ ወርሶ ,,,,,,,,,,,,,ብላ ጀምራ የረዥም አመታት ታሪክ አወራች።

ቀጥላ " ጠበቃዉ የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ተሸነፈ ፣ ዝም አልኩ። ይኸው ይግባኙንም ተሸነፈ ። ሲኩነሰነስ የሚያሸንፍ ጠበቃ ይመስላል ። ተበላሁ ፣ አስበላኝ ፣ ወይኔ ልጅት ! " አለች ።

እኔም ነደደኝ በሰጨኝ ጠበቃው አሳዘነኝ ።
" ችሎት ሳይቀርብሽ በተገቢው ተከራክሮ ከተሸነፈ ተሸነፈ ነው ።
ደግሞ የጠበቃሽ ትልቁ ችግር ከ1966 ዓ.ም ጀምሮ የተቡካካ ጉዳይሽን መያዙ ነው ።
ጠበቃ ባለሙያ እንጂ አስማተኛ አይደለም ።
ደግሞ ጠበቃ ቀጠርኩ እንጂ እንደሸቀጥ ገዛሁ አይባልም ።
የማይረባ ጉዳይ እንጂ የማይረባ ጠበቃ ጥቂት ነው ። " ብዬ ተንጣጥቼ ተነስቼ ችሎት ዉስጥ ገባሁ።

ገብቼም ለሚስኪኑ ጠበቃ ይቺን ስንኝ ቋጠርኩ።😥

አይ ጠበቃ !🤔
ተምረህ ነገር ስንጠቃ
ተንገላተህ ስታበቃ
ለምስጋና እንኳን አትበቃ

አይ ጠበቃ !🤔
የጠበቃ ፍዳ ጅምሩ
ገንዘብ ገና ከመቁጠሩ
ክሱን ከመጀመሩ
መዝገብ ከመመርመሩ
ግፊት ስኳር መደርደሩ

አይ ጠበቃ !🤔
ተምረህ ነገር ስንጠቃ
የምትገዛ እንደ እቃ
ለዉዳሴም የማትበቃ
በሰው ነገር የምትንቃቃ
ጭንቀት ታቅፈህ የምትነቃ
አይ ጠበቃ !🤔

"ይህቺ ስንኝ አበርክቶቱ ለመላው የጠበቆች ማህበረሰብ ትሁንልኝ" ጠበቃ mesi Bahiru

ትላለች ።😀😀😂 ስሜት ኮርኳሪ ሆና በድጋሜ አገኘኋት እና ላጋራችሁ ወደድኩ ።

The Real Echo ,,,,,,,

28/07/2026

With ጠበቃ ይልቃል/Attorney Yelkal Yizengaw – I just made it onto their weekly engagement list by being one of their top engagers!

Address

Belay Zeleke Street
Addis Ababa
0000

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ጠበቃ ይልቃል/Attorney Yelkal Yizengaw posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to ጠበቃ ይልቃል/Attorney Yelkal Yizengaw:

Shortcuts

Share