ጂኔላ ወረዳ ወጣቶች ሊግ/Genela wereda youth league

  • Home
  • Ethiopia
  • Harar
  • ጂኔላ ወረዳ ወጣቶች ሊግ/Genela wereda youth league

ጂኔላ ወረዳ ወጣቶች ሊግ/Genela wereda youth league It's not having time it's about making time

12/11/2023
ጽዳት አንዴ ብቻ ተሰርቶ በቃ የሚባል ጉዳይ አይደለም ምክንያቱም በየጊዜ መቆሸሽ ስላለ ለዛም ነው አካባቢን ማጽዳት ባህል ማድረግ ያለብን ይህንን በማስመልከት ለህብረተሰቡም ግንዛቤን ለማስጨበ...
12/11/2023

ጽዳት አንዴ ብቻ ተሰርቶ በቃ የሚባል ጉዳይ አይደለም ምክንያቱም በየጊዜ መቆሸሽ ስላለ ለዛም ነው አካባቢን ማጽዳት ባህል ማድረግ ያለብን ይህንን በማስመልከት ለህብረተሰቡም ግንዛቤን ለማስጨበጥ ከትላንት ቅዳሜ የቀጠለ የጽዳት ዘመቻ ከወረዳው ከፍተኛ አመራሮች እና ከወረዳው ወጣቶች ጋር ተካሂ--ዷል

በክቡር ፕሬዝዳንታችን የተጀመረውን የከተማችንን ውበት  የመጠበቅ እና የማስቀጠል ስራ በምክትል ፕሬዝዳንት ማዕረግ የከተማ ልማት ሀላፊ የሆኑት ክብርት ወ/ሮ አሚና አብዱልከሪም እና የጂኔላ ወ...
11/11/2023

በክቡር ፕሬዝዳንታችን የተጀመረውን የከተማችንን ውበት የመጠበቅ እና የማስቀጠል ስራ በምክትል ፕሬዝዳንት ማዕረግ የከተማ ልማት ሀላፊ የሆኑት ክብርት ወ/ሮ አሚና አብዱልከሪም እና የጂኔላ ወረዳ አስተዳደር ሀላፊ አቶ ፈቲ ሀሰን እና ሌሎች ከፍተኛ የክልል እንዲሁም የወረዳችን አመራሮች በተገኙበት ከወረዳው ማህበረሰብ በተለይም ከወረዳው ወጣቶች ጋር በመሆን የፅዳት መርሀ-ግብር ተካሂዷል:: በማጠቃለያም የወረዳችን ዋና አስተዳደር የሆኑት አቶ ፈቲ እንዳሉት ይህ አካባቢያችንን፣መንደራችንን እንዲሁም ክልላችንን የማፅዳት እና ለኑሮ ምቹ የማድረጉ ሂደት ከላይ ከክልላችን ከፍተኛ አመራሮች ጀምሮ እስከ ታቺኛው ማህበረሰብ ድረስ ለሚመጡት ወራት የሚቀጥል መሆኑ አፅንኦት ሰተው ተናግረዋል::

ኢምራን ጀማል!

05/11/2023
የጅንኤላ ወረዳ የብልጽግና ፓርቲ የወጣት ሊግ ኮንፍረንስ ተካሄደ።       ከሶስቱ ቀበሌዎች የተውጣጡ የሊግ አባላት የተገኙበትን ኮንፍረንስ የመሩት የጅንኤላ ወረዳ ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ሐ...
29/10/2023

የጅንኤላ ወረዳ የብልጽግና ፓርቲ የወጣት ሊግ ኮንፍረንስ ተካሄደ።
ከሶስቱ ቀበሌዎች የተውጣጡ የሊግ አባላት የተገኙበትን ኮንፍረንስ የመሩት የጅንኤላ ወረዳ ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ሐላፊ አቶ ነሰረዲን ጁሃር የወረዳው ምክትል አስተዳዳሪ አቶ ኢብሳ አሊዩ እና የወረዳው የፖለቲካ ዘርፍ ሐላፊው አቶ ሰሚር ሙክታር ከተሳታፊዎች ለተነሱ በርካታ ጥያቄዎች ማብራሪያና ምላሽ ሰጥተዋል በመጨረሻም በቀጣይ ተግባራት ላይ በጥልቀት በመወያየት አቅጣጫ በማስቀመጥ መግባባት ላይ ተደርሶ ኮንፍረንሱ ተጠናቋል ሲል የጅንኤላ ወረዳ ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት አሳውቋል።

