Attorney & conseltant at law

Attorney & conseltant at law Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Attorney & conseltant at law, Jinka.

18/01/2026

ይርጋ በውርስ ጉዳይ
አንድ ሰው በሕይወት ዘመኑ በጥረቱ ያፈራቸው ንብረቶች ባለቤት ሲሆን ይኸውም የንብረት መብት በኢ.ፌ.ዲ.ሪ ሕገመንግሥት አንቀጽ 40 መሠረት ጥበቃ ተደርጎለታል፡፡ አንድ ሰው በሕይወት ዘመኑ በጥረቱ ያፈራውን ንብረት የመያዝ፣ የመጠቀም፣ የመሸጥ፣ የማውረስ መለወጥ እና የማስተላለፍ መብት አለው፡፡ ይህ የንብረት መብት በባለንብረቱ መሞት ወደ ሕጋዊ ወራሾቹ የሚተላለፍ ሲሆን እነዚህ ወራሾችም የአውራሹን መሞት ተከትሎ የንብረቱ ባለቤትነት በውርስ እንዲተላለፍላቸው መጠየቅ ይችላሉ፡፡ ታዲያ ከአውራሹ መሞት በኋላ በምን ያህል ጊዜ ውስጥ የይገባኛል ጥያቄ ማቅረብ ይኖርባቸዋል? የውርስ ይገባኛል ጥያቄያቸውን በሕግ በተወሰነው የጊዜ ገደብ ውስጥ ባያቀርቡ መብታቸው ምን ይሆናል? የሚለው መሠረታዊ ጉዳይ ነው፡፡ በዚህ አጭር ጽሁፍም የይርጋን ምንነት መሠረታዊ ጽንሰ ሀሳብ እና የሕግ ሽፋን የምንዳስስ ይሆናል፡፡

የይርጋ ሕግ ምንነት
እንደ ብላክስለው መዝገበ ቃላት ይርጋ ማለት አንድ መብቱ ወይም ጥቅሙ የተነካበት ሰው በሌላ ሰው ላይ ክስ፣ አቤቱታ ወይም የይገባኛል ጥያቄ እንዲያቀርብ በሕግ ተለይቶ የተቀመጠ የክስ ማቅረቢያ ጊዜ ነው፡፡ በዚህም በሕግ በግልጽ የተደነገገን መብትና ወይም ግዴታ በሕጉ በተወሰነዉ ወይም በተገደበዉ ጊዜ ዉስጥ እንዲፈጸም ለፍርድ ቤት ወይም ሥልጣን ላለዉ አካል ጥያቄ ካልቀረበ መብቱ ወይም ግዴታው ቀሪ ይሆናል፡፡ የይርጋ ፅንሰ ሃሳብ እንዲኖር ያስፈለገባቸው መሠረታዊ ምክንያቶችም ከሳሽ በተገቢ ትጋትና በቂ ምክንያት መብቱን እንዲጠይቅ ለማስቻል፣ ተከሳሽ በጣም ዘግይተው የሚመጡ ክሶችን ለመከላከል ማስረጃዎች እንዳያጣ ለማድረግ እና እጅግ ዘግይተው የሚቀርቡ ክሶችና አቤቱታዎች ፍትሕ ከማስገኘት ይልቅ ለማጥቂያ መሳሪያነት ስለሚውሉ ይህንኑ ለመከላከል ነው፡፡

