Tsegaye Demeke - Lawyer

Tsegaye Demeke - Lawyer በፍትሐብሔርና በወንጀል ጉዳዮች የማማከርና የጥብቅና አገልግሎት እንሰጣለን፡፡ We provide Advocacy and Consultancy Services.
(2)

ይግባኝ ማስፈቀጃ /ጊዜ ካለፈ በኋላ የሚቀርብ አቤቱታ/=================በህጉ የተቀመጠው የይግባኝ ማቅረቢያ ጊዜ ካለፈ በኋላ ይግባኝ ለማቅረብ እንዲፈቀድ የሚቀርብ አቤቱታ ነው።አንድ...
27/04/2026

ይግባኝ ማስፈቀጃ /ጊዜ ካለፈ በኋላ የሚቀርብ አቤቱታ/
=================
በህጉ የተቀመጠው የይግባኝ ማቅረቢያ ጊዜ ካለፈ በኋላ ይግባኝ ለማቅረብ እንዲፈቀድ የሚቀርብ አቤቱታ ነው።
አንድ ፍ/ቤት ይግባኝ ማቅረቢያ ጊዜው ያለፈበት ምክንያት በቂ መሆኑን ሲረዳ ይግባኙ እንዲቅርብ ሊፈቅድ እንደሚገባ በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 326/1/ ስር ተመልክቷል፡፡ በመሆኑም ፍ/ቤቱ የቀረበለት ምክንያት በቂ መሆን አለመሆኑን በአግባቡ ሊመረምረው ይገባል፡፡ በእርግጥ በቂ ምክንያት የሚባሉት ነገሮች ሕጉ ዘርዝሮ ያላስቀመጣቸው በመሆኑ ለመወሰን አስቸጋሪ መሆኑ ግልጽ ነው፡፡ በመሆኑም የምክንያቱ በቂ መሆን አለመሆን በእያንዳንዱ ጉዳይ ከሚቀርቡ ፍሬ ነገሮች ጋር ተገናዝበው ሊመዘኑ ይገባል፡፡
ሰ/መ/ቁ. 38145 ቅጽ 8፣ ፍ/ስ/ስ/ህ/ቁ. 326/1/
በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 324/1/ መሠረት ለአንድ ፍርድ ቤት መዝገብ ሹም የተሰጠው ሥልጣን ይግባኝ ማቅረቢያ ጊዜ ማለፍ አለማለፉን በመመልከት ይግባኝ መዝገቡ እንዲከፈት ማድረግ ሲሆን ይግባኙ ጊዜውን ጠብቆ ያልቀረበ ከሆነ ማመልከቻውን መመለስ፣ ማመልከቻው የተመለሰበት ወገን የይግባኝ ጊዜው ያለፈበት ሕጋዊ ምክንያት ካለው ማስፈቀጃ አቤቱታውን በማቅረብ ይኸው ጊዜው ያለፈበት ይግባኝ ለማቅረብ እንዲፈቀድለት ራሱን የቻለ አቤቱታ አቅርቦና ይህ መዝገብ ተከፍቶ ጉዳዩ ለችሎት ቀርቦ ችሎቱ የይግባኝ ማስፈቀጃውን በመመርመር በፍ/ብ/ስ/ስ/ሕ/ቁ. 325 እና 326 መሠረት ተገቢ ነው ያለውን ትእዛዝ የሚሰጥበት ነው፡፡
የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 324/1/ ከፍ/ብ/ስ/ስ/ሕ/ቁ. 325 እና 326 ድንጋጌዎች ጋር አንድ ላይ ሲነበቡ የመዝገብ ቤት ሹም ጊዜው ያለፈበት ይግባኝ ለችሎት እንዲቀርብ የመፍቀድ ስልጣን የሌለው መሆኑን የሚያሳዩ ሲሆን ፋይሉ ተከፍቶ ቀርቦ ከሆነም ችሎቱ ጉዳዩን መርምሮ ይግባኙ የቀረበው ጊዜው ከአለፈ በኋላ ነው በማለት መዝገቡን ከመዝጋት የሚከለክለው አይደለም፡፡
ሰ/መ/ቁ. 61843 ቅጽ 11፣ ፍ/ስ/ስ/ህ/ቁ. 324-326

ማን ያሸንፋል? በትክክል የገመቱ 3 ሰዎች ካርድ ይሸለማሉ!
27/04/2026

ማን ያሸንፋል? በትክክል የገመቱ 3 ሰዎች ካርድ ይሸለማሉ!

በግል ተሰሚነት መነገድ የሙስና ወንጀል ➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖የሙስና ወንጀሎች አዋጅ ቁጥር 881/2007 አንቀጽ 29 & 16 ላይ እንደተመለከተው በግል ተሰሚነት መነገድ የሙስና ወንጀል የሚባለው:...
27/04/2026

በግል ተሰሚነት መነገድ የሙስና ወንጀል
➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖
የሙስና ወንጀሎች አዋጅ ቁጥር 881/2007 አንቀጽ 29 & 16 ላይ እንደተመለከተው በግል ተሰሚነት መነገድ የሙስና ወንጀል የሚባለው:-
📌ማንኛውም ሰው የመንግስት ወይም የህዝባዊ ድርጅት ሠራተኛ ባለመሆኑ በዚህ አዋጅ በአንቀጽ 16 ለመንግስት ወይም ለህዝባዊ ድርጅት ሠራተኛ የተደነገገው የማይመለከተው ቢሆንም፣ ያለውን ወይም እንዳለው ያስመስለውን ተሰሚነት በመጠቀም በአንድ የመንግስት ወይም የህዝባዊ ድርጅት ሠራተኛ ብቻ ሊሰጥ የሚችለውን ልዩ መብት ወይም ጥቅም ለሌላ ሰው ለማስገኘት ሲል ከሌላው ሰው ገንዘብ፣ ስጦታ፣ እጅ መንሻ ወይም ሌላ ጥቅም የጠየቀ፣ የተቀበለ ወይም እነዚህን በተመለከተ የተስፋ ቃል የተቀበለ እንደሆነ፣ ከአንድ ዓመት በማያንስ ቀላል እስራት እና ከሦስት ሺህ ብር በማያንስ መቀጮ ይቀጣል፡፡
📌በአንድ የመንግስት ወይም የህዝባዊ ድርጅት ሠራተኛ ብቻ ሊሰጥ የሚችለውን ልዩ መብት ወይም ጥቅም ለራሱ ለማግኘት ወይም ለሌላ ሰው ለማስገኘት በማሰብ ገንዘብ፣ ስጦታ እጅ መንሻ ወይም ሌላ ጥቅም የሰጠ ወይም ለመስጠት የተስማማ ከአንድ ዓመት በማያንስ ቀላል እስራት እና ከሦስት ሺህ ብር በማያንስ መቀጮ ይቀጣል፡፡
📌ማንኛውም የመንግስት ወይም የህዝባዊ ድርጅት ሠራተኛ በሥራው ምክንያት ባለው ወይም አስመስሎ ባቀረበው ተሰሚነት፡-
አግባብ ባለው ባለስልጣን ወይም ኃላፊ ተወስኖ የሚሰጥ የሥራ ደረጃ፣ ሹመት፣ ሥራ፣ ሽልማት፣ የአገልግሎት ዋጋ፣ ልዩ ችሮታ፤ በቁጥጥሩ ወይም በአመራሩ ሥር በሚገኙ ባለስልጣኖች ኃላፊዎች ወይም የአስተዳደር ክፍሎች የሚደረግ ውል፣ የንግድ ስምምነት፣ የሥራ ጨረታ፣ የዕቃ ማቅረብ ውል፣ ወይም ሌላ ጥቅም ለማግኘት በማሰብ ለማንኛውም የመንግስት ወይም የህዝባዊ ድርጅት ሠራተኛ ስጦታ ወይም ሌላ ጥቅም የሰጠ ወይም ለመስጠት የተስማማ አንደሆነ ከአንድ ዓመት በማያንስ ቀላል እስራት እና ከሦስት ሺህ ብር በማያንስ መቀጮ ይቀጣል፡፡
📌በምርጫ ላይ የሚሰጥ መደለያ
ማንኛውም ሰው የመምረጥ ወይም የመመረጥ መብት ያለው ሌላ ሰው በመብቱ በተወሰነ መንገድ እንዲጠቀም ወይም መብቱን እንዲተው ለማድረግ በቀጥታ ወይም በተዘዋዋሪ መንገድ ገንዘብ ወይም ማናቸውም ሌላ ዓይነት ጥቅም የሰጠ፣ ወይም ለመስጠት ቃል የገባ እንደሆነ፣ ከአምስት ዓመት በማይበልጥ ፅኑ አስራት እና ከአምስት ሺህ ብር በማይበልጥ መቀጮ ይቀጣል፡፡
📌እንዲጠቀምበት ወይም በአንድ በተወሰነ መንገድ እንዲጠቀምበት ወይም ሳይጠቀምበት እንዲቀር ገንዘብ ወይም ማናቸውም ሌላ ዓይነት ጥቅም የተቀበለ ወይም ለመቀበል የተስማማ ማንኛውም ሰው ከአንድ ዓመት በማያንስ ቀላል እስራት እና ከሦስት ሺህ ብር በማያንስ መቀጮ ይቀጣል፡፡

ከባድ የእምነት ማጉደል የሙስና ወንጀል ==================በአዋጅ ቁጥር 881/2007 አንቀጽ 31 መሠረት1. ማንኛውም የመንግስት ወይም የህዝባዊ ድርጅት ሠራተኛ ተገቢ ያልሆነ ብል...
27/04/2026