ይበል የሚየስብል ጅማሮ ነው ይህ የተጀመረው ኮንፍረንስ ሊግ ተጠናክሮ መቀጠል አለበት የተቀመጡ እና የተነሱት ሀሳቦች በሙሉ እንደሚተገበር ተስፋ አለኝ በርቱና አበርቱን ። ኢምራን ጀማል !

09/09/2023

ትናንትና በክልል ደረጃ በሁሉም ወረዳዎች በተደረገው የአመራር ሽግሽግና ሹመት ለጅንኤላ ወረዳ አዲስ የተመደቡ አመራሮችን እናስተዋውቃችሁ።
አቶ ፈቲህ ሀሰን የጅንኤላ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ
አቶ ኢብሳ አለዩ " " " ም/አሰተዳዳሪ
አቶ ነስረዲን ጁሀር " " ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ሐላፊ
አቶ ሰሚር ሙክታር " " " "የፖለቲካ ዘርፍ ሐላፊ
አቶ መሐመድ ሁሴን " " " የአደረጃጀት ዘርፍ ሐላፊ
አቶ አህመድ መሐመድ " " የሰላምና ጸጥታ አሰተባባሪ
አቶ አይመን አብዶሽ " "የከተማ ልማት አሰተባባሪ
አቶ ፈርሃን ቶውፊቅ " " የሚሊሺያ ዘርፍ አስተባባሪ ሆነው መመደባቸውን ከክልሉ የመንግስት ጉዳዮች ኮሚኒኬሽን የፌስቡክ ገጽ ላይ አግኝተነዋል።

መልካም የሥራ ዘመን ይሁንላቹ ።

በብሔር፣ በፖለቲካ፣ በጾታ፣ በፖለቲካ እሳቤ ተከፋፍለዋል ብለው የሚያስቡ አካላት ስህተት ሰርተዋል፡፡መላው ኢትዮጵያውያን አገር ስትደፈር በአንድነት ተሰልፎ የመትመም ቆየት ታሪክ ያለን ሕዝቦች...
22/10/2022

በብሔር፣ በፖለቲካ፣ በጾታ፣ በፖለቲካ እሳቤ ተከፋፍለዋል ብለው የሚያስቡ አካላት ስህተት ሰርተዋል፡፡መላው ኢትዮጵያውያን አገር ስትደፈር በአንድነት ተሰልፎ የመትመም ቆየት ታሪክ ያለን ሕዝቦች መሆናችን ሊታወቅ ይገባል።

ኢትዮጵያ ከዚህ ቀደምም በባህል፤ በሃይማኖት በቋንቋ፤ በፖለቲካ እሳቤ የሚለያዩ ሰዎች የነበሯት፣ ነገር ግን ልዩነቶቻቸው ሳያግዳቸው በኢትዮጵያዊነት ስለሚግባቡ ለኢትዮጵያ ህልውና በጋራ ተሰልፈው ነፃ አገር እንዳስረከቡን ሁሉ ዛሬም ከእያንዳንዱ ክልል፤ ከእያንዳንዱ ሃይማኖት፤ የተለያየ የፖለቲካ እሳቤ ውስጥ ያሉ ሕዝቦች ቢሆኑም ጠላቶቻችን ኢትዮጵያን ለመድፈር ሲፈልጉ በጋራ የምንቆምና ህልውናችንን የምናስከብር መሆናችንን ከትናንትናው ድላችን መማር ይገባቸዋል።

