ኢትዮ - ሕግ/Ethio - Law

ህፃናት ወራሾች በሆኑበት የንብረት ክርክር ይርጋ የሚቆጠረው 18 አመት ከሞላቸው በ10 አመት ውስጥ እንደሆነበ10 አመት ውስጥ ካላቀረቡ ይርጋ እንደሚያልፍባቸው በቅፅ 27 ሰ/መ/ቁ 239453...
25/05/2026

ህፃናት ወራሾች በሆኑበት የንብረት ክርክር ይርጋ የሚቆጠረው 18 አመት ከሞላቸው በ10 አመት ውስጥ እንደሆነ
በ10 አመት ውስጥ ካላቀረቡ ይርጋ እንደሚያልፍባቸው በቅፅ 27 ሰ/መ/ቁ 239453 ውሳኔ ተሰጥቶበቷል

ለፌደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ተገልጋይ በሙሉ👇
28/04/2026

ለፌደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ተገልጋይ በሙሉ👇

26/04/2026

አዳዲስ የጊዜ ገደቦች

አዲሱ የወንጀል ሕግ ሥነ ሥርዓት እና ማስረጃ ዐዋጅ ቁጥር 1410/2018 ከሚደነቅባቸው አንዱ ነገር ብዙ አዳዲስ የወንጀል ፍትሕ ሂደት የጊዜ ገደቦችን መደንገጉ ነው:: ከእነዚህ መካከል ዋና ዋናዎቹን እንጠቃቅሳለን::👴🏽
(By Hailu Hasena (Lawyer)

1. የተጨማሪ የወንጀል ምርመራ ጊዜ ቀጠሮ በአንድ ጊዜ እስከ 14 ቀን ሊፈቀድ የሚቻል ሲሆን አጠቃላይ የምርመራ ጊዜ ግን #በማናቸውም ምክንያት ከ4 (አራት) ወር ሊበልጥ አይችልም: ተብሎ ትደንግጓል:: አንቀጽ 119(2)

ይሁንና ወንጀሎች ቀላል፣ መካከለኛ እና ከባድ ተብለው የተከፋፈሉ እንደመሆኑ አጠቃላይ የምርመራ ጊዜ ቀጠሮም በዚህ አግባብ ቢከፋፈል ጥሩ ነበር::👴🏽

2. የወንጀል ምርመራው ተጠናቆ በዐቃቤ ሕግ ክስ እስኪመሠርት ያለው የመሸጋገሪያ ጊዜ ቀጠሮ በመደበኛነት እስከ 20 ቀን ሆኖ በአጠቃላይ ግን ከ 34 ቀን ሊበልጥ አይችልም: ተብሎ ተደንግጓል:: አንቀጽ 119(4)፣ 197(1)፣ 198(2)
* የጊዜ ገደቡ የሚሠራው ተጠርጣሪው ተይዞ ያለ ከሆነ ብቻ ነው::

3. ፍርድ ቤት በዐቃቤ ሕግ የተመሠረተን መደበኛ ክስ አይቶ ውሳኔ የሚሰጥበት ጊዜ ተገድቧል:: አንቀጽ 232 (1), (2)::
በዚህ መሠረት:-
*ቀላል ክሶች=3 ወር (+45 ቀን) ማለትም በአጠቃላይ በ4 ወር ከ15 ቀን ውስጥ በፍ/ቤት ውሳኔ ማግኘት አለባቸው::
*መካከለኛ ክሶች =6 ወር (+3ወር) ማለትም በአጠቃላይ በ9 ወር ውስጥ በፍ/ቤት ውሳኔ ማግኘት አለባቸው::
*ከባድ ክሶች=12 ወር (+6ወር) ማለትም በአጠቃላይ በአንድ ዓመት ከ6 ወር ውስጥ በፍ/ቤት ውሳኔ ማግኘት አለባቸው::
~ያልገባኝ በእነዚህ የጊዜ ገደቦች ውስጥ ውሳኔ ካልተሰጠ ውጤቱ ምን ይሆናል የሚለው ነው—ዳኛው መዝገቡን ባለበት ይዘጋል ቢባል ጥሩ ነበር::🙄

4. በዋስትና በመስጠት፣ በመከልከል ወይም በተፈቀደ የዋስትና ዓይነት ወይም መጠን ላይ ይግባኝ ማቅረብ የሚቻለው ብይኑ በተሰጠ በ20 ቀን ውስጥ ነው::

*ይህ እንኳን ከጊዜ ገደብ አኳያ አዲስ አይደለም—ከነባሩ የወ/መ/ሥ/ሥ/ቁ. 75(1) ጋር ተመሳሳይ ነው::
ይሁንና የዋስትና ይግባኝ የቀረበለት ፍ/ቤት ይግባኙ ከቀረበበት ቀን ጀምሮ ባሉት 5 ቀናት ውስጥ በይግባኙ ላይ ውሳኔ መስጠት እንዳለበት ተደንግጓል:: አንቀጽ 152(1), 153

*ይሁንና በተለይ በቀድሞው የወ/መ/ሥ/ሥ/ቁ. 66 ሥር ማናቸውም ፍ/ቤት የዋስትና ጉዳይ ሲመጣለት በ48 ሰዓት ውስጥ መወሰን አለበት ከሚለው አኳያ ሲታይ አዲሱ ሕግ ያዘገየዋል::

5. ፍ/ቤት የቅጣት ውሳኔ የሚሰጥበት ጊዜ ተገድቧል:: ይህም ፍ/ቤት በተከሳሽ ላይ የጥፋተኛነት ፍርድ ከሰጠ በኋላ ግራ ቀኝ የቅጣት አስተያየታቸውን አጠቃለው ካቀረቡበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ቀናት ውስጥ ፍ/ቤቱ የቅጣት ውሳኔ ማስተላለፍ አለበት ተብሎ ተደንግጓል:: አንቀጽ 301(1)

6. በዋናው የወንጀል ጉዳይ ላይ ይግባኝ የሚቀርብበት ጊዜ ፍርዱ፣ ውሳኔው፣ ብይኑ ወይም ትእዛዙ ከተሰጠበት ቀን ጀምሮ ባሉት 60 ተከታታይ ቀናት ውስጥ እንዲሆን ተደንግጎአል:: አንቀጽ 332(4)