ከባድ የእምነት ማጉደል የሙስና ወንጀል
==================
በአዋጅ ቁጥር 881/2007 አንቀጽ 31 መሠረት
1. ማንኛውም የመንግስት ወይም የህዝባዊ ድርጅት ሠራተኛ ተገቢ ያልሆነ ብልፅግና ለራሱ ለማግኘት ወይም ለሌላ ሰው ለማስገኘት በማሰብ የመንግስት ወይም የህዝባዊ ድርጅት የሆነውንና ለአንድ ለተወሰነ አገልግሎት ወይም በአደራ የተሰጠውን ዋጋ ያለውን ነገር ወይም ጥሬ ገንዘብ በሙሉ ወይም በከፊል ለራሱ ያደረገ፣ ወይም ለሌላ ሰው ያደረገ፤ የወሰደ፣ ያስወሰደ፣ የሰወረ፣ ወይም ለራሱ ወይም ለሌላ ሰው አገልግሎት ያዋለ ወይም ይህን የመሳሰለውን ማናቸውንም አድራጎት የፈጸመ እንደሆነ ከሦስት ዓመት እስከ ሰባት ዓመት በሚደርስ ፅኑ እስራት እና ከአሥር ሺህ ብር እስከ ሃምሳ ሺህ ብር በሚደርስ መቀጮ ይቀጣል።
2. የተገኘው ጥቅም ከፍተኛነት፣ የጥፋተኛው የሥልጣን ወይም የኃላፊነት ደረጃ ወይም በመንግስት፣ በህዝባዊ ድርጅት፣ በህዝብ ወይም በግለሰብ ጥቅም ላይ የደረሰው ጉዳት ከፍተኛነት በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (1) መሠረት የተፈጸመውን ወንጀል ከባድ አድርጎት እንደሆነ፣ ቅጣቱ ከሰባት ዓመት እስከ ሃያ አምስት ዓመት በሚደርስ ፅኑ እስራት እና ከሃምሳ ሺህ ብር እስከ አንድ መቶ ሺህ ብር በሚደርስ መቀጮ ይሆናል፡፡
3. ለዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (1) እና (2) አፈጻጸም፡-
ሀ/ተከሳሹ በእምነት እንዲሸጥ ወይም እንዲገዛ ወይም እንዲለውጥ ወይም ለተወሰነ አገልግሎት እንዲያውል የተሰጠውን ገንዘብ ወይም ዕቃ ወይም ዋጋ ያለውን ነገር በተባለው መሠረት ፈፅሞ በምትኩ ያገኘው ገንዘብ፣ ወይም ዕቃ ወይም ዋጋ ያለው ነገር የሌላ ሰው እንደሆነ ይቆጠራል፡፡
ለ/ ተከሳሹ ሲጠየቅ በእምነት ወይም በአደራ የተሰጠውን ገንዘብ ወይም ዕቃ ወይም ዋጋ ያለውን ነገር ለመመለስ ወይም ለመክፈል ወይም ዕቃው ያለበትን ሁኔታ ለማሳየት ወይም ለተገቢው አገልግሎት ያዋለው መሆኑን ለማስረዳት ካልቻለ ንብረቱን ለራሱ ወይም ለሌላ ሰው ያልተገባ ጥቅም የማዋል አሳብ እንዳለው ይቆጠራል።
4. ለዚህ አንቀፅ አፈፃፀም ሲባል “እምነት ማጉደል” ማለት ተገቢ ያልሆነ ብልፅግና ለማግኘት ወይም ለሌላ ሰው ለማስገኘት በማሰብ የሌላ ሰው የሆነውንና ለአንድ ለተወሰነ አገልግሎት ወይም በአደራ የተሰጠውን ገንዘብ ወይም ዕቃ ወይም ዋጋ ያለውን ነገር ወይም ጥሬ ገንዘብ በሙሉ ወይም በከፊል ለራሱ ወይም ለሌላ ሰው የማድረግ የመውሰድ፣ የማስወሰድ፣ የመሰወር፣ ወይም ለራሱ ወይም ለሌላ ሰው አገልግሎት የማዋል፣ ወይም ይህን የመሳሰለውን ማናቸውም እምነት የማጉደል ወንጀልን ያካትታል።

©℗®

https://t.me/Consultancy2012
Call us for
©Tsegaye Demeke - Lawyer

"ያላግባብ ጉዳይን ማጓተት"  የሙስና ወንጀል መሆኑን ያውቃሉ?================== “የሙስና ወንጀሎች አዋጅ ቁጥር 881/2007” አንቀጽ 18 ላይ እንደተመለከተው:- ማንኛውም የመን...
27/04/2026

"ያላግባብ ጉዳይን ማጓተት" የሙስና ወንጀል መሆኑን ያውቃሉ?
==================
“የሙስና ወንጀሎች አዋጅ ቁጥር 881/2007” አንቀጽ 18 ላይ እንደተመለከተው:-
ማንኛውም የመንግስት ወይም የህዝባዊ ድርጅት ሠራተኛ በኃላፊነቱ ወይም በሥራው ምክንያት በቀረበለት ጉዳይ ላይ ጥቅም ካለው ማንኛውም ሰው በቀጥታ ወይም በተዘዋዋሪ ጥቅም ለማግኘት በጉዳዩ ላይ ጥቅም ያለውን ማንኛንውም ወገን ወይም ለመጥቀም ወይም ለመጉዳት ሲል ከህግ፣ ከስራ ደንብ፣ ከመመርያ ወይም ከተለመደው አሰራር ውጪ ያለበቂ ምክንያት ያልወሰነ፣ ያዘገየ ወይም ባለጉዳይን ያጉላላ እንደሆነ እንደነገሩ ሁኔታ በመቀጮ ወይም በቀላል እስራት ወይም ከአምስት ዓመት በማይበልጥ ፅኑ አስራት እና ከአምስት ሺህ ብር በማይበልጥ መቀጮ ይቀጣል፡፡

ትዕዛዝ፣ ብይን፣ ፍርድና ውሳኔ===================ትእዛዝ (order ) ,,,ብይን ( Ruling ) ,, ፍርድ (Judgement ),,ዉሳኔ ( Decision /Decree )እነዚህ ...
27/04/2026

ትዕዛዝ፣ ብይን፣ ፍርድና ውሳኔ
===================
ትእዛዝ (order ) ,,,ብይን ( Ruling ) ,, ፍርድ (Judgement ),,ዉሳኔ ( Decision /Decree )

እነዚህ አራት ቃላት በሕግና በፍርድ ቤት የሥራ ሂደት ዉስጥ ተመሳሳይ ቢመስሉም የራሳቸው የሆነ የተለየ የሕግ ትርጉምና ደረጃ አላቸው ,,,,,,,,

1, ትእዛዝ ( Order )
" ትእዛዝ " ማለት አንድ የፍርድ ቤት ክርክር ከመጀመሩ በፊት ወይም በሂደት ላይ እያለ ፍርድ ቤቱ አንድን ነገር እንዲደረግ ወይም እንዳይደረግ የሚሰጠው መመሪያ ነው ።
ባህሪው
ጉዳዩ መዝጋት ወይም መጨረስ ሳይሆን ለሂደቱ መቀላጠፍ የሚሰጥ ነው ።
ለምሳሌ :
"ይህ ንብረት ለጊዜው እንዳይሸጥ እንዳይለወጥ ታግዶል " ወይም " ተከሳሽ ለቀጣይ ቀጠሮ ምስክሮች ይዞ ይቅረብ " የሚሉ መመሪያዎች ትእዛዝ ይባላል ።

2, ብይን ( Ruling )
" ብይን" የሚሰጠው በክርክሩ ሂደት ዉስጥ ለሚነሱ መከራከሪያ ነጥቦች ( Interlocutory matters ) ምላሽ ለመስጠት ነው ።
ባህሪው
ዋናው የክርክር ዉጤት ( ማን አሸነፈ ? ማን ተሸነፈ ?) ሳይሆን በመሀል የሚነሱ የህግ ክርክሮችን ለመወሰን ነው ።
ለምሳሌ ;
" ፍርድ ቤቱ ይህንን ክስ ለማየት ስልጣን አለው / የለዉም " ወይም " ክሱ በይርጋ ይታገዳል / አይታገድም " የሚለው ዉሳኔ ብይን ይባላል ።
ብይን ብዙ ጊዜ ክርክሩን አያበቃዉም ይልቁንም ሂደቱን ይቀጥላል ።

3, ፍርድ ( Judgement )
" ፍርድ " ማለት ፍርድ ቤቱ የቀረበለትን ማስረጃዎች መርምሮ ; የግራ ቀኙን ክርክር ሰምቶና መዝኖ የሚሰጥ የመጨረሻ ድምዳሜ ነው ።
ባህሪው
ፍርድ ቤቱ በጉዳዩ ላይ የደረሰበትን የሐቅና የህግ ድምዳሜ በዝርዝር የሚያስቀምጥበት ሰነድ ነው ።
ለምሳሌ ;
" ከሳሽ የንብረቱ ባለቤት መሆናቸውን ፍርድ ቤቱ አረጋግጧል "
የሚለው ሰነድ ፍርድ ነው

4,ዉሳኔ ( Decision /Decree )
" ዉሳኔ " በፍርድ ላይ ተመስርቶ የሚሰጥ ተግባራዊ ትዕዛዝ ነው ።
በፍርድ መደምደሚያ ላይ " በዚህ መሠረት ",,,,,,,,,ተብሎ የሚቀመጠው ነጥብ ነው ።
ባህሪው
በፍርድ የተረጋገጠውን መብት ወይም ግዴታ ለይቶ የሚያስቀምጥና ተፈፃሚ የሚሆን ነው ።
ለምሳሌ ;
ፍርዱ " ከሳሽ ባለቤት ናቸው " ካለ,,,,,
ዉሳኔዉ " ተከሳሽ ቤቱን ለከሳሽ በአንድ ወር ጊዜ ዉስጥ ያስረክቡ" የሚለው የመጨረሻ ትዕዛዝ ነው ።

ማጠቃለያ / ልዩነት
/ቃል/ ትኩረት / መቼ ይሰጣል ?

# ትእዛዝ
ለስራ ሂደት መመሪያ መስጠት
በማንኛውም ጊዜ
# ብይን
በመሀል ለሚነሱ መከራከሪያዎች መልስ መስጠት
በሂደት ላይ
# ፍርድ
ማስረጃ መዝኖ ድምዳሜ ላይ መድረስ
በክርክሩ ማብቂያ
# ዉሳኔ
መብትና ግዴታን ለይቶ መወሰን
በፍርድ መጨረሻ

ምንጭ:- ጠበቃ እስከዳር አወቀ

27/04/2026

''የወር አበባ የተፈጥሮ እንጂ የቅንጦት አይደለም!''