አብዛኛዎቹ የሕግ ጉዳዮች ላይ ክስ ለማቅረብ ወይም መብትን ለመጠየቅ የሚቻልባቸው ሁኔታዎች በጊዜ ገደብ ተለክቶ ክስ የማቅረቢያ ጊዜ የተቀመጠላቸዉ ናቸው፡፡ በመሆኑም ማናቸዉም ባለገንዘብ መብቱን በጊዜ መጠየቅ ይኖርበታል፡፡ ባለዕዳዉም ቢሆን ዕድሜ ልኩን ባለዕዳነቱን እያሰበ ተሸማቆ ሊኖር አይገባም፡፡ በሕግ በተወሰነዉ ጊዜ ዉስጥ መብትን በመጠየቅ ክስ ካልቀረበ የንብረት ጠያቂው መብት በይርጋ የሚታገድ እንደመሆኑ ንቁ ባለእዳ ክሱን በሕግ በተወሰነዉ የጊዜ ገደብ ዉስጥ ባለማቅረቡ የተነሳ በይርጋ መታገዱን ገልጾ ውድቅ እንዲደረግ ሊከራከር ይችላል፡፡ የውርስ ይርጋም የአውራሽን መሞት ተከትሎ የውርስ ይገባኛል ጥያቄ ለማቅረብ የተቀመጠ የጊዜ ገደብ ሲሆን ዝርዝሩን እንደሚከተለዉ እንመለከታለን፡፡

የውርስ ይርጋ
በኢትዮጵያ የፍትሐብሔር ሕግ 5ኛ አንቀጽ የአገሪቱ የዉርስ ሕግ ተደንግጎ ይገኛል፡፡ ዉርስ የሟች ንብረት ያለ ኑዘዜ ወይም በሟች ኑዛዜ መሠረት ለወራሾች የሚተላለፍ እንደመሆኑ በሁለቱም የውርስ ሥርአት ሕጉ የይርጋ ጊዜ ደንግጎ ይገኛል፡፡

የኑዛዜን መጽናት በመቃወም የሚቀርብ ክስ ይርጋ ጊዜ
ውርስ በሟች ኑዛዜ መሠረት በሚፈጸምበት ጊዜ ኑዛዜው ሲነበብ የነበሩ ወይም በሌላ ሰው የተወከሉ ወራሾች ኑዛዜ አይጸናም በማለት ወይም በውርስ አጣሪዉ በቀረበዉን የድልድል አመዳደብ ሀሳብ ላይ ተቃውሞ ካላቸው በፍትሐብሔር ሕጉ ቁጥር 973 መሠረት ኑዛዜዉ ከተነበበት አንስቶ በሚቆጠር የ15 ቀናት ጊዜ ውስጥ መቅረብ አለበት፡፡ ይህን ተቃውሞ ለዉርስ አጣሪዉ ከገለጹ በኋላ ባሉት ቀጣይ 3 ወራት ዉስጥ ደግሞ ክሳቸውን ካላቀረቡ ኑዛዜው ወይም በኑዛዜው የተነገረውን ዝርዝር ቃል አይጸናም በሚል ክስ ለማቅረብ አይችሉም፡፡ በሌላ በኩል በፍትሐብሔር ሕጉ አንቀጽ 974(1) መሠረት ኑዛዜው ሲነበብ በራሳቸው ላልነበሩ ወይም በተወካይ ቀርበው ላልሰሙ ሰዎች የይርጋ ጊዜው መቆጠር የሚጀምረው ውርስ አጣሪው ስለ ድልድሉ አመዳደብ፣ ስለ ክፍያው ሀሳቡን ከነገራቸው ቀን ጀምሮ ነው፡፡

ከዚህ ባለፈ በሕጉ በአንቀጽ 974(2) መሠረት ኑዛዜ ከፈሰሰበት (ከተነበበት) ጊዜ ወይም ኑዛዜ ከሌለ አውራሽ ከሞተበት ጊዜ አንስቶ ከአምስት ዓመት በኋላ ስለ ኑዛዜ መጽናት፣ ስለ ክፍያ፣ አመዳደብ፣ በአጣሪ የቀረበውን የድልድል ሀሳብ በማናቸዉም ምክንያት መቃወም አይቻልም፡፡ ስለዚህ የኑዛዜን አይጸናም ክስ ማቅረብ የሚፈልጉ ወራሾች ጉዳያቸውን እንደ ሁኔታው ከላይ በገለጽናቸው ጊዜ ገደብ ውስጥ ማቅረብ እንዳለባቸዉ የፍትሐብሔር ሕጉ ቁጥሮች 973 እና 974 ያስገነዝባሉ፡፡ በዚሁ ጊዜ ውስጥ ያልቀረበ የኑዛዜ መቃወሚያ ሕጋዊ ተቀባይነት የለውም፡፡

