Argoba Nation Special Woreda Prosperity Party Youth Wing Office

Argoba Nation Special Woreda Prosperity Party Youth Wing Office ይህ የአርጎባ ብሔረሰብ ልዩ ወረዳ ወጣቶች ክንፍ ጽ/ቤት ፔጅ ነው

እንኳን ለ1 ሺህ 447ኛው የዒድ አል-አደሃ (የዓረፋ) በዓል በሰላም አደረሳችሁ።​የአርጎባ ብሔረሰብ ልዩ ወረዳ ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ መሃመድ ሰይድ አረቡ ለመላው ...
26/05/2026

እንኳን ለ1 ሺህ 447ኛው የዒድ አል-አደሃ (የዓረፋ) በዓል በሰላም አደረሳችሁ።

​የአርጎባ ብሔረሰብ ልዩ ወረዳ ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ መሃመድ ሰይድ አረቡ ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።

አቶ መሃመድ ባስተላለፉት መልዕክት፣ የዒድ አል-አድሃ በዓል በእስልምና እምነት ተከታዮች ዘንድ ትልቅ መንፈሳዊ ትርጉም የሚሰጠውና የአብሮነት እሴቶች በጉልህ የሚንጸባረቁበት መሆኑን ገልጸዋል። ሕዝበ ሙስሊሙ ከመቼውም ጊዜ በላይ በመተባበር፣ አብሮነትን በማጠናከር፣ እርስ በእርስ በመደጋገፍና በመቻቻል በዓሉን ሊያከብር እንደሚገባም አሳስበዋል።

​ኃላፊው አክለውም፣ የተቸገሩ ወገኖችን መርዳት የዓረፋ በዓል ዋነኛ መገለጫ መሆኑን በመጥቀስ፣ ሕዝበ ሙስሊሙ እንደ ከዚህ ቀደሙ ሁሉ አንድነቱን በማጠናከር እምነቱ በሚያዘው መሠረት አቅመ-ደካሞችን በመርዳትና ካለው ለሌለው በማካፈል በዓሉን ሊያከብር እንደሚገባ ጥሪ አቅርበዋል።

ከተገነባው ጠንካራ አንድነት ጋር የተሻለችና የበለጸገች ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ አብሮነትን፣ ወንድማማችነትንና ይቅር ባይነትን በበለጠ ማጎልበት እንደሚገባም አስገንዝበዋል።

​አቶ መሃመድ ሰይድ አረቡ በመጨረሻም፣ ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች በሙሉ ይህ የዒድ አል-አደሃ (የዓረፋ) በዓል የሰላም፣ የአንድነት፣ የመተሳሰብ፣ የደስታና የፍቅር እንዲሆንላቸው መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል።
​ዒድ ሙባረክ!

ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች በሙሉ፣ እንኳን ለ1447ኛው የኢድ አል-አድሃ (አረፋ) በዓል በሰላም፣ በጤና እና በደስታ አደረሳችሁ። ይህ ታላቅ በዓል ነቢዩ ኢብራሂም (ዐ.ሰ) ለአላህ ...
26/05/2026

ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች በሙሉ፣ እንኳን ለ1447ኛው የኢድ አል-አድሃ (አረፋ) በዓል በሰላም፣ በጤና እና በደስታ አደረሳችሁ።

ይህ ታላቅ በዓል ነቢዩ ኢብራሂም (ዐ.ሰ) ለአላህ (ሱ.ወ) ያላቸውን ፍጹም ታዛዥነት፣ ታማኝነትና ታላቅ መስዋዕትነት በተግባር ያሳዩበት፣ የእምነት ጥንካሬ የተመሰከረበት ታሪካዊና መንፈሳዊ ክስተት የሚዘከርበት ዕለት ነው።

በመሆኑም ይህንን በዓል ስናከብር አቅም የሌላቸውንና የተቸገሩትን ወገኖቻችንን በመደገፍና ማዕድ በማጋራት፣ የታመሙትንና መጠለያ ያጡትን በመጠየቅና በማፅናናት ሊሆን ይገባል።

ከዚህም ባሻገር በአካባቢያችን ያለውን ዘላቂ ሰላም፣ ፍቅርና ወንድማማችነት ይበልጥ በማጠናከር እንዲሁም ለሀገራችን ኢትዮጵያና ወረዳችን ሰላምና ብልጽግና በጋራ ዱዓ በማድረግ ልናሳልፈው ይገባል። በድጋሜ በዓሉ ለወረዳችን ማህበረሰብ እና የእምነቱ ተከታዮች የፍቅር፣ የደስታ እና የሰላም እንዲሆንልን ከልብ እመኛለሁ።

ኢድ ሙባረክ!

