Addis Kefeta - አዲስ ከፍታ

Addis Kefeta - አዲስ ከፍታ አዲስ ከፍታ a new hight is a new dimensions to uplift Ethiopians marching towards the new height of togetherness unification.

26/10/2023
የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈጻሚ በሠራተኞቻቸው  ወርቅ ተሸለሙ********ከዋና ሥራ አስፈጻሚ ክቡር አቶ ረሻድ ከማል በተጨማሪ ለአራቱም ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚዎች ከሰራተኛው...
05/10/2023

የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈጻሚ በሠራተኞቻቸው ወርቅ ተሸለሙ
********

ከዋና ሥራ አስፈጻሚ ክቡር አቶ ረሻድ ከማል በተጨማሪ ለአራቱም ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚዎች ከሰራተኛው እውቅና አግኝተዋል፡፡

ክቡር አቶ ረሻድ ከማል በኮርፖሬሽኑ ታሪክ እጅግ ስኬታማው እና የመሪነትን ገጽታ የተላበሱ ዋና ሥራ አስፈጻሚ በመሆን ከሰራተኞቻቸው ወርቅ ተሸልመዋል፡፡

የወርቅ ሽልማቱን የኢትዮጵያ ሰራተኞች ማህበራት ኮንፌዴሬሽን(ኢሠማኮ) ፕሬዜዳንት አቶ ካሳሁን ፎሌ ለክቡር ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ረሻድ ከማል ሠጥተዋል፡፡

አቶ ካሳሁን ፎሌ ኮርፖሬሽኑ ለአሰሪ ተቋማት ሞዴል ተቋም መሆኑን እና የኮርፖሬሽኑ መሪዎች የሰራተኛውን ጥቅም ለማስጠበቅ ላከናወኑት ውጤታማ ተግባርም ኢሰማኮ እውቅና እንደሚሰጠው ተናገረዋል፡፡

ክቡር ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ረሻድ ከማል በመልዕክታቸው ለተበረከተላቸው ሽልማት አመስግነው፣ ሠራተኞች በተገኘው ውጤት ሳይኩራሩ ለአገራዊ በልጽግና እድገት እንዲተጉ ሲሉም አሳስበዋል፡፡

ዋና ሥራ አስፈጻሚው መላ ሠራተኛውን ለለውጥ በማነሳሳት አገራዊ ለውጡን መነሻ በማድረግ ውጤታማ የተቋም ግንባታ በማካሔድ ትራፋማ ጠንካራ የልማት ድርጅት መፍጠር እንደቻሉ ተገልጿል፡፡

በክቡራ አቶ ረሻድ ከማል መሪነት ተቋሙ አጠቃላይ ሀብቱ 260 ቢሊየን የደረሰ ሲሆን ገቢው ከዘጠኝ እጥፍ በላይ ጭማሪ በማሳየት 2 ነጥብ 7 ቢሊየን ብር የኮርፖሬሽኑ ዓመታዊ ገቢ ሆኖ መመዝገቡም ነው የተነገረው፡፡

ተቋሙ እንደዋነኛ ሥራው አድርጎ የነበረው የቤት ማስተዳደር ሥራ ቢሆንም በቅጡ እንኳን የቤቶችን ቁጥር የማያውቅ የነበረው ኮርፖሬሽን ፣ በአሁኑ ሰዓት መረጃዎችን አደራጅቶ ፣ቤቶቹን ቆጥሮ ለእያንዳንዱ ቤት መላያ ታግ እስከለመለጠፍ መድረሱም የሳቸው አሻራ በጉልህ የታየበት መሆኑም ተጠቅሷል፡፡

ከ28 ዓመት በላይ ቆመ የነበረው ቤት ግንባታ እንደአዲስ በክቡር ዋና ሥራ አስፈጻሚው ተጀምሮ በአዲስ አበባ ከተማ ከ12 ሳይቶች በላይ ግንባታ በማስጀመር በአሀኑ ሰዓት ስደስት ሳይቶችን ማጠናቀቅ እንደታቻለም ሠራተኞቹ አንስተዋል፡፡

ከሀገር በቀሉ ኦቪድ ጋር በመጣመር በ18 ወራት አንድ መንደር መገንባት የሚያስችል ለአገር የተረፈ አቅምና ችሎታ በመፍጠር ረገድም የዋና ሥራ አስፈጻሚው ደርሻ ከፍተኛ መሆኑ ተነስቷል ፡፡

የራሱን ቤቶች እንኳ በአግባቡ ማደስ የማይችለው ተቋም ግንባታው ዘርፍ አውራ ሆኖ መውጣቱና የግንባታ ቴክኖሎጂዎችን እና ልምዶችን በመላ አገሪቱ ለማካፈልም ለማስፋፈትም የተመረጠ ብቁ ተቋም እንዲሆን ክቡር ዋና ሥራ አስፈጻሚው መስራታቸውም ነው ሠራተኞቹ ያነሱት፡፡

