Yonas Misganaw Law Office

Yonas Misganaw Law Office Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Yonas Misganaw Law Office, Lawyer & Law Firm, Addis Ababa.

26/05/2026
28/04/2026
08/02/2026

የአለም ጤና ድርጅትን 20 በመቶ በጀት የምትሸፍነዋ አሜሪካ ከድርጅቱ ነቅላ ወጥታለች። ሰንደቋም ከጀኔቫ ወርዷል።
አንድ አሜሪካዊ ሰው ሲናገር የሰማውት ነገር ያስገርማል። እንደሱ አባባል ከሆነ በአለም ጤና ድርጅት ውስጥ ተቀጥሮ የሚሰራ ከፍተኛ የጤና ባለሙያ እና አሜሪካን አገር ውስጥ በጤናው ዘርፍ ተቀጥሮ የሚሰራ ተመሳሳይ ባለሙያ (ሲቪል ሰርቫንት) መካከል ከፍተኛ ልዩነት አለ።
ለምሳሌ
1. በአለም ጤና ድርጅት ውስጥ ተቀጥሮ የሚሰራ ከፍተኛ ባለሙያ በአመት በአማካኝ የተጣራ 100 ሺ ዶላር ይከፈለዋል። አሜሪካን አገር ውስጥ ከፍተኛ የጤና ባለሙያ (ሲቪል ሰርቫንት) አመታዊ አማካኝ የተጣራ ደሞዙ 85 ሺ ዶላር ነው።
2. የአለም ጤና ድርጅት ሰራተኞች አብዛኞቹ ከደሞዛቸው ላይ ታክስ አይከፍሉም። 🤔
3. የአለም ጤና ድርጅት ሰራተኞች የልጆቻቸው የትምህርት ቤት ከፍያ በድርጅቱ ይሸፈናል። (በአመት በአማካኝ 20,000 ዶላር ይከፈላቸዋል)
4. የአለም ጤና ድርጅት ሰራተኞች ሌሎች ጥቅማጥቅሞችም አሏቸው።
የአለም ጤና ድርጅት እና መሰል የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ተቋማት ከትራምፕ ወደ ስልጣን መምጣት በሗላ ከፍተኛ የበጀት እጥረት እየገጠማቸው ነው። ተቋማቱ ከአባል አገራት በሚሰበሰብ መዋጮ በዋናነት ሰራተኞቻቸውን የተቀናጣ ኑሮ እያኖሩ ነው እንጅ ጠብ የሚል ስራ አይሰሩም የሚል ቅሬታ ይቀርብባቸዋል።
በእርግጥ በእኛ አገር ሳይቀር UN ውስጥ የሚሰሩ ሰራተኞች የኑሮ ሁኔታቸው ከልክ ያለፈ ቅንጦት የተሞላበት ነው። በዚህ ምክንያት እኛ አገር NGO ሲባል ሰው አእምሮው ውስጥ የሚመጣው ከፍተኛ ደሞዝ ወይም የቅንጦት ህይወት ነው።
ይህ ግን ስህተት ነው። ሲጀመር የተባበሩት መንግስታት ድርጅት NGO አይደለም።
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አሁን ደግሞ በትራምፕ የሰላም ቦርድ የመሰልቀጥ እድሉ እየሰፋ ይመስላል። የትራምፕ የሰላም ቦርድ ይህንን ድርጅት ጠቅልሎ ጡረታ ቢያስወጣው ጥሩ ነው።
Yonas MG

25/01/2026
11/01/2026

የጠበቆች ሒሳብ መዝገብ የመያዝ ጉዳይ የማይቀር እየሆነ ነው።

የፌዴራል ጠበቆች ማህበር የጠበቆችን ተቀናሽ የሚደረጉ ወጭዎች ዝርዝር በተመለከተ ጥናት እያደረገ መሆኑንና ለሚመለከተው አካል ለማቅረብ በዝግጅት ላይ መሆኑን ጠበቃ Yonas Woldeyes ነገሮናል።
ነገርየው በጣም ጠቃሚ ነው በመሆኑም ሁሉም ጠበቃ የተዘጋጀውን መጠይቅ በደንብ ሞልቶ ለማህበሩ መላክ አለበት። መጠይቁን ለመሙላት ይህንን ሊንክ ይጠቀሙ።
https://forms.office.com/pages/responsepage.aspx?id=k2E77e7UKkuF-nNdwUfdFl1C72EucyRKi74IK3Lxoo1UMlZZR0E5SzhaOVM3Nk8zNUJXS0k4OUZFMC4u&fbclid=IwZXh0bgNhZW0CMTEAc3J0YwZhcHBfaWQPMjc1MjU0NjkyNTk4Mjc5AAEe9bhLyJTxx0dNCMViuAoFDV_OcflgWWNC0WmXU1yaM6D0IrQO2E8eG1QOLM4_aem_IEbvvytO3zmerGfIZxx-Bw&route=shorturl