*ይህም በቀድሞው የወ/መ/ሥ/ሥ/ቁ. 187 (1)፣ (2) መሠረት ይግባኝ ለማለት የሚፈልግ አካል ለይግባኝ የመዝገብ ግልባጭ እንዲሰጠው ውሳኔው በተሰጠ 15 ቀን ውስጥ ለወሰነው ፍ/ቤት ማመልከቻ የማቅረብ እና እና የውሳኔ ግልባጩ በደረሰው 30 ቀን ውስጥ ይግባኝ የማከፈት በድምሩ የ45 ቀን አሳሳች አሠራርን ቀሪ የሚያደርግ ነው::
ስለሆነም የወንጀልና የፍ/ብሔር ይግባኝ አቀራረብ የጊዜ ገደብ ተመሳሳይ ሆነ ማለት ነው::

7. የሰበር አቤቱታ የሚቀርብበት ጊዜ የመጨረሻ ውሳኔ በተሰጠ 90 ተከታታይ ቀናት ውስጥ መሆን እንዳለበት ተደንግጎአል:: አንቀጽ 344(3)
*ያው በቀድሞው የወ/መ/ሕ/ሥ/ሥ ኮድ ውስጥ ባለመጠቀሱ ምክንያት ለፎርማሊቲ ያህል አዲስ ነው ብለን ጠቀስነው እንጂ በተግባር አዲስ አይደለም::

8. የፍ/ቤት መጥሪያ ከቀነ ቀጠሮ 10 ቀን በፊት እንዲደርስ ተደንግጓል:: ማለትም የዐ/ሕግ ክስ ማመልከቻ ፍ/ቤቱ ቀጠሮ ክስ ለማንበብ ከያዘው ቀን አሥር (10) ቀን ቀደም ብሎ ለተከሳሽ ሊደርሰው ይገባል:: አንቀጽ 214(3)

እንዲሁም የተከሳሽ የመከላከያ ማስረጃ ዝርዝር መግለጫ ፍ/ቤቱ የመከላከያ ማስረጃ ለመስማት ከቀጠረበት ቀን አስቀድሞ ከ10 ቀናት በፊት ለዐ/ሕግ ሊደርሰው ይገባል:: አንቀጽ 288(2)

9. የግል አቤቱታ (private prosecution) እንዲያቀርብ በዐ/ሕግ የተፈቀደለት ሰው ፈቃዱን ባገኘ 15 የሥራ ቀን ውስጥ ክሱን አዘጋጅቶ ሥልጣን ላለው ፍ/ቤት ማቅረብ አለበት።
በመሆኑም ይህ ጊዜ ካለፈ በኋላ ክስ ማቅረብ አይችልም:: አንቀጽ 200(3)

10. የግል የወንጀል ምርመራ አቤቱታ (complaint) የሚያቀርብ ሰው አቤቱታውን ባቀረበ 10 የሥራ ቀናት ውስጥ ቀርቦ ለመርማሪ ፖሊስ ካላስረዳ የግል አቤቱታው ይሠረዛል::
አቤቱታው ከተሠረዘ በኋላ በጉዳዩ ላይ ድጋሚ አቤቱታ ማቅረብ አይችልም: ተብሎ ተደንግጓል:: አንቀጽ 64(4)

11. በልዩ የወንጀል ምርመራ ዘዴ ማስረጃ እንዲሰበሰብ በፍ/ቤት የሚሰጥ ጊዜ በመደበኛነት ከሦስት ወር አይበልጥም:: ይሁንና በዚህ ዘዴ ማስረጃ እንዲሰበሰብ በፍ/ቤት የሚሰጥ ጊዜ በማንኛውም ምክንያት ከ12 ወራት ሊበልጥ አይችልም::
አንቀጽ 105 (1)፣ (2)፣ (3)

12. የጥፋተኛነት ድርፍር (Plea bargaing) ማድረጊያ ጊዜም ተገድቧል:: ማለትም ዐቅም በላይ የሆነ ምክንያት ካላጋጣመ በስተቀር ዐ/ሕግና ተከሳሹ (ጠበቃው) የጥፋተኛነት ድርድር ለማካሄድ ከተስማሙበት ቀን ጀምሮ 45 (አርባ አምስት) ቀናት ውስጥ ድርድሩ መጠናቀቅ አለበት፡፡
አንቀጽ 175(4)
*"ከዐቅም በላይ የሆነ ምክንያት ድርድሩ እስከመቼ እንደሚራዘም ቁርጥ ገደብ ቢቀመጥ ሸጋ ነበረ::

13. ተከሳሽ በሌለበት የተሰጠ ፍርድ ድጋሚ እንዲታይ የሚቀርብ አቤቱታ በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ መቅረብ አለበት:: አንቀጽ 221
*ይህ ጊዜ ከቀድሞው የወ/መ/ሥ/ሥ/ቁ. 198 ጋር ተመሳሳይ ነው::
ይሁንና በቀድሞው ኮድ የአንድ ወሩ ጊዜ መቆጠር የሚጀምረው ተከሳሹ በሌለበት ጉዳዩ ታይቶ ፍርድ እንደተሰጠበት ካወቀበት ቀን አንሥቶ ሲሆን በአዲሱ ኮድ ግን በሌለበት ጉዳዩ ታይቶ ፍርድ እንዲሰጥበት ያደረገው ምክንያት ከቀረበት ወይም ከተወገደበት ቀን ጀምሮ ነው::

*በነገራችን ላይ ጉዳዩ ተከሳሽ በሌለበት በመታየት ሂደት ላይ ያለ (ፍርድ ያላገኘ) ከሆነ ተከሳሹ በማንኛውም ጊዜ ክርክሩን መቀላቀል ይችላል:: ማለትም ፍ/ቤቱ በሌለህበት ጉዳዩን ለማየት ብይን (Ex parte ruling) ስለሰጠሁ ወደ ክርክሩ መግባት አትችልም ሊለው አይችልም:: አንቀጽ 218(4)

* አደራ! ተከሳሽ በሌለበት (trial in absentia) የተሰጠ ፍርድን ድጋሚ ማየት [አንቀጽ 218-222] እና ተከሳሽ ባለበት (trial in praesentia) ታይቶ የተሰጠ ፍርድን ድጋሚ ማየት [አንቀጽ 353-357] የተለያዩ ፅንሰ ሀሳቦች ናቸውና አይቀላቀል::
በዚህ መሠረት ተከሳሽ ባለበት ታይቶ የተሰጠ ፍርድ ድጋሚ እንዲታይ (review of judgement) ለመጠየቅ የሚቀርብ አቤቱታ የመጨረሻው ፍርድ ከተሰጠ በኋላ በማንኛውም ጊዜ ፍርዱን ለሰጠው ፍ/ቤት ሊቀርብ ይችላል:: አንቀጽ 355(1)

