23/08/2026
የሀዘን መግለጫ😭😭😭
ወ/ሮ ሮማን ሮባ፣ በሀይቅ ዳር ክፍለ ከተማ ገቢዎች ባለሥልጣን ባለሙያ ሆና በትጋትና በታማኝነት ሕዝብን ስታገለግል የነበረችው፣ ባደረባት ሕመም ስትታከም ቆይታ በቀን 17/12/2018 ዓ.ም. ከዚህ ዓለም በሞት ተለይታለች።
የወ/ሮ ሮማን ሮባ ሞት በእጅጉ አሳዝኖናል። ለቤተሰቦቿ፣ ለዘመድ አዝማዶቿ፣ ለጓደኞቿ፣ እንዲሁም አብረዋት ለሰሩ የሥራ ባልደረቦቿና ለሚያውቋት ሁሉ ከልብ የመነጨ የሀዘን መግለጫችንን እናቀርባለን።
የቀብር ሥነ-ሥርዓቷም ነገ የሚፈጸም መሆኑን በሀዘን እናሳውቃለን።
በዚህ አስከፊ የሀዘን ጊዜ እግዚአብሔር ለቤተሰቦቿና ለወዳጅ ዘመዶቿ መጽናናትን ይስጥ። ነፍሷን በሰላም ያኑርልን።
እግዚአብሔር ነፍሷን በሰላም ያኑር።