ETHIO tv

ETHIO tv Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from ETHIO tv, Legal, Addis Ababa.

19/05/2022
https://youtu.be/_uSIftANhSo
17/05/2022

https://youtu.be/_uSIftANhSo

ethio 24 ታማኝ የመረጃ ምንጭ ሰብስክራይብ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ #

በአማራ ክልል ከማክሰኞ ጀምሮ የጦር መሳሪያ ምዘገባ ሊካሄድ ነውኢትዮ 24በአማራ ክልል ከማክሰኞ ጀምሮ በግለሰቦች እጅ የሚገኝ የጦር መሳሪያ ምዝገባ ሊካሄድ መሆኑን የክልሉ የሰላምና የፀጥታ ...
16/05/2022

በአማራ ክልል ከማክሰኞ ጀምሮ የጦር መሳሪያ ምዘገባ ሊካሄድ ነው

ኢትዮ 24

በአማራ ክልል ከማክሰኞ ጀምሮ በግለሰቦች እጅ የሚገኝ የጦር መሳሪያ ምዝገባ ሊካሄድ መሆኑን የክልሉ የሰላምና የፀጥታ ቢሮ አስታወቀ።

የጦር መሳሪያ ምዝገባው ከነገ ከማክሰኞ ግንቦት 09/2014 ዓ.ም. ጀምሮ እስከ አርብ ድረስ ለአራት ተከታታይ ቀናት እንደሚካሄድ የቢሮው ኃላፊ አቶ ደሳለኝ ጣሰው ለክልሉ መገናኛ ብዙኃን ገልጸዋል።

በዚህም መሠረት ከዚህ በፊት ያልተመዘገበ ማንኛውንም የጦር መሳሪያ የታጠቁ ግለሰቦች በየአካባቢያቸው ባሉ ማዕከላት በመገኘት እንዲያስመዘግቡ የክልሉ ሰላምና ፀጥታ ቢሮ ጥሪ አቅርቧል።

የቢሮው ኃላፊ አቶ ደሳለኝ ጣሰው የጦር መሳሪያ ምዝገባው አስፈላጊነት "የአማራን ሕዝብ ደኅንነትን ለማስጠበቅ አጋዥ ኃይል ለማጠናከር" መሆኑን አመልክተዋል።

ከዚሁ ጋር ተያይዞም የክልሉን ሕዝብ ደኅንነት ለማስጠበቅ ያለመ የተደራጀ ሥልጠና ሊሰጥ መሆኑንም የሰላምና ፀጥታ ቢሮ አስታውቋል።

አቶ ደሳለኝ ህወሓት "ወደ ዳግም ጦርነት ለመግባት ዝግጅት እያደረገ እንደሚገኝ በተጨባጭ እያሳየ ነው" በማለት "ይህንን ለማክሸፍ ከመንግሥት የፀጥታ ኃይል በተጨማሪ ማንኛውም የጦር መሳሪያ ያለው ምዝገባ ካካሄደ በኋላ የተደራጀ ሥልጠና እንዲወስድም ይደረጋል" በማለት ተናግረዋል።

ከጥቂት ቀናት በፊት የአማራ ክልል የፀጥታ ምክር ቤት የክልሉን ሰላምና ፀጥታ ሁኔታ ላይ ተወያይቶ ባወጣው መግለጫ ላይ በክልሉ ያለው "የሕግ ማስከበር ሥራ መላላት" እንደታየበት ጠቅሶ፣ እየተስፋፋ መጥቷል ያለው "ሕገወጥ የጦር መሣሪያ ዝውውር የክልሉን ሰላምና ደኅንነት ስጋት ውስጥ እየጣለ ይገኛል" ብሏል።

ጨምሮም ሕገወጥነትና ሥርዓት አልበኝነት ስር እየሰደደ በመምጣቱ በሕገወጥ ታጣቂዎች ምክንያት በክልሉ ልማት፣ በዜጎች እንቅስቃሴ፣ የኢንቨስትመንት እድሎች፣ በሥራ ዕድል ፈጠራ ላይና በሌሎችም ላይ እንቅፋት በመፍጠር "የክልሉን ልማት በአደገኛ ሁኔታ እየተፈታተነ እንደሚገኝ" አጽንኦት ሰጥቷል።

