Christ Centered Missionary Gospel Ministry

Christ Centered Missionary Gospel Ministry Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Christ Centered Missionary Gospel Ministry, wholeworld, Hossana.
(6)

በእግዚአብሔር አብ፣ በእግዚአብሔር ወልድ ፣በእግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ አንድ አምላክ እናምናለን አሜን🙏
ይህ ኢየሱስ ክርስቶስን ማዕከል ያደረገ ሚስዮናዊ የወንጌል ስርጭት አገልግሎት ነው።

👉 ወንጌል ስርጭት እናደርጋለን
👉 ለቤተክርስቲያን ድምጽ እንሆናለን
👉 ክርስቲያን ዜናዎችን እንሰራለን
👉 ወቅታዊና አዳዲስ ጠቃሚ ነገሮችን እናስተላልፋለን

11/08/2026

ምን ውስጥ እንዳላችሁ አላውቅም፤ ግን የእግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስ ክርስቶስ ከእናንተ ጋር እንደሆነ ልንገራችሁ ብዬ ነው🥺።

 ! የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን መካነ ኢየሱስን በብሔራዊ ደረጃና በበርካታ የሲኖዶስ ሀላፊነቶች በቅንነትና ታማኝነት ሲያገለግሉ የነበሩት ቄስ ስምዖን ዜና ከተሰማ በኋላ ቤተክርስቲያ...
11/08/2026

!

የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን መካነ ኢየሱስን በብሔራዊ ደረጃና በበርካታ የሲኖዶስ ሀላፊነቶች በቅንነትና ታማኝነት ሲያገለግሉ የነበሩት ቄስ ስምዖን ዜና ከተሰማ በኋላ ቤተክርስቲያን የቄስን ዜና እረፍት በታላቅ ሀዘን መስማቷን ጠቅሷ መጽናናትን ተመኝታለች።

ቤተክርስቲያን በመግለጫዋ አባታችን ቄስ ስምዖን የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን መካነ ኢየሱስን በምክትል ፕሬዝዳንት፤ ዋና ኮሚቴ አባልነት፤ የሥራ አስፈጻሚ ቦርድ አባልነት፤ እንዲሁም በማዕከላዊ ደቡብ ኢትዮጵያ ሲኖዶስ በምክትል ፕሬዝደንትነት፤ የወንጌል ተልዕኮና ቲኦሎጂ መምሪያ ዳይሬክተርነት የአገልግሎት ሀላፊነቶች ቤተ ክርስቲያንን አገልግለዋል።

በተጨሪም አባታችን የአማሮና አከባቢው ሲኖዶስ የመጀመሪያ ፕሬዝዳንት በመሆን ያገለገሉ ሲሆን፤ በጡረታ ጊዜያቸውም በምክርና አቅጣጫን በማሳየት የአባትንት ሀላፊነታቸውን እየተወጡ በነበሩበት ጊዜ ባጋጠማቸው ህመም ምክንያት በህክምና ሲረዱ ቆይተው ወደሚወዱትና ወዳገለግሉት ጌታ ሄደዋል።

ቄስ ስምዖን በአማሮ፤ በቡርጂ እና በበርካታ የደቡብ ኢትዮጵያ አከባቢዎች የእግዚአብሔር ቃል ያስተናሩ የወንጌል አርባኛ ነበሩ።

የቀብር ሥነ-ሥርዓቱ ነገ በኬሌ ከተማ መካነ ኢየሱስ ማህበረ ምዕመናን የሚፈጸም ሲሆን
ለቤተሰባቸው፤ ወዳጅ ዘመዶች፤ ላገለገሏቸው ምዕመናን እና ለሁላችን እግዚአብሔር መጽናናቱን እንዲሰጥ ተመኝተዋል።

7ቱ መጽሐፍ ቅዱሳዊ  የክርስቲያን ጋብቻ መሠረቶች 1. አመሰራረቱ መለኮታዊ  ነው (Institution)ጋብቻ የሰው ልጅ ፈጠራ ሳይሆን የእግዚአብሔር ስጦታ ነው። እግዚአብሔር በመጀመሪያ ወንድ...
11/08/2026