ወቅቱን ያልጠበቀ የሞዴስ (Sanitary Pads) ዋጋ መጨመር በብዙ እህቶቻችን ጤና እና ስነ-ልቦና ላይ ከፍተኛ ጫና እየፈጠረ ይገኛል።

የወር አበባ ተፈጥሯዊ ሂደት እንጂ ምርጫ አይደለም፤ በመሆኑም የንጽህና መጠበቂያዎች ዋጋ ተመጣጣኝ መሆን የግድ ይላል።

የሚመለከታችሁ አካላትና ነጋዴዎች የሴት እህቶቻችንን እንግልት በመረዳት የዋጋ ማስተካከያ እንድታደርጉ ጥሪያችንን እናቀርባለን።

የኑዛዜ መሻር፤ የኑዛዜ መሻር ውጤት፤ የኑዛዜ ውድቅ መሆን (Lapse of will)==========================የኑዛዜ ተፈፃሚነት በተዛዡ ፍላጐት ላይ የተመሰረተ ነው፡፡ ኑዛዜ አ...
27/04/2026

የኑዛዜ መሻር፤ የኑዛዜ መሻር ውጤት፤ የኑዛዜ ውድቅ መሆን (Lapse of will)
==========================
የኑዛዜ ተፈፃሚነት በተዛዡ ፍላጐት ላይ የተመሰረተ ነው፡፡ ኑዛዜ አድራጊው ሰው በፈለገው ጊዜ ኑዛዜ የማድረግ፣ የመሻር ወይም የመለወጥ መብት አለው፡፡ አንድ ተናዛዥ የተናዘዘውን ኑዛዜ ምንም አይነት ምክንያት ሳያስፈልገው መሻር ይችላል፡፡ ተናዛዡ ይህን የሚያደርገው ኑዛዜውን ባደረገው ፎርም ነው፡፡ ይህ ማለት ኑዛዜውን ያደረገው በራሱ በተናዛዡ ጽሁፍ ከሆነ በዚያው ፎርም፤ በግልጽ በሚደረግ ኑዛዜ ከሆነ በዚያው ፎርም ኑዛዜውን መሻር ይችላል፡፡ ይህም የመሻር ሙሉ የኑዛዜ ቃሉን ወይም ደግሞ የኑዛዜውን የተወሰነ ቃል ብቻ ሊሆን ይችላል፡፡

ተናዛዡ ኑዛዜውን ለመሻር ወይም ለመለወጥ ያለውን ሀሳብ በግልጽ በሚያሳይ መልክ ኑዛዜውን በማንኛውም ጊዜ በማጥፋት፣ በመቅደድ ወይም አነጋገሩን በመሰረዝ የኑዛዜውን ቃል ለመለወጥ ይችላል፡፡ እንዲ በሚሆንበት ጊዜ ተቃራኒ የሆነ ማስረጃ ካልቀረበ በቀር ኑዛዜውን ራሱ ፈልጐ እንደሻረው ይቆጠራል፡፡ (ፍ/ሕ/ቁ 900)

የኑዛዜ መሻር ውጤት

ኑዛዜውን ተናዛዡ በራሱ ፍላጐት ከሻረው የተናዘዘው ቃል ቀሪ ይሆናል፡፡ ይህም ማለት ተናዛዡ ኑዛዜውን በሙሉ ከሻረ ኑዛዜው ቀሪ ሆነ ማለት ነው፡፡ በከፊል የኑዛዜውን ቃል የሻረው ከሆነ ይህ የተሻረው ቃል ቀሪ ሆኖ የተቀበረው የኑዛዜ ቃል ተፈፃሚ ይሆናል፡፡ በፍ/ብ/ሕ/ቁ 901/1/ እንደተገለፀው ተቃራኒ ቃል ከሌለ በቀር ያንዱ ኑዛዜ መሻር አስቀድሞ ተደርጐ የነበረውን ኑዛዜውን ቃል አያፀድቀውም፡፡

የኑዛዜ ውድቅ መሆን (Lapse of will)

የኑዛዜ ውድቅ መሆን ማለት የኑዛዜውን መፈፀም አቅም ከተናዡ ፍቃድ ውጭ በሕግ ኑዛዜው ቀሪ የሚሆንበት ሁኔታ ነው፡፡ የኑዛዜው ውድቅ መሆን ምክንያቶች እንደየ ኑዛዜ ፎርሟች ይለያያል፡፡ በቃል የተደረገ ኑዛዜው ኑዛዜው ከተደረገ ከሶስት ወር በኋላ ተናዛዡ በሕይወት ካለ ኑዛዜው ውድቅ ይሆናል፡፡ ኑዛዜው በተናዛዡ ጽሑፍ የተደረገ ከሆነ ኑዛዜው በተደረገ በሰባት አመት ጊዜ ውስጥ ለማዋዋል ሥልጣን በተሰጠው ሰው ወይም በፍርድ ቤት መዝገብ ቤት ዘንድ ያልተቀመጠ እንደሆነ ውድቅ ይሆናል፡፡

ኑዛዜው ከተደረገ በኋላ ልጅ መውለድ ኑዛዜውን ውድቅ ያደርገዋል፡፡ የተናዛዡ ባለቤት ወይም በምትክነት ፈቅዶ ለወራሽነት የቀረበ ወደታች የሚቆጠር ተወላጅ ከተወለደ ኑዛዜው ውድቅ ይሆናል፡፡ ከኑዛዜ በኋላ የተወለደን ልጅ ፈቃድ ለማግኘት በተሻሻለው የቤተሰብ ሕግ አንቀጽ 216 መሠረት በሞግዚቱ ወይም በንብረት አስተዳዳሪ ተወካይነት መሆኑ ተገልጿል፡፡ ተናዛዡ ልጅ የተፀነሰ መሆኑን እያወቀ ኑዛዜውን ያደረገ እንደሆነ ወይም ተናዛዡ ጉዳዩን ቢያውቅ ኑሮ ስጦታውን አያሰቀርም ነበር ተብሎ የሚገመት የሆነ እንደሆነ ዳኞች የኑዛዜ ስጦታዎች በሙሉ ወይም በከፊል እንደፅኑ ለማድረግ ይችላሉ፡፡ ነገር ግን ተናዛዡ የወለደው ልጅ ወይም ወደታች የሚቆጠር ተወላጅ ቢያንስ የውርሱን ሁለት ሶሶተኛ ሁሌም (በማንኛውም ሁኔታ) ማግኘት አለበት (በፍ/ብ/ሕ/ቁ 905) ፡፡

ሌላው ኑዛዜን ውድቅ የሚያደርገው ባል ለሚስት በኑዛዜ ስጦታ ሰጥቶ ወይም ሚስት ለባሏ በኑዛዜ ሰጦታ ስጥታ እያለ ጋብቻው ከሞተ ውጭ በሆነ ምክንያት የፈረሰ እንዲሆን ነው፡፡

በኑዛዜ ስጦታ የተደረገለት ሰው ከሰጭው አስቀድሞ ከሞተ፣ ስጦታውን ለመቀበል ካልቻለ ወይም ደግሞ ለመቀበል ፈቃዱን ካልገለፅ የኑዛዜው ስጦታም እንደውርስ ሁሉ ውድቅ ይሆናል፡፡ ይህ ማት የኑዛዜ ስጦታ የተደረገለት ሰው ተናዛዡን ቀድሞ ከሞተ (በሕይወት ያለመሆን)፣ ለወራሽነት የማይገባ መሆን እና ኑዛዜውን ለመቀበል ፍቃደኛ አለመሆን የስጦታ ኑዛዜውን ውድቅ ያደርገዋል፡፡

የኑዛዜ ስጦታ የተደረገለት ሰው ከተናዛዡ በፊት ከሞተ የሱ ምትክ ሊወርስ (ስጦታውን ሊቀበል) የሚችልበት አጋጣሚ አለ፡፡ይህም፡-

1ኛ. ተናዛዡ ጠቅላላ ሀቡቱን የሰጠው እንደሆነ ወይም
2ኛ. ልዩ ስጦታ በሆነ ጊዜ ተቀባዩ ባለመኖሩ ሀብቱ ለመንግስት የሚተላለፍ ሲሆን ነው፡፡

የልዩ ስጦታ ዘመዶች የሚገቡት የናዛዡ እስከ አራተኛ ደረጃ የሚቆጠር ዘመዶች ከሌሉ ብቻ ነው፡፡

👉በምርጫ ሂደት የወንጀል ተጠያቂነት የሚያስከትሉ ጥፋቶች‼️📌የአንድ አገር ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ ማረጋገጫ ብሎም ሕዝብ የሥልጣን ባለቤትነቱን የሚያረጋግጥበት እና የወደፊት ዕጣ ፈንታውን...
26/04/2026

👉በምርጫ ሂደት የወንጀል ተጠያቂነት የሚያስከትሉ ጥፋቶች‼️

📌የአንድ አገር ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ ማረጋገጫ ብሎም ሕዝብ የሥልጣን ባለቤትነቱን የሚያረጋግጥበት እና የወደፊት ዕጣ ፈንታውን የሚወስንበት ወሳኝ የፖለቲካ መድረክ ነው። ይሁን እንጂ ይህ ሂደት ትርጉም ያለው፣ ሰላማዊ ብሎም ፍትሐዊ ሊሆን የሚችለው በምርጫው ሂደት የሚሳተፉ ሁሉም አካላት ሕጋዊ ግዴታቸውን ሲወጡና ከተከለከሉ ተግባራት ሲቆጠቡ ብቻ ነው። በኢትዮጵያ የምርጫ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባና የምርጫ ሥነ-ምግባር አዋጅ ቁጥር 1162/2011 በአዋጅ ቁጥር 1394/17 እንደተሻሻለው የምርጫውን ሂደት የሚያሰናክሉ ተግባራት እና የሚያስከትሉትን ተጠያቂነት ደንግጎ ይገኛል፡፡ በዚህ ጽሑፍ በምርጫ ወቅት ሕግን መተላለፍ የሚያስከትለውን የወንጀል ተጠያቂነት በአጭሩ እንመለከታለን፡፡

🚫 #የተከለከሉ ተግባራትና ተጠያቂነታቸው‼️

📌አዋጁ የተከለከሉ እንዲሁም በወንጀል ጭምር የሚያስጠይቁ ተግባራትን በዝርዝር ደንግጓል፡፡ በመሠረታዊነት የፖለቲካ ታርቲን ዓላማ በኃይል ወይም በማስፈራራት ለማስረፅ ማንኛውንም ሰው ወይም ቡድን ማደራጀት ወይም ማሰልጠን ወይም ሰዎችን በግድ መመልመል እንዲሁም ለዚሁ ድርጊት እርዳታ ማድረግም ሆነ መተባባር የተከለከለና አግባብ ባለው ሕግ የሚያስቀጣ ተግባር መሆኑን አዋጅ ቁጥር 1162/2011 እንደተሻሻለው አንቀጽ 160 ተደንግጓል፡፡

