Waajjiira Haqaa Bul/Mag/Kamisee የከሚሴ ከተማ አስተዳደር ፍትህ ጽ/ቤት

  • Home
  • Ethiopia
  • Kemise
  • Waajjiira Haqaa Bul/Mag/Kamisee የከሚሴ ከተማ አስተዳደር ፍትህ ጽ/ቤት

Waajjiira Haqaa Bul/Mag/Kamisee የከሚሴ ከተማ አስተዳደር ፍትህ ጽ/ቤት Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Waajjiira Haqaa Bul/Mag/Kamisee የከሚሴ ከተማ አስተዳደር ፍትህ ጽ/ቤት, Lawyer & Law Firm, Kemise 05, Kemise.

07/07/2023
12/05/2023
20/03/2023
ሀሰተኛ ሰነዶችን በመጠቀም የአንድን ግለሰብ ቤት ከባለቤቱ ዕውቅና ውጭ በ11.5 ሚሊዮን ብር የሸጡ የመሬት አስተዳደር እና ወሳኝ ኩነት ጽ/ቤት ሰራተኞችን ጨምሮ ሶስት ተከሳሾች ላይ በከባድ ...
08/12/2022

ሀሰተኛ ሰነዶችን በመጠቀም የአንድን ግለሰብ ቤት ከባለቤቱ ዕውቅና ውጭ በ11.5 ሚሊዮን ብር የሸጡ የመሬት አስተዳደር እና ወሳኝ ኩነት ጽ/ቤት ሰራተኞችን ጨምሮ ሶስት ተከሳሾች ላይ በከባድ የሙስና ወንጀል ክስ ተመሰረተ፡፡

በኢ.ፌ.ዲ.ሪ ፍትህ ሚኒስቴር የጠቅላይ ዐቃቤ ህግ ዘርፍ የሙስና ወንጀል ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ጀነራል ዐቃቤ ህግ 1ኛ ዳንኤል ተስፋዬ ፣ 2ኛ ያሬድ በየነ፣ 3ኛ አድማሱ ሙላቱ፣ 4ኛእስራኤል ደጀኔ እና 5ኛ ብርሃኑ ዳግም በተባሉ ተከሳሾች ላይ ፈጸመዋል ባለው ከባድ የሙስና ወንጀል በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ የሙስና ወንጀል ችሎት ህዳር 21 ቀን/2015 ዓ.ም 4 ክሶችን መስርቶባቸዋል፡፡

የተከሳሾችን የዋስትና መብት ጥያቄ በተመለከተ የተከሰሱበት የህግ ድንጋጌ ዋስትና የሚያስከለክል በመሆኑ ጉዳያቸውን በማረሚያ ቤት ሆነው እንዲከታተሉ ዐቃቤ ህግ በጠየቀው መሰረት ፍርድ ቤቱ ጉዳያቸውን በማረሚያ ቤት ሆነው እንዲከታተሉ አዟል፡፡

የዐቃቤ ህግ መዝገብ እንደሚያስረዳው በ1ኛ ክስ በ1ኛ፣ በ2ኛ እና በ3ኛ ተከሳሾች ላይ ብቻ ሲሆን 1ኛ ተከሳሽ በአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ ወረዳ 05 ወሳኝ ኩነት ጽ/ቤት ሲስተም አድሚኒስትሬተር ሆኖ ሲሰራ እንዲሁም 2ኛ ተከሳሽ በክፍለ ከተማ የመሬት ልማትና አስተዳደር ጽ/ቤት ውስጥ ረዳት የቅየሳ ባለሙያ ሆኖ ሳለ በተሰማሩበት የስራ ዘርፍ በግል ስራ ከሚተዳደረውና በሙስና ወንጀል ልዩ ተካፋይ ከሆነው 3ኛ ተከሳሽ ጋር በመመሳጠር ተገቢ ያልሆነ ጥቅም ለራሳቸው ለማግኘት በማሰብ በወረዳው የሚገኘውን የአቶ ግደይ ገብረእግዚያብሄርን ቤት በህገ-ወጥ መንገድ በመሸጥ ለግል ጥቅማቸው ለማዋል 1ኛ ተከሳሽ ባልተሰጠው ስልጣን ለ3ኛ ተከሳሽ ከወረዳው በአቶ ግደይ ገ/እግዚያብሄር ስም ሀሰተኛ የነዋሪነት መታወቂያ ካርድ እንዲሁም ያላገባ ምስክር ወረቀት አዘጋጅቶ ይሰጠዋል፡፡

