20/08/2026
የአክሲዮን ማህበራትን በተመለከተ ትኩረት ሊሰጣቸው የሚገቡ ነጥቦች
ነሀሴ 14/2018
ከሃምሳ በላይ አባላት ያላቸው የአክስዮን ማህበራት በተቋሙ ቀርበው ድንገተኛ እና መደበኛ የባለ አክሲዮኖች ጉባኤ የሚያስተላልፏቸው ውሳኔዎችን በተመለከተ፣
1. በሕግ አግባብ የተዘጋጀ የቃለ ጉባኤ ሰነድ፣
2. ስብሰባው በመመስረቻ ጽሁፍ ወይም በህጉ መሠረት መጠራቱን የሚገልጽ ማስረጃ መቅረብ አለበት፡፡
3. ቃለጉባኤው የማህበሩ ሙሉ ስም፣ ስብሰባው የተደረገበት ቦታ፣ ስብሰባው የተደረገበት ቀን፣ በስባሰባው ላይ የተገኙ አባላት ዝርዝር፣ በስብሰባው ላይ ያልተገኙ አባላት ዝርዝር፣ የሁሉም አባላት የአክስዮን ድርሻ መጠን፣ የስብሰባው አጀንዳዎች፣ የውሳኔው ይዘት መግለጽ ይኖርበታል፡፡
4. በድንገተኛም ሆነ በመደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ የተገኙ አባላትን የሚገልጽ የአቴንዳስ ሽት ከቃለ ጉባኤው ጋር ተያይዞ መቅረብ ይኖርበታል፡፡
5. የድንገተኛም ሆነ የመደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ የስብሰባ ቃለጉባኤዎች በተለያዩ ሰነዶች ተዘጋጅተው መቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
6. የአባላቱ ቀጥር ከ50 በላይ የሆነ አክሲዮን ማህበር ተቋሙ ሰነድ አረጋጋጭ ባለሞያ እንዲላክለት ሲጠየቅ ከደብዳቤ ጋር ስብሰባውን ማን እንደጠራ፤ የስብሰባውን አይነት ድንገተኛ ወይም ጠቅላላ ጉባኤ በሚል መለየት፤ ስንተኛ ጥሪ እንደሆነ፤ ጥሪ ያደረገበትን መንገድ እንዲሁም አጀንዳዎቹን አስቀድሞ ከደብዳቤው ጋር ሊገለፅ ይገባል፡፡
7. የአክሲዮን ማህበራት መመስረቻና መተዳደሪያ ደንባቸው ድንገተኛ ወይም መደበኛ ጠቅላላ ጉበኤዎችን የሚጠሩበትን የጥሪ መንገዶች ወስነው ስለመግለጻቸው ማረጋገጥ ይገባል፡፡
8. በአክሲዮን ማህበር ስብሰባዎች ላይ የሚቀርቡ አጀንዳዎች ከጉባኤው ስልጣን ውጪ መሆን አለመሆናቸውን በአግባቡ ማጣራት ያስፈልጋል፡፡
9. አክሲዮን በሽያጭ ከማህበሩ አባል ውጭ ለሆነ ሰው ሲዘዋወር በቅድሚያ ከማህበሩ አባላት በቀዳሚነት የመግዛት መብት የነበረባቸው ባለአክሲዮኖች በሰነዱ ላይ በመፈረም የተስማሙ ስለመሆናቸው ማረጋገጥ . ይገባል፡፡
10. በጥሬ ገንዘብ ካፒታልን ካሳደጉ በኋላ ይህንን ለማህበሩ የገባውን ገንዘብ በዓይነት መዋጮ ለመለወጥ የሚቀርብ ቃለጉባኤ የህግ መሰረት ስለሌለው ሊመዘገብ አይገባም፡፡ በዓይነት የገባውንም መዋጮ በተመሳሳይ ሁኔታ በጥሬ ገንዘብ መለወጥ አይቻልም፡፡
11. የንግድ ማህበራት በቃለ ጉባኤ የሚያደርጓቸው ማሻሻያዎች ሰነዱ ከፀደቀበት ቀን አንስቶ እስከ ሁለት ወር ድረስ ካላስመዘገቡ ተቋሙ አገልግሎት አይሰጥበትም፡፡
12. የንግድ ማህበራት የማፍረስ ውሳኔ ከወሰኑ በኋላ ማህበሩን በነበረበት ለማስቀጠል ከፈለጉ
ዋና ምዝገባና የንግድ ፈቃድ፣
ከንግድና ቀጣናዊ ትስስር ማህበሩ ያልተሰረዘ ለመሆኑ፣
ከገቢዎች የድጋፍ ደብዳቤ ሊቀርቡ ይገባል፡፡