SOUTH OMO TVET Department

SOUTH OMO TVET Department Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from SOUTH OMO TVET Department, Legal, Demeka, Hamer.

25/04/2025
20/03/2025

በቀን 10/7/2017 አ/ም የቱርሚ ኮ/ኢ ኮሌጂ ግንባታ ያለበት ደረጃ ለማየትና በቀጣይ ግንባታው እሰከ ሰኔ 30/2017 አ/ም ድረስ እንዲጠናቀቅ ለማድረግ ከክልል የደብብ ኢትዮጱያ ክልል መንግስት ቴ/ሙ/ት/ስልጠና ቢሮ:የደቡብ ኢትዮጱያ ክልል መንግስት ዲዛይንና ግንባታ ቁጥጥር ድርጂት ;ቀፊት ግንባታውን የሚያከናውኑ ባለሙያዎች እንዲሁም የኮሌጅ ዋና ዲንና ምክትል ዲን በተገኙበት በቱርሚ ኮሌጂ ሰፋ ያለ ውይይት ተደርጓል።በውውይቱ ወቅትም ከክልል ዲዛይንናግንባታ ቁጥጥር ድርጂት የመጡ የህንፃ ግንባታ ባለሙያዎች የህንፃ ግንባታ በሚያሰቀምጠው ኖርምና አሰራረ መሠረት በፊት የነበረውን የኮሌጁን ግንባታ ግንባታውን ይሰሩ ከነበሩ ባለሙያዎች የቀረበውን ሪፖርት በጥልቀት ካዮ በሃላ ግንባተውን ዙረው አይተው።በፊት ይሰሩ ለነበሩ ባለሙያዎች ህንፃ ግንባታ ከሳይንሱና ኖረም አንፃር የነበሩ ቫሬሽኖች ላይ ሰፋ ያለ አሰተያየት ሰጥተዋል። እንዲሁም የክልሉ ቴ/ሙ/ት ስልጠና መምሪያ ሃላፊ በፊት የነበረው ግንባታ ላይ የነበሩ የአሰራር ችግሮችን በማንሳት በቀጣይ ለሚካሄደው ግንባታ አሰራር የግንባታ አሰራር ኖርምና ህጉን በጠበቀ መንገድ እስከ ሰኔ 30/2017 አ/ም እንዲጠናቀቅ በማሳሰብ ስብሰባው ተጠናቋል። ይሁንና ከክልል ዲዛይንና ግንባታ ቁጥጥር የመጡ ባለሙያዎች በፊት ስለነበው ግንባታ አጠቃላይ ሁኔታ ሰፋ ያለ ሪፓርት እንደሚያቀርቡ በተስፋ የሚጠበቅ ጉዳይ ነው።

30/01/2025

በደቡብ አሞ ዞን በሊሞ ጌንቶ ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ኮሌጅ የክሮፕ ፕሮዳክሽን አሠልጣኝ የነበሩት አቶ እሱባለው ሙናች በባለቤታቸው በደረሰባቸው ድንገተኛ ግድያ ምክንያት ከዚህ አለም በሞት ተለይተዋል።በአቶ እሱባለው ሙናች በደረሰው ድንገተኛ ሞት የደቡብ ኦሞ ዞን ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና መምሪያ ሠራተኞች የተሠማንን ጥልቅ ሀዘን እየገለጥፅን ለአቶ እሱባለው ሙናች በደረሰዉ ድንገተኛ ሞት ለወዳጆቹና ለቤተሠቦቹ መጥጥናናትን እየተመኘኘን ወንድማችን እሱባለው ሙናች እዚሀብሄር በብሄረ ገነት ነፋሱን እንዲቀበልልን የእግዚሀብሄር ፋቃድ ይሁንልን።