👉በተያያዘም የአዋጁ አንቀጽ 158 እና 159 (በማሻሻያ አዋጁ እንደተሸጋሸገው) በወንጀል የሚያስጠይቁ ዝርዝር ተግባራትን ደንግጓል፡፡ ይኸውም:-
👉ከምርጫ ቦርድ ፈቃድ ውጪ የምርጫ ሰነዶችና ቁሳቁሶችን ማተም፣ ማባዛት፣ መፈብረክ፣ መያዝ ወይም ለሌሎች ማደል በእስራት ወይም በመቀጮ የሚያስቀጣ ነው፡፡ ይህም በወንጀል ሕጉ ላይ ስለቅጣት በተቀመጡት ድንጋጌዎች መሠረት የሚፈፀም ነው፡፡
👉በድምፅ መስጫ ዕለት በድምፅ መስጫ ጣቢያ አካባቢ ድምፅ ከመስጠት ወይም የተሰጠን ሕጋዊ ተግባር ከማከናወን ውጪ ሌላ ማንኛውንም የፖለቲካ እንቅስቃሴ ማድረግ፣ መሳተፍ ወይም ባልተገባ ወይም በተከለከለ ጊዜ የምርጫን ውጤት ማተም ወይም ማዛባት ከብር 80,000 (ሰማንያ ሺ) እስከ ብር 100,000(አንድ መቶ ሺ) በሚደርስ የገንዘብ መቀጮ ወይም ከ1 (አንድ) እስከ 3 (ሶስት) ዓመት በሚደርስ ቀላል እስራት የሚያስቀጣ ነው፡፡
👉በቦርዱ ወይም በምርጫ አስፈፃሚዎች ገለልተኝነት ጣልቃ ለመግባት መሞከር በተለይም መደለያ ወይም የተስፋ ቃል መሥጠት ወይም ለመሥጠት መሞከር
👉የምርጫ ሚስጥራዊነትን መጣስ
👉ከድምጽ እና ከምርጫ ቁሳቁስ ጋር የተያያዙ ክልከላዎችን መተላለፍ
👉የቦርዱን ወይም የምርጫ አስፈፃሚዎችን እንቅስቃሴ ማወክ
👉የፖለቲካ እንቅስቃሴዎች ወይም የምርጫ ውጤት አገላለፅ፣ የመራጮችን ወይ የፓርቲዎችን መብት አስመልክቶ የተጣሉ ክልከላዎችን መጣስ
👉ምርጫን ለማወክ ወይም እንዳይካሄድ ለማድረግ ወይም በምርጫው ሂደት ወይም ውጤት ላይ ጫና ለመፍጠር በማሰብ ጥላቻን ወይም ፍርሀትን የሚቀሰቅስ ወይም በምርጫው ሂደት ወይም በምርጫው ውጤት ላይ ጫና የሚፈጥር የሐሰት መረጃ አሳትሞ ማሰራጨት ወይም ለማሰራጨት መሞከር
📌🚫ከብር 30,000 (ሰላሳ ሺ) እስከ ብር 50,000 (ሀምሳ ሺ) የገንዘብ መቀጮ ወይም ከ6 (ስድስት ወር በማያንስ ከ1(አንድ) አመት በማይበልጥ ቀላል እስራት የሚያስቀጣ ይሆናል፡፡ እንዲሁም

🚫የምርጫ ዋና አስፈፃሚ ወይም የቦርዱ ሠራተኛ ሥልጣኑን ወይም ተግባሩንና ኃላፊነቱን በሚያከናውንበት ወቅት ሆነ ብሎ እንቅፋት መሆን ወይም ማደናቀፍ
🚫የቦርዱ የስብሰባ ሂደት ሆነ ብሎ ማቋረጥ ወይም በነዚሁ ቦታዎች በማንኛውም ሁኔታ ያልተገባ ተግባር መፈፀም
🚫ሆነ ብሎ በቦርዱ የሥራ ቦታ ወይም በመታየት ላይ ባለ ጉዳይ ላይ በሚሰጠው ውሳኔ ወይም ትዕዛዝ ላይ ተገቢ ያልሆነ ተፅዕኖ ለማሳደር ሲባል ማንኛውም የኃይል ተግባር መፈፀም ከብር 30,000 (ሰላሳ ሺ) የገንዘብ መቀጮ ወይም ከ1 (አንድ) አመት በማይበልጥ ቀላል እስራት የሚያስቀጣ ነው፡፡

🚫በተጨማሪም ምርጫ ከተጀመረበት ቀን አንስቶ ውጤት እስከሚገለፅበት ቀን ድረስ የማንኛውንም እጩ ተወዳዳሪ ፖስተርን ወይም የምርጫ ማስታወቂያን ማበላሸት፣ ማስወገድ ወይም መቅደድ ከ1(አንድ) አመት በማይበልጥ እስራት ወይም በመቀጮ እንደሚያስቀጣ በአዋጁ አንቀጸ 159(በማሻሻያ አዋጁ እንደተሸጋሸገው) ተደንግጓል፡፡

📌 #በአጠቃላይ በምርጫ ሂደት ተሳታፊ የሆኑ ሁሉም አካላት የኢትዮጵያ የምርጫ አዋጅ ቁጥር 1162/2011(1394 እንደተሻሻለው) የተደነገጉ ክልከላዎች በመረዳትና በማክበረ ከሕገ-ወጥ ተግባራት ሊቆጠቡ ይገባል፡፡

📌በፍትሕ ሚኒስቴርን የንቃተ ሕግ ትምህርትና ሥልጠና ዳይሬክቶሬት ተዘጋጅቶ በዳሎቻ ወረዳ ፍትህ ጽ/ቤት የንቃተ ሕግ ትምህርትና ሥልጠና ዳይሬክቶሬት በኩል የቀረበ!!

⚖ህግን አለማወቅ ከተጠያቂነት አያድንም!!⚖

26/04/2026

የወንጀል ምስክሮችና ጠቋሚዎች ጥበቃ
========================
በአንድ አገር ውስጥ የህግ የበላይነትን ለማስፈን፣ የወንጀል ድርጊትን ለመቆጣጠር እና ለመከላከል የህብርተሰቡ ሚና ከፍተኛ ነው፡፡ የወንጀል ድርጊት ሲፈፀም ጥቆማ መስጠት እና ምስክር መሆን ድግሞ ህብረተሰቡ ወንጀልን በመከላከል ረግድ ከሚያበረክተው አስተፅኦ ዋነኛው ነው፡፡ በአንፃሩም ጠቋሚዎችና ምስክሮች ጥቆማና ምስክርነት በሚሰጡበት ጊዜም ሆነ ከሰጡም በኋላ ጠቋሚ ወይም ምስክር በመሆናቸው ምክንያት በእነርሱ እና በቤተሰቦቻቸው ላይ ሊደርስ ከሚችል ጉዳት መጠበቅ አለባቸው፡፡ በዚህም ምክንያት የተለያዩ የአለማችን ሀገራት ለወንጀል ጠቋሚዎችና ምስክሮች ጥበቃ የሚያደርጉ ሲሆን ይህን የሚያደርጉትም ከባድ እና የተደራጁ ወንጀሎችን በሚመለከት ለሚቀርቡ ጠቋሚዎችና ምስክሮች ነው፡፡ ሀገራችንም ይህንኑ በመረዳት የወንጀል ምስክሮችና ጠቋሚዎች ጥበቃ አዋጅ ቁጥር 699/2003 አውጥታ በህግ በተመለከቱ ወንጀሎች ላይ ምስክሮችና ጠቋሚዎች ለሆኑ ሰዎች ጥበቃ ለማድረግ ጥረት በማድረግ ላይ ትገኛለች፡፡ በዚህ ፅሁፍ የምስክር እና ጠቋሚዎችን ጥበቃ ምንነትና የጥበቃ ስምምነት፣ የጥበቃ እርምጃ ዓይነቶችን እና ጥበቃ የሚደረግባቸውን ወንጀሎች በአጭሩ እንዳስሳለን፡፡

የጠቋሚዎችና ምስክሮች ጥበቃ ምንነት እና የጥበቃ ስምምነት
የጠቋሚዎችና ምስክሮች ጥበቃ ማለት አንድን ወንጀል በተመለከተ የሚያውቀውን ለፍርድ ቤት ወይም ለፖሊስ ለመግለፅ የተስማማ ጠቋሚ ወይም ምስክር ቃሉን ወይም መረጃውን በመስጠቱ ምክንያት በራሱ ወይም በቤተሰቡ ላይ ከሚቃጣበት ጉዳት የሚጠበቅበት በህግ የተዘረጋ ሥርአት ነው፡፡ ይህም በጥበቃ ስምምነት መሰረት የሚፈፀም ሲሆን ስምምነቱ በጥበቃ ተጠቃሚው እና በፍትህ ሚኒስቴር መካከል የሚደረግ ነው፡፡ በአዋጁ አንቀፅ 2(2) መሰረት የጥበቃ ተጠቃሚ ከሚኒስቴሩ ጋር የጥበቃ ስምምነት የተፈራረመ ጠቋሚ ወይም የምስክር ወይም የጠቋሚ ወይም የምስክር ቤተሰብ አባል ነው፡፡ የጥበቃ ተጠቃሚው አካለ መጠን ያላደረሰ ወይም በፍርድ የተከለከለ ሰው ከሆነ የጥበቃ ስምምነቱ ከወላጆቹ ወይም ከአሳዳሪው ጋር የሚፈረም ሲሆን ነገር ግን የጥበቃ ተጠቃሚው አካለ መጠን ከደረሰ ወይም የህግ ችሎታውን መልሶ ካገኘ በኋላ ጥበቃው የሚቀጥል ከሆነ ስምምነቱን የጥበቃ ተጠቃሚው ራሱ መፈረም እንዳለበት በአዋጁ አንፅ 8(3) ተደንግጎ ይገኛል፡፡

የጥበቃ ተጠቃሚ የሆነው አካለ መጠን ያላደረሰ ልጅ መረጃ ወይም ምስክርነት የሚሰጠው በወላጁ ወይም በአሳዳሪው ላይ ሲሆን፣ ወላጅ ወይም አሳዳሪ የሌለው ሲሆን፣ አስፈላጊው ጥረት ተደርጎ ወላጁን ወይም አሳዳሪውን ማግኘት ያልተቻለ እንደሆነ፣ ወላጁ ወይም አሳዳሪው በቂ ባልሆነ ምክንያት ፈቃዱን ሳይሰጥ ሲቀር ወይም በማናቸውም ምክንያት ፈቃዱን መስጠት ሳይችል ሲቀር ሚኒስቴሩ ከልጁ ጋር ልዩ የጥበቃ ስምምነት ሊፈራረም እንደሚችል ከአዋጁ አንቀፅ 9(1) መረዳት ይቻላል፡፡ ሆኖም አካለ መጠን ካላደረሰ ልጅ ጋር የተደረገ ልዩ የጥበቃ ስምምነት ከተፈረመበት ዕለት ጀምሮ ባሉት አስር ቀናት ውስጥ ለፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ቀርቦ መጽደቅ አለበት፡፡ ፍርድ ቤቱም አካለ መጠን ያላደረሰው ልጅ ጥቅምና ደህንነት ይበልጥ ሊረጋገጥ የሚችልበትን ሁኔታ ግምት ውስጥ በማስገባት የጥበቃ ስምምነቱን መሻር፣ ማጽደቅ ወይም ማሻሻል እንደሚችል በአዋጁ አንቀጽ 9(4) ስር ተደንግጎ ይገኛል፡፡