ነገሮች እየተወሳሰቡ፣ ጽሑፉም እየረዘመ ስለሆነ እዚህ እንቋጨው::😌

ማሳሰቢያ:- ስማችን ሳይጠቀስ በሌላ ገጽ ላይ ኮፒ-ፔስት ሲደረግ እውነቱን ለማያውቅ ሰው እኛው ራሳችን የሌላን ሰው ጽሑፍ የሰረቅን ሁሉ ሊያስመስል ስለሚችል ደስ አይለንም::😔

መልካም ጊዜ!👴🏽

7 (ሰባት) ዳኞች በተሰየሙበት ችሎት የተሰጠ የሰበር ውሳኔ፤ መዝገብ ቁጥር 246230ከዚህ ቀደም በሰ/መ/ቁ 186946 የተሰጠው ውሳኔ ‘‘በአንድ ቦታ ላይ ሁለት የተለያዩ ሰዎች የይዞታ ማረ...
09/04/2026

7 (ሰባት) ዳኞች በተሰየሙበት ችሎት የተሰጠ የሰበር ውሳኔ፤ መዝገብ ቁጥር 246230

ከዚህ ቀደም በሰ/መ/ቁ 186946 የተሰጠው ውሳኔ ‘‘በአንድ ቦታ ላይ ሁለት የተለያዩ ሰዎች የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ ቢኖራቸው አንደኛው ቤት ቢሰራ ሌላኛው ወገን በይዞታዬ ላይ እየተቃወምኩኝ ቤት ስለሰራ ያፍርስልኝ በማለት መጠየቅ የማይችል መሆኑን’’ የሚገልጸው ውሳኔ ተለውጧል፡፡

7 (ሰባት) ዳኞች በተሰየሙበት ችሎት መዝገብ ቁጥር 246230
“በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በመ/ቁ186946 በሚያዝያ 26/2013 ዓ.ም የተሰጠው አስገዳጅ ትርጉም እና ሌሎች መዝገቦች ላይ የተያዘዉ ተመሳሳይ አቋም ተለውጦ፤ በአንድ ባለይዞታ ሊመዘገብ የሚገባን የከተማ ይዞታ ከአንድ በላይ የሆነ የይዞታ ማረጋገጫ ወይም ካርታ ለተለያዩ ሰዎች ተደርቦ ተሰጥቶ ሲገኝ ለቦታው ባለመብትነት ቅድሚያ የሚሰጠው መጀመሪያ ያስመዘገበው ሰው ነው’’ በሚል ተተርጉመዋል፡፡

የውሳኔውን ሙሉ ይዘት በቴሌግራም ቻናላችን ያገኙታል።
Telegram:- https://t.me/fscethiopiaPR/4601

⚖️ የሰነድ አለመኖር የካሳ መብትን ያሳጣልን? (አስገዳጅ የሰበር ውሳኔ ትንተና)​ለመሆኑ አንድ ግለሰብ ለአሥርተ ዓመታት የቆየ ይዞታ እያለው፣ ይዞታውን የሚያረጋግጥ "የባለቤትነት ማረጋገጫ ...
03/04/2026

⚖️ የሰነድ አለመኖር የካሳ መብትን ያሳጣልን? (አስገዳጅ የሰበር ውሳኔ ትንተና)

​ለመሆኑ አንድ ግለሰብ ለአሥርተ ዓመታት የቆየ ይዞታ እያለው፣ ይዞታውን የሚያረጋግጥ "የባለቤትነት ማረጋገጫ ካርታ ወይም ደብተር" ስለሌለው ብቻ ያለ ካሳ ከመሬቱ እንዲፈናቀል ሕጉ ይፈቅዳል?

​የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በመዝገብ ቁጥር 198400 (ሐምሌ 27 ቀን 2013 ዓ.ም) በሰጠው ውሳኔ ለዚህ ጥያቄ ግልጽ ምላሽ ሰጥቷል።

​🔍 የክርክሩ መነሻ

​አመልካች በጅማ ከተማ ውስጥ ለረጅም ዘመን የቆየ ይዞታ ያላቸው ሲሆን፣ የከተማው አስተዳደር "ይዞታው ለሕዝብ ጥቅም ይፈለጋል" በሚል ለልማት ሲነሳ አመልካች "የባለቤትነት ማረጋገጫ ሰነድ (ካርታ) የላችሁም" በሚል ካሳ ሳይከፈል እንዲነሱ መወሰኑ ክርክሩን አስነስቶታል።

​⚖️ የሰበር ሰሚ ችሎት ውሳኔ

​መደበኛ ፍርድ ቤቶች "አመልካች በቅድሚያ የይዞታ ማረጋገጫ ማውጣት ነበረባቸው" በሚል የሰጡትን ውሳኔ የሰበር ሰሚ ችሎቱ በመሻር የሚከተሉትን መሠረታዊ የሕግ ነጥቦች አስፍሯል፦
​የሕገ-መንግሥታዊ ጥበቃ፦ በሕገ-መንግሥቱ አንቀጽ 40(1) እና (7) መሠረት ማንኛውም ኢትዮጵያዊ በጉልበቱ ወይም በገንዘቡ በሠራው ንብረት ላይ ሙሉ መብት አለው። መንግሥት ለሕዝብ ጥቅም ሲል ንብረቱን በሚወስድበት ጊዜም ተመጣጣኝ ካሳ በቅድሚያ የመክፈል ግዴታ አለበት።

​የሰነድ አለመኖር እና የይዞታ መብት፦ አንድ ግለሰብ ይዞታው ላይ ለረጅም ዘመን መቆየቱ እየታወቀ፣ አስተዳደራዊ በሆኑ ምክንያቶች ወይም በወቅቱ የነበሩ አሠራሮች ባለመኖራቸው ምክንያት የይዞታ ማረጋገጫ ሰነድ ባይኖረውም፣ ይዞታው ለሕዝብ ጥቅም ሲፈለግ "ሰነድ የለህም" በሚል ብቻ ያለምንም ካሳ እንዲነሳ ማድረግ የሕግ መሠረት የለውም።

​የአስተዳደሩ ግዴታ፦ ይዞታው ለሕዝብ ጥቅም ሲፈለግ፣ አስተዳደሩ በቅድሚያ ይዞታው የአመልካች መሆኑንና ለምን ያህል ጊዜ እንደቆዩ አጣርቶ ተገቢውን ካሳ ሊከፍል ይገባል እንጂ፣ ካሳ ላለመክፈል የሰነድ አለመኖርን እንደ መከላከያ ሊጠቀምበት አይችልም።