ይህንኑ ጉዳይ በማስመልከት የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በቅጽ 27 በመዝገብ ቁጥር 245055 ላይ በመጋቢት 27 ቀን 2016 ዓ.ም በሰጠው ውሳኔ ኑዛዜ ሲነበብ(ሲፈስ) በአካል ያልነበሩ፣ ያልተወከሉ፣ አልያም ስለ ክፍያ፤ ድልድል አመዳደብ ሃሳብ በውርስ አጣሪ ያልተነገራቸው ሰዎችን የሚመለከተው በፍሐብሔር ሕግ ቁጥር 974(2) ሥር የተመለከተው የአምስት ዓመት ይርጋ መሆኑን እና ይሄውም ይርጋ ፍፁም (Absolute) ይርጋ ስለመሆኑ ውሳኔ ሰጥቷል፡፡ ሰበር ሰሚ ችሎቱ የሕጉን አንቀጽ 973(3) እና 974(1) ከቁጥር 974(2) ጋር በማነጻጸር የ3 ወር እና የ5 ዓመት ኑዛዜ መቃወሚያ ይርጋን ልዩነት በተመለከተ አመልካች ኑዛዜዉ ሲነበብ ያልነበሩ ከሆነ በጉዳዩ ላይ ተፈጻሚነት ያለው ይርጋ የፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 974(2) ሥር የተመለከተው የአምስት ዓመት ይርጋ መሆኑን እና በፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 973(3) እና 974(1) መሠረት የተደነገገው የ3 ወር ይርጋ አለመሆኑን ወስኗል፡፡ እዚህ ላይ መታወቅ የሚገባው ኑዛዜ ሲነበብ ወይም ሲፈስ መኖርና አለመኖርን፣ ስለ ክፍፍሉ፣ ድልድል ሀሳቡ በውርስ አጣሪው አለመነገር ኑዛዜውን ወይም በኑዛዜው የተነገረን ቃል ለመቃወም የሚቻልበትን የጊዜ ገደብ ላይ ያለውን ሕጋዊ ውጤት ነው። ኑዛዜን የሚቃወም ወራሽ በውርሱ መነበብ ወይም መፍሰስ በራሱም ሆነ በውክልና ባይገኝ ወይም ስለ ውረሱ ድልድል፣ አመዳደብ ሀሳብ በውርስ አጣሪው ባይገለጽለትም የኑዛዜውን መጽናት በመቃወም ክስ ማቅረብ የሚቻለው በአምስት ዓመት የጊዜ ገደብ ውስጥ ብቻ ሲሆን ይህ ጊዜ ካለፈ በኋላ የሚቀርብ የኑዛዜ ይፍረስልኝ ክስ በማናቸውም ምክንያት ተቀባይነት የለውም፡፡

ኑዛዜ ሳይኖር በወራሾች የሚቀርብ የውርስ ይገባኛል ክስ ይርጋ
ሌላው የሚነሳው የውርስ ይርጋ ወራሽ ሳይሆን ያለአግባብ የውርሱን ንብረት በእጁ ካደረገዉ ሰዉ ላይ ንብረቱን ለማስመለስ የሚቀርበዉ ክስ የሚቀርብበት የጊዜ ገደብ ነው፡፡ እንዲህ ባለው ጊዜ ከሳሹ የውርሱ ንብረቶች በተከሳሹ መያዛቸዉን ባወቀ በ3 ዓመት ጊዜ ዉስጥ ክሱን ማቅረብ እንዳለበት በፍህትሐብሔር ሕጉ አንቀጽ 1000(1) ተገልጿል፡፡ ከሳሹ ይህን ጉዳይ ያላወቀ ከሆነ ሟቹ ከሞተ ወይም ከሳሹ በመብቱ ለመሥራት ከቻለበት ቀን አንስቶ 15 ዓመት ካለፈ በኋላ የውርስ ንብረት ለማስመለስ ጥያቄ ለማቅረብ እንደማይቻል የፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 1000(2) ድንግጎ ይገኛል፡፡