የጥበቃ እርምጃ ዓይነቶች
ለወንጀል ጠቋሚዎችና ምስክሮች የሚደረጉ የጥበቃ እና የጥንቃቄ እርምጃዎች በአዋጁ አንቀጽ 4 ስር ተዘርዝረው ይገኛሉ፡፡ የጥበቃ እና የጥንቃቄ እርምጃዎች እንደ ሁኔታው በተናጠል ወይም በጣምራ ለጥበቃ ተጠቃሚ ተፈጻሚ የሚደረጉ ሲሆን ይህም ፡-
 የአካልና ንብረት ደህንነት ጥበቃ
 የመኖሪያ ስፍራ መቀየርን ጨምሮ ደህንነቱ የተጠበቀ የመኖሪያ ቦታ መስጠት
 ማንነትንና ባለንብረትነትን መደበቅ
 ማንነትን መቀየር
 ለራስ መጠበቂያ የነፍስ ወከፍ መሳሪያ መስጠት
 መረጃ በተሰጠበት የወንጀል ድርጊት ያለመከሰስ
 መረጃ በሚሰጥበት የወንጀል ጉዳይ ላይ የመጨረሻ ውሳኔ ከመሰጠቱ በፊትም ሆነ በኋላ ተከሳሽ በጥበቃ ተጠቃሚው መኖሪያ ወይም የሥራ ቦታ ወይም ትምህርት ቤት አካባቢ እንዳይደርስ ማገድ
 የፍርድ ሂደት ተጀምሮ ምስክርነት እስከሚሰጥ ድረስ የምስክር ማንነት እንዳይገለጽ ማድረግ
 ምስክርነት በዝግ ችሎት እንዲሰጥ ማድረግ
 ምስክርነት በአካል ሳይታይ ከመጋረጃ በስተጀርባ ሆኖ ወይም ማንነትን በመሸፈን እንዲሰጥ ማድረግ
 ማስረጃ በኤሌክትሮኒክስ ወይም በሌላ የተለየ ዘዴ እንዲቀርብ ማድረግ
 በሚስጥር መያዝ ያለበት ካልሆነ በስተቀር ለጠቋሚ ጥቆማ ባቀረበበት ጉዳይ ላይ ወቅታዊ መረጃና ምክር መስጠት
 እንዲመሰክር ለተጠራ ምስክር የጉዞና የውሎ አበል መስጠት
 የጥበቃ እርምጃው የመኖሪያ ስፍራን ለውጥ ካስከተለ የጓዝ ማንሻ ወጪን መሸፈን
 በበቀል የተወሰደ አስተዳደራዊ እርምጃ እንዲታገድ ወይም እንዲሻር ማድረግ ወይም ተመጣጣኝ የሆነ የማካካሻ እርምጃ መውሰድ
 በበቀል እርምጃ ለደረሰ ጉዳት የህክምና አገልግሎት በመንግሥት ሆስፒታል በነጻ መስጠት
 በጥበቃ እርምጃው ምክንያት ለደረሰ የገቢ ማጣት ወይም በበቀል እርምጃ ለደረሰ የመሥራት ችሎታ ማጣት የመሠረታዊ ፍላጎት ማሟያ ወጪን መሸፈን
 በጥበቃ ሥር እያለ ለደረሰ ሞት የቀብር ማስፈጸሚያ ወጪ መሸፈንና ለቤተሰብ የገንዘብ ድጋፍ ማድረግ
 የጥበቃ ተጠቃሚው የሥራና የትምህርት ዕድል እንዲያገኝ መርዳት
 ለምስክሩ ወይም ለጠቋሚው የምክር አገልግሎት መስጠት ወይም እንዲያገኝ ማድረግን የሚያካትት ነው፡፡

ለምስክር ወይም ጠቋሚዎች ጥበቃ የሚደረግባቸው ወንጀሎች
የምስክር እና ጠቋሚዎች ጥበቃ የሰለጠነ የሰው ሀይል፣ ጊዜ እና ወጪን የሚጠይቁ በመሆኑ ከአገራችን እድገት እና የኢኮኖሚ አቅም አኳያ ለሁሉም ምስክሮች እና የወንጀል ጠቋሚዎች ከለላ እና ጥበቃ ማድረግ አይቻልም፡፡ ስለሆነም ለምስክሮች ወይም ለጠቋሚዎች ጥበቃ የሚደረገው በህጉ ለተመለከቱት ወንጀሎች ሲሆን በወንጀል ምስክሮችና ጠቋሚዎች ጥበቃ አዋጅ ቁጥር 699/2003 አንቀጽ 3 መሰረት የጥበቃ እና የጥንቃቄ እርምጃዎች ማግኘት የሚቻለው የፅኑ እስራት መነሻው ግምት ውስጥ ሳይገባ 10 (አስር አመት) እና ከዚያ በላይ በሆነ ፅኑ እስራት ወይም በሞት ሊያስቀጣ በሚችል ወንጀል ምስክርነት ወይም ጥቆማን የተመለከተ ሆኖ
 የወንጀል ድርጊቱ ያለምስክሩ ወይም ያለጠቋሚው ምስክርነት ወይም ጥቆማ በሌላ ማናቸውም መንገድ ሊረጋገጥ ወይም ሊደረስበት የማይችል ሲሆን እና
 በምስክሩ፣ በጠቋሚው ወይም በቤተሰቡ ህይወት፣ አካላዊ ደህንነ፣ ነፃነት ወይም ንብረት ላይ ከባድ አደጋ ያደርሳል ተብሎ ሲታመን እንደሆነ ከአዋጁ አንቀፅ 3(1) መረዳት ይቻላል፡፡
ለአብነትም በኢትዮጵያ የሽብር ወንጀልን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር የወጣው አዋጅ ቁጥር 1176/2012 አንፅ 16 እና በሰው የመነገድ እና ሰውን በህገ ወጥ መንገድ ድንበር የማሻገር ወንጀልን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የወጣው አዋጅ ቁጥር 1178/2012 አንቀፅ 25 የወንጀል ምስክሮችና ጠቋሚዎች በአዋጅ ቁጥር 699/2003 መሰረት ለወንጀል ምስክሮችና ጠቋሚዎች ስለሚደረግ ጥበቃ ደንግገው ይገኛሉ፡፡

ነገር ግን አዋጁ ይህንን መስፈርት ቢያስቀምጥም የፍትህ ሚኒስቴሩ የጥበቃ ተጠቃሚ ላልሆኑ ለማንኛቸውም ምስክሮችና ጠቋሚዎችም በዚህ አዋጅ አንቀጽ 4 ስር ከተቀመጡ አንዳንድ ጥበቃዎችን እንደአስፈላጊነቱ ሊያደርግ ይችላል፡፡ ይህም
 በሚስጥር መያዝ ያለበት ካልሆነ በስተቀር ለጠቋሚ ጥቆማ ባቀረበበት ጉዳይ ላይ ወቅታዊ መረጃና ምክር መስጠት
 እንዲመሰክር ለተጠራ ምስክር የጉዞና የውሎ አበል መስጠት
 በበቀል የተወሰደ አስተዳደራዊ እርምጃ እንዲታገድ ወይም እንዲሻር ማድረግ ወይም ተመጣጣኝ የሆነ የማካካሻ እርምጃ መውሰድ
 በበቀል እርምጃ ለደረሰ ጉዳት የህክምና አገልግሎት በመንግሥት ሆስፒታል በነጻ መስጠት
 ለምስክሩ ወይም ለጠቋሚው የምክር አገልግሎት መስጠት ወይም እንዲያገኝ ማድረግን የሚያካትት ነው፡፡

ማጠቃለያ
በአጠቃላይ የህግ የበላይነትን በማስፈን ሂደት የህብረተሰቡ ተሳትፎ ወሳኝ ሲሆን የሚመለከታቸው የመንግስት አካላት ወንጀል ጠቆሚዎች እና ምስክሮች ወንጀልን በማጋለጣቸው ምክንያት ጉዳት እንዳይደርስባቸው ተገቢውን የህግ ጥበቃ ማድረግ እና ህጉን ተፈፃሚ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል፡፡

የማታለል ወንጀሎች በኢ.ፌ.ዲ.ሪ የወንጀል ህግ ➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖ወንጀል በሰው ልጆች አካል፣ ክብር ወይም ንብረት ላይ ሊፈፀም የሚችል እኩይ ተግባር ሲሆን የተለያዩ ማህበራዊ፣ኢኮኖሚያዊ እ...
26/04/2026

የማታለል ወንጀሎች በኢ.ፌ.ዲ.ሪ የወንጀል ህግ
➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖
ወንጀል በሰው ልጆች አካል፣ ክብር ወይም ንብረት ላይ ሊፈፀም የሚችል እኩይ ተግባር ሲሆን የተለያዩ ማህበራዊ፣ኢኮኖሚያዊ እንዲሁም ስነ ልቦናዊ ጉዳትን ያስከትላል፡፡ ወንጀል እንዳይፈፀም መከላከል አንደኛው እና ዋናው የፍትህ አካላት እና የህብረተሰብ ሀላፊነት ነው፡፡ ከዚህ ባለፈ የወንጀል ድርጊት ተፈፅሞ ሲገኝ ደግሞ ተገቢውን ህጋዊ የእርምት እና የቅጣት እርምጃ መውሰድ ተገቢ ነው፡፡ በመሆኑም የወንጀል ህግ ወንጀል ናቸው ብሎ እንዳይፈፀሙ የከለከላቸውን ወይም ደግሞ ያለመፈፀም ወይም ያለማድረግ የወንጀል ሀላፊነት እንደሚያስከትል የተቀመጡትን ድንጋጌዎች ማክበር ግድ ይላል፡፡ በኢ.ፌ.ዲ.ሪ. የወንጀል ህግ ለንብረት ጥበቃ ከሚያደርጉእና በንብረት ላይ ሊፈፀሙ የሚችሉ ወንጀሎች ከሚዘረዝሩ ድንጋጌዎች መካከል የአታላይነት ወይም የማታለል ወንጀል አንዱ ነው፡፡ የተለያዩ የማታለል ድርጊቶችን በመፈፀም የሰዎች ንብረት የአታላዮች ሲሳይ ሲሆን መስማት በእለት ተእለተ እንቀስቃሴችን ውስጥ የሚያጋጥመን ጉዳይ ነው፡፡ በመሆኑም በዚህ አጭር የንቃተ ህግ ፅሁፍየማታለል ወንጀል ምንነት፣በኢ.ፌ.ዲ.ሪ. የወንጀል ህግ የተካተቱ የአታላይነት ወንጀሎች፣ ስለ ከባድ አታላይነት እንዲሁም ወንጀሎቹ የሚያስከትሉት የወንጀል ተጠያቂነት ይዳሰሳሉ፡፡

