13/08/2026
በ2003ዓም የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ፕሮጀክት ግንባታ ሲጀመር ፕሮጀክቱ ተጠናቆ 5,150 ሜጋዋት ሀይል ማመንጨት ሲጀምር በአመት ከ1ቢሊዮን የአሜሪካን ዶላር ገቢ ያመጣል ተብሎ ነበር። አሁን ደግሞ ይህ የባለውን 5,150 ሜጋ ዋት እያመረተ ቢገኝም ሌሎቹም በአገሪቱ ውስጥ ያሉ ግድቦች ተጨምረው 1 ቢሊዮን ዶላር ገቢ አላመጡም። ምክንያቱም አጠቃላይ የተገኘው ገቢ ብር 121 ቢሊየን ብር ገደማ ሲሆን ይህ ወደ ዶላር ሲቀየር ወደ 781 ሚሊዮን ዶላር ነው የሚሆነው። እንዲሁ ነው ሆዳችንን ያጮሁት!!
ነሐሴ 7 2018
በኢትዮጵያ እየተመረተ ካለው የኤሌክትሪክ ኃይል ግማሽ ያህሉ ከህዳሴ ግድብ መሆኑ ተነገረ።
በአሁኑ ወቅት የታላቁ ህዳሴ ግድብ በሙሉ አቅሙ ማለትም 5 ሺህ 150 ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል እያመረተ መሆኑን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ነግሮናል፡፡
እየተጠናቀቀ ባለው የ2018 ዓመት እንደ ሀገር 38 ሺህ ጊጋ ዋት ሰዓት ኃይል ለማምረት ውጥን ተይዞ 35 ሺህ 671 ጊጋ ዋት ሰዓት ኃይል መመረቱንና፤ከተመረተው ግማሽ ያህሉ ማለትም 18 ሺህ 360 ጊጋ ዋት ሰዓት የተመረተው ከህዳሴ ግድብ መሆኑን የተቋሙ የኮሚኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ሞገስ መኮንን ነግረውናል፡፡
ከአፍሪካ ግዙፉ የሀይል ማመንጫ የሆነው ግድቡ ኢትዮጵያ የምታመርተውን የኤሌክትሪክ ኃይል መጠን የመጨመሩን ያክል ሃገሪቱ ለሽያጭ የምታቀርበውን የኃይል መጠንም ጨምሮታል የሚሉት አቶ ሞገስ፤
የኃይል ምርቱ ከአምናው በ23 በመቶ መጨመሩን ተከትሎ ከሃይል ሽያጭ የተገኘው ገቢም ከ75 ቢሊዮን ብር በ2018 ዓመት ወደ 121 ቢሊዮን ብር ከፍ ማለቱንም አስረድተዋል፡፡
ኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ ኃይል የማምረት አቅሟ ከዓመት ዓመት እያደገ መምጣቱን የሚናገሩት አቶ ሞገስ፤ ለዚህ ትልቁን ድርሻ የሚይዘው የህዳሴ ግድብ ነው፤ስራው ተጠናቆ ሁሉም ዩኒቶች እየሰሩ መሆኑና ባለፈው ዓመት ግድቡ በቂ ውሃ በመያዙ በሙሉ አቅሙ ማምረት ችሏል ብለዋል።
ይህም የሃገሪቱን ኃይል የማመረት አቅም 9 ሺህ 730 ሜጋ ዋት አድርሶታል ብለውናል፡፡
ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ.....
https://tinyurl.com/4337rxau
ምንታምር ፀጋው