የውርስ ንብረቱ የመሬት ይዞታ መብት ከሆነም በዚሁ አግባብ የሚታይ ሲሆን ከውርስ ውጪ በሆነ ሁኔታ የገጠር መሬት ባልተገባው ሰው ተያዘብን በሚል የሚቀርብ ክስ በገጠር መሬት አስተዳደር እና አጠቃቀም አዋጅ ቁጥር 1324/2016 አንቀጽ 64(2) መሠረት መብቱን መጠየቅ ከነበረበት ወይም ካወቀበት ጊዜ ጀምሮ በ15 ዓመት ውስጥ ክስ ካላቀረበ በይርጋ ቀሪ እንደሚሆን ደንግጎ ይገኛል፡፡ በዚህ ጉዳይ ላይ የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ትርጉም ሰጥቷል፡፡ በዚሁ መሠረት በመዝገብ ቁጥር 52407 (በቅጽ 11 የታተመ) እንደወሰነው የፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 1000 ላይ የተመለከተው የይርጋ ድንጋጌ ተፈጻሚነት የሚኖረው ወራሽ በሆኑ ተከራካሪዎች መካከል መሆኑን ነገር ግን ወራሽ በሆኑ እና ባልሆኑ ወገኖች መካከል ክርክሩ የሚደረግ ከሆነ ተፈጻሚነት ያለው የፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 1000 ድንጋጌ ሳይሆን በየፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 1845 ላይ የተመለከተው የ10 ዓመት የይርጋ ድንጋጌ መሆኑን የሕግ ትርጉም የሰጠበት ጉዳይ ነው፡፡ ይህ የ10 ዓመት ይርጋ ጊዜ መቆጠር የሚጀምረው አውራሽ ከሞተበት ወይም ከሳሽ መብቱን ለመጠየቅ ሕጋዊ ችሎታ ካገኘበት ቀን ጀምሮ እንደሆነ ሕጉ ያመለክታል፡፡ እዚህ ላይ ፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በመዝገብ ቁጥር 171038 በየካቲት 25 ቀን 2012 ዒ.ም እና በመዝገብ ቁጥር 239453 በሐምሌ 26 ቀን 2015 ዓ/ም እንደወሰነው የሟች ንብረት ወራሽ ባልሆኑ ሰዎች ሲያዝ ህጻናት የነበሩ የሟች ወራሾች በመብታቸው መሥራት እና ንብረቱ እንዲለቀቅ ክስ ማቅረብ የሚችሉት እድሜያቸው 18 ዓመት ሲሞላ ሲሆን የውርስ ንብረቱ ሲያዝ አካለ መጠን ያልደረሱ የሟች ልጆችም ተፈጻሚነት ያለው የይርጋ ጊዜ 10 ዓመት ሲሆን ይህ የ10 ዓመት ጊዜ መቆጠር የሚጀምረው እድሜያቸው 18 ዓመት ከሞላበት ጊዜ ጀምሮ ስለመሆኑ ውሳኔ ሰጥቷል፡፡ በዚህም ሟች ወይም አውራሽ ሲሞት ወይም የውርስ ንብረቱ በማይገባው ሰው መያዙን ሲያውቁ እድሜያቸው ከ18 ዓመት በታች የሆኑ ወራሾች እድሜቸው 18 ዓመት ከሞላበት ቀን ጀምሮ ቀጥሎ ባሉ 10 ዓመታት የውርስ ንብረት ይገባኛል ክስ አቅርበው የውርስ ንብረቱን ካላስመለሱ ክሱ በይርጋ ቀሪ ይሆናል ማለት ነው፡፡

