15/11/2023
።
የስር ፍርድ ቤትም አመልካች የቀረበባቸውን [የመጀመሪያ ደረጃ] የመቃወሚያ ክርክር ለመከላከል ወራሽነቴን በ1997 ዓ.ም አሳውጃለው በማለተ ያነሱትን ማስረጃና መከራከሪያ የማስረጃ አቀራረብ ስርዓቱን የተከተለ አይደለም በማለት ሳይቀበለው ቀርቷል።
ይሁንና ከሳሽ የሆነ ወገን በክሱ ላይ ተከሳሽ የሚያቀርበውን የመጀመሪያ
ደረጃ መቃወሚያ አስቀድሞ ገምቶ ለዚህ የሚረዳውን [ክርክርና] ማስረጃ ከክሱ ጋር አያይዞ እንዲያቀርብ አይጠበቅም፡፡
ከላይ ከጠቀስነው የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 245 ድንጋጌ መገንዘብ እንደሚቻለው መቃወሚያ ሲቀርብ ፍርድ ቤቱ ሌላው ተከራካሪ ወገን በመቃወሚያው ላይ የሚያቀርበውን ክርክር ከሰማ በኋላ መቃወሚያውን ለመወሰን ተገቢ መስሎ የሚገምተው ማስረጃ እንዲቀርብለት ትዕዛዝ እንደሚሰጥና በመጨረሻም የቀረበው መቃወሚያ ከማስረጃው አንፃር መርምሮ ተገቢው ብይን መስጠት ይኖርበታል።
ስለሆነም አመልካች ላቀረቡት ክስ ከተጠሪዎች የቀረበውን የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ተመልክተው መቃወሚያውን ውድቅ ለማስደረግ የበኩላቸውን ክርክር በማቅረብ ክርክራቸውንም በማስረጃ ለማስደገፍ ያቀረቡት ጥያቄ የስር ፍርድ ቤት የማስረጃ አቀራረብ ስርዓቱን የተከተለ አይደለም በማለት
ማስረጃውን ተቀብል ከቀረበው መቃወሚያና ከክሱ ይዘት አንጻር ሳይመረምር ብይን መስጠቱ ህጉን የተከተለ ሆኖ አላገኘነውም፡፡ የበላይ ፍርድ ቤቶችም ይህን ሳያርሙ ማለፋቸው የሚነቀፍ ነው፡፡