የኮንስትራክሽን ዘርፉን የግብዓት አቅርቦት የሚያቃልል በየዓመቱ ከ4 ቢሊየን ብር በላይ ገቢ የሚያስገኝ የኮንክሪት ውህድና የብሎኬት ማምረቻ ተከላ ሥራም ማስጀመራቸውም የዋና ሥራ አስፈጻሚው የመሪነት ብቃት የታየበት ሌላኛው የስኬት ማሳያ እንደሆነም ተገልጿል፡፡

ምክትል ሥራ አስፈጻሚዎችም የዋና ሥራ አሰፈጻሚው ራዕይና ግብ እንዲሳካ ላደረጉት የላቀ አስተዋጽኦ ከሠራተኞቹ እውቅና አግኝተዋል፡፡

ሰውነት  ይበልጣል!!በሃገራችንም ይሁን በአፍሪካ  ብዙም ያልተለመደ ነገር ነው፡፡በእርግጥ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትሩ እንደዚህ አይነት ልማድ እንዳላቸው ይታወቃል፡፡ የኢፌድሪ የህዝብ ተወካዮች ም...
30/07/2023

ሰውነት ይበልጣል!!

በሃገራችንም ይሁን በአፍሪካ ብዙም ያልተለመደ ነገር ነው፡፡

በእርግጥ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትሩ እንደዚህ አይነት ልማድ እንዳላቸው ይታወቃል፡፡

የኢፌድሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግስት ዋና ተጠሪ ሚኒስትር አቶ ተስፋዬ በልጅጌ አንድ ልማድ አላቸው ፤ ለከተማው ነዋሪ ግን አዲስ አይደለም። በተወለዱበትና ባደጉበት ከተማና ዞን በሚሄዱበት ጊዜ ማምሻውን በመውጣት በእግራቸው እየተዘዋወሩ አየር ይወስዳሉ፤ ከከተማው ነዋሪ ጋር ይገናኛሉ፤ የቀድሞ ጓደኞቻቸውን አግኝተው በአነስተኛ ቤቶች ሻይ ቡና ይላሉ፤ ሲላቸውም የመንገድ ዳር ጨዋታዎችን ጭምር ተጫውተው ወደ ቤታቸው ይገባሉ፡፡

እነዚህ ፎቶዎች በትናትናው እለት በሳውላ ከተማ መንገዶችና አካባቢዎች ሲዘዋወሩ የተወሰዱ ምስሎች ናቸው፡፡

ብዙ ሰው እሳቸውን እንደዚህ እንደማይገምታቸው ስላወቅሁ ነው ይህንን የከተብኩት ፤ነገር ግን ይህ የአመታት ልምዳቸው ነው፡፡

ይህ ብቻ ሳይሆን በጣም ተጫዋች ቀልድ አዋቂና ለመቅረብ የሚወደዱ መሆናቸውንም የጎፋ ህዝብ ይመሰክርላቸዋል፡፡

ቀለል ያሉ ሰው ናቸው ። ህዝቡም ሲያያቸው ቀለል አድርጎ ያወራቸዋል፤
ይቀርባቸዋል፤ ተስፍዬ እያለ አካባቢያቸውን ይከባል፡፡

ተወልደው ባደጉበት አካባቢ እንደ ልጅነታቸው መዞርና ከእኩዮቻቸው መገናኘትን መተው አይፈልጉም፡፡
ቀለል ብሎ መኖርን ይመርጣሉ።

አመራርነት ተራራነት አይደለም፤ አመራርነት የምትመራውን ከባቢ አየር ጓዳ ፤ሰፈርና አካባቢ ማወቅ ፤ሽታ ማወቅ ያስፈልጋል፡፡
በመጨረሻም አንተ ሁሌም ሰው ነህና👌 ስልጣንም ዘላለማዊ አይደለምና🙏

ለማንኛውም መልካም ልማድ ነው ብዬ የታዘብኩትን አካፈልኳችሁ!!

12/03/2023
09/03/2023

ኢትዮጵያዊነት የኢትዮጵያውያን የመተሣሠሪያ ማንነት ነው። ብዝኃ ባህል፣ ብዝኃ ቋንቋ፣ ብዝሃ እምነት፣ ብዝኃ አመለካከት ያለንን ኢትዮጵያውያን አንድ አድርጎ ለአንድ ሀገራዊ ዓላማ የሚያቆመን ዕሴት - ኢትዮጵያዊነት ነው። ለኢትዮጵያዊነታችን ብዝኃነታችን ማገሩ፣ ጀግንነታችን አጥሩ፣ አንድነታችን ዓምዱ፣ ነጻነታችን መንገዱ ነው ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር።

Itoophiyummaan walitti hidhata eenyummaa Itoophiyaanotaati. Duudhaan Itoophiyaanota danummaa aadaa, danummaa afaanii, danummaa amantaa, danummaa ilaalchaa qabnu tokko godhee kaayyoo biyyoolessaa tokkoof nudhaabu - Itoophiyummaadha.
Itoophiyummaa keenyaaf danummaan keenya dagalee, gootummaan keenya dallaa, tokkummaan keenya utubaa, walabummaan keenya daandii isaati. Itoophiyaan bara baraan haa jiraattu.

13/02/2023
22/01/2023

Address

Piyassa
Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Addis Kefeta - አዲስ ከፍታ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share

Category