3ኛ ተከሳሽም የወጣለትን ሃሰተኛ መታወቂያ በመጠቀም ከዳሽን ባንክ የሂሳብ ቁጥር ከከፈተ በኋላ አቶ ግደይ እንደሆነና ቤቱ የእርሱ መሆኑን ገልጾ ይዞታውን ለመሸጥ እንደሚፈልግ ተናግሮ ወሰን ሃ/ማርያም የተባለ የግል ተበዳይ ቤቱን ለመግዛት ይቀርባል፤ ሀሰተኛ የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ ኮፒ ቤቱን ለመግዛት ለቀረበው ለአቶ ወሰን በመስጠት የይዞታው ባለቤት መሆኑን እንዲያምን በማድረግ ይዞታውን በ11 ሚሊየን 500 ሺ ብር ለመሸጥ በመስማማት በዳሸን ባንክ በከፈተው የሂሳብ ቁጥር በተለያዩ ቀናት የቅድመ ክፍያ ብር 5,ሚሊየን 300ሺ ይወስዳል፡፡

2ኛ ተከሳሽም ይዞታው በይዞታው ትክክለኛ ባለቤት በአቶ ግደይ ገ/እግዚአብሄር አማካኝነት የይዞታ ይመዝገብልኝ አገልግሎት ጥያቄ ቀርቦ ሂደቱ በእሱ እንዲከናወን ሃላፊነት ተሰጥቶት በነበረበት ወቅት ያገኘውን መረጃ አሳልፎ ለ3ኛ ተከሳሽ በመስጠትና 3ኛ ተከሳሽ ከግል ተበዳይ ወሰን ሃ/ማርያም ጋር ባደረገው ውል መሰረት ካርታው ተመዝግቦ ሲመጣ የአጠቃላይ የሽያጩን ቀሪ 6,200,000 ሺ ብር እንደሚከፈለው በተዋዋለው መሰረት የካርታውን ዝግጅት በመጨረስ የአቶ ግደይ ገ/እግዚአብሄርን ይዞታ በህገ-ወጥ መንገድ እዲሸጥ በማድረግ ለዚህም ስራው ከ3ኛ ተከሳሽ 150,000 ሺ ብር፣ ከ4ኛ ተከሳሽ 200,000 ሺ ብር በአጠቃላይ ሶስት መቶ ሃምሳ ሺ ብር ያልተገባ ጥቅም የተቀበለ በመሆኑ፣ተከሳሾች እርስ በእርስ በመመሳጠር በፈጸሙት በስልጣን ያለአግባብ መገልገል ከባድ የሙስና ወንጀል መከሰሳቸውን የዐቃቤ ህግ አንደኛ ክስ ያመላክታል ፡፡

2ኛ ክስ በ3ኛ ተከሳሽ ላይ ብቻ ሲሆን ተከሳሽ ከላይ በ1ኛ ክስ በዝርዝር በተገለጸው አግባብ የተዘጋጁትን ሀሰተኛ ሰነዶች ተጠቅሞ ተበዳይም ይህ

የከሚሴ ከተማ ፍትህ ጽ/ቤት ከዪ.ኤን.ዲ.ፒ በተገኘ የበጀት ድጋፍ  በዛሬው እለት የሕግ በላይነት እና የሴቶች እና ህፃናት መብት ጥበቃ ርዕሰ ጉዳይ ላይ ለ ሀገር ሽማግሌዎች፣ የሀይማኖት አባ...
07/10/2022

የከሚሴ ከተማ ፍትህ ጽ/ቤት ከዪ.ኤን.ዲ.ፒ በተገኘ የበጀት ድጋፍ በዛሬው እለት የሕግ በላይነት እና የሴቶች እና ህፃናት መብት ጥበቃ ርዕሰ ጉዳይ ላይ ለ ሀገር ሽማግሌዎች፣ የሀይማኖት አባቶች፣ ለማህበራዊ ፍ/ቤት ዳኞች እንዲሁም ከየቀበሌው ለተወጣጡ የሴቶች ጉዳይ ባለሙያዎች እና የማህበረሰብ ክፍሎች ስልጠና ሰጠ።

🏆ሻንፒዬኑ🏆 የከሚሴ ከተማ ፍትህ ጽ/ቤት በዛሬው እለት በሠላም እሴት ግንባታ ፣ግጭት መከላከል/መቆጣጠር እና የሕግ በላይነት ርዕሰጉዳይ  ላይ በዘርፉ በተካኑ አሰልጣኝ በመታገዝ ለባለ ድርሻ ...
24/09/2022

🏆ሻንፒዬኑ🏆 የከሚሴ ከተማ ፍትህ ጽ/ቤት በዛሬው እለት በሠላም እሴት ግንባታ ፣ግጭት መከላከል/መቆጣጠር እና የሕግ በላይነት ርዕሰጉዳይ ላይ በዘርፉ በተካኑ አሰልጣኝ በመታገዝ ለባለ ድርሻ አካላት ስልጠና ሰጥቷል ።

Address

Kemise 05
Kemise

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Waajjiira Haqaa Bul/Mag/Kamisee የከሚሴ ከተማ አስተዳደር ፍትህ ጽ/ቤት posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share