​አቶ መሃመድ ኑር አብዱ
የአርጎባ ብሄረሰብ ልዩ ወረዳ አስተዳዳሪ

በአርጎባ ብሔረሰብ ልዩ ወረዳ በዶሮ እርባታ ዘርፍ "የሌማት ቱሩፋት" እቅድን ለማሳካት በሰፊው እየተሰራ እንደሚገኝ ተገለጸ፤​በአርጎባ ብሔረሰብ ልዩ ወረዳ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥና የነዋ...
25/05/2026

በአርጎባ ብሔረሰብ ልዩ ወረዳ በዶሮ እርባታ ዘርፍ "የሌማት ቱሩፋት" እቅድን ለማሳካት በሰፊው እየተሰራ እንደሚገኝ ተገለጸ፤

​በአርጎባ ብሔረሰብ ልዩ ወረዳ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥና የነዋሪዎችን ተጠቃሚነት ለማሳደግ በዶሮ እርባታ ዘርፍ የ"ሌማት ቱሩፋት" መርሃ-ግብርን ስኬታማ ለማድረግ ሰፊ ጥረት እየተደረገ መሆኑን የወረዳው እንስሳት እና ዓሳ ሀብት ልማት ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ጌታቸው አሰፋ ገልጸዋል።

​ኃላፊው እንደተናገሩት፣ በልዩ ወረዳው የእንስሳት ተዋጽኦ ምርትን በማሳደግ የቤተሰብን የአመጋገብ ሥርዓት ለማሻሻልና የአካባቢውን ኢኮኖሚ ለማጠናከር በትኩረት እየተሰራ ይገኛል። በተለይም በዶሮ እርባታው ዘርፍ የተያዙ የሌማት ቱሩፋት ግቦችን ለማሳካት ዘመናዊ አሰራሮችንና ግብዓቶችን ለነዋሪው ተደራሽ የማድረግ ስራ በስፋት እየተከናወነ ነው ብለዋል።

​የሌማት ቱሩፋት ንቅናቄ በወረዳው ውስጥ ውጤታማ እየሆነ መምጣቱን ያመለከቱት አቶ ጌታቸው፤ ህብረተሰቡ በየደረጃው በንቅናቄው ላይ በንቃት በመሳተፍ የዶሮ ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ እያደረገ ያለው ጥረት የሚበረታታ መሆኑን ገልጸዋል።

24/05/2026
በደቡብ ወሎ ዞን በአርጎባ ብሄረሰብ ልዩ ወረዳ 02 ድቤ ቀበሌ ፓርቲያችን ብልፅግና የሚደግፍ ህዝባዊ የድጋፍ ሰልፍ እየተካሄደ ነው።‎ብልፅግናን ይምረጡ!‎ምልክታችን የስንዴ ነዶ ነው!
24/05/2026

በደቡብ ወሎ ዞን በአርጎባ ብሄረሰብ ልዩ ወረዳ 02 ድቤ ቀበሌ ፓርቲያችን ብልፅግና የሚደግፍ ህዝባዊ የድጋፍ ሰልፍ እየተካሄደ ነው።

‎ብልፅግናን ይምረጡ!
‎ምልክታችን የስንዴ ነዶ ነው!

በደቡብ ወሎ ዞን በአርጎባ ብሄረሰብ ልዩ ወረዳ 01 ፈጠቆማ ቀበሌ ፓርቲያችን ብልፅግና የሚደግፍ ህዝባዊ የድጋፍ ሰልፍ እየተካሄደ ነው።‎ብልፅግናን ይምረጡ!‎ምልክታችን የስንዴ ነዶ ነው!
24/05/2026

በደቡብ ወሎ ዞን በአርጎባ ብሄረሰብ ልዩ ወረዳ 01 ፈጠቆማ ቀበሌ ፓርቲያችን ብልፅግና የሚደግፍ ህዝባዊ የድጋፍ ሰልፍ እየተካሄደ ነው።

‎ብልፅግናን ይምረጡ!
‎ምልክታችን የስንዴ ነዶ ነው!

በአርጎባ ብሄረሰብ ልዩ ወረዳ በመዲና ከተማ የብልፅግና ፓርቲ የምርጫ ቅስቀሳ የድጋፍ  ሰልፍ በፎቶ
24/05/2026

በአርጎባ ብሄረሰብ ልዩ ወረዳ በመዲና ከተማ የብልፅግና ፓርቲ የምርጫ ቅስቀሳ የድጋፍ ሰልፍ በፎቶ

24/05/2026
24/05/2026
22/05/2026
22/05/2026

Address

Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Argoba Nation Special Woreda Prosperity Party Youth Wing Office posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share

Category