• የማታለል ወንጀል ምንነት

ማታለል ሆን ብሎ ሰውን በማጭበርበር ዋጋ ያለውን ነገር በአብዛኛው የገንዘብ ጥቅምን ለማግኘት የሚፈፀም ተግባር ነው፡፡ በአጠቃላይ ማታለል የሚፈጸመው ለማሳሳት ወይም ለማታለል የታሰበ የሀሰት መግለጫዎችን ወይም ታማኝነት የጎደለው ድርጊት በመጠቀም ሲሆን በንብረት ላይ ጉዳት የማስከተል ውጤት ይኖረዋል፡፡ የማታለል ድርጊት የወንጀል እና ፍትሐ ብሄር ሀላፊነትን የሚያስከትል ሲሆን የፍትሐ ብሄር ሀላፊነት ንብረቱን የማስመለስ ወይም ካሳ ማስከፈልን ተግባራዊ ያደርጋል፡፡ በሌላ በኩል የወንጀል ተጠያቂነት የእስራት እና የገንዘብ መቀጮ ቅጣቶችን የሚያስከትል ሲሆን በመቀጠል በወንጀል ህጉ የአታላይነት ምንነት ለመረዳት የሚጠቅመንን የህግ ድንጋጌ እንመለከታለን፡፡

በ1996 ዓ/ም በወጣው የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. የወንጀል ህግ አንቀፅ 692 ስር እንደተደነገገው ማንም ሰው የማይገባ ብልፅግና ለራሱ ለማግኘት ወይም ለሌላ ሰው ለማስገኘት በማሰብ አሳሳች የሆኑ ነገሮችን በመናገር፣የራሱን ማንነት ወይም ሁኔታ በመሰወር ወይም መግለጽ የሚገባውን ነገር በመደበቅ ወይም የሌላውን ሰው የተሳሳተ እምነት ወይም ግምት በመጠቀም፣በማድረግም ሆነ ባለማድረግ ሌላውን ሰው አታልሎ የራሱን ወይም የሶስተኛ ወገንን የንብረት ጥቅም የሚጎዳ አድራጎት እንዲፈፀም ያደረገ እንደሆነ የአታላይነት ወንጀል እንደተፈፀመ ያስቀምጣል፡፡ በመሆኑም ይህ ወንጀል በቀላል እስራት ወይም እንደነገሩ ከባድነትከአምስት ዓመት በማይበልጥ ፅኑ እስራትና በገንዘብ መቀጮ ያስቀጣል፡፡

ከድንጋጌው መገንዘብ እንደሚቻለው የአታላይነት ወንጀልን ለማቋቋም አራት መሰረታዊ ማቋቋሚያዎች ያሉ ሲሆን እነሱም፡-
 ወንጀለኛውበአንቀፁ የተዘረዘሩትን ተግባራት ሆን ብሎ የፈፀመ እንደሆነ ፣
 በዚህ ድርጊት የተነሳ ተበዳዩ ከተታለለ ወይም በአጥፊው ወይም በወንጀለኛው የተገለፀውን አምኖ የተቀበለ እንደሆነ(ለምሳሌ ስለሞያው ወይም ስለስራው የተሳሳተ ንግግር ተበዳዩ ያመነ እንደሆነ፣የሀሰት ውክልና አሳይቶ ያንን ውክልና ያመነ እንደሆነ)፣
 በሀሰት የተገለፀውን በማመን የፈፀመው ተግባር ያለ እንደሆነ (ለምሳሌ ገንዘብ፣ጌጣ ጌጥ፣ንብረት የሰጠ እንደሆነ፣በቂ ገንዘብ የሌለውን ቼክ በመቀበል ግብይት ፈፅሞ እንደሆነ)፣
 እንደዚሁም ተበዳዩ በመታለሉ የተነሳ የራሱ ወይም ሶስተኛ ወገን ያጣው የገንዘብ ወይም ዋጋ ያለው ነገር ጥቅምመኖር መቻል ያለበት መሆኑ ናቸው ፡፡

ከባድ አታላይነት

አንድ የማታለል ወንጀል በከባድ አታላይነት የሚያስቀጣው ፡-
o አድራጊው የማህበር፣ የባንክ፣ የንግድ፣ የአክሲዮን ገበያ ወይም የኢንዱስትሪ መስሪያ ቤት አክሲዮን፣ የእዳ ሰነድ፣ የቦንድ ወይም ማናቸውንም የዋስትና ሰነድ በማውጣት ከህዝብ ገንዘብ ለመሰብሰብ ጥሪ ያደረገ ወይም ለራሱ ወይም ለድርጅቱ ወይም አድራጊው የአክሲዮን ባለድርሻ ለሆነበት ድርጅት የሸጠ እንደሆነ ወይም
o ወንጀሉን የፈፀመው በሕዝብ አስተዳደር ወይም በሕዝብ አገልግሎት ላይ እንደሆነ ከአስር አመት በማይበልጥ ፅኑ እስራትናእስከ ብር ሃምሳ ሺህ በማይበልጥ መቀጮ እንደሚቀጣ በወንጀል ህጉ አንቀፅ 696 ስር ተደንግጎ ይገኛል፡፡
በሌላ በኩል የማታለል ወንጀል የተፈፀመው በየመንግስት ወይም የህዝባዊ ድርጅት ሠራተኛ ከሆነ ከሶስት ዓመት እስከ አስር ዓመት በሚደርስ ፅኑ እስራት እና ከሶስት ሺህ ብር እስከ ሰላሳ ሺህ ብር በሚደርስ የገንዘብ መቀጮ እንደሚያስቀጣ የሙስና ወንጀሎች አዋጅ ቁጥር 881/2007 አንቀፅ 32/1 ይደነግጋል፡፡ እንዲሁም በማታለል ወንጀሉ የተገኘው ጥቅም ከፍተኛ ወይም በመንግስት ወይም በህዝባዊ ድርጅት ወይም በህዝብ ጥቅም ላይ የደረሰው ጉዳት ከፍተኛ ከሆነ፣ በወንጀል አድራጊው የስልጣን ደረጃ የወንጀሉ አፈፃፀም ከባድ አድርጎት እንደሆነ ቅጣቱ ከአምስት ዓመት እስከ አስራ አምስት ዓመት የሚደርስ ፅኑ እስራት እና ከአስር ሺህ ብር እስከ አንድ መቶ ሺህ ብር በሚደርስ የገንዘብ መቀጮ እንደሚቀጣ የአዋጁ እንቀፅ 32/2 ያስቀምጣል፡፡ በተጨማሪም ወንጀሉ የተፈፀመው በሕዝብ አስተዳደር ወይም በሕዝብ አገልግሎት ላይ እንደሆነ እንደነገሩ ሁኔታ ከላይ ከተመለከቱት ቅጣቶች በአንዱ እንደሚቀጣ በአዋጁ እንቀፅ 32/3 ስር ተደንግጎ ይገኛል፡፡

ማታለልን ያካተቱ ወንጀሎች እና የሚያስከትሉት ቅጣት

የተለያዩ የማታለል ወንጀሎች በተበዳዮች ላይ ሲፈፀሙ እንሰማለን፡፡ ከእነዚህም ውስጥ የራስን እውነተኛ ማንነት በመደበቅ በማህበራዊ ሚዲያ ነፃ የትምህርት እድል እንደሚሰጡ በመግለፅ፣ የፍቅር ጓደኝነት በመመስረት ከተግባቡ በኋላ ወደ ወጪ ሀገር እንደሚወስዱ በመግለፅ በተለያየ መንገድ በማሳመን ገንዘብ መቀበል፣ ፈጣን ሎተሪ ደርሶት ገንዘቡን ለመውሰድ መታወቂያ ስለሌለው በተበዳይ መታወቂያ እንዲያወጣ በማሳመን ለመያዣነት ስልክ፣ ገንዘብ፣ ኮምፒውተር፣ ገንዘብ እና የመሳሰሉትን በመቀበል መሰወር ፣ በባንክ ደብተር ውስጥ በቂ ገንዘብ ሳይኖር ገንዘብ እንዳለ በማሳመን ግብይት መፈፀም፣የስልክ ቁጥሩ የሎተሪ አሸናፊ እንደሆነ በመግለፅ ገንዘቡ እንዲላክላቸው የሞባይል ካርድ እንዲሞሉ ወይም የባንክ አካውንት ውስጥ ገንዘብ እንዲያስገቡ በማሳመን ገንዘብ መቀበል ለአብነት ሊጠቀሱ የሚችሉ የማታለል ወንጀሎች ናቸው፡፡

እነዚህ እና ሌሎች የማታለል ድርጊቶች በወንጀል ህጉ ያላቸውን ሽፋን እና የሚያስከትሉትን ቅጣት እንደሚከተለው እናያለን፡፡

 የሚያዝበት ገንዘብ ሳይኖር ቼክ ማውጣት በወንጀል ህጉ እንቀፅ 693/1/ እና 2 ስር የሚስጠይቅ ሲሆን ማንም ሰው ቼክ በሚያወጣበት ወይም ለባንክ በሚያቀርብብት ጊዜ የሚያዝበት በቂ ገንዘብ አለመኖሩን እያወቀ ቼክ ያወጣወይም የሰጠ እንደሆነ በቀላል እስራት (ከአስር ቀን እስከ 3 ወር) ወይም እንደነገሩ ከባድነት ከአስር ዓመት በማይበልጥ ፅኑ እስራትና በመቀጮ እንደሚቀጣ ይደነግጋል፡፡ እንዲሁም በቼክ የማታለል ድርጊቱ የተፈፀመው በቸልተኝነት(ለምሳሌ ተከሳሹ በአካውንቱ ውስጥ በቂ ገንዘብ ያለው መስሎት ያለውን የገንዘብ መጠን ሳያረጋግጥ የፈረመ) እንደሆነ በገንዘብ መቀጮ ወይም ከአንድ አመት በማይበልጥ ቀላል እስራት ይቀጣል፡፡
 በተጭበረበረ ሁኔታ የአክሲዮን ገበያን ንግድ ማካሄድ ሌላው በወንጀል ህጉ የተካተተ የማታለል ወንጀል አይነት ሲሆን ማንም ሰው በአክሲዮን ገበያ ወይም በሌላ ገበያ አማካኝነት የአክሲዮን ወይም የአክሲዮን የገቢያ ዋጋ በሚመለከት የህዝብ አክሲዮን ንግድ እንዳለ የሚያስመስል ሀሰተኛ ወይም አሣሣች መልክ ለመፍጠር በማሰብ፡-
o በአክሲዮን ባለቤትነት ላይ ምንም ጠቃሚ ለውጥ የማያመጣ የአክሲዮን ንግድ ያካሄደ እንደሆነ፣
o አክሲዮኖቹ በተጠየቁት ተቀራራቢ መጠን ፣ተቀራራቢ ጊዜ እና በተቀራራቢ ዋጋ በዚያው ሰው ወይም በሌላ ሰው እንደተገዛ ወይም ለዚያው ሰው ወይም ለሌላ ሰው የገዢው ጥያቄ እንደቀረበ ወይም እንደሚቀርብ እያወቀ አክሲዮኖቹን ለመግዛት ጥያቄ ያቀረበ እንደሆነ ወይም፣
o አክሲዮኖቹ በተጠየቁት ተቀራራቢ መጠን፣ተቀራራቢ ጊዜ እና ተቀራራቢ ዋጋ በዚያው ሰው ወይም በሌላ ሰው እንዲሸጡ ወይም ለዚያ ሰው ወይም ለሌላ ሰው የሽያጭ ጥያቄ እንደቀረበ ወይም እንደሚቀርብ እያወቀ አክሲዮኖችን ለመሸጥ ጥያቄ ያቀረበ እንደሆነ በቀላል እስራት ወይም ነገሩ ከባድ ሲሆን ከአምስት ዓመት በማይበልጥ ፅኑ እስራት ይቀጣል፡፡