ማጠቃለያ
በኑዛዜም ሆነ ያለ ኑዛዜ የሚቀርብ የውርስ ንብረት ይገባኛል ክስ በማናቸውም ጊዜ የሚቀርብ ሳይሆን ሕጉ ባስቀመጠው የጊዜ ገደብ ውስጥ መቅረብ ያለበት ነው፡፡ በውርስ ሕጉ መሠረት ይህን አውቆ ክሱን የይርጋ ጊዜው ከማለቁ በፊት ያላቀረበ ወራሽ የመውረስ መብቱን አውቆ በራሱ ነጻ ፈቃድ እንደተወው ግምት ተወስዶ መብቱን ያጣል፡፡ ስለሆነም የውርስ ይገባኛል ክሶች የይርጋ ጊዜያቸው ከማለቁ በፊት ሥልጣን ላላቸው ፍርድ ቤቶች ቀርበው ውሳኔ ማግኘት ይኖርባቸዋል፡፡

04/07/2024

በአሠሪና ሠራተኛ አዋጅ 1156/2011 ቁጥር 163 መሰረት በቅጥር ላይ ከተመሰረተ ግንኙነት የመነጨ ማንኛዉም ክስ የመብቱን ጥያቄ ለማቅረብ ከሚቻልበት ቀን ጀምሮ እስከ 1 ዓመት ድረስ፣ ወደ ሥራ ልመለስ በሚል የሚቀርብ ክስ ዉሉ በተቋረጠ በ3 ወር ጊዜ ዉስጥ፤ የደመወዝ፣የትርፍ ሰዓትና የሌሎች ክፍያዎች ጥያቄ መጠየቅ ከሚገባዉ ጊዜ ጀምሮ እስከ 6 ወር ባለዉ ጊዜ እና የሥራ ዉል በመቋረጡ ምክንያት በሰራተኛዉም ሆነ በአሠሪዉ የሚቀርብ ጥያቄ ሥራ ዉሉ በተቋረጠ በ6 ወር ጊዜ ዉስጥ ካልቀረበ በይርጋ ይታገዳል፡፡

8. የእንደራሴነትና የዉክልና ህግ ይርጋ
🛑🛑🛑🛑🛑🛑🛑🛑🛑🛑✅

በፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር. 2187 (2) መሰረት ሿሚዉ (ወካዩ) ካወቀበት ጊዜ ጀምሮ ማለትም በተሰጠ ዉክልና ላይ የጥቅም ግጭት ተከስቶ ከሆነ ይህ ጥቅም ግጭት ያስነሳዉ ዉል መደረጉን ካወቁ ከ 2 ዓመት በኋላ እንዲፈረስ መጠየቅ በይርጋ የሚታገድ ነዉ፣ ወካይ የሆነ ወገን በተወካይ አማካኝነት የተደረገን ህገ ወጥ ዉል እንዲፈረስ በሚል የሚቀርበዉ አቤቱታ በፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 1845 መሰረት በ10 ዓመት ይርጋ እንጂ በ 2 ዓመት የሚታገድ አለመሆኑን የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በሰ/መ/ቁ 67376 ዉሳኔ ሰጥቷል፡፡

9. የሽያጭ ዉል ይርጋ
🛑🛑🛑🛑🛑✅

በፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 2298 መሰረት ገዢዉ እንደዉሉ ትክክል አለመሆኑን (ጉድለት ያለበት መሆኑን) ካወቀ ዉሉ እንዲፈርስ ለመጠየቅ 1 ዓመት ይርጋ፣ ቁጥር. 2391 ሻጭ የሸጠዉን መልሶ ለመግዛት 2 ዓመት ይርጋ እና ቁጥር 2692 የማይንቀሳቀስ ንብረት የሸጠ ሰዉ እንደዉሉ ይፈጽምልኝ ብሎ ለመጠየቅ የሚችለዉ 1 ዓመት ጊዜ ዉስጥ ነዉ፡፡