7ቱ መጽሐፍ ቅዱሳዊ የክርስቲያን ጋብቻ መሠረቶች
1. አመሰራረቱ መለኮታዊ ነው (Institution)
ጋብቻ የሰው ልጅ ፈጠራ ሳይሆን የእግዚአብሔር ስጦታ ነው። እግዚአብሔር በመጀመሪያ ወንድና ሴትን ፈጥሮ ያጣመራቸው እርሱ ነው። ከምንም ተቋም በፊት በእግዚአብሔር የተጀመረ ራሱ እግዚአብሔር አስተዳዳሪውና አሳዳሪው የሆነ ነው። ስለዚህ አመሰራረቱ መለኮታዊ ሆኖ ሂደቱ ስጋዊ ሊሆንና በስጋዊያንም ሊፈርስ አይገባም።
"ስለዚህ ሰው አባቱንና እናቱን ይተዋል፥ ከሚስቱም ጋር ይባበራል፤ ሁለቱም አንድ ሥጋ ይሆናሉ።" (ዘፍጥረት 2፡24)
2. አንድነትን አብዝቶ ይወዳል (Unity)
በክርስትና ጋብቻ ውስጥ "ሁለት" መሆን ያበቃና "አንድ" መሆን ይጀምራል። ይህም በሥጋ ብቻ ሳይሆን በሐሳብና በመንፈስ መዋሐድን ያመለክታል። "ስለዚህ አንድ ሥጋ ናቸው እንጂ ወደፊት ሁለት አይደሉም። እግዚአብሔር ያጣመረውን እንግዲህ ሰው አይለየው።" (ማቴዎስ 19፡6) በጋብቻ ውስጥ እኛ እና የእኛ እንጂ እኔነት አሰራምና ሁሉንም ነገር በአንድነትና በኅብረት በማድረግ እንድነታችንን አብዝተን እንጠብቅ። ትዳርና ክርስትና አንድነትና ኅብረት ይወዳል ።
3. ታማኝነት (Faithfulness/Covenant)
ጋብቻ በሁለት ሰዎች መካከል ብቻ የሚደረግ ቅዱስ ቃል ኪዳን ነው። ይህ ቃል ኪዳን እስከ ሞት ድረስ የሚቆይና ከዝሙት የጸዳ መሆን አለበት። "መጋባት በሁሉ ዘንድ ክቡር ይሁን፥ መኝታውም ንጹሕ ይሁን፤ ሴሰኞችንና አመንዝሮችን ግን እግዚአብሔር ይፈርድባቸዋል።" (ዕብራውያን 13፡4) በጋብቻ ውስጥ ያለውን ታማኘት አጉድለን ቃልኪዳኑን ከሰበርን ራሱ ባለቤቱና ባለመብቱ እግዚአብሔር ተቋሙን ባፈረሱት ልጆቹ ላይ ቅጣትን ይልካልና በታማኝነትና በንፅህና እንኑር ። ባልና ሚስት ለእግዚአብሔር ታማኝ ለእርስ በእርሳቸው አማኝ ሊሆኑ ይገባል።
4. ፍቅር (Love - Agape)
የክርስቲያን ጋብቻ ትልቁ መሠረት ክርስቶስ ለቤተክርስቲያን ያሳየው ዓይነት መስዋዕትነት ያለበት ፍቅር ነው።
"ባሎች ሆይ፥ ክርስቶስ ደግሞ ቤተ ክርስቲያንን እንደ ወደዳትና ስለ እርስዋ ራሱን አሳልፎ እንደ ሰጠ፥ ሚስቶቻችሁን ውደዱ።" (ኤፌ 5፡25) ባሎችም ሆኑ ሚስቶች ከባልና ሚስት ፍቅር በላይ የክርስቶስን ፍቅር አልቀውና አድምቀው ጌታን ብቻ እያዩ ሳይለያዩ እየተዋደዱ ሊኖሩ ይገባል። ፍቅር የእርስ በእርስ ማሰሪያ የጥላቻ መግደያ መሳሪያ ነው ።
5. መከባበርና መገዛዛት (Respect and Submission)
ባልና ሚስት እርስ በርስ ሊከባበሩ ይገባል። ይህ መገዛዛት አንዱ ሌላውን መጨቆን ሳይሆን፣ በፍቅርና በክርስቶስ ፍርሃት የሚደረግ ነው። "ለእያንዳንዳችሁ በክርስቶስ ፍርሃት እርስ በርሳችሁ ተገዙ።" (ኤፌሶን 5፡21) መከባበር ከመቀባበር ያድናል። እንግዳ ማክበር ባህላችን ሆኖ ሳለ እርስበእርሳችን መከባበር ግን ተመልሶ እንግዳ ይሆንብናል። ለምን? የትዳር መበልፀግ ዋናው መሰረቱ መከባበርና መተባበሩ መሆኑን አንዘንጋ ።

6. ቅድስና (Holiness)
ጋብቻ ባልና ሚስት ይበልጥ ወደ እግዚአብሔር እንዲቀርቡና እንዲቀደሱ የሚያግዝ መንገድ ነው። ዓላማው ለሥጋዊ ደስታ
"እግዚአብሔር ለርኩሰት ሳይሆን በቅድስና ጠርቶናልና።"1ተሰ 4፡7 ደግሞ እኔ ቅዱስ ነኝና እናንተም ቅዱሳን ሁኑ ብሎ የጋበዘን ዋናው የጋብቻው CEO ነውና የድርጅቱን መስራች እንስማ። ቅድስና መጀመሪያ ለእግዚአብሔር ቀጥሎ ለትዳር ይሁን።
7. ይቅርባይነት (Forgiveness)
ፍጹም ሰው ስለሌለ፣ በጋብቻ ውስጥ አለመግባባቶች ሲፈጠሩ በይቅርታ መታለፍ አለባቸው። ክርስቶስ እኛን ይቅር እንዳለን እኛም ለትዳር አጋራችን ይቅርታ ማድረግ መሠረታዊ ጉዳይ ነው። "እርስ በርሳችሁም ቸሮችና ርኅሩኆች ሁኑ፥ እግዚአብሔርም ደግሞ በክርስቶስ ይቅር እንዳላችሁ ይቅር ተባባሉ።" (ኤፌሶን 4፡32) የተማረ ሰው ይምራል የተፈታ ሰው ይፈታል ። ይቅርታን የሚያውቅ ሰው እንቅልፉ ጣፋጭ ኑሮው ዘናጭ ነው። ስለዚህ ከምንኮራረፍ በይቅርታ እንረፍ !