​💡 ትምህርት

​ይህ ውሳኔ በተለይ በከተማም ሆነ በገጠር በይዞታቸው ላይ ለረጅም ዘመን የቆዩ ነገር ግን በተለያዩ ምክንያቶች የይዞታ ማረጋገጫ ሰነድ (ካርታ) ያልወጣላቸው ዜጎች፣ ለልማት ሲነሱ የመካስ መብታቸውን የሚያስከብር ነው።

የኢትዮጵያ አዲሱ የፈዴራል የወንጀል ሕግ ሥነ-ሥርዓት እና የማስረጃ ሕግ (Criminal Procedure and Evidence Law) ለበርካታ አስርት ዓመታት ሲያገለግል የነበረውን የ1954ቱ...
03/04/2026

የኢትዮጵያ አዲሱ የፈዴራል የወንጀል ሕግ ሥነ-ሥርዓት እና የማስረጃ ሕግ (Criminal Procedure and Evidence Law) ለበርካታ አስርት ዓመታት ሲያገለግል የነበረውን የ1954ቱን የሥነ-ሥርዓት ሕግ የሚተካ ሲሆን፣ ዘመኑን የዋጁ እና የሰብዓዊ መብቶችን አጠባበቅ የሚያጠናክሩ በርካታ አዳዲስ ለውጦችን አካቷል።
ዋና ዋና ይዘቶቹና ለውጦቹ የሚከተሉት ናቸው፦
# # # 1. የሥነ-ሥርዓት እና የማስረጃ ሕግ መዋሃድ
ቀደም ሲል የወንጀል ሥነ-ሥርዓት ሕግ እና የማስረጃ ሕግ ተለያይተው (የማስረጃ ሕጉም በረቂቅ ደረጃ ብቻ ለረጅም ጊዜ ቆይቶ) የነበረ ቢሆንም፣ አዲሱ ሕግ ግን ሁለቱንም በአንድ ላይ አጣምሮ ይዟል። ይህ መሆኑ በወንጀል ፍትሕ ሥርዓቱ ላይ ግልጽነትና ቅልጥፍናን ይፈጥራል።
# # # 2. የዲጂታል ማስረጃዎች ዕውቅና
ሕጉ የቴክኖሎጂ ለውጥን ያገናዘበ ሲሆን፣ የዲጂታል ወይም የኤሌክትሮኒክስ ማስረጃዎችን (ለምሳሌ፦ የቪዲዮ ምስሎች፣ የድምፅ ቅጂዎች፣ የኮምፒውተር መረጃዎች፣ የማኅበራዊ ሚዲያ መልዕክቶች) እንደ ትክክለኛ ማስረጃ እንዲቀበሉ ሕጋዊ መሠረት ሰጥቷል።
# # # 3. የምርመራ ዘዴዎች እና የሰብዓዊ መብቶች
* የምርመራ ዘዴዎች፦ እንደ ስልክ ጠለፋ እና የድብቅ ክትትል ያሉ ዘመናዊ የምርመራ ዘዴዎች በምን ዓይነት ጥብቅ የሕግ ማዕቀፍ እና የፍርድ ቤት ፈቃድ መከናወን እንዳለባቸው ይደነግጋል።
* የተጠርጣሪዎች መብት፦ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ሲውሉ ያላቸው መብት፣ የምርመራ ጊዜ ገደብ እና በምርመራ ወቅት ጠበቃ የማግኘት መብታቸው በግልጽ ተቀምጧል።
# # # 4. የዐቃቤ ሕግ ስልጣን እና ክስ መመስረት
* የክስ ድርድር (Plea Bargaining)፦ ይህ ትልቅ ለውጥ ሲሆን፣ አንድ ተጠርጣሪ ጥፋተኛነቱን አምኖ ከዐቃቤ ሕግ ጋር በመደራደር ቅጣቱ እንዲቀልለት ወይም ክሱ እንዲቋረጥ የሚያስችል ሥርዓት ነው። ይህ የፍርድ ቤቶችን የሥራ ጫና ይቀንሳል።
* ክስን ማንሳት ወይም ማቋረጥ፦ ዐቃቤ ሕግ ክስ ለማንሳት የሚችልባቸው ምክንያቶችና ቅድመ ሁኔታዎች በዝርዝር ተቀምጠዋል።
# # # 5. የምሥክሮች እና የጥቁሚዎች ጥበቃ
በከባድ ወንጀሎች ላይ መረጃ የሚሰጡ ጥቆማ ሰጪዎች እና ምሥክሮች ከበቀል ወይም ከጥቃት እንዲጠበቁ የሚያስችል የሕግ ከለላ ተካቷል።
# # # 6. የፍርድ ቤት ሥነ-ሥርዓት ቅልጥፍና
* ቅድመ-ችሎት ስብሰባ (Pre-trial Conference)፦ ክርክሩ ከመጀመሩ በፊት ግልጽ የሆኑ ነጥቦችን ለመለየት እና ሂደቱን ለማፋጠን የሚረዱ አሰራሮችን አስተውቋል።
* የጊዜ ቀጠሮ አሰጣጥ፦ የምርመራ ጊዜ ቀጠሮ አሰጣጥ ላይ ጥብቅ ቁጥጥር በማድረግ ተጠርጣሪዎች ያለ ፍርድ ለረጅም ጊዜ እንዳይታሰሩ የሚረዱ ድንጋጌዎችን ይዟል።
# # # 7. የተጎጂዎች መብት
ወንጀል የደረሰባቸው ሰዎች (Victims) በፍትሕ ሂደቱ ውስጥ ያላቸው ተሳትፎ፣ ጉዳታቸው የሚካካስበት መንገድ እና የሚደረግላቸው ጥበቃ ትኩረት አግኝቷል።
ማሳሰቢያ፦ ይህ ሕግ በሀገሪቱ የፍትሕ ሥርዓት ላይ ከፍተኛ ለውጥ ያመጣል ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን፣ አፈጻጸሙም ከሕገ-መንግሥቱ እና ከዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብቶች ድንጋጌዎች ጋር የተጣጣመ እንዲሆን ታስቦ የተዘጋጀ ነው።