ስለዚህም ይህንን ሕገወጥነት በአጭር ጊዜ ማረም አስፈላጊ መሆኑን በመጥቀስ "ለሕዝብ ሰላምና ደኅንነት ሲባል መልክ መያዝ" እንደሚያስፈልግ የአማራ ክልል የፀጥታ ምክር ቤት ውሳኔ አሳልፎ ነበር።

እንዲሁም ምክር ቤቱ ህወሓት "በየቀኑ የጦርነት ነጋሪት እየጎሰመ የትግራይን ሕዝብ ለጦርነት እያነሳሳ በአማራ ክልል ላይ ዳግም ጦርነት አውጇል" ያለ ሲሆን፣ በዚህም ቡድኑ ሊሰነዝር ይችላል ላለው ወረራ የክልሉ የፀጥታ መዋቅር ዝግጁ እንዲሆን ትዕዛዝ አስተላልፏል።

ከዚህ አንጻር ከፌደራል የፀጥታ መዋቅር ጋር በመቀናጀት "ከህወሓት የሚሰነዘርን ጥቃት ለመከላከል ዝግጁ በመሆን፤ በሌላ በኩል ደግሞ. . . ሕገወጦችንና ሥርዓት አልበኞችን በመቆጣጠር የክልሉን ሰላምና ደኅንነት ማስጠበቅ ግንባር ቀደም የትኩረት አቅጣጫ" እንዲሆን መወሰኑን ገልጾ ነበር።

ለዚህም የፀጥታ ምክር ቤቱ በየደረጃው የፀጥታ ግብረ ኃይል አቋቁሞ "ሕገወጥነትን ለመቆጣጠርና ሕግን ለማስከበር ተገቢ ነው ያላቸውን ሕጋዊ እርምጃዎችን እንዲወስድ" ውሳኔ ማሳለፉን የምክር ቤቱ መግለጫ አመልክቷል።

ድምፃዊ ታረቀኝ ሙሉ ዘበጥያ ወረደ
15/05/2022

ድምፃዊ ታረቀኝ ሙሉ ዘበጥያ ወረደ

14/05/2022

የአማራ ክልል የፀጥታ ምክር ቤት ከህወሓት በኩል ሊሰነዘር ይችላል ላለው ወረራ የክልሉ የፀጥታ መዋቅር ዝግጁ እንዲሆን ትዕዛዝ አስተላለፈ።

ምክር ቤቱ በመግለጫው በክልሉ ያለው ሰላምና ፀጥታ ሁኔታ መገምገሙን አስታውቆ፣ ህወሓት "በየቀኑ የጦርነት ነጋሪት እየጎሰመ የትግራይን ሕዝብ ለጦርነት እያነሳሳ በአማራ ክልል ላይ ዳግም ጦርነት አውጇል" ብሏል።

ጨምሮም የክልሉ ሕዝብ ዳግም ለወረራና ለጥቃት እንዳይዳረግ የፀጥታ መዋቅሩ ቅድሚያ ሰጥቶ እንዲዘጋጅና ደጀኑ ሕዝብም የራሱን ኃላፊነት ለመወጣት ዝግጁ መሆን እንዳለበት በዚሁ መግለጫ ጥሪ አቅርቧል።

ለዚህም ከፌደራል መንግሥቱ የፀጥታ መዋቅር ጋር በመቀናጀት የሚሰነዘርን ጥቃት ለመከላከል በተጠንቀቅ መቆም፤ በሌላ በኩል ደግሞ በክልሉ ያሉ "ሕገ ወጦችንና ሥርዐት አልበኞችን በመቆጣጠር" የክልሉን ሰላምና ደኅንነት የማስጠበቅ ግንባር ቀደም ትኩረት ይሆናል ብሏል።

