Ethio Legal Forum - ፎረም ሕጊ

Ethio Legal Forum - ፎረም ሕጊ All about law

02/12/2025

⚖️ የ ኢሜይል ማስረጃ አግባብነትና ተቀባይነት
ABRHAM YOHANES
የሰበር መዝገብ ቁጥር: 192981
📅 ሰኔ 30 ቀን 2013 ዓ/ም
(ውሳኔው ሐምሌ 2 ቀን 2013 ዓ/ም በችሎት ተነቧል)
👤 አመልካች: ወ/ሮ ገነት ራይክል
👥 ተጠሪ: ወ/ሮ መዓዛ ስዩም
📝 የጉዳዩ አጭር ማጠቃለያ
• ክርክሩ: የውርስ ይጣራልኝ ክርክር ሲሆን፣
• መነሻ: አመልካችና ተጠሪ ወላጅ እናታቸው ሟች ወ/ሮ አምሳለ መካሻ ከዚህ ዓለም በሞት ከተለዩ በኋላ፣ ሟች በሕይወት እያሉ ያፈሯቸው የሚንቀሳቀሱና የማይንቀሳቀሱ ንብረቶች ውርስ ተጣርቶ ድርሻዋ እንዲከፈላት በመጠየቅ በፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ክስ መሥርተዋል።
• የተጠሪ ክርክር: ተጠሪ በበኩላቸው አከራካሪዎቹ ንብረቶች (🏘 በአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ የሚገኘው ቤት፣ 📈 አክስዮኖች እና 🏢 አፓርትመንት) በስማቸው ያሉ የግላቸው እንጂ የውርስ ሀብት አለመሆናቸውን በመግለጽ ተከራክረዋል።
• የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ውሳኔ: ፍርድ ቤቱ፣ ንብረቶቹ በተጠሪ ስም የተመዘገቡት ሟች እናታቸው ከባለቤታቸው ጋር በነበራቸው የፍቺና የንብረት ክፍፍል ክርክር ምክንያት ንብረት ለማሸሽ 🛡 ባደረጉት ውሳኔ እንደሆነ በማስረጃ መረጋገጡን በመጥቀስ፣ አከራካሪዎቹ ንብረቶች የውርስ ሀብት ናቸው በማለት ግራ ቀኙ እንዲከፋፈሉ ወስኗል።
• የከፍተኛ ፍ/ቤት ውሳኔ: ተጠሪ የይግባኝ አቤቱታ ሲያቀርቡ፣ የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ንብረት በስሙ የተመዘገበ ሰው የንብረቱ ባለቤት ነው የሚለው የሕግ ግምት (ፍ/ብ/ሕ/ቁ. 1196) በአመልካች በአግባቡ ስላልተስተባበለ፣ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የፈጸመውን ስህተት በማረም ንብረቶቹ የግለሰብ ናቸው በማለት ወስኗል።
• የሰበር አቤቱታ: አመልካች ለፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት ያቀረቡት ቅሬታም ውድቅ ከተደረገ በኋላ፣ አመልካች መሠረታዊ የሕግ ስህተት ተፈጽሟል በማለት ለሰበር ችሎት አቤቱታ አቅርበዋል። አመልካች ክርክሩ የማስረጃ ሚዛን ጉዳይ በመሆኑ እና ንብረት የማሸሽ ዓላማን የሚያሳዩ የኢሜል ልውውጦች 📧 ቀርበው እያለ፣ ፍርድ ቤቶቹ የባለቤትነት የሕግ ግምትን አስመልክቶ የፍትሐብሔር ሕግ ድንጋጌዎችን በአግባቡ አልተረጎሙም በማለት ተከራክረዋል።

👨‍⚖️ የሕግ ትርጓሜ እና የችሎቱ ትንታኔ
የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት፣ የክርክሩን አመጣጥ እና የቀረቡትን የሕግ ነጥቦች በመመርመር እንደሚከተለው አብራርቷል፦
• 👑 የባለሀብትነት የሕግ ግምት:
o የፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 1195 የባለሀብትነት ምስክር ወረቀት የተሰጠው ሰው የንብረቱ ባለሀብት እንደሆነ እንደሚቆጠር ይደነግጋል። አከራካሪ የሆኑት ቤት እና አክስዮኖች በተጠሪ ስም የተመዘገቡ በመሆናቸው፣ ተጠሪ የንብረቱ ባለቤት ናት የሚለው የሕግ ግምት በሕጉ አግባብ የማስተባበል ግዴታ በአመልካች ላይ የወደቀ ነው። ይህ የሕግ ግምት በተቃራኒ ማስረጃ የሚስተባበል ቢሆንም፣ አመልካች ሕጉን መሠረት በማድረግ ግዴታቸውን መወጣት ይጠበቅባቸዋል።
• 💰 በገንዘቡ ላይ የተሰጠ ትንታኔ:
o ከዚህ ቀደም በሰበር መዝገብ ቁጥር 46720 ላይ የተሰጠው ውሳኔ $1,165,815.94 ዶላር የጋራ ንብረት ሆኖ እንዲካፈል መወሰኑን እንጂ፣ ይህ ገንዘብ በተጠሪ ስም በተከፈተ ሂሳብ ገቢ መሆኑን አያመለክትም። የሥር ፍርድ ቤቶችም የውርስ ሀብት የሆነ ገንዘብ በተጠሪ የባንክ ሂሳብ ቁጥር ገቢ መሆኑን የሚያሳይ ማስረጃ አለመቅረቡን አመልክተዋል። በመሆኑም አመልካች የሚካፈሉት የውርስ ገንዘብ አይኖርም።
• 🚧 የሰበር ችሎት ሥልጣን ገደብ:
o ክርክሩ ለውሳኔ ምክንያት የሆኑት ቤት እና አክስዮኖች