በአዲሱ የወንጀል ሥነ-ሥርዓት እና ማስረጃ ሕግ ውስጥ የዋስትና መብት እና የክስ ድርድር እጅግ አስፈላጊ እና መሠረታዊ ለውጦች የተደረገባቸው ክፍሎች ናቸው። ዝርዝር ይዘታቸውም የሚከተለውን ይመስላል፦
# # # 1. የዋስትና መብት (Bail)
አዲሱ ሕግ የዋስትና መብትን እንደ መሠረታዊ መብት (Rule)፣ መከልከልን ደግሞ እንደ ልዩ ሁኔታ (Exception) ነው የሚመለከተው።
* የዋስትና ዓይነቶች፦ ሕጉ ግልጽ የሆኑ የዋስትና ዓይነቶችን አስቀምጧል። እነሱም፦ በግል ማረጋገጫ (Recognizance)፣ በሰው ዋስትና፣ በንብረት ዋስትና ወይም በገንዘብ ማስያዝ ሊሆን ይችላል።
* ዋስትና የሚከለከልባቸው ሁኔታዎች፦ ተጠርጣሪው ዋስትና ቢፈቀድለት "ይጠፋል" ወይም "ማስረጃ ያጠፋል" ወይም "ተጨማሪ ወንጀል ይፈጽማል" ተብሎ ሲታመን ዋስትና ሊከለከል ይችላል። እንዲሁም የቅጣቱ መጠን ከባድ በሆነባቸው (ለምሳሌ የሞት ወይም የዕድሜ ልክ እስራት በሚያስቀጡ) ወንጀሎች ላይ ገደብ ሊኖር ይችላል።
* የዋስትና ቅድመ ሁኔታዎች፦ ፍርድ ቤቱ ዋስትና ሲፈቅድ ተጠርጣሪው ከአገር እንዳይወጣ ፓስፖርት እንዲያስረክብ፣ የተወሰኑ ቦታዎች ላይ እንዳይገኝ ወይም በየጊዜው ፖሊስ ጣቢያ ቀርቦ እንዲፈርም ትዕዛዝ ሊሰጥ ይችላል።
* ቅሬታ ማቅረብ፦ ዋስትና የተከለከለ ተጠርጣሪ ወይም ዋስትና የተፈቀደለትን ተቃውሞ ያለው ዐቃቤ ሕግ ለበላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ የማለት መብታቸው በግልጽ ተቀምጧል።
# # # 2. የክስ ድርድር (Plea Bargaining)
ይህ አሰራር በኢትዮጵያ የፍትሕ ሥርዓት ውስጥ አዲስ ሲሆን፣ ዓላማውም ጊዜንና ወጪን ለመቆጠብ እንዲሁም የፍርድ ቤቶችን ጫና ለመቀነስ ነው።
* ሂደቱ፦ ክስ ከመመሥረቱ በፊት ወይም ክስ ከተመሠረተ በኋላ ፍርድ እስከሚሰጥ ድረስ ባለው ጊዜ ውስጥ ተጠርጣሪው/ተከሳሹ ጥፋተኛነቱን አምኖ ከዐቃቤ ሕግ ጋር ሊደራደር ይችላል።
* የድርድር ዓይነቶች፦
* የክስ ድርድር፦ ከባድ የሆነውን ክስ ወደ ቀለል ያለ የወንጀል ዓይነት በመቀየር መደራደር።
* የቅጣት ድርድር፦ በክሱ ላይ ተስማምቶ ቅጣቱ እንዲቀልለት መደራደር።
* የፍርድ ቤት ሚና፦ ድርድሩ የተደረገው በፈቃደኝነት መሆኑን፣ ተከሳሹ መብቶቹን መረዳቱን እና ድርድሩ የሕዝብን ጥቅም የማይጎዳ መሆኑን ፍርድ ቤቱ ማረጋገጥ አለበት። ፍርድ ቤቱ ድርድሩን ውድቅ የማድረግ ሥልጣን አለው።
* የተጎጂዎች ተሳትፎ፦ ዐቃቤ ሕግ የክስ ድርድር ሲያደርግ የወንጀል ተጎጂዎችን (Victims) ፍላጎትና ስሜት ግምት ውስጥ ማስገባት እንዳለበት ሕጉ ይደነግጋል። ተጎጂው ካሳ የሚያገኝበት መንገድም በድርድሩ ውስጥ ሊካተት ይችላል።
* ጥቅሙ፦ ተከሳሹ የቅጣት ቅናሽ ያገኛል፣ መንግሥት ለምስክሮች እና ለረጅም ክርክር የሚያወጣውን ወጪ ይቆጥባል፣ ተጎጂዎች ደግሞ የፍርድ ሂደቱን ሳይጠብቁ ካሳ ወይም ይቅርታ ሊያገኙ ይችላሉ።
ባጭሩ፦ እነዚህ ለውጦች ፍትሕን በፍጥነት ለመስጠት እና የተጠርጣሪዎችንም ሆነ የተጎጂዎችን መብት በተሻለ ሁኔታ ለማስጠበቅ የተነደፉ ናቸው።