 በአክሲዮኖች ወይም በሸቀጦች መቆመር ፡- ማንም ሰው በሀገር ውስጥም ሆነ ከአገር ውጪ የተመዘገቡ ወይምያልተመዘገቡ ኩባንያዎች ወይም ሌሎች የንግድ ድርጅቶች አክሲዮኖች ወይም ማናቸውም ዕቃዎች ወይም ሸቀጦች ዋጋቸውን ዝቅ ወይም ከፍ ማለቱን ምክንያት በማድረግ ገቢ ወይም ትርፍ ለማግኘት በማሰብ አክሲዮኖቹን ወይም ዕቃዎቹን ወይም ሸቀጦቹን የራስ የማድረግ እውነተኛ ሀሳብ ሳይኖረው እነዚህን ነገሮች የሚሸጥ ወይም የሚገዛ በማስመሰል ማናቸውንም ዓይነት ውል በፅሁፍም ሆነ በቃል ያዘጋጀ ወይም የፈረመ እንደሆነ በቀላል እስራት ወይም ነገሩ ከባድ ሲሆን ከአምስት ዓመት በማይበልጥ ፅኑ እስራት እንደሚቀጣ በአንቀፅ 695 ስር ተደንግጎ ይገኛል፡፡

 ኢንሹራንስ በሚመለከት የሚፈፀም የአታላይነት ድርጊት በወንጀል ህጉ አንቀፅ 698 መሰረት የሚያስቀጣ ሲሆን ማንም ሰው የማይገባ ብልፅግና ለራሱ ለማግኘት ወይም ለሌላ ሰው ለማስገኘት በማሰብ፡-
o ኢንሹራሱን የተገባበትን አደጋ በመፍጠር ወይም
o በውል ውስጥ በተገለፀው ጥቅም ላይ ተፅዕኖ በሚያደርግ አኳኃን የኢንሹራንሱን ገንዘብ ልክ፣ የውሉን ዘመን፣ ወይም የኢንሹራንሱን ተጠቃሚዎችን የሚመለከት ፍሬ ነገር በመደበቅ፣በማሳሳት፣በማረጋገጥ ወይም ይህንኑ በሚመለከት ሀሰተኛ መግለጫ በመስጠት አንድ የኢንሹራንስ ማህበርን ካታለለ፣
o በማናቸውን ሌላ መንገድ ከኢንሹራንስ እንቅስቃሴ ጋር በተያያዘ የአታላይነት ድርጊት ከፈፀመ በቀላል እስራት ወይም ሁኔታዎች ይበልጥ ከባድ ሲሆኑ ከአምስት ዓመት በማይበልጥ ፅኑ እስራትና ከብር ሀምሳ ሺ በማይበልጥ መቀጮ ይቀጣል፡፡

 በህዝብ እምነት በመጠቀም ማታለል፡- ማንም ሰው ለራሱ ብልፅግና ለማግኘት አስቦ መንፈስ እጠራልሃለሁ፣ጋኔን እስብልሃለሁ፣ ደንቃራ እጥልልሃለሁ፣ እጠነቁልልሃለሁ፣ ዕድልህን እነግርሃለሁ፣ ነገርን እገልፅልሃለሁ፣ ኮከብህን እቆጥርልሃለሁ፣ ህልምን እፈታልሃለሁ፣ የወደፊት ዕድልህን አውቅልሃለሁ፣ ወስጥ እጅህን አነብልሃለሁ፣ ከሞተ ሰው ጋር አነጋግርሃለሁ በማለት፣ ወይም በሰው እምነት ያለአግባብ መገልገል በሚያስችል በማናቸውም ሌላ መንገድ ሰውን ያታለለ እንደሆነ የግል አቤቱታ ሲቀርብበት አፈፃፀሙ በደንብ መተላለፍ ድንጋጌዎች የሚያስቀጣ ካለሆነ (ቀላል ካልሆነ) በቀር በመቀጮ ወይም የተደጋገመ ወንጀል በፈፀመ ጊዜ በቀላል እስራት ወይም ነገሩ ከባድ ሲሆን ከአምስት ዓመት በማይበልጥ እስራት እንደሚያስቀጣ የወንጀል ህጉ እንቀፅ 700 ይደነግጋል፡፡
በተጨማሪ ማንም ሰው ከባድ በሽታ ወይም ጉድለት አለብኝ ወይም ከፍተኛ አካላዊ ወይም ስነ- ልቦናዊ ጉዳት ወይም የገንዘብ ወይም ሌላ ማቴሪያላዊ ኪሳራደረሰብኝ በማለት የሀሰት ንግግር በማድረግ ወይም የሰዎችን ሀዘኔታ ስሜት በሚስብ በማናቸውም ሌላ የማታለል ዘዴ በመጠቀም ከግለሰብ ወይም ከሕዝብ ገንዘብ ወይም ማቴሪያላዊ ነገር የሰበሰበ እንደሆነ እንዲሁም ከላይ ከተዘረዘሩትነገሮች አንዱ በሌላ ሰው ላይ የደረሰ አስመስሎ የተባለውን ሰው ለሕዝብ በማቅረብ በመለመኛነት የተገለገለበት እንደሆነና ይህንኑ ለመርዳት ነው በማለት ከግለሰቦች ወይም ከሕዝብ ገንዘብ ወይም ማቴሪያላዊ ነገር የሰበሰበ እንደሆነ እንደነገሩ ሁኔታ በቀላል እስራት ወይም በመቀጮ ወይም ከአምስት ዓመት በማይበልጥ ፅኑ እስራት እና በመቀጮ ይቀጣል፡፡እንዲሁም ማንም ሰው በሌላ ሰው ላይ ጉዳት በማድረስ ከላይ ለተመለከተው ዓላማ የተጠቀመበት እንደሆነ ከሶስት ዓመት እስከ አስር ዓመት ለመድረስ በሚችል ጽኑ እስራት እና በገንዘብ መቀጮ ይቀጣል፡፡

በሌላ በኩል ማንም ሰው ፖለቲካዊ፣ ሃይማኖታዊ፣ ባህላዊ፣ ማህበራዊ ወይም ሰብዓዊ ጉዳዮችን ወይም ማናቸውንም ሌላ ዓላማ ምክንያት በማድረግ በህግ ወይም አግባብ ባለው ባለስልጣን ተፈቅዶለትም ሆነ ሳይፈቀድልት ከግለሰብ ወይም ከህዝብ ላይ ገንዘብ ወይም ማናቸውንም ማቴሪያላዊ ነገር ሰብስቦ ይህንኑ ገንዘብ ወይም ማቴሪያላዊ ነገር በሙሉ ሆነ በከፊል ከሰበሰበበት ዓላማ ውጪ ያለአግባብ ያዋለ እንደሆነ ገንዘብ ያለፍቃድ ስለመሰብሰብ የተመለከተው የወንጀል ህጉ አንቀፅ 862 ድንጋጌ እንደተጠበቀ ሆኖ ከአስር ዓመት በማይበልጥ ፅኑ እስራት እና ከሰላሳ ሺህ ብር በማይበልጥ መቀጮ ይቀጣል፡፡

በአጠቃላይ የሰዎችን እምነት በመጠቃም ወይም በተለያዩ ንግግሮች እና ድርጊቶች ሰዎችን በማሳሳት የገንዘብ ወይም ዋጋ ያለው ነገርን ለራስ ማድረግ በአታለይነት ወንጀል የሚያስጠይቅ ተግባር ነው፡፡ ማህበረሰቡ ንብረቱ የአታላዮች ሲሳይ እንዳይሆን በወንጀለኞች የሚደረጉ ንግግሮችን እና ድርጊቶች ከማመኑ በፊት መጠራጠር እና ቆም ብሎ ማሰብ ይኖርበታል፡፡ የበለጠም ጥቅምና ንብረቱን መጠበቅ እንዲሁም ንብረቱን ከመስጠቱ በፊት ጥንቃቄ ማድረግ ፣ ነገሮችን ማጣራትና ማረጋገጥ ያስፈልጋል፡፡ የማታለል ድርጊቶቹ ተፈጽማውሲገኙም ለሚመለከተው የህግ አካል በማቅረብ አጥፊዎች እንዲቀጡ ሌሎችም እንዲማሩ ማድረግ ተገቢ ነው፡፡

የወንጀል ህግ ምንነት፣ ዓላማውና ህገ መንግስቱ====================የሰው ልጅ ሠላማዊ ህይወትን ለመምራት ከወንጀል የፀዳ ህብረተሠብ መፍጠር አለበት፡፡ ለዚህ ደግሞ ያለው አማራጭ የ...
26/04/2026