10. የመያዣ ዉል
🛑🛑🛑🛑🛑✅

በፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 3058 የማይንቀሳቀስ ንብረት መያዣን በፍርድ ቤት ለመጠየቅ ከተጻፈበት ቀን አንስቶ 10 ዓመትይርጋ እና ቁጥር 3086 በማይንቀሳቀስ ንብረት መያዣ ላይ የተደረገዉን ንብረት የመሸጥ ፣ የመለወጥ ስምምነት መግለጫ ለገንዘብ ጠያቂዉ ለማሳወቅ 1 ዓመት ይርጋ ተፈፃሚ ናቸዉ፡፡

11. የፍትሐብሔር ሥነ ሥርዓት ህግ ይርጋ
🛑🛑🛑🛑🛑🛑🛑✅
ይግባኝ
የይግባኝ አቤቱታ ለይግባኝ ሰሚዉ ፍርድ ቤት መቅረብ የሚገባዉ ይግባኝ በሚባልበት ጉዳይ ላይ በተፈረደ በ60 ቀን ዉስጥ ነዉ፡፡
የአፈፃፀም ይርጋ
በፍትሐብሔር ሥነ-ሥርዓት ሕግ ቁጥር 384 ስር እንደተመለከተዉ የፍርድ ባለመብት ፍርዱን ለማስፈጸም ምንም ዓይነት ህጋዊ እንቅስቃሴ ሳያደርግ ከቆየ በ10 ዓመት የጊዜ ገደብ ይታገዳል፡፡

የይርጋ ጊዜ አቆጣጠር
🛑🛑🛑✅✅✅🛑🛑🛑✅
የይርጋ ቀን መቆጠር የሚጀምረዉ ግዴታዉን ለመጠየቅ ተገቢ ከሆነዉ ወይም ዉሉ የሚሰጠዉ መብት ከተሰራበት ቀን ጀምሮ ነዉ (የፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 1848 ይመለከቷል)፡፡ ለምሳሌበንግድሕግቁጥር 674 (1) ላይ በኢንሹራንስ ውል ምክንያት የሚቀርብ ክስ መቅረብ ያለበት በሁለት ዓመት ጊዜ ውስጥ መሆኑን ያመለክትና የይርጋ ጊዜው መቆጠር የሚጀምረው ለክሱ ምክንያት የሆነው ጉዳት ከደረሰበት ቀን ጀምሮ ወይም በጉዳዩ ጥቅም ያላቸው ወገኖች ጉዳቱን ካወቁበት ቀን ጀምሮ መሆን እንዳለበት መገለፁ እንደ ጥሩ ምሳሌ ሊወሰድ ይችላል፡፡የይርጋ ቀን ሲቆጥር ግምት ዉስጥ መግባት ያለባቸዉ ነገሮች፡-

- የይርጋዉ መጀመሪያ ቀን ከይርጋዉ ዘመን ሂሳብ ዉስጥ ገብቶ አይታሰብም፡፡
- የይርጋ ቀን የሚሞላዉ ለይርጋዉ የተወሰነ መጨረሻ ቀን ካለፈ በኋላ ነዉ፡፡ነገርግን ምንአልባት ይህ ቀን ገንዘቡ በሚከፈሉበት ቦታ በህግ የታወቀ የበዓል ቀን የሆነ እንደሆነ ይርጋዉ የሚሞላዉ ከበአሉ ተከታይ በሆነዉ በአል ባልሆነዉ ቀን ነዉ፡፡

