07/25/2025
# #ለክልላዊ ማንሰራራት ጉዞ የበጎ ፍቃድ አገልግሎት አይነተኛ ሚና አለው።
በጎ ፈቃደኝነት በክልላችን ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና አካባቢያዊ ችግሮችን ለመፍታት የሚያስችል ታላቅ ተግባር ነው። ለማህበረሰባችን በችግር እና በድንገተኛ ጊዜ፣ በፈተና እና በአስቸጋሪ ሁኔታዎች ውስጥ ሁሉ ግንባር ቀደም ደራሻዎች በጎ ፈቃደኞች ናቸው።
# በክልላችን ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ ያለውን በጎ ፈቃደኝነት ተግባራት ለችግሮች ሁሉ መፍትሔ የሚሆን ታላቅ ተግባር ነው። ለዚህም ሁሉም ሰው በጎ ፈቃደኝነት በሁሉም አከባቢ አዘወትሮ መሰራት ያለበት መልካም ተግባር ሁላችንም እንገነዘባለን ።
#በክልላችን ደቡብ ኢትዮጵያ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ከማህበረሰባችን የአኗኗር ዘይቤ፣ ከሃይማኖት፣ ከባህል እና ከእምነት አስተምርሆ ጋር በጥብቅ የተቆራኘና በደስታ፣ በሀዘንና ሌሎች ሰው ሰራሽና ተፈጥሯዊ ችግሮች ሲከሰቱ የመረዳትና የመደጋገፍ የረዥም ጊዜ ታሪክ ያለው መልካም ተግባርና የማህበረሰባችን ዕሴት ነው ፡፡
#በወጣቶች አስተባባሪነት የክረምት ወራት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ለማህበረሰቡ በተደራጀ መንገድ የተለያዩ አገልግሎቶች በመሰጠት ላይ የሚገኝ ሲሆን ይህም ወጣቶችን ጨምሮ ዜጎች ለማህበረሰባቸው ብሎም ለክልላቸው በጎ አስተሳሰባቸውን፣ ጊዜያቸውን፣ ጉልበታቸውንና እውቀታቸውን እንዲያበረክቱ በማድረግ የልማት ክፍተቶችን መሙላት የሚያስችል ታላቅና መልካም ተግባር ነው ።
በክልላችን እየተከናወነ ባለው በጎ ፍቃድ አገልግሎት ሲጀመር ከነበረበት አሳታፊነቱና ምህዳር ሰፊነቱም በእጅጉ እያደገ ሁሉ ዓቀፍ ተደራሽ እየሆነ ያለ ከማህበረሰባችን የወረስነው እና ለትውልድ የምናስተላልፈው አኩር ዕሴታችን ነው ፡፡
ይህ የሚያሳየው አሁንም ወደፊትም በቅንነት ተነሳስተን ከተባበርንና በትጋት ከሰራን ችግሮቻችን ደረጃ በደረጃ መፍታትም ሆነ በዘላቂነት መቅረፍ የሚያስችል እምቅ አቅም በእጃችን ላይ ያለ መሆኑን ነው። እናም ይህን አቅማችንን አቀናጅተን በምልዓት ልንጠቀምበት ይገባል። የጋራ ቅንጅትም በእጅጉ ያሰፈልጋል ።
ተጠባቂው የክረምት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት አሁን ላይ በክልላችን በሁሉም አከባቢ በአስደማሚ ሁነታ መካሄድ ከተጀመረ ሳምንታት ተቋጥሯል።
ይህንንም ተከትሎ ክልላዊ እቅዱን መነሻ ያደረገ እንቅሰቃሴ በየአካባቢው እየተጀማመረ በመሆኑ ከአምናው በተሻለ በጎ አስተሳሰብና በጎ አስተዋጾአችንን ማበርከትም ሆነ እምቅ አቅማችንን መጠቀም የምንችልበት ዘንድሮም ክልላዊ የማንሰራራት ጉዞን እውን ለማድረግ በጋራ መቀናጀት መቻል አለብን ።
#ታዲያስ እርስዎ እንደአንድ በጎ፣ ቅን አሳቢ ዜጋ ላሉበት ማህበረሰብ፣ ለሚኖሩበት አካባቢ እና ክልላዊ ማንሰራራት ጉዞ ለማሳካት ምን ለማበርከት ተዘጋጅተዋል?
የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ትንሸ የለውም።
#ይነስም ይብዛም የእርስዎ አስተዋጾዖ ለውጥ ያመጣልና ከቅን ልቦና በመነጨ ለመልካም ስራ ዘወትር ይተባበሩ። ይጀግኑ፥ የድርሻዎን እየተወጡ የበጎ ፈቃድ አርበኛም ይሁኑ መልዕክታችን ነው።
#ደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የመቻቻል የሠላምና የብልጽግና ጉዞን እውን እናደርጋለን!!🙏