የወንጀል ህግ ምንነት፣ ዓላማውና ህገ መንግስቱ
====================
የሰው ልጅ ሠላማዊ ህይወትን ለመምራት ከወንጀል የፀዳ ህብረተሠብ መፍጠር አለበት፡፡ ለዚህ ደግሞ ያለው አማራጭ የወንጀል ፍትህ አስተዳደርን መዘርጋት ነው፡፡ ይህ የወንጀል ፍትህ አስተዳደር እንዲኖር ህግ አውጭ፣ ህግ ተርጓሚና አስፈፃሚ አካላት መኖር አለባቸው፡፡ በዚሁ መሠረት ህግ አውጪው እንደ ወንጀል አድርጐ የሚቆጥራቸው ድርጊቶች እና ተገቢ ብሎ ያመነባቸውን ቅጣቶች ዘርዝሮ በህግ ያወጣል፤ ህግ ተርጓሚው ወንጀል ፈፅመዋል ተብለው የተከሰሱ ሠዎችን ሲቀርቡለት ማስረጃውን አዳምጦ ተገቢውን ውሣኔ ይሰጣል፡፡ አስፈፃሚው አካል በፖሊስ አማካኝነት ወንጀል እንዳይፈፀም ይከላከላል ተፈፅሞም ከሆነ ተጠርጣሪዎች ይዞ ለፍርድ ያቀርባል፡፡ ዓቃቤ ህግ መንግስትን በመወከል ክስ ያቀርባል፡፡ ማረሚያ ቤቶች ቅጣት የተወሰነባቸውን ጥፋተኞች ተቀብለው ያሰራሉ ሌሎች ቅጣቶችም ተወስነው ከሆነ ያስፈፅማሉ፡፡
ስለሆነም የወንጀል ህግና የወንጀል የፍትህ አስተዳደር መሠረታዊ አላማዎች የወንጀል አይነቶችን አስቀድሞ በማሣወቅ የአንድ ህብረተሠብ አባላት ይህንን አውቀው ከጥፋት እንዲታቀቡ ማድረግና ይህን ማስጠንቀቂያ በማይከተሉ ላይ ቅጣት መፈፀም ናቸው፡፡ በዚህም መሠረት የወንጀል ህግ የተለያዩ የህብረተሠብ አባላት ማለትም ሰዎች ከሠዎች ወይም ከቡድኖች ወይም ከመንግስት ጋር ያላው ግንኙነት ይወስናል፡፡ በህግ እውቅና በተሠጠው ግንኙነት መሠረት ድርጊታቸውን ማስተካከል የሚችሉ ህጉ ተፈፃሚ የማይሆንባቸው ሲሆን ይህን ማድረግ የማይቻላቻው በህጉ መሠረት ይዳኛሉ፡፡
ኢትዮጵያ ከላይ የተጠቀሰውን አላማ ለማሣካት በተለያዩ ጊዜያት የወንጀል ህጐች ድንግጋ በተግባር ላይ አውላለች፡፡ በ1923 ዓ.ም የተደነገገው ለመጀመሪያ ጊዜ በስራ ላይ የዋለው የወንጀል ህግ ነው፡፡ 1949 ዓ.ም የወጣው ደግሞ ሁለተኛውና ከ40 ዓመት በላይ በስራ ላይ የነበረ የወንጀል ህግ ነው፡፡ በየመሃሉም ተጨማሪና ያለውን ከፍተት ሊሞሉ የሚችሉ ህጐች በስራ ላይ ነበሩ፡፡
ኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የወንጀል ህግ ከ1949 ዓ.ም ጀሞሮ በስራ ላይ የነበረውን የወንጀለኛ መቅጫ ህግ በመተካት ከግንቦት 1 ቀን 1997 ዓ. ም ጀምሮ በተግባር ላይ ውሏል፡፡ በኢፌድሪ ህገ መንግስት አንቀፅ 52(5) ላይ በተሰጠው ስልጣንና ሃላፊነት መሠረት በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የወጣ ነው፡፡ ይህ የወንጀል ህግ ህብረተሠቡን በጉዳት ለመጠበቅ የወጣና እንደ ወንጀል የሚቆጠሩ ድርጊቶችና ለነዚህ የተከለከሉ ድርጊቶች ተገቢ ተብለው የተዘረዘሩ ቅጣቶችን የሚዘረዝር ህግ ነው፡፡ ስለሆነም ቅጣት እና ወንጀል ሁለቱ የወንጀል ህግ መሠረታዊ ጉዳዮች ናቸው፡፡
ወንጀል ምን ማለት ነው?

ወንጀል ምን ምን አይነት ባህሪያትን ያካትታል ብሎ ቋሚና አለም አቀፋዊ ትርጉም ለመስጠት ያስቸግራል፡፡ ወንጀል የሚባሉት ባህሪያት ከማህበረሠብ ማህበረሰብ ይለያያሉ፡፡ ማህበረሠቡ ሲያድግ ይለወጣሉ፡፡ ስለሆነም በዛሬ ጊዜ ወንጀል ተብሎ የተደነገገ ድርጊት ወይም ያለማድረግ ከዚህ በፊት ወንጀል ላይሆን ይችላል፡፡ ወይም ከዚህ በፊት ወንጀል ተብሎ የተደነገገ ጉዳይ ዛሬ ወንጀል ላይሆን ይችላል፡፡
የወንጀል ህግ ህግ እና ቅጣቶቹ በአብዛኛው የአለማችን ሃገሮች በመሠረታዊ ጉዳዮች ላይ ተመሣሣይነት ቢኖራቸውም በዝርዝር ጉዳዮች ላይ ሊለያዩ ይችላሉ፡፡ እንዲህ አይነት ልዩነት ሊፈጠር የሚችለው የተለያዩ ሃገሮች ህዝቦች በተወሰኑ ጉዳዮች ያላቸው የአመለካከት ልዩነት ነው፡፡ ይህ ልዩነት ሃይማኖት ከባህል በስልጣኔ እድገት በሰው ልጆች መብት አጠባበቅ ብለው አስተሣሠብ ሊመነጨ ይችላል፡፡ በዚሁም መሠረት የአልኮል መጠጦችን ማዘዋወር፣ ዝሙት አዳሪዎች፣ ግብረሰዶም፣ ፅንስ ማስወረድ የመሣሠሉት ድርጊቶች በአንዳንድ ሃገሮች የወንጀል ድርጌት ተብለው ክልከላ ተደርጐባቸው ግርፋት ወይም የሞት ቅጣት የመሣሠሉትን ሊያስከትሉ ይችላሉ፡፡ በሌሎች ሃገሮች ግን ይሄንኑ ተመሣሣይ ድርጊቶች ያልተከተሉ ወይንም በወንጀል ህግ የማያስጠይቁ ሆነው እናገኛቸዋለን፡፡ ሆኖም ግን በሠፊው ተቀባይነት ያገኘው ትርጉም የሚከተለውን ይመስላል
ወንጀል ማለት ፡- በወንጀል ህግ የተከለከሉ ድትጊቶችን መፈፀም ወይም እንዲፈፀሙ ትዕዛዝ ወይም ግዴታ የተጣለበቸውን ድርጊቶች አለመፈፀም ነው፡፡
በዚህ መሠረት የወንጀል ህጉ ኃላፊነትን የማያስከትል ተግባር የፈፀሙ ሠዎች በወንጀል እንዳይጠቁ ማድረጊያና ወንጀል የፈፀሙ ቢሆንም እንኳን በህጉ ላይ ከተመለከተው ቅጣት ውጪ በዘፈቀደና ኢ-ሰብአዊ በሆነ መንግድ እንዳይቀጡ መከላከያ መሣራያ ነው፡፡
የወንጀል ህግ አላማና ግብ

የወንጀል ህጉ አንቀፅ 1 ሁለት ፓራግራፎች ያሉት ሲሆን በመጀመሪያው አላማውን ሲገልፅ ሁለተኛው ግቡን ያብራራል፡፡
አንቀፅ 1
የወንጀል ሕግ ዓላማ፣ ለጠቅላላው ጥቅም ሲባል የአገሪቱን መንግሥት፣ የሕዝቦቹን፣ የነዋሪዎቹን፣ ሰላም፣ ደህንነት፣ ሥርዓት፣ መብትና ጥቅም መጠበቅና ማረጋገጥ ነው፡፡
የወንጀል ሕግ ግብ ወንጀል እንዳይፈፀም መከላከል ሲሆን ይህንን የሚያደርገው ስለወንጀሎችና፣ ስለቅጣታቸው በቅድሚያ ማስጠንቀቂያ በመስጠት፣ ማስጠንቀቂያነቱ በቂ ባልሆነበት ጊዜ ወንጀል አድራጊዎቹ ተቀጥተው ሌላ ወንጀል ከመፈፀም እንዲቆጠቡና ለሌሎች ማስተማሪያ እንዲሆኑ ወይም እንዲታረሙ በማድረግ ወይም ተጨማሪ ወንጀሎች እንዳይፈፅሙ እርምጃዎች እንዲወሰድባቸው በማድረግ ነው፡፡


የወንጀል ህግ አላማ

የወንጀል ህግ አላማ ከፍ ብሎ በተቀመጠው አንቀፅ 1 የመጀመሪያው ፓራግራፍ እንደተመለከተው የሃገሪቱ መንግስት፣ የህዝቦቹን፣ የነዋሪዎቹን፣ ሰላም ደህንነት ስርዓት መብትና ጥቅም መጠበቅና ማረጋገጥ ነው ይላል፡፡ ይህ ህጉ በመጨረሻ ሊደረስበት ያስበውን አላማ ያመለክታል ስለዚህም የወንጀል ህጉ አላማ አጠቃላይ ህብረተሠቡን ከወንጀል ድርጊቶች መጠበቅና ሰላምን ማረጋገጥ ነው፡፡
በአንቀፁ የተገለፀው “ህዝቦች” የሚለው ቃል የሚያመለክተው ህገ መንግስቱ ለብሔር ብሔረሰቦች እና ህዝቦች ከፍተኛ ጥበቃ ያደረገላቸው በመሆኑ የወንጀል ህጉ ይህንን ሊያንፀባርቅና ህጉ ነዋሪዎቹ በግለሰብነታቸው ብቻ ሣይሆን በልዩ ልዩ ህብረት በተቋቋሙበት ሁኔታ ጥበቃ ሊደረግላቸው እንደሚገባ ነው፡፡ በተጨማሪም ዜጐቹንም ሆነ በአገሪቱ ውስጥ የሚገኙትን የውጭ ሃገር ሰዎች ስለሚያጠቃልልና ወንጀል ህግ ጥብቃ የሚያደርገው ለሰዎች ሁሉ ስለሆነ “ዜጐች” ተብሎ በቅድሞው ህግ ተገልፆ የነበረው ነዋሪዎች በሚለው ተተክቷል፡፡
የወንጀል ህጉ አላማ የነዋሪዎቹን ሰላም ማረጋገጥ ነው፡፡ ይህ በግልፅ የሚያመለክተው ከግለሰቦች መብት ይልቅ የህዝቦች መብት ቅድሚያ እንደተሠጠው ነው፡፡ ስለሆነም አንድ የወንጀል ድርጊት ሲፈፀም በህብረተሠቡ አጠቃላይ ጥቅም ላይ ጉዳት ደርሷል ተብሎ ይገመታል፡፡ በዚህም መሠረት የህዝብ ስርዓት ፣ ሰላምና ፀጥታ ሊጠበቅ የሚችለው የግለሰቦች መብት ሲጠበቅ በመሆኑ በእነዚህ መብቶች ላይ የሚደርስ ጥቃት በህዝብ ጥቅም ወይም መብት ላይ እንደተፈፀመ ወንጀል ይቆጠራል፡፡

Address

Jamo
Addis Ababa

Opening Hours

Monday 09:00 - 17:00
Tuesday 09:00 - 17:00
Wednesday 09:00 - 17:00
Thursday 09:00 - 17:00
Friday 09:00 - 17:00
Saturday 09:00 - 17:00

Telephone

+251924024402

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Tsegaye Demeke - Lawyer posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Tsegaye Demeke - Lawyer:

Share

Category