22/11/2025

የሰ/መ/ቁ. 241561 ግንቦት 30 ቀን 2016 ዓ.ም
በወንጀለኛ መቅጫ ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 145 ላይ አንድ ምስክር በፖሊስ ምርመራ ወቅት የሰጠው ቃል ዓቃቤ ሕግ ወይም ተከሳሹ ባመለከተ ጊዜ የተሰጠውን ምስክርነት ፍርድ ቤቱ ሊመለከተው እንደሚችል የተደነገገ ቢሆንም የዚህ ድንጋጌ መሰረታዊ አላማም በምርምራ ጊዜ ተሰጠ የተባለውን የምስክርነት ቃል በፍርድ ቤት ምስክሩ ቀርቦ ቢለውጠው ይኼው ምስክርነት እንዲቃናና ፍርድ ቤት ለያዘው ክስ ሁልጊዜ ከብደት እንዲሰጠው ለማድረግ ነው ተብሎ አይታሰብም፡፡
በፖሊስ ምርመራ ወቅት የተሰጠ የምስክሮች ቃልን እንደ ማስረጃ ፍርድ ቤት ሲቀበል በተለይ የተከሳሹን መብት ከመጠበቅ አኳያ ያሉትን መሰረታዊ መብቶች በጠበቀና ባከበረ መንገድ ሊተረጎሙ የሚገባ መሆን አለበት፡፡ ስለሆነም የወ/መ/ስ/ስ/ህ/ቁ 145 “ን” በመተርጎም በምርመራ ወቅት በፖሊስ የተሰጠን የምስክረነት ቃል ፍ/ቤቶች ሲቀበሉ እንደ ማነጻጸሪያ ማዕቀፍ ( as reference frame) የተከሳሹን መሰረታዊ መብቶች ማለትም በህገ-መንግስቱ አ.ቁ 20 /4/ መሰረት “ የቀረበባቸውን ማናቸውንም ማስረጃ የመመልከት ፣ የቀረቡባቸውን ምስክሮች የመጠየቅ… ” መብት ያለው ስለመሆኑ ኢትዮጵያ በህገ-መንግስቱ ቁጥር 13 (2) ላይ ባጸደቀቻቸው ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብቶች (UDHR) አ.ቁ 10 እና 11 ላይ እንዲሁም ዓለም አቀፍ የፖለቲካ እና ሲቪል መብቶች የቃል-ኪዳን ሰነዶች (ICCPR) አ.ቁ 14 እና 16 ላይ በዝርዝር የተከሰሱ ሰዎችን የመሰማት እና የሚቀርባቸውን ምስክሮች የማወቅና የመጠየቅ መብት እንዳላቸው እንዲሁም የወ/መ/ስ/ስ/ህ/ቁ 136(2) መሰረት አንድ በምስክርነት የተጠራ ሰው የሚሰጠው ቃል እንደ ማስረጃ ለመቆጠር ከሚያስፈልጉት ቅድሚያ ሁኔታዎች ውስጥ አንዱና ዋነኛው ምስክሮቹ እውነቱን ለመናገር ወይም ለማረጋገጥ መማል ያለባቸው መሆኑ ነው፡፡ በመሆኑም በፖሊስ ምርመራ ወቅት የሚሰጥ ምስክርነት መስቀለኛ ጥያቄ ሊቀርብበት ወይም በመሀላ ሥር ሆኖ የሚሰጥ ባለመሆኑ የወ/ስ/ስ/ህ/ቁ 145 ይህን መሰረታዊ የወንጀል ክስ-ስነስርዓት ሂደት ከግምት ያስገባ መሆን አለበት፡፡
በፖሊስ በወንጀል ምርመራ ወቅት ምስክሩ የሚሰጠዉ ቃል ልክ እንደመደበኛዉ የዳኝነት አካል ወይም የዳኝነት ነክነት ወይም መሰል ተቋም ቃለ መሃላ ፈጽሞ የሚሰጥ የምስክርነት ቃል ካለመሆኑም በተጨማሪ ምስክሩ በፖሊስ የምርመራ መዝገብ ላይ የሰጠዉ የምስክርነት ቃል እና በፍርድ ቤት የሰጠዉ የምስክርነት ቃል መካከል ልዩነት በተፈጠረ ጊዜ በፖሊስ የሰጠዉ የምስክርነት ቃል እዉነት ነዉ ነገር ግን በፍርድ ቤት የሰጠዉ የምስክርነት ቃል ሀሰት ነዉ ለማለት የምስክሩ ቃል መለያየት ብቻዉን በቂ ማስረጃ ነዉ ብሎ ለመዉሰድ የሚያስችል የህግ መሰረት የሌለው ስለመሆኑ የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በሰ/መ/ቁ. 153228 ትርጉም ሰጥቶበታል፡፡
በወ/መ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ.145 መሰረት የሚቀርብ ማስረጃ ከሌሎች ማስረጃዎች ጋር ተገናዝቦ የሚታይ እንጂ ብቻውን አመልካቾች ወንጀል መፈጸም አለመፈጸሙን የሚያሳዩ እንደ ህጋዊነት፣ ግዙፋዊነት፣ ሞራላዊነት ያሉ መሰረታዊ የወንጀል ማቋቋሚያ ፍሬ ነገሮችን የሚያሟላ አይደለም ፡፡ @ዋና ደጋፊዎችደጋፊዎች ማሳሰቢያ ይህ ሃሳብ ከውሳኔው የተወሰደ ስለሆነ ሙሉውን አንብበው የውሳኔውን ሙሉ ይዘትና መንፈስ መረዳት ይችላሉ።
firm Ethiopia

22/11/2025

🌸ወራሾች አሊያም አውራሾች ሳይቃወሙ ከወራሾች በአንደኛው በጋራ ውርስ ይዞታ ላይ የተሰራ ቤት በተመለከተ ሕጉ ምን ይላል?
🎸🎸🎸🎸🎸🎸🎸🎸🎸🎸🎸🎸🎸

🌸የወራሾች የጋራ በሆነ ይዞታ ላይ በአንደኛው ወራሽ የተሰራው ቤት በራስ ወጪ የተሰራ መሆኑ ቤቱ የሰራ ወራሽ ማረጋገጥ ይጠበቅበታል።

🌸ስለሆነም አውራሻቸው በህይወት ኖሩም አልኖሩም በይዞታው ላይ አንደኛው ወራሽ ቤቱን ሲሰራ ከአውራሻቸውም ሆነ ከሌሎች ወራሾች ቤቱ እንዳይሰራ የቀረበ ተቃውሞ የነበረ ስለመሆኑ ማረጋገጥ ይጠበቅባቸዋል።

🌸ስለሆነም በይዞታው ላይ አንደኛው ወራሽ ቤቱን ሲሰራ ከአውራሻቸውም ሆነ ከሌሎች ወራሾች ቤቱ እንዳይሰራ የቀረበ ተቃውሞ የነበረ ለመሆኑ የቀረበ ክርክርም ሆነ የተረጋገጠ ነገር ከሌለ ያለተቃውሞ የተሰራ ቤት ለመሆኑ ግምት የሚያስወስድ ነው።