በደስታ! የክስ ድርድር (Plea Bargaining) እና የዋስትና
አፈጻጸም ሂደቶች በሕጉ መሠረት እንዴት እንደሚከናወኑ ደረጃ በደረጃ እንመልከት፦
# # # 1. የክስ ድርድር አፈጻጸም ሂደት (Step-by-Step)
የክስ ድርድር በዘፈቀደ የሚደረግ ሳይሆን ጥብቅ ሥርዓት ያለው ሂደት ነው፦
* ሀ. ድርድሩን መጀመር፦ ድርድሩን ተከሳሹ/ተጠርጣሪው ወይም ጠበቃው ሊጀምሩት ይችላሉ። ዐቃቤ ሕግም ቢሆን ለፍትሕ አሰጣጥ ጠቃሚ ነው ብሎ ካመነ ድርድር እንዲጀመር ሃሳብ ማቅረብ ይችላል።በፀጋዬ ደመቀ
https://t.me/ethiolawtips
* ለ. የድርድር ነጥቦች፦ ድርድሩ በሁለት ነገሮች ላይ ሊሆን ይችላል፦
1. ከባድ ወንጀልን ወደ ቀለል ባለ ወንጀል ለመቀየር (ለምሳሌ፦ "በከባድ ግድያ" ፋንታ "በቀላል ሰው መግደል" እንዲከሰስ)።
2. የቅጣት መጠን እንዲቀነስ (ለምሳሌ፦ ከ10 ዓመት እስራት ወደ 5 ዓመት እንዲወርድ)።
* ሐ. ስምምነቱን በጽሑፍ ማዘጋጀት፦ ስምምነቱ ሲደረስ በዐቃቤ ሕግ እና በተከሳሹ/በጠበቃው ተፈርሞ በጽሑፍ መዘጋጀት አለበት። በዚህ ስምምነት ላይ ተከሳሹ ጥፋቱን በፈቃደኝነት ማመኑ በግልጽ መስፈር አለበት።
* መ. የፍርድ ቤት ማረጋገጫ፦ ይህ ወሳኙ ደረጃ ነው። ስምምነቱ ለፍርድ ቤት ይቀርባል። ዳኛው ተከሳሹን ለብቻው በማነጋገር፦
* ድርድሩን ያደረገው ያለ ማስገደድ (በፈቃዱ) መሆኑን፣
* ጥፋተኛነቱን ማመኑ የሚያስከትለውን ውጤት መረዳቱን፣
* ምስክር የመጠየቅ መብቱን መተዉን ማረጋገጥ አለበት።
* ሠ. ውሳኔ፦ ፍርድ ቤቱ ድርድሩ ፍትሐዊ ነው ብሎ ካመነ ስምምነቱን መሠረት አድርጎ ፍርድ ይሰጣል። ፍትሐዊ ካልሆነ ግን ድርድሩን ውድቅ አድርጎ መደበኛው የፍርድ ሂደት እንዲቀጥል ያዛል።
# # # 2. የዋስትና መብት አፈጻጸም ሂደት
ዋስትና ተከሳሹ ከእስር ወጥቶ ጉዳዩን በውጭ ሆኖ እንዲከታተል የሚፈቀድበት ሥርዓት ነው፦
* ሀ. ማመልከቻ ማቅረብ፦ ተጠርጣሪው ፖሊስ ጣቢያ ወይም ፍርድ ቤት ቀርቦ የዋስትና ጥያቄውን በቃል ወይም በጽሑፍ ያቀርባል።
* ለ. የዐቃቤ ሕግ መቃወሚያ፦ ዐቃቤ ሕግ "ዋስትና ሊፈቀድ አይገባም" የሚል ከሆነ ምክንያቱን (ለምሳሌ፦ ምስክር ያባብላል፣ ከአገር ይወጣል) ለፍርድ ቤቱ ማስረዳት አለበት።
* ሐ. የዋስትና መጠን መወሰን፦ ፍርድ ቤቱ ዋስትና ሲፈቅድ እንደ ወንጀሉ ክብደት የገንዘብ መጠን ይወስናል። ገንዘብ የሌለው ሰው ከሆነ "የሰው ዋስ" (ታማኝ ግለሰብ) እንዲያቀርብ ሊታዘዝ ይችላል።
* መ. ግዴታዎችን ማስፈረም፦ ተከሳሹ እና ዋሶቹ "በቀጠሮ ቀን ካልቀረበ ይህን ያህል ብር ለመንግሥት እንከፍላለን" የሚል ውል ይፈርማሉ።
* ሠ. መለቀቅ፦ ፎርማሊቲው እንደተጠናቀቀ ፍርድ ቤቱ ለቤት ማረሚያ ወይም ለፖሊስ ጣቢያ የመልቀቂያ ትዕዛዝ (Release Order) ይጽፋል።
# # # ልዩ ነጥብ፦ የተጎጂው ድርሻ
በአዲሱ ሕግ፣ በክስ ድርድር ወቅት ዐቃቤ ሕግ የወንጀል ተጎጂውን ማነጋገር ወይም ጥቅሙ እንዳይጎዳ የማድረግ ግዴታ አለበት። ለምሳሌ ተከሳሹ ቅጣቱ እንዲቀልለት ሲደራደር፣ ለተጎጂው ተገቢውን ካሳ እንዲከፍል እንደ ቅድመ ሁኔታ ሊቀመጥ ይችላል።በፀጋዬ ደመቀ
https://t.me/ethiolawtips

“ግዛት ተሸጋሪ” ስልጣን - ለኦሮሚያ ፍርድ ቤት****/በዳንኤል ፍቃዱ ጠበቃና የህግ አማካሪ/መጋቢት 24 ቀን 2018 ዓ.ም. የጸደቀው አዲሱ የወንጀል ሥነ-ሥርዓት እና የማስረጃ ሕግ፣ በተለ...
03/04/2026

“ግዛት ተሸጋሪ” ስልጣን - ለኦሮሚያ ፍርድ ቤት
****
/በዳንኤል ፍቃዱ ጠበቃና የህግ አማካሪ/

መጋቢት 24 ቀን 2018 ዓ.ም. የጸደቀው አዲሱ የወንጀል ሥነ-ሥርዓት እና የማስረጃ ሕግ፣ በተለይም አንቀጽ 25(3) ላይ ለኦሮሚያ ክልል ፍርድ ቤቶች በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ለሚገኙ የክልሉ ተቋማትና ሠራተኞች የሰጠው የዳኝነት ሥልጣን፣ በሕግ ባለሙያዎችና በፖለቲካ ተዋንያን ዘንድ ሰፊ ክርክር አስነስቷል። ይህንን ድንጋጌ ከሕግ መርህ፣ ከሕገ-መንግሥታዊ ፋይዳ እና ከተግባራዊ ተግዳሮቶች አንጻር እንደሚከተለው በዝርዝር መመልከት ይቻላል፦