ይርጋ ሊቋረጥ የሚችልባቸዉ ሁኔታዎች
🛑🛑🛑🛑🛑🛑✅✅🛑
1. ባለዕዳዉ ዕዳዉን ሲያምን ይልቁንም ወለድ ወይም ከዕዳዉ ላይ በከፊል ሰጥቶ ሲገኝ ወይም መያዣ የሰጠ እንደሆነ፣
2. ባለገንዘቡ መብቱ እንዲታወቅለት በፍርድ ቤት ክስ አቅርቦ ለባለዕዳዉ አስታዉቆ የተገኘ እንደሆነ ነዉ፡፡

የይርጋዉ መቋረጥ ዉጤት ደግሞ፡

🛑 ይርጋዉ ከተቋረጠበት ጀምሮ እንደገና አዲስ የይርጋ ዘመን መቆጠር ይጀምራል፡፡(የፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 1852 ይመለከቷል)፡፡

🛑 እዳዉ በአንድ ማስረጃ ወይም በአንድ ፍርድ የተረጋገጠ እንደሆነ አዲሱ የይርጋ አቆጣጠር ዘመን ሁልጊዜ 10 ዓመት ነዉ፡፡

የይርጋ ሕግን አለማክበር የሚያስከትለዉ ዉጤት

የይርጋ በሕግ ስርዓት ውስጥ መካተቱ ተከሳሹን የሚጠቅመዉን ያህል በአንፃሩ የፅንሰ ሃሳቡ መኖር ከሳሹን በእጅጉ የሚጎዳ ነው፡፡ በይርጋ ጊዜያት መለያየት፣ ትክክለኛ የይርጋ ጊዜን ባለማወቅ፣ ሕግን ባለማወቅ እንዲሁም በቸልተኝነት የሕግ ድጋፍና በቂ ማስረጃ እያላቸው በርካቶች መብታቸውን አጥተዋል፡፡ በተለያዩ ጊዜያት በፍርድቤት ይረጋን አስመልክቶ በተደረጉ ክርክሮች ምክንያት ጥቂት የማይባሉ መዝገቦች ተዘግተዋል፡፡ ይሁን እንጂ ይርጋ በመላው ዓለም በስፋት ተቀባይነት ያገኘ የሕግ ፅንሰ ሀሳብ ነዉ፡፡

በይርጋ የማይታገዱ ጉዳዮች

ጥቂት በሆኑ ጉዳዮች ላይ ክስ የማቅረቢያ ወይም መብት የመጠየቂያ ጊዜ ገደብ እንደሌለውና ክስ ለማቅረብ ምክንያት የሆነው ድርጊት ከተፈፀመበት ጊዜ ጀምሮ ያለምንም ጊዜ ገደብ በማንኛውም ጊዜ ክስ ለማቅረብ ወይም መብት ለመጠየቅ የሚቻልባቸው ጉዳዮች እንዳሉ በተለያዩ ሕጎች ውስጥ ተመልክቷል፡፡ እነርሱም፡- የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በቅጽ 10 የሰበር መዝገብ ቁጥር 43600 ላይ በሰጠው አስገዳጅ ውሳኔ መሰረት የማይንቀሳቀስ ንብረትን አስመልክቶ ባለመብት የሆነው ሰው መብት ሳይኖረው በእጁ ካደረገው ሰው ወይም ከያዘው ሰው ላይ ሀብቱ ይገባኛል ሲል የሚያቀርበው የመፋለም ክስ በይርጋ ቀሪ ሊሆን አይችልም፡፡

በፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 1678፣ 1716 እና 1718 እንዲሁም የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በቅፅ 14 የሰበር መዝገብ ቁጥር 79394 እናቅፅ 12 የሰበር መዝገብ ቁጥር 43226 መሠረት የውል መሠረታዊ ዓላማ በሕግ ያልተፈቀደና የተከለከለ ሆኖ ሲገኝ ፍርድ ቤቶች ሕገ ወጥ የሆነው ውል በቀረበላቸው ማንኛውም ጊዜ ሕጋዊ ውጤትና ተፈፃሚነት የለውም በማለት ለመወሰን የሚችሉና ሕገ ወጥ የሆነውን ውል ውድቅ ለማድረግ በሕጉ የተደነገገው የይርጋ ጊዜ ገደብ መቃወሚያ ሊሆን አይችልም፡፡