🌸 በመሆኑም በውርስ ይዞታው ላይ ያለማንም ተቃውሞ በአንደኛው ወራሽ ወጪ የተሰራው ቤቱ የግል ሀብት የሚሆን ነው። የቤቱ ግምት ተከፍሎ ከሌሎች ወራሾች ጋር እኩል የሚካፈልበት የህግ አግባብ የለም። ቅጽ 27 ሰመቁ 178714

🌸በጠቅላላው በውርስ ይዞታው ላይ ያለማንም ተቃውሞ በአንደኛው ወራሽ ወጪ የተሰራው ቤቱ የግል ሀብት የሚሆን እና የቤቱ ግምት ተከፍሎ ከሌሎች ወራሾች ጋር እኩል የሚካፈልበት የህግ አግባብ የሌለ ስለመሆኑ የፌደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በቅጽ 27 በሰመቁ 178714 ላይ አስገዳጅ ውሳኔ ሰጥቷል።

22/11/2025

የእትዮጵያ የመንግስት ሠራተኞች የጡረታ መመሪያ

1⃣ ማንኛውም የመንግስት ሠራተኛ በተቀጠረው በ60 ቀናት ውስጥ ለጡረታ በማህበራዊ ዋስትና ኤጀንሲ መመዝገብ አለበት፡፡

2⃣ የጡረታ አበል ለቀጣይ ተቀማጭ የሚሆነው ገንዘብ ከሠራተኛ 7% ሲሆን ከመንግስት ደግሞ 11% በድምሩ 18% ሆኖ ለፖሊስና ለመከላከያ ግን ከሠራተኛ 7% እና ከመንግስት 25% በድምሩ 32% ነው፡፡

3⃣ ጡረታ የሚያስወጡ ምክንያቶች
1) በእድሜ ምክንያት 60 ዓመት ሲሞላው
2) በራሱ ፈቃድ
3) በጤና ጉድለት
4) በስራ ለይ በደረሰ አካል ጉዳት
5) በሞት ናቸው፡፡

4⃣ የጡረታ አበል በውክልና የሚከፈለው:-
1) በእርጅና
2) በህመም
3) ወደ ውጭ ሀገር በመሄድ
4) በትምህርት ወዳ ሌላ ቦታ በመሄድ
5) በእስራት ምክንያት ናቸው፡፡

5⃣ የጡሮታ አበል በይርጋ የሚዘጋው
1) የጡረታ አበል ጥያቄ ሳይቀርብ ወይም የተወሰነለትን ጡረታ ሳይወስድ ከ3 ዓመት በላይ ከቆየ አይከፈለውም፡፡ በቀጣይ ከአመለከተበት ቀን ጀምሮ ይከፈለዋል፡፡

2) የዳራጎት ጡረታ ሳይጠየቅ ቀርቶ ወይም የተጠየቀውን 3ዓመት ድረስ ሳይወስድ ከቆየ በይርጋ ይዘጋል (አይከፈልም)::

6⃣ በእድሜ 60 ዓመት ሲሞላው ለሠራተኛው የሚሰጥ የጡረታ አበል ስሌት:-
= ከተቀጠረበት ቀን ጀምሮ እስከ 10 ዓመት ድረስ ያለው አገልግሎት በ30% ሲባዛ ከ10 ዓመት በላይ ያለው እያንደንዱ አገልግሎት ግን 1.25 ይባዛል፡:ለምሳሌ 28 አመት አገልግሎት ያለው ስሌት 10ዓመት×30% + 18ዓመት ×1.25= 30+22.5= 52.5% ነው፡፡ በዚህም መሠረት ለጡረታ የሚያዘው ደመወዝ የመጨረሻው የ36ወራት (3ዓመት) ብቻ ስለሆነ በ3ዓመቱ ሲከፈል የነበረው ደመወዝ 5,000 ቢሆን ጡረታው 52.5% ×5,000ብር = 2,625 ብር ጡረታ ያገኛል ማለት ነው፡፡

7⃣ በጀማሪ ቅጥር ወቅት ቀንና ወር ሳይሞላ ዓ,ም ብቻ በህይወት ታሪክ ተሞልቶ ከተገኘ የጡረታ ቀንና ወር የሚያዘው በኢ/ያ አቆጣጠር ከሆነ ነሐሴ 30 ተብሎ ሲያዝ እ.ኤ.አ ከሆነ ታህሳስ 31 ቀን ተብሎ ይታሰባል፡፡

8⃣ በረሱ ፍላጎት ጡረታ የመውጣት መብት እድሜው 55 ዓመት ሲሆንና 25 ዓመት አገልግሎት ሲኖረው ሆኖ ለፖሊስና ለመከላከያ ሠራዊት ግን ከሚወጡበት ዓመት 5ዓመት ቀድሞ መውጣት ይችላሉ ፡፡

9⃣ የሟች ጡረታ የሚወርሱ ልጆች ከ18ዓመት በታች ወይም አካል ጉዳተኛ ልጅ ከሆነ 21ዓመት በታችና የሟች እናትና አባት ናቸው፡፡

🔟 ለጡረታ አበል ለማስፈፀም የሚያስፈልጉ ማስረጀዎች:-
1) በህይወት ታሪክ የተሞላው መረጃ (ጡ1እና 2)
2) የሙከራና የቋሚ ቅጥር ደብደቤ
3) የጡረታ መለያ ቁጥር
4) የ36 ወራት የደመወዝ መረጃ
5) የዝውውር፣ የደረጃ ዕድገትና የደመወዝ ለውጥ የተደረገበት ደብደቤ
6) የጋብቻ እና የልጆች ማስረጃ
7) የባለጡረታ ወይም የወራሽ ፎቶ ግራፍ
ናቸው፡፡

22/11/2025

የሰበር መዝ/ቁ 217195
****ያልታተመ****
~~
ለእኔ እና ለልጆቼ የቤት መስሪያ ቦታ ሳይሰጥ እና በቀሪው ይዞታ ላይም ካሳ ሳይከፈለኝ ይዞታውን ለሌሎች ግለሰቦች ስለሰጠብኝ ለእኔ እና ለልጆቼ የቤት መስሪያ ቦታ እንዲሰጠን፣ በቀሪው ይዞታ ላይ ደግሞ ካሳ እንዲከፈለን በሚል የሚጠየቅ ዳኝነት ላይ የአማራ ክልል የወረዳ ፍርድ ቤቶች አከራክሮ ለመወሰን ስልጣን ኣላቸው።

22/11/2025

በኢትዮጵያ ፍ/ር ሕግ መሠረት የውል መፍረስ (invalidations) እና ውል መሠረዝ(Cancelation ) የዳኝነት ጥያቄ እና መሠረታዊ ሀሳቦች.......