ሰብስክራይብ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ
23/04/2022

ሰብስክራይብ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ

ሰብስክራይብ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ

ፖለቲካሩሲያ አዲስ አህጉር አቋራጭ ባላስቲክ ሚሳዔል ሞከረች“ስማርት” አህጉር አቋራጭ የባላስቲክ ሚሳዔሉ አንድ ጊዜ እስከ 10 የኒኩሌር አረር የመሸከም አቅም አለውEthio online tv o...
21/04/2022

ፖለቲካ

ሩሲያ አዲስ አህጉር አቋራጭ ባላስቲክ ሚሳዔል ሞከረች

“ስማርት” አህጉር አቋራጭ የባላስቲክ ሚሳዔሉ አንድ ጊዜ እስከ 10 የኒኩሌር አረር የመሸከም አቅም አለው

Ethio online tv official youtube channel

“ስማርት” አህጉር አቋራጭ የባላስቲክ ሚሳዔል ሙከራ

ፑቲን፤ “ሙከራው ለሩሲያ ጠላቶች ቆም ብለው እንዲያስቡ የሚያደርግ የቤት ስራን የሰጠ ነው” ብለዋል
ሩሲያ በአይነቱ ለየት ያለ አዲስ ስማርት አህጉር አቋራጭ የባላስቲክ ሚሳዔል ሙከራ ማደረጓን አስታወቀች።
አዲሱ የሩሲያ አህጉር አቋራጭ ሚሳዔል በደቡብ ምዕራብ ሩሲያ ከምትገኘው ፕሌስክ የተወነጨፈ ሲሆን፤ በሌላኛው የሩሲያ አካል በሆነችው ሩቅ ምስራቅ ካማችታካ ማረፉ ተነግሯል።
አህጉር አቋራጭ ባላስቲክ ሚሳዔሉ በአጠቃላይ 6 ሺህ ኪሎ ሜትሮችን እንደተጓዘም ነው የተገለፀው

በሰዓት ከ6 ሺህ ኪሎ ሜትር በላይ የሚምዘገዘገው ሃይፐርሶኒክ ሚሳዔል

አዲሱ የሩሲያ ባላስቲክ ሚሳዔል የቴክኒክና የታክቲክ ብቃታቸው ከፍተኛ እንዲሁም ዘመናዊ የሚሳዔል መከላከያ ስርዓቶችን መቋቋም የሚችል ነው ተብሏል።
የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን፤ “ሚሳዔሉ እስካሁን ካሉት የተለየ መሳሪያ ነው፤ የሰራዊታችንን የመዋጋት አቅም ያሳድጋል” ያሉ ሲሆን፤ “በአስተማማኝ ሁኔታ ሩሲያን ከውጭ አደጋዎች መከላከል እንዲሁም ሩሲያን ለማስፈራራት ለሚሞክሩም በቂ ምለሽ ለመስጠት የሚያስችል ነው” ብለዋል።
“ሙከራው ለሩሲያ ጠላቶች ቆም ብለው እንዲያስቡ የሚያደርግ የቤት ስራን የሰጠ ነው” ሲሉም ፕሬዝዳንት ፑቲን አስታውቀዋል።
የዓለም አቀፉ የስትራቴጂክ ጥናት ማእከል የኤሮስፔስ ባለሙያ የሆኑት ዶጉላስ ባሪ፤ ሩሲያ አዲስ ያደረገችው ሙከራ ለሀገሪቱ አዲስ የስኬት መንገድ መሆኑን አስታውቀዋል።



ሩሲያ ሚሳዔሎችን በስራ ላይ ለማዋል ተደጋጋሚ ሙከራዎችን ማድረግ ይጠበቅባታል ያሉት ባሪ፤ አዳዲሱቹ ሚሳዔሎች ስራ ላይ ሲውሉ SS-18 እና SS-19 የተባሉ እድሜ ጠገብ የሩሲያ ሚሳዔሎችን ይተካሉ ብለዋል።
ስማርት የተባለው አዲሱ ሩሲያ ሚሳዔል በአንድ ጊዜ እስከ 10 የኒኩሌር አረር የመሸከም አቅም እንዳላቸውም ባለሙያው ተናግረዋል።

Address

Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ETHIO tv posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share

Category