በአጠቃለይ ይርጋ ተከራካሪ ወገኖች በጥንቃቄ ሊያጤኑት የሚገባ ለክርክር የቀረበን ጉዳይ እጣፈንታ ሊወስን የሚችል ጉዳይ በመሆኑ ማናቸዉም ሰዉ በሀግ በተቀመጠዉ የጊዜ ገደብ ዉስጥ ክሱን ለፍርድ ሰጭ አካላት አቀርቦ መፍትሔ ማግኘት ይጠበቅበታል። ጠበቃ አክሊሉ ኤርምያስ በፌደራል በማናቸውም ፍርድ አቤት ጠበቃ እና የሕግ አማካሪ

15/02/2024

Informing all friends that almost all Facebook accounts are being cloned by hackers. They are using your profile picture and your name to create a new Facebook account and then try to add your friends to that account. Your friends think it's you and they join it. Since then, those hackers can write whatever they want under your name!!!

I want you to know that I don't have a reason to open a new Facebook account right now. So please take care and do not accept any friend request coming from a new FB account made with my name!!

If anyone gets a message from my account about obscene, communal, casteism or money, it will be fake because I don't have to do so.

(Copy and paste this message on your timeline, so that no friend accepts the request from such a fake account made with your name)
ሁሉም የፌስቡክ አካውንቶች ማለት ይቻላል በጠላፊዎች እየተዘጉ መሆናቸውን ለሁሉም ጓደኞች ማሳወቅ። አዲስ የፌስቡክ አካውንት ለመፍጠር የእርስዎን ፕሮፋይል ፒክቸር እና ስምዎን እየተጠቀሙ ነው እና ጓደኛዎችዎን ወደዚያ መለያ ለመጨመር ይሞክሩ። ጓደኞችዎ እርስዎ እንደሆኑ አድርገው ያስባሉ እና ይቀላቀላሉ. ከዚያን ጊዜ ጀምሮ እነዚያ ሰርጎ ገቦች የፈለጉትን በስምህ መፃፍ ይችላሉ!!!

አሁን አዲስ የፌስቡክ አካውንት የምከፍትበት ምክንያት እንደሌለኝ እንድታውቁልኝ እፈልጋለሁ። ስለዚህ እባካችሁ ተጠንቀቁ እና ከአዲስ የFB አካውንት በስሜ ከተሰራው የጓደኛ ጥያቄ እንዳትቀበሉ!!

ማንም ሰው ከእኔ አካውንት ስለ ጸያፍ፣ የጋራ፣ የጥላቻ ወይም ገንዘብ መልእክት ቢደርሰው፣ ማድረግ ስለሌለብኝ የውሸት ይሆናል።

(ይህንን መልእክት በጊዜ መስመርህ ላይ ገልብጠው ለጥፍ፣ ማንም ጓደኛህ በስምህ ከተሰራ የውሸት አካውንት ጥያቄውን እንዳይቀበል)

18/09/2023

43 likes, 5 comments. Check out Aklilulawyer's video.

14/08/2018

መግደል መሸነፍ ነው ። ኢትዮጵያ እናት አገራችንን የምናበለጽጋት እኛ እረሥ በእርሣችን ሥንፋቀር ብቻ ነው ። ጠባብ ብሔርተኝነት ለአገራችን ጠንቅ ነው ........

08/07/2018
13/06/2018

ዘረኝነትን ከኢትዮጵያ ለማጥፋት የትምህርት ፖሊሲው መቀየር አለበት ።

Address

Jinka

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Attorney & conseltant at law posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share