1. ከግዛታዊ የዳኝነት ሥልጣን መርህ (Territorial Jurisdiction) አንጻር
በዓለም አቀፍ የሕግ ሥርዓት ውስጥ የወንጀል ዳኝነት ሥልጣን ዋነኛው መሠረት "የግዛት መርህ" ነው። ይህ መርህ "አንድ ወንጀል የተፈጸመበት ግዛት ባለቤት የሆነው መንግሥት ወይም አካል የመዳኘት ሥልጣን አለው" የሚል ነው።
• ተቃርኖው፦ አዲስ አበባ ራሷን የቻለች አስተዳደር (Charter City) እንደመሆኗ፣ በእሷ ግዛት ውስጥ የሚፈጸሙ ወንጀሎች በፌዴራል ወይም በከተማዋ ፍርድ ቤቶች መታየት ነበረባቸው።
• ልዩነቱ፦ አዲሱ ሕግ ይህንን መርህ በመተው "የተከራካሪዎች ማንነት" (Identity-based) ወይም "የተቋማት ባለቤትነት" ላይ የተመሠረተ ሥልጣን (Subject-matter coupled with Persona) አስተዋውቋል። ይህም በአንድ ጂኦግራፊያዊ ወሰን ውስጥ ሁለት የተለያዩ የክልል/የፌዴራል የዳኝነት ሥልጣናት እንዲኖሩ በማድረግ የግዛታዊ ሥልጣን መርህን ይሸረሽራል። Fikadu Law Office
2. ከኢትዮጵያ ሕገ-መንግሥት አንጻር
የፌዴሬሽኑ ሕገ-መንግሥት በአንቀጽ 49(5) ላይ የኦሮሚያ ክልል በአዲስ አበባ ላይ "ልዩ ጥቅም" እንዳለው ይደነግጋል።
• የሕግ ሙግቱ፦ ደጋፊዎች "ልዩ ጥቅም" የሚለው ጽንሰ-ሀሳብ ክልሉ የራሱን ተቋማትና ሠራተኞች በራሱ ሕግና ፍርድ ቤት እንዲያስተዳድር ይፈቅዳል ይላሉ።
• የተቃውሞው ነጥብ፦ ተቃዋሚዎች ግን የሕገ-መንግሥቱ አንቀጽ 5ዐ(4) "የክልል ሥልጣን በክልሉ ወሰን ብቻ የተገደበ ነው" የሚለውን መሠረታዊ መርህ ይጠቅሳሉ። የዳኝነት ሥልጣን የሉዓላዊነት መገለጫ በመሆኑ፣ ከአንድ ክልል ወሰን ወጥቶ በሌላ ክልላዊ/ከተማ አስተዳደር ወሰን ውስጥ መተግበሩ የሕገ-መንግሥታዊ የሥልጣን ክፍፍሉን ያደበዝዘዋል።
3. ከሌሎች የፌዴራል አገራት ተሞክሮ
በአብዛኞቹ የፌዴራል አገራት (ለምሳሌ አሜሪካ፣ ናይጄሪያ ወይም ጀርመን) የጋራ መቀመጫ በሆኑ ከተሞች ውስጥ የዳኝነት ሥልጣን አያያዝ ጥንቃቄ የተሞላበት ነው።
• ተሞክሮ፦ በአሜሪካ ዋሽንግተን ዲ.ሲ. ውስጥ የፌዴራል ሕንፃዎች ቢኖሩም፣ በሕንፃዎቹ ውስጥ የሚፈጸሙ ወንጀሎች የሚታዩት በፌዴራል ፍርድ ቤቶች እንጂ ተቋማቱ የመጡበት የሌላ ክፍለ-ሀገር (State) ፍርድ ቤቶች በዚያ ግዛት ውስጥ ገብተው አይዳኙም።
• የኢትዮጵያ ለውጥ፦ የኢትዮጵያ አዲሱ አሠራር ግን "Extra-territorial Jurisdiction" (ከግዛት ውጭ ያለ ሥልጣን) የሚስጥ አሠራር በመሆኑ፣ በፌዴራሊዝም ተሞክሮ ውስጥ አዲስና አወዛጋቢ አካሄድ ነው።
4. ከሕግ መርህና ፍልስፍና አንጻር
የሕግ ፍልስፍና አንዱ ዓላማ "የሕግ እርግጠኝነትን" (Legal Certainty) ማስፈን ነው።
• የዳኝነት አንድነት፦ በአንድ ግዛት ውስጥ የሚኖሩ ሰዎች የሚዳኙበት ሕግና ፍርድ ቤት የታወቀ ሊሆን ይገባል። አዲሱ አዋጅ ግን በአዲስ አበባ ውስጥ ለሚገኙ ሰዎች "ማን ነህ? የት ነው የምትሠራው?" የሚሉ ጥያቄዎችን በመጠየቅ የተለየ ፍርድ ቤት እንዲሰየም ማድረጉ፣ በሕግ ፊት እኩል የመሆንን መርህ (Equality before the law) ጥያቄ ውስጥ ይከተዋል። ለምሳሌ፣ ሁለት ግለሰቦች አዲስ አበባ ውስጥ ተመሳሳይ የሙስና ወንጀል ቢፈጽሙ፣ አንደኛው የኦሮሚያ ክልል ሠራተኛ በመሆኑ "ጨፌ ኦሮሚያ" ባወጣው ሕግና በክልሉ ፍርድ ቤት ሲዳኝ፣ ሌላው ግን በፌዴራል ሕግና ፍርድ ቤት ሊዳኝ ነው። Fikadu Law Office
5. በተግባር ሊፈጠሩ የሚችሉ ተግዳሮቶች
ይህ የሥልጣን ውክልና በፍትሕ አሰጣጡ ሂደት ላይ የሚከተሉትን ችግሮች ሊያስከትል ይችላል፦
• የፖሊስ ምርመራ ውዝግብ፦ ወንጀሉ ሲፈጸም መጀመሪያ የሚደርሰው የአዲስ አበባ ፖሊስ ወይስ የኦሮሚያ ፖሊስ? የኦሮሚያ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ ቢሰጥ በአዲስ አበባ ፖሊስ ላይ ተፈጻሚነት ይኖረዋል?
• የማስረጃ አሰባሰብ፦ በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ የሚገኙ የፌዴራል ወይም የግል ተቋማት ለኦሮሚያ ክልል ፍርድ ቤቶች ማስረጃ እንዲሰጡ የሚገደዱበት የሕግ ማዕቀፍ ግልጽነት ሊጎድለው እና አሰራሩም እጀግ አስቸጋሪ ሊሆን ይችላል።

ማጠቃለያ
አዲሱ ሕግ የኦሮሚያ ክልልን ተቋማዊ ደኅንነትና "ልዩ ጥቅም" ለማስከበር ታስቦ የተደነገገ ቢሆንም፣ ከግዛት የዳኝነት ሥልጣን መርህ ጋር ይጋጫል። በተግባርም በፌዴራል እና በክልል የፍትሕ ተቋማት መካከል የሥራ መደራረብንና የሥልጣን ሽኩቻን የመፍጠር ዕድሉ ከፍተኛ ነው፡፡ Fikadu Law Office

የወንጀል ሕግ ሥነ-ስርአት እና የማስረጃ ሕግ ረቂቅ አዋጅ ፀደቀ---------------------- የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በ13ኛ መደበኛ ስብሰባው፤ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪ...
02/04/2026

የወንጀል ሕግ ሥነ-ስርአት እና የማስረጃ ሕግ ረቂቅ አዋጅ ፀደቀ
----------------------
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በ13ኛ መደበኛ ስብሰባው፤ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የወንጀል ሕግ ሥነ-ስርአት እና የማስረጃ ሕግ ረቂቅ አዋጅን አፅድቋል፡፡

በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሕግና ፍትህ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ የተከበሩ ወ/ሮ እፀገነት መንግስቱ ሪፖርት እና የውሳኔ ሀሳብ አቅርበዋል፡፡

ረቂቅ ሕጉ በወንጀል ፍትህ አስተዳደር ሥርዓት የወንጀል ፍርድ ሂደት የተጠርጣሪን እና የተከሳሽን እንዲሁም በወንጀል ምክንያት የተጎዱ ሰዎችን ሰብአዊ መብቶች ለማክበርና ለማስከበር የሕግ የበላይነት በማስፈን የአሰራር ስርዓትን ለመዘርጋት የሚያስችል መሆኑን ሰብሳቢዋ ገልጸዋል፡፡