31/12/2024

በቱርሚ ኮ/ኢ ኮሌጂ በቀን 21/04/2017 አ.ም ከኮሌድ ቦርድ አባላት;ከኮሌጅ ሠራተኞች:ከዞን ቴክኒክና ሙያ ባለሙያዎች እና ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በኮሌጅ
1ኛ_በመማር ማስተማር የእርስ በእርስ አስተዳደር ችግሮች;
2ኛ_ከብልሹ አሰራር የፀዳ የኮሌጅ ምን ይመስላል በሚሉት አጀንዳ የቦርድ ሰብሳቢ አቶ አመሀ ስብሰባው የተጀመረ ሲሆን በዚህ ስብሰባም በኮሌጅ ባሉ አሠልጣኞችና ሌሎች ባለሙያዎች የኮሌጅ ነባራዊና አሁን ያለበት ወቅታዊ ችግሮችን አስቀምጠዋል።በተለይም ኮሌጅ ለወርክሾች ግብአት የሚሆኑ በጀቶችንም ሆነ ሌሎች ከክልል የሚለቀቁ በጀቶች በአግባቡ ና በግልጠኝነት ለታለማላቸው አላማ እንደማይውሉ የኮሌጅ ባለሙያዎች በተደጋጋሚ በስሜት ገልፀዋል።የኮሌጅ የቦርድ አባላት ና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ከኮሌጅ ባለሙያዎች ይህን ከሰሙ በሃላ የተጀመረው አጠቃላይ የኮሌጁ የ10 አመት ፋይናሻያል እንቅስቃሴ ኦዲት ተሎ ተጠናቆ የኦዲት ግኝቱ ሪፓርት እንዲደረግና የኮሌጅ ዲንና ም/ዲኖች አሁን ካሉበት ችግር በተሎ እንዲወጡ በአጥኖት አሳሰበዋል።ይህንም ሀሳብ የኮሌጅ ዲንና ሁለቱ ም/ዲኖች ችግሩን ለመፋታት ከመቸውም ጊዜ የበለጠ ጠንክረውና ተናበው እንደሚሰሩ ተማምነው ስብሰበው ተጠናቋል።በአጠቃላይ በዚህ ስብሰባ ኮሌጅን አንድ ምእራፋ የሚያሸጋግር ጥሩ ውይይቶ የተደረገበት ሲሆን ዋናው ቁልፋ ነገር ግን የተባሉት ሁሉ በተግባር ተቀይሮ ማየት መሆኑ አያጠያይቅም።ይሁንና ኮሌጅ በዞኑ ካለው የሠልጣኝ ቅበላና በዞኑ ከኢንተርፕራይዝና ስራ እድል ፈጠራ ጋር በተያያዘ 11000 ሠልጣኞችን ተቀብሎ ለ ማሰልጠን አሁንም በቂ ክላስ ናሌሎች ማቴሪያል ጉድለት በመኖሩ የሚመለከተው አካል ሁሉ ኮለጅ ተግባር ተኮር የተማረ የሠው ሀይል የሚፈራበት ተቋም እንደመሆኑ የሁሉን እርብርብ የሚጠይቅ መሆኑ አያጠያይቅም።

24/11/2024

የአንድ ሀገር እድገት የሚለካው ባላት የተማረ የሠው ሀይል ነው።ጀርመን በ2ኛው የአለም ጦርነት ከገባችበት የኢኮኖሚ ድቀት የወጣችው በቂ የተማረ የሠው ሀይል ስለነበራት ነበር።በተለይ የቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች ተግባር ተኮር የቸማረ የሠው ሀይል ከማፋራት አንፃር ድርሻቸው የላቀ ነው።ይሁንና እነዚህ ኮሌጆች ተማሪዎች ከቲወሪ ይልቅ በተግባር የተደገፈ እውቀት ለማስጨበት የተግባር ልምሞድ የሚያደርጉባቸው የወርክሾፕ ማቴርያልና ሌሎች ግብአቶች እጥረት ማነቆ እነደሆነ በብዙ የኢትዮጱያ ክፋሎች ይታቃል።ስለሆነም ሁሉም ኢትዮጱያዊ በየአካባቢው ያሉ የቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች ቢደግፋ ለሀገራችን እድገት ድርሻው የጉላ መሆኑ አያጠራጥርም

22/10/2024

ኢትዮጵያ ሀገራችን አሁን ካለችበት አስከፊ ድህነት ለመላቀቅ የተማረ የሠው ሀይል አስተዎፆኦው ከፋተኛ ነው።በተለይ የቴክኒክና ሙያ ተቋማት የሀገራችንን ነባራዊ ችግሮች ለመቅረፋ ከከፋተኛ ት/ት ተቋማት የበለጠ ድርሻ አላቸው።እንደ አብነት ብንወስድ ዶክተር ኢንጅነር ቅጣው እጅጉ