በነገው ዕለት በመላ አገሪቱ የሚካሄደው ሰላማዊ ሰልፍ የሽብር ቡድኑ በትግራይ ሕዝብ ላይ የሚፈፀመውን ግፍና መከራ ወደ ጎን በመተው ኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ ጫና የሚፈጥሩ አካላትን በቃችሁ የሚል ጥቅል መልዕክትን የያዘ ነው። ኢትዮጵያውያን ይህንን በሉአላዊነት ላይ የተጋረጠ መልከ ብዙ ጫና በጋራ ቆመው ድምጻቸውን ለማሰማት ነገ ማለዳ ቀጠሮ ይዘዋል።

የኢትዮጵያን የግዛት አንድነትን ለማስጠበቅ መንግስት እያደረገ ያለውን ጥረት የሚደግፍ ሰልፍ የፊታችን ቅዳሜ በአዲስ አበባ የሚካሄድ ሲሆን "ለኢትዮጵያ እቆማለሁ ድምጼን አሰማለሁ" በሚል መሪ ሃሳብ መንግስት የግዛት አንድነትን ለማስጠበቅ እያደረገ ያለውን ጥረት መደገፍ፣ የአንዳንድ የውጪ አገራትን አሉታዊ ጣልቃ ገብነት ማውገዝ እና ከኢትዮጵያ ጎን የቆሙ አገራትን የማመስገን ዓላማ አለው።

ሁሉም ኢትዮጵያዊ ለማይቀረው የኢትዮጵያ ብልጽግና ጉዞ የበኩሉን ሊወጣ እንደሚገባ በአንድ ወቅት ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ መልዕክት ማስተላለፋቸው አይዘነጋም።

ሠላማችን እና ፀዳታችን በእጃችን አብሮነታችንን እናዳብር በሚል መርህ በየሳምንቱ ቅዳሜ በመናሃሪያ የሚደረገው የጽዳት ስራ ዛሬም ተጠናክሮ እንደቀጠለ ይገኛል ።The weekly clean-up ...
28/05/2022

ሠላማችን እና ፀዳታችን በእጃችን አብሮነታችንን እናዳብር በሚል መርህ በየሳምንቱ ቅዳሜ በመናሃሪያ የሚደረገው የጽዳት ስራ ዛሬም ተጠናክሮ እንደቀጠለ ይገኛል ።

The weekly clean-up operation in Mahariha is still being carried out on the principle of peace and cleanliness.

⏩በሐረሪ ክልል በጂኔላ ወረዳ የሚገኙ 2ኛ እና 3ተኛ ዙር የብሔራዊ የበጎ ፈቃድ ማህበረሰብ ልማት አገልግሎት ሰጪ ወጣቶች🔈ምግቤን በጓሮ በሚል መሪ ቃል ዛሬ ለጎሮ አትክልት መትክያ ቦታዎችን ...
26/05/2022

⏩በሐረሪ ክልል በጂኔላ ወረዳ የሚገኙ 2ኛ እና 3ተኛ ዙር የብሔራዊ የበጎ ፈቃድ ማህበረሰብ ልማት አገልግሎት ሰጪ ወጣቶች🔈ምግቤን በጓሮ በሚል መሪ ቃል ዛሬ ለጎሮ አትክልት መትክያ ቦታዎችን በማዘገጀት እና የአትክልት ዘሮችን የመዝራት ስራ በመስራት በበጎነት የማገልገል ተግባራቸውን ቀጥለዋል ፡፡

⏩ኢትዮጵያን 🇪🇹፡፦ እናልማ፣እንገንባ ፣እንዘጋጅ

⏩Biyyaa kenyaa Haa misomsinu, Haa ijaruuu ,Haa qophofnuu

❤ኦርነት ደይነትሌ❤
❤Gaarummaa Wajjiin jireenyaf❤
❤በጎነት ለአብሮነት ❤

#ሼር በማድረግ ይተባበሩን❕

☄️ግንቦት 17,2014

Address

Harar

Telephone

+251924904882

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ጂኔላ ወረዳ ወጣቶች ሊግ/Genela wereda youth league posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to ጂኔላ ወረዳ ወጣቶች ሊግ/Genela wereda youth league:

Share