የተቀላጠፈ የፍትህ ሥርዓት እንዲኖር ለማስቻል እና ልዩ የወንጀል ምርመራ ዘዴን እንዲሁም ለተጎጂዎች ካሣ የሚከፈልበትን አግባብ ያካተተ ዓለም አቀፍ መርህን የተከተለ ረቂቅ ሕግ እንደሆነ የተከበሩ ወ/ሮ እፀገነት መንግስቱ አያይዘው አስረድተዋል፡፡

ረቂቅ ሕጉ ከኢትዮጵያ ሕገ-መንግሥት እና ኢትዮጵያ ከተቀበለቻቸው ዓለም አቀፍ ስምምነቶች፣ መርሆች እና እሴቶች እንዲሁም ከወንጀል ህጉ ጋር የተጣጣመና ዘመናዊ በመሆኑ ጠቀሚ እንደሆነ ሰብሳቢዋ ጠቁመዋል፡፡

ረቂቅ ህጉ በህገ መንግስቱ፣ በወንጀል ሕጉ፣ ዓለም አቀፍ ህጎች እና በሌሎች አግባብነት ባላቸው ህጎች የተረጋገጡ ልዩ ትኩረት ለሚያሻቸው ለሴቶች፣ ህፃናት እና አካል ጉዳተኞች የተሰጣቸውን መብቶች ለማረጋገጥ የሚያስችል እንደሆነም የተከበሩ ወ/ሮ እፀገነት መንግስቱ ገልጸዋል፡፡

የምክር ቤት አባላት በበኩላቸው ረቂቅ አዋጁ ረጅም ጊዜ የቆየና የዘገየ ቢሆንም በህዝቡ ዘንድ የቅሬታ ምንጭ የነበሩ ችግሮችን ለመፍታት ወቅቱን የሚመጥን አዋጅ በመሆኑ የህዝብን የፍትህ ሥርዓቱን ለማስፈን እንደሚያግዝ ገልጸዋል፡፡

የዜጎችን ሰብአዊ እና ዲሞክራሲአዊ መብቶችን ለማስከበር እና የፍትህ ሥርዓቱን በማዘመን ወቅቱን ያዋጅ አግልግሎት ለመስጠት ረቂቅ አዋጁ ሚናው የጎላ መሆኑን የምክር ቤት አባላት አመላክተዋል፡፡፡

በሌላ በኩል የምክር ቤት አባላት በበኩላቸው፤ ረቂቅ አዋጁ በአተገባበር ሂደት ላይ ሊያጋጥሙ የሚችሉ ችግሮችን ታሳቢ በማድረግ ከፍትህ አካላት ጋር መወያየት እንደሚያስፈልግ አስገንዝበዋል፡፡

ከምርመራ ሂደት እና ከዲጂታል አሰራሮች ጋር በተያያዘ ዜጎችን ህገ መንግስታዊ መብትን በጠበቀ መልኩ መሆን እንዳለበት የምክር ቤት አባላቱ አስገንዝበው፤ በማረሚያ ቤት ቆይተው ፍርድ ቤት ነፃ የሚላቸው ዜጎች የካሳ ክፍያ ሥርዓትን ለመዘርጋት በግልጽ በረቂቅ አዋጁ ማስቀመጥ እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡

ምክር ቤቱ፤ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የወንጀል ሕግ ሥነ-ስርአት እና የማስረጃ ሕግ ረቂቅ አዋጅ ፤ አዋጅ ቁጥር 1410/2018 አድረጎ በሁለት ተቃውሞ፤ በአብላጫ ድምጽ አጽድቋል፡፡

(መኩሪያ ፈንታ - ሕ/ተ/ም/ቤት)

ከፍተኛ የህግ ባለሙያደመወዝ 25,510ልምድ 4/2(LL.b,LL.m)Join👇https://t.me/ethiolawtips
29/03/2026

ከፍተኛ የህግ ባለሙያ
ደመወዝ 25,510
ልምድ 4/2(LL.b,LL.m)
Join👇
https://t.me/ethiolawtips

 #ሊታረም የሚችል ስህተት እስከሆነ ድረስ ስህተቱ ሊፈጠር የቻለው በተከራካሪ ወገኖች ይሁን በፍርድ ቤቱ ልዩነት ሳይደረግ ሊታረም የሚችል ስለመሆኑ እና በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 208 መሠረት የሚ...
29/03/2026

#ሊታረም የሚችል ስህተት እስከሆነ ድረስ ስህተቱ ሊፈጠር የቻለው በተከራካሪ ወገኖች ይሁን በፍርድ ቤቱ ልዩነት ሳይደረግ ሊታረም የሚችል ስለመሆኑ እና በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 208 መሠረት የሚሻሻል ሰለመሆኑ
#ከመነሻው ያቀረቡት ክስ ደሳለኝ ሀብቴ በሚል ክስ አቅርበው ነበር በሚል የስም ይታረምልኝ አቤቱታቸው ውድቅ የሚደረግበት የህግ ምክንያትጰየለም፡፡የሰበር መ/ቁ 245834 ጥቅምት 07 ቀን 2017 ዓ/ም
-----------
አመልካች በውሳኔው ላይ የተፈጠረው የስም ስህተት እንዲታረምላቸው የጠየቁ ሲሆን ስህተቱ ሊፈጠር የቻለው አመልካች እራሳቸው አስቀድመው ባቀረቡት ክስ ላይ ስማቸው ደሱ ሀብቴ መባል ሲገባው ደሳለኝ ሀብቴ በማለት በመጥቀሳቸው ነው፡፡
የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 208 አንድ ፍርድ ቤት በሰጠው ውሳኔ ላይ የተፈፀመ ስህተት ስለሚታረምበት ሁኔታ የሚደነግግ ሲሆን ስህተተቶቹም ባለማስተዋል የተፈጠሩ የጽህፈት ወይም የቁጥር ግድፈቶች ስለመሆናቸው ተመልክቷል፡፡ መሰል በድንጋጌው መሰረት ሊታረም የሚችል ስህተት እስከሆነ ድረስ ስህተቱ ሊፈጠር የቻለው በተከራካሪ ወገኖች ይሁን በፍርድ ቤቱ ልዩነት ሳይደረግ ሊታረም የሚችል ስለመሆኑ ይህ ሰበር ሰሚ ችሎት በሰ/መ/ቁ 236245 ከሰጠው ትርጉም መገንዘብ ይቻላል👇👇
https://t.me/ethiolawtips

Address

Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ኢትዮ - ሕግ/Ethio - Law posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to ኢትዮ - ሕግ/Ethio - Law:

Share

Category