በፍ/ር ህጋችን የውል ግዴታ ቀሪ የሚሆኑባቸው የተለያዩ መንገዶች ሲኖሩ ከእነዚህም ሁለቱ የሆኑትን ውል መፍረስ እና ውል መሠረዝን በተመለከተ ምን ማለት እንደሆኑ፣ መሠረታዊ ልዩነታቸውን እና አንድነታቸውን በመለየት ግንዛቤ ለማስጨበጥ እንሞክራለን።

1. የውል አመሰራረት(Establishment of contract)...
ውል በሁለት ተዋዋይ ወገኖች መካከል በገዛ ፍቃዳቸው ማንም ሳያስገድዳቸው ለመዋዋል በህግ ችሎታ በተሰጣቸው ሰወች(በህግ እና በተፈጥሮ) መካከል የህጉን ውለታ በሚጠይቀው መንገድ ተገቢውን ህጋዊ የፎርም አቀራረጽ በመከተል ህጋዊ እና ሊፈጸም በሚችል መልኩ ስምምነት ሊደረግ የሚችል ነው። የፍ/ር ህግ 1676

2. ውል የሚካሄድባቸው ዘዴዎች(means of contract agreement) :- ውል በዋናነት በጹሁፍ ወይም በቃል ሊደረግ የሚችል ሲሆን እዚህ ላይ ሊታሰብ የሚገባው ነገር ግን ውሉ ሊደረግ የሚችልበትን መንገድ የውሉ አቀራረጽ በህጉ ልዩ ፎርም ሊከተል የሚገባ መሆኑን ህጉ ሲያስገድድ ተዋዋይ ወገኖች የግድ ያንን በህግ የተጣለባቸውን ስረአት ሊከተሉ ያስፈልጋል።

3. ውል መሠረዝ(cancelation of contract) የፍ/ህግ 1808 ፥1815/1/፥1817/1/ እና 2 :-በተዋዋይ ወገኖች መካከል የተደረጉ የሚጸኑ ውሎች በተዋዋይ ወገኖች መካከል እንደ ህግ ተደርጎ ሊቆጠር የሚችል መሆኑን በፍ/ር ህግ ቁጥር 1731 ላይ ተደንጎግ የተቀመጠ ነው። ይሁን እንጂ በውል አለመፈጸም ወይም አፈጻጸም ችግር ምክንያት በአንድኛው ተዋዋይ የአፈጻጸም ቸልተኝነት ወይም ጉድለት ምክንያት በሌላይኛው ወገን ላይ በመዘግየት ወይም ከውሉ ስምምነት ውጭ አካሄድ ምክንያት የከፋ ውጤት እየተከተለበት ስለመሆኑ ሲረዳ የውል ይሰረዝልኝ ጥያቄ በፍ/ር ህግ ቁጥር 1771 መሠረት ሊያቀርብ ይችላል። ይህን ተከትሎ የውል መሠረዝ ስረአት ሊፈጸም ይችላል ማለት ነው።

ከዚህ የምንረዳው ውልን በሚጸና መንገድ ተዋዋይ ወገኖች ካደረጉ በኋላ በውሉ አፈጻጸም ጉድለት ምክንያት ውሉ ቀሪ የሚሆንበት መንገድ ሲሆን በዚህ ምክንያት በውሉ አፈጻጸም ችግር ምክንያት ተጎጂ ነኝ ውሉ ሊሰረዝ ይገባል የሚለው አካል ዳኝነት ስልጣን ባለው ፍርድ ቤት በመጠየቅ ውሉ እንዲሰረዝለት መጠየቅ ይችላል።

እዚህ ላይ ጠያቂው ወሉን ተገዶ ሌላይኛው ወገን ከሚፈጽም ይልቅ መሠረዙ ምክንያታዊ እና ውጤታማ ስለመሆኑ ተገቢወውን ጥናት ሊያደርግ ያስፈልጋል። የፌ/ጠ/ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት 248670 ይመልከቱት።

4. ውል መፍረስ(invalidation) የፍ/ር ህግ 1815/1/ 1817 (ውል ከመሠረቱ አራት በውል ውስጥ መካተት የሚገባቸውን መሠረታዊ ነገሮች በሟሟላት ሊመሠረት የሚገባ እንደሆነ በህግ ቁጥር 1676 ላይ የተቀመጠ ነው።

4.1 ፈቃድ ሲሆን ...
ይህ ያለ ማንም አሰገዳጅነት ተዋዋይ ወገኖች ነጻ ሆነው ስምምነት የሚፈጽሙበት ነው።

4.2 የህግ ችሎታ ... ይህ ተዋዋይ ወገኖች ውልን ለመዋዋል የሚያስችል ስልጣን ሊኖራቸው የሚችል መሆኑን የሚያሳይ ሲሆን በእድሜ ለምሳሌ ከ18 በላይ መሆኑ በህግ በተለየ ሁኔታ ካልተደነገገ በቀር እድሜ 18 እና ከዚያ በላይ መሆኑ፣ይህን ለማድረግ የህግ ወይም የፍርድ ክልከላ የሌለበት ስለመሆኑ በአጠቃላይ ይህን የውል ስምምነት ለማድረግ በህግ ሙሉ ስልጣን ያለው ስለመሆኑ ሊረጋገጥ የሚገባ ነው።