ቀኑ እንደ ሌባ በድንገት ይመጣባቸዋል‼
11/08/2026

ቀኑ እንደ ሌባ በድንገት ይመጣባቸዋል‼

ኢየሱስ ያድናል ‼✊
11/08/2026

ኢየሱስ ያድናል ‼✊

1ኛ የዮሐንስ መልዕክት 5 (አማርኛ 1954)¯¯¯  ¹¹ እግዚአብሔርም የዘላለምን ሕይወት እንደ ሰጠን ይህም ሕይወት በልጁ እንዳለ ምስክሩ ይህ ነው።¹² ልጁ ያለው ሕይወት አለው፤ የእግዚአብ...
10/08/2026

1ኛ የዮሐንስ መልዕክት 5 (አማርኛ 1954)
¯¯¯ ¹¹ እግዚአብሔርም የዘላለምን ሕይወት እንደ ሰጠን ይህም ሕይወት በልጁ እንዳለ ምስክሩ ይህ ነው።
¹² ልጁ ያለው ሕይወት አለው፤ የእግዚአብሔር ልጅ የሌለው ሕይወት የለውም።
¹³ የዘላለም ሕይወት እንዳላችሁ ታውቁ ዘንድ በእግዚአብሔር ልጅ ስም ለምታምኑ ይህን ጽፌላችኋለሁ።

የዮሐንስ ወንጌል 10 (አማርኛ 1954)¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯⁷ ኢየሱስም ደግሞ አላቸው። እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ እኔ የበጎች በር ነኝ።⁸ ከእኔ በፊት የመጡ ሁሉ ሌቦችና ወንበዴዎች ናቸው፤ ዳ...
10/08/2026

የዮሐንስ ወንጌል 10 (አማርኛ 1954)
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯⁷ ኢየሱስም ደግሞ አላቸው። እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ እኔ የበጎች በር ነኝ።
⁸ ከእኔ በፊት የመጡ ሁሉ ሌቦችና ወንበዴዎች ናቸው፤ ዳሩ ግን በጎቹ አልሰሙአቸውም።
⁹ በሩ እኔ ነኝ፤ በእኔ የሚገባ ቢኖር ይድናል፥ ይገባልም ይወጣልም መሰማሪያም ያገኛል።
¹⁰ ሌባው ሊሰርቅና ሊያርድ ሊያጠፋም እንጂ ስለ ሌላ አይመጣም፤ እኔ ሕይወት እንዲሆንላቸው እንዲበዛላቸውም መጣሁ።
¹¹ መልካም እረኛ እኔ ነኝ። መልካም እረኛ ነፍሱን ስለ በጎቹ ያኖራል።

 🎂🎊በእድሜዬ ላይ ዛሬም ኑሪ ብለህ እድሜን በምህረትህ የጨመርክልኝ የእኔም የዘመናቱም  ጌታ እግዚአብሔር አምላኬ ሆይ ተመስገን!ብዙ እንደተደረገለት በዘመኑ ሁሉ ቸርነትህን እንዳገነንክለትና ...
09/08/2026

🎂🎊

በእድሜዬ ላይ ዛሬም ኑሪ ብለህ እድሜን በምህረትህ የጨመርክልኝ የእኔም የዘመናቱም ጌታ እግዚአብሔር አምላኬ ሆይ ተመስገን!
ብዙ እንደተደረገለት በዘመኑ ሁሉ ቸርነትህን እንዳገነንክለትና እንደረዳኸው ሰው ከልቤ አመሰግንሀለሁ!
እንኳን ተወለድኩ!!!

ስደክም ጉልበቴ ስበረታ ክብሬ
አንተ አልተለወጥክም ይኸው እስከዛሬ
ቀናቶች ሲያልፋ አመታት ሲሆኑ
የነገስታት ንጉስ አለህ በዙፉኑ
አንተ ብቻ ነህ

አንተ ብቻ ነህ

አንተ ብቻ ነህ……

Address

Wholeworld
Hossana

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Christ Centered Missionary Gospel Ministry posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Christ Centered Missionary Gospel Ministry:

Shortcuts

Share