ለምሳሌ የሚከተሉት ወጭዎች የግድ ተቀናሽ መደረግ ይገባቸዋል ብየ አስባለሁ።

1. የራይድ ትራንስፓርት፣ መኪና ያላቸው የነዳጅ እና ጥገና ወይም አዲስ መኪና (ኮድ 2 የሆኑትን ጨምር) ግዥ፣ኢንሹራንስ እና ተያያዥ ወጭዎች

2. የቢሮ ኪራይ፣ የቢሮ ፈርኒቸር፣ ስቴሽነሪ መሳሪያዎች፣ የቢሮ ፅዳት፣ ጥገና፣ ቢሮ ውስጥ የሚዘጋጁ ሻይ፣ቡና፣ ውሀ እና የመሳሰሉ ወጭዎች

3. ደረጃውን የጠበቀ ሙሉ ሱፉ ከነጫማው ቢያንስ በአመት ሁለት ጊዜ እና ከዚህ ጋር የተያያዙ የንፅህና መጠበቂያ ወጭዎች

4. ሙያውን ለማሳደግ የሚወስዳቸው የአገር ውስጥ ወይም የውጭ አገር ስልጠና፣ የቢዝነስ ስብሰባና መሰል ወጭዎች

5. ጠበቃው ከያዘው ጉዳይ ጋር በተያያዘ ማስረጃ ለማግኘት የሚያወጣቸው ወጭዎች። ለምሳሌ የልዩ ባለሙያዎች አስተያየት ወይም ምክር፣ የፓሊስ ሪፓርት፣ የህክምና ሪፓርት፣ የአስተዳደር ተቋማት ሪፓርት፣ የምስክሮች ትራንስፓርትና መሰል ወጭዎች፣ የሰነድ ማረጋገጥ ወጭዎች

6. ኮፒ፣ ፕሪንት፣ ትርጉም፣ ፀሀፊ ወዘተ

7. ኢንተርኔት፣ ስልክ እና ተያያዥ ወጭዎች

8. ሰራተኛ ወይም ጉዳይ አስፈፃሚ ካለው የእነሱ ደሞዝና ሌሎች ወጭዎች

9. ደረጃውን የጠበቀ ካባ ቢያንስ በአመት አንድ ጊዜ

10. ላፕቶፕ እና የስራ ስልክ ግዥ እና ጥገና

11. የሙያ ፈቃድ እድሳት፣ የሙያ ማህበራት የአባልነት ክፍያ ወጭዎች

12. የነፃ ጥብቅና አገልግሎት ወጭዎች ግምት

13. የሕግ ሶፍትዌሮች ግዥ ወይም ክፍያ ለምሳሌ የሌጋል ቴክ እና የመሳሰሉ ሰብስክሪብሽን ክፋያዎች። ለስራው የሚጠቅሙ የሚከፈልባቸው ዙም፣ቲም፣ወርድ እና የመሳሰሉ ወጭዎች

14. የቢዝነስ ካርድ ህትመት፣ ዌብሳይት ማበልፀግና ማስተዳደር ወጭዎች

15. ከደንበኛው ጋር በሚኖረው ቀጠሮ የሚያወጣቸው ከአልኮል ውጭ የሆኑ ሻይቡና፣ምሳ ወይም እራት እና ተያያዥ ወጭዎች (የራሱን የጠበቃውን ወጭ ላይጨምር ይችላል)

16. የባንክ አገልግሎት ክፍያዎች፣ ከስራው ጋር በተያያዘ ለተበደረው ብድር የሚከፈሉ የብድር ክፍያዎች ከነወለዳቸው።

17. ደረሰኝ ሊቀርብባቸው የማይችሉ ግን ማስረጃ ያላቸው ሌሎች ጥቃቅን ወጭዎች

18. ......

11/01/2026

Address

Addis Ababa

Opening Hours

Monday 09:00 - 17:00
Tuesday 09:00 - 17:00
Wednesday 09:00 - 17:00
Thursday 09:00 - 17:00
Friday 09:00 - 17:00
Saturday 09:00 - 13:00

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Yonas Misganaw Law Office posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Yonas Misganaw Law Office:

Shortcuts

Share