22/11/2025

ያልታተሙ የፌደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ዉሳኔ አስገዳጅነት አላቼዉ❓(ጠበቃ አደም ሰይድ ከማል)
✅✅✅✅✅✅✅✅✅✅✅✅✅✅✅✅✅
ያልታተሙ የሰበር ዉሳኔዎች አስገዳጅነት ላይ በፌስቡክ ገጽ ተከታታዮቼ በርካታ ጥያቄዎች ይቀርባሉ፤ስለሆነም በአጭሩ ያልታተሙ የሰበር ዉሳኔዎች አስገዳጅነት ላይ አጭር ዳሰሳ እናደርጋለን ፡፡ያልታተሙ የሰበር ዉሳኔዎች የምንላቼዉ ከቅጽ 1-27 ባሉት ህትመቶች ዉስጥ ያልተካቱትን ማለታችን ነዉ፡፡እነዚህ የሰበር ዉሳኔዎች በጠበቃ አደም ሰይድ ከማል እምነት አስገዳጅ ናቼዉ ባይ ነኝ ለምን ካለችሁኝ በሚከተሉት ምክንያቶች፡፡
1. የፌዴራል ፍርድ ቤቶች ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 1234/2013 አንቀጽ 10(2) የፌደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ከአምስት ያላነሱ ዳኞች በተሰየሙበት የሰበር ሰሚ ችሎት የሚሰጠዉ የህግ ትርጉም ዉሳኔዉ ከተሰጠበት ቀን ጀምሮ በየትኛዉም የክልል ሆነ የፌደራል ፍ/ቤት አስገዳጅ ነዉ በማለት ይደነግጋል፡፡በዚህ ድንጋጌ መሰረት አስገዳጅነቱ ዉሳኔዉ ከተሰጠበት ቀን ጀምሮ እንጅ በቅጽ ከታተመበት ጀምሮ የሚል ቃል አልተቀመጠም፡፡አሁን ባለዉ የፌደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ነባራዊ ሁኔታ ከቅጽ 1-27 ለህትመት የበቃ ቢሆንም በርካታ ዉሳኔዎች በቅጽ ታትመዉ የሚወጡት ከአመታት በኋላ ነዉ፡፡ለምሳሌ በቅጽ 27 ላይ መዝገብ ቁጥር 200023 ዉሰኔ የተሰጠዉ ጥቅምት 29/2014 ዓ/ም ሲሆን በቅጽ ታትሞ የወጣዉ ደግሞ 2017 ዓ/ም ነዉ፡፡በተመሳሳይ በቅጽ 27 ላይ መዝገብ ቁጥር 201028 ዉሰኔ የተሰጠዉ ጥቅምት 05 /2014 ዓ/ም ሲሆን በቅጽ ታትሞ የወጣዉ ደግሞ 2017 ዓ/ም መጋቢት ነዉ፡፡በቅጽ 26 ላይ መዝገብ ቁጥር 205626 ዉሰኔ የተሰጠዉ ጥቅምት 39/2014 ዓ/ም ሲሆን በቅጽ ታትሞ የወጣዉ ደግሞ 2016 ዓ/ም ነዉ፡፡እንድህ አይነት በርካታ የሰበር ዉሳኔዎችን እናገኛለን፡፡ታድያ እነዚህ ዉሳኔዎች በቅጽ ታትመዉ እስካልወጡ ድረስ አስገዳጅ አይደሉም የምንል ከሆነ በአንቀጽ 10(2) የፌደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ከአምስት ያላነሱ ዳኞች በተሰየሙበት የሰበር ሰሚ ችሎት የሚሰጠዉ የህግ ትርጉም ዉሳኔዉ ከተሰጠበት ቀን ጀምሮ በየትኛዉም የክልል ሆነ የፌደራል ፍ/ቤት አስገዳጅ ነዉ ከሚለዉ ድንጋጌ ጋር የምንላተም ይሆናል፡፡
2. ሁለተኛዉ መከራከሪያየ ራሱ የሰበር ሰሚ ችሎቱ ያልታተሙ የሰበር ዉሳኔዎችን በዉሳኔዉ ላይ ሲጠቅስ መስተዋሉ ነዉ፡-የሰበር ሰሚ ችሎቱ አስገዳጅ የህግ ትርጉም በሚሰጥባቼዉ ዉሳኔዎች ያልታተሙ የሰበሩን መዝገብ መጥቀስ እየተለመደ መጥቷል፡፡ለምሳሌ በሰበር መዝገብ ቁጥር 44218 ችሎቱ በመዝገብ ቁጥር 43197 የሰጠዉን አስገዳጅ የህግ ትርጉም ሲጠቅስ ይስተዋላል፡፡ነገር ግን ይህ መዝገብ በቅጽ ታትሞ የወጣ አይደለም፡፡ለጊዜዉ መጥቀስ ያልቻልኳቼዉ በርካታ ተመሳሳይ መዛግብቶችን ተመልክቻለሁ፡፡ይህ ደግም ያልታተሙ የሰበር የሰበር ዉሳኔዎችን አስገዳጅነት ሰበሩም ተቀብሎታል ብሎ ድምዳሜ ላይ መድረስ ይቻላል፡፡
3. በተመሳሳይ ስነ-ስርዓትና የዳኛ ቁጥር የሚሰጡ መሆናቼዉ ፡፡የታተሙትም ሆነ ያልታተሙት የሰበር ዉሳኔዎች በተመሳሳይ የችሎት ስረዓት፤በተመሳሳይ ፍ/ቤት፤በተመሳሳይ የዳኛ ቁጥር እና ተመሳሳይ ደረጃ ላይ በሚገኙ ዳኖች የሚሰጡ ዉሳኔዎች ናቼዉ፡፡የሁለቱ ልዩነት የታተሙት ተጠቃሎ በመጽሐፍ መልክ የወጡ ሲሆን ያልታተሙት ደግሞ ተበታትነዉ ለየብቻ መገኘታቼዉ ነዉ፡፡ለህትመት ማብቃት ያለማብቃት የጠቅላይ ፍ/ቤት ስራ ነዉ፡፡በተጨማሪም ጠቅላይ ፍ/ቤቱ ካልታተሙት የሰበር ዉሳኔዎች ዉስጥ የተወሰኑትን አጠቃሎ በቅጽ ሲያሳትም የታተሙት ካልታተሙት የሚለይበት ግልጽ መስፈርትም የለዉም፡፡

03/11/2025

ሓደ ዳይና ባዕሉ ተወዲኡ ዝሓደረ እዩ ዝብል መቃወምያ ኣልዒሉ መዝገብ ክዓፁ ይኽእል ዶ?

ሰበር መዝገብ ቑፅሪ 182044 ዕለት 25/06/207 ዓ/ም

ዓይነት ጉዳይ ፦ ተኸሳሲ ተፀዊዑ መልሲ ኣብ ዘይሃበሉ ጉዳይ ዳይና ባዕሉ ተወዲኡ ሓዲሩ ክብል ይኽእል ዶ፣ ብርግፅ ጉዳዩ ከ ተወዲኡ ዝሓደረ ደዩ ኣይኾነን ንዝብል ዝተውሃበ ውሳነ እዩ።

1. ዝቐረበ ጥርዓን፡ ተፀዋዒት ብውህብቶ ይኹን ብግዝኢት ከይተመሓላለፈ ገዛይ ብሽማ ኣስሪሓ ሒዛቶ ስለእትርከብ እቲ ካርታ ይምኸነለይ ዝብል እዩ። ተፀዋዒ ብዘየለሉ ክቐርብ ሰለዘይኸኣሉ ጉዳዩ ብዘየለሉ ንክርአ ኣዚዙ።

2.ይኹን እምበር ኣብ ግዜ ክሲ ምስማዕ ምስ ኣመልካቲትን በዓል ገዛኣን ህውከት ፈጢርኩም ተባሂልና ተኸራኺርና ዝተፈጠረ ህውከት የለን ተባሂሉ ጉዳዩ ብኣፈፃፀም ተወዲኡ ዝሓደረ እዩ ብምባል ነቲ ቤት ፍርዲ ስለዝገለፁ እቲ ተወዲኡ ሓዲሩ ዝተበሃለ መዝገብ ስሒቡ ተወዲኡ ሓዲሩ እዩ ብምባል ዓፅይዎ።

3. ይኹን እምበር ኣመልካቲት፦ ቕድም ክብል ዝነበረ ጉዳይ ህውከት ይወገደለይ ዝብል እምበር ናይ ትሕዝቶ ይኹን ናይ ካርታ ይምኸነለይ ዝብል ክሲ ስለዘይኾነ፣ ተፀዋዒት ቐሪባ ኣብ ዘይተኸራኸረትሉን ካርታ ኣብ ዘይመኸነሉን ተወዲኡ ዝሓደረ ምባሉ ኣግባብነት የብሉን ብምባል ወሲኑ።

ውሳነ ሰበር

1. ብፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቑ 244(3) ተኸሳሲ ዘየቕረቦም መቃወምያታት ከምዝሓደጎም ተጌሮም ከመዝውሰዱ ብግልፂ ተቐሚጡ እዩ። ይኹን እምበር ተኸሳሲ ቐሪቡ መቃወምያ ኣብ ዘየልዐለሉ ወይ ድማ ቤት ፍርዲ ብዝኾነ መንገዲ ኣብ ዝፈለጠሉ ግዜ ዝህልዎ ሚና ዝምልከት እንታይ እዩ ብዝብል ሪኦሞ።

2. ኣብ መዝገብ ቑፅሪ 36780 ናይ ፍረ ነገር ጭብጢ ኣብ ክልቲኡ ተመሳሳሊ እንተኾይኑን፣ እቲ ናይ መጀመርታ ግን ናይ መወዳእታ ፍርዲ ዝዓረፈሉ ከምዝኾነ ተቓውሞ ከምዝቐረበሉ እንተተረጋጊፁ ተወዲኡ ሓዲሩ እዩ። ነዚ ውሳነ ወሃቢ(ሪፈር) ጌሩ ድማ ኣብ መ/ቑ 124660 ተወሳኺ ውሳነ ሂቡ እዩ። ሓፂር ትሕዝቶኡ ድማ ኸሳሲ ይኹን ተኸሳሲ ኣብ ዘየልዐሉዎ ናይ ፍትሕን ናይ ንብረት ምቅሊትን ዝምልከት መቃወምያ ባዕሉ ቤት ፍርዲ ኣልዒሉ ምዕፃዉ ስነ ስርዓታዊ ዋላ ኣይኹን ብውፅኢት ደረጃ ተወዲኡ ኣብ ዝሓደረ ጉዳይ መሊስኻ ምኽሳስ ኣግባብነት ስለዘይብሉ ኣፅኒዑዎ እዩ።

3. ይኹን እምበር እዚ ጉዳይ ተኸሳሲ ብዘየለሉ ኣብ ዝርእየሉ ግዜ ወይ ተኸሳሲ ቐሪቡ መቃወምያ ኣብ ዘየልዐለሉ ግዜ ጉዳዩ ብዘየለሉ እንትርአ ዝህልዎ ውፅኢት ኣብቶም ክልተ ናይ ሰበር መዛግብቲ ኣይተነፀረን። ይኹን እምበር ተመሳሳሊ ዕላማ ስለዘሳኽዕ ነዚ ጉዳይ እውን ተፈፃምነት ኣለዎ ተባሂሉ እዩ።

4. እዚ ጉዳይ ተወዲኡ ዝሓደረ ድዩ ኣይኾነን ንዝብል እንትርአ ድማ ኣብ ናይ መጀመርታ መዝገብ ህውከት ተፈጢሩ ዶ ኣይተፈጠረን ዝብል እንትኸውን ኣብቲ ናይ ሐዚ መዝገብ ድማ ናይቲ ንብረት በዓል ዋና መን እዩ? ዝብል ስለዝኾነ ተወዲኡ ዝሓደረ እዩ ዝበሃል ኣይኾነን ብምባል ወሲኑ ።
ኣየ ሰበር ሕውስውስ ኮ ኾይና😛😛🥸

ሎሚ ድማ ናይ ይግበአኒ ሰማዒ ቤት ፍርዲ ቅሬታ ናይ ምስማዕ ደረት-ስልጣን (scope of hearing appeal) ኣመልኪቱ ምስ ፍ/ስ/ስ/ሕ/ቑ 182(1) ን 329(1) ብምሙርኳዝ ፌዴራል ...
11/10/2025

ሎሚ ድማ ናይ ይግበአኒ ሰማዒ ቤት ፍርዲ ቅሬታ ናይ ምስማዕ ደረት-ስልጣን (scope of hearing appeal) ኣመልኪቱ ምስ ፍ/ስ/ስ/ሕ/ቑ 182(1) ን 329(1) ብምሙርኳዝ ፌዴራል ሰበር መጋባእያ ዝሃቦም ሰለስተ ናይ ሰበር ውሳነታት ክንርኢ ኢና።

ብመጀመርታ እንሪኦ መዝገብ ቑፅሪ 37761 ዝምልከት እዩ። ሓፂር ትሕዝቶኡ ድማ ከምዝስዕብ እዩ።

1. ኸሳሲ ናይ መኪና ፅገና ዝምልከት ምስ ተኸሳሲ ብዝተዋዓዓልናዮ መሰረት ኣነ ነፃ ናይ ሞያ ኣገልግሎት ክህብ፣ ተኸሳሲ ድማ ንመፀገኒ ዘድልዩ መለዋወጢ ኣቑሑት ገንዘብ ክትእ እዩ ኔሩ ይኹን እምበር ንመለዋወጢ ዘውፃእኹዎም ወፃእታት ተኸሳሲ ሰለዘይኸፈለኒ ክኸፍለኒ ይግባእ ብምባል ናይ ተኸሳስነት ክሲ ኣቕሪቡ። ሱር ቤት ፍርዲ(ፌዴራል መጀመርያ ደረጃ ቤት ፍርዲ) እዞም ንብረታት ከምዘይተጠቐመሎም ክሳብ ዘይከሓደ ክትክእ ይግባእ ብምባል ወሲኑ።

2. ይኹን እምበር እዚ ጉዳይ ብይግብአኒ ዝርኣየ ፌዴራል ማእኸላይ ቤት ተኸሳሲ ተኸሳሲ ኣብ ሱር ቤት ፍርዲ ዘየቕረቦ “ኣነ ንኸሳሲ ናይ መለዋወጠ ኣቑሑት ንክግዝእ ኣይፈቐድኹን ዝብል መልስን ናይ ክርክር ምኽንያትን ዘየቕረበ እናሃለወ” ካብ ኣፍልጦይ ወይ ድማ ካብ ፍቃደይ ወፃኢ እዮም ተገዚኦም ብዝብል ዘቕረቦ ቅሬታ መሰረት ብምግባር ዝወፀ ናይ ኣቑሑት መለዋወጢ ክኸፍል ኣይግደድን ብምባል ስዒርዎ። ናብ ላዕለዋይ ቤት ፍርዲ ፌዴራል እንተኸደ እውን ፀኒዑ።
3. ይኹን እምበር ጉዳዩ ኣብዚ ልዕል ክብል ዝተገለፀ መዝገብ ቑፅሪ ዘተኣናገደ ፌዴራል ሰበር መጋባእያ ተኸሳሲ ኣብ ሱር ቤት ፍርዲ “ኣነ ንኸሳሲ ናይ መለዋወጠ ኣቑሑት ንክግዝእ ኣይፈቐድኹን” ዝብል መልስን ናይ ክርክር ምኽንያትን ዘየቕረበ ብኡ ልክዕ ዝተተሓዘ ጭብጢ እውን ዘየለ እናሃለወ ብይግብአኒ ደረጃ ሓዱሽ መከራኸሪ ምኽንያት ምቕራቡ ይኹን እዚ መከራኸሪ ምኽንያት ተቐቢሉ ብይግብአኒ ምውሳኑ ይግብአኒ ሰማዒ ቤት ፍርዲ ኣብ ፍ/ስ/ስ/ሕ/ቑ 182(1) ብዋናኡ ደማ ፍ/ስ/ስ/ሕቑ 329(1) ዝጠሓሰ እዩ ብምባል ውሳነ ሱር ቤት ፍርዲ ኣፅኒዑዎ እዩ።

መበል ኻልኣይ ድማ መዝገብ ቑፅሪ 25026 እንትኸውን ሓፂር ትሕዝቶኡ ድማ ከምዝስዕብ እዩ።

1. ኸሳሲ ንተኸሳሲ ዝገዛእኹዎ ገዛን ቦታን ከረክበኒ ፍቓደኛ ሰለዘይኾነ የረክበኒ ብምባል ኣለኒ ዝብልዎ መረዳእታታት ኣተሓሒዙ ምስ ኣቕረበ ተኸሳሲ መፀዋዕታ ፈሊጡ ብዘይምቕራቡ ብዘየለሉ ተራአዩ። ስዒቡ ድማ ውዕሊ ከምዘሎን ከምዝተገዝአን ኸሳሲ ብመረዳእታ ስለዘረጋገፀ ንከረክብ ተባሂሉ ተወሲኑ። እዚ ብዘየለሉ ዝተውሃበ ውሳነ እውን ኣይተልዓለን።

2. ይኹን እምበር ተኸሳሲ ብይግብአኒ ጥራሕ “እዚ ዝቐረበ ውዕሊ ኣብ መዝጋቢ ኣካል ስለዘይፀደቐ ኣግባብነት የብሉን” ዝብሉን ኻልኦት ናይቲ ውዕሊ ሕጋውነትን ፎርማሊትን መሰረት ዝገበሩ ቅሬታት ምስ ምስኣቕረበ በቶም ዝቐረቡ ቅሬታት ሱር ቤት ፍርዲ ዝሃቦ ውሳነ ስዒርዎ።

3. ይኹን እምበር ናይቲ ውዕሊ ሕጋውነትን ካልኦት ዝምልከቱ መከራኸሪ ነጥብታትን ተኸሳሲ ኣብ ሱር ቤት ቐሪቡ ስለዘይተኸራኸረሎምን ስለዘይቐረበን፣ ኣብ ይግበአኒ ሰማዒ ቤት ፍርዲ ከቕርቦምን፣ ይግብአኒ ሰማዒ ቤት ፍርዲ እውን ነዚ ተቐቢሉ ምስዓሩ ስነ ስርዓታዊ ኣይኾነን ብምባል ምስ ፍ/ስ/ስ/ሕ/ቑ 182(1) ፀሪሑ ነቲ ናይ ወረዳ ቤት ፍርዲ ውሳነ ኣፅኒዑዎ።

4. (ብተዘዋዋሪ መንገዲ ዘይንቀሳቐስ ንብረት ውዕሊ መሸጣ ኣመልኪቱ ዝቐርብ ክሲ ተኸሳሲ መልሲ እንተይኣቕረበ ብዘየለሉ እንተቐፂሉ ሕጋውነት እዚ ውዕሊ ምስ ፍ/ሕ/ቑ 1723 ተሓሳቢ ጌሩ ባዕሉ ቤት ፍርዲ ጭብጢ ከልዕል ኣይኽእልን ዝብል ትሕዝቶ ዘለዎ ስለዝኾነ ምስቲ “ተኸሳሲ ብዘየለሉ እንትርአ ከምዘይኣመነ ተሓሳቢ ተጌሩ ጭብጥን መርትዖን ክንፀር ኣለዎፅ” ብምባል ኣብ ኻልእ መዝገብ ዝተውሃበ ውሳነ ብኸመይ ይሳነ ንዝብል ሕቶ የልዕል እዩ።

ናይ መወዳእታ ድማ መዝገብ ቑፅሪ 31547 እንትኸውን ካብ መቐለ ዝኸደ እዩ።

1. ኸሳሲት ኣብ ልዕሊ 7 ተኸሰስቲ ካብ ፍቓደይ ወፃኢ ናይ ውርሲ ሃፍቲ ስለዝሸጡ ብፅሒተይ ይኽፈሉኒ ብምባል ዳይነት ምስ ሓተተት ወረዳ ቤት ፍርዲ እቲ ዝግብኣ ኢሉ ዘኣመኖ መጠን ገንዘብ ወሲኑላ።

2. ይኹን እምበር ብይግብአኒ ዝርኣየ ናይ ናይ ክልል ትግራየ ሰበር መጋባእያ ካብ 1-6 ዝነበሩ ተኸሰስቲ ናይ ከሳሲት ፍቓድ ከይረኸቡ እዚ ገዛ ስለዝሸጡ እዚ ድማ ኣግባብነት ስለዘይብሉ እዚ ገዛ ንኸሳሲትን ካብ 1-6 ዘለዉ ተኸሰስትን ክኸውን፣ 7ይ ተኸሳሲ (ዓዳጊ) ግን እቲ ናይ ዕድጊት ውዕሉ ክፈርስ ወሲኖም። (ንእሽተይ ኽምስ ተብል እያ)

3. ይኹን እምበር ፌዳራል ሰበር መጋባእያ ኣብ ሱር ቤት ፍርዲ ዝተሓተተ ዳይነት ብፅሒት ገንዘብ ይውሃበኒ ዝብል እናሃለወ ላዕለዋይ ቤት ፍርዲ ክልል ትግራይ ኣብ ምፍራስን ምፅናዕን ውዕሊ ኣመልኪቱ ከም መከራኸሪ ጭብጢ ጌሩ እቲ ውዕሊ ንክፈርስ ዝተውሃበ ውሳነ ኣግባብነት የብሉን።
4. ኸሳሲት ካብ መፈለምታኡ ዘቕረበቶ ቅሬታ ኣብ ሱር ቤት ፍርዲ መከራኸሪ ነጥቢ/ Point of Dispute/ ዘይነበረ ስለዝኽን ክብዚ ብተወሳኺ ዘይነበረ ጭብጢ ስለዝኾነ ፣ ይግብአኒ ሰማዒ ቤት ፍርዲ ኣብ ሱር ቤት ፍርዲ ዘይነበረ ጭብጢ ይኹን ዘይነበረ መከራኸሪ ነጥቢ / Point of Dispute/ መሰረት ጌሩ ዝሃቦ ውሳነ ኣብ ዘይስልጣኑን፣ ንፍ/ስ/ስ/ሕ/ቑ 182(1) ዝፃረርን እዩ ብምባል ናይ ወረዳ ቤት ፍርዲ ውሳነ ኣፅኒዑ፣ ናይ ላዕለዋይ ቤት ፍርዲ ውሳነ ስዒርዎ። እዚ ውሳነ ብወገነይ ብጣዕሚ መምሃራይ እዩ ኔሩ። ይኹን እምበር ኣከራኻርነቱ ግን ቐሊል እዩ ኔሩ። ምኽንያቱ ኸሳሲት ብሽም ይግብአኒ ሓዱሽ ክሲ፣ ሓዱሽ ዳይነት እያ ኣቕሪባ ምባል ይከኣል።

07/08/2025
1. ኢንሹራንስ ካምፓኒ ብናይ በዓልዋና ተሽከርካሪ ጥፍኣት ንዝበፅሐ ጉድኣት ካሕሳ ክኸፍል ሓላፍነት የብለይን ዝብለሉ ናይ ሕጊ ኣግባብ ከምዘየለ።2. ናይ ኢንሸራንስ ካምፓኒ ዘለዎ መማረፂ ካሕ...
23/07/2025

1. ኢንሹራንስ ካምፓኒ ብናይ በዓልዋና ተሽከርካሪ ጥፍኣት ንዝበፅሐ ጉድኣት ካሕሳ ክኸፍል ሓላፍነት የብለይን ዝብለሉ ናይ ሕጊ ኣግባብ ከምዘየለ።
2. ናይ ኢንሸራንስ ካምፓኒ ዘለዎ መማረፂ ካሕሳ ምስኸፈለ እቲ ዝተኸፈለ ካሕሳ ንክምለሰሉ ዓርሱ ዝኸኣለ ዳይነት ምሕታት ጥራሕ ከምዝኾነ
3. ኢንሹራንስ ካምፓኒ ካብ ዝኣተዎ ውዕሊ ንላዕሊ ክክሕስ ዋላ ዘይግደድ እንተኾነ እቲ ክፍሊት ብሰዓቱ ቐሪቡ ብዘይምኽፋሉ ብመሰረት ፍ/ስ/ስ/ሕ/ቑ 462 ንዝወፀ ወፃኢ ብተወሳኺ ክኸፍል ከምዝግባእ ኣብ መፅሓፍ 25 ቑፅሪ ሰበር መዝገብ 196878 ዝተውሃበ ውሳነ

Shout out to my newest followers! Excited to have you onboard! Henok Gebremaryam, Mulu Belete, Mule Araya, Mulugeta Mese...
23/07/2025

Shout out to my newest followers! Excited to have you onboard! Henok Gebremaryam, Mulu Belete, Mule Araya, Mulugeta Mesele, Zinabu T Abreha, Gashe Mengstu, Angesom Gwahd, Haftamu Gebru Ferede, Huluf Temesgen, Kidus Kindeya, Amanuel Kidanemariam, Dirriba Tura, ግዜ ለኩሉ, Kidu Hailu, Gebremeskel Mebrahtu, Muez Abay, ኣብረሃለይ ኣለነ, G Slasie G Amlak, Abraham Brhane

Address

Tigrai
Maych'ew

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ethio Legal Forum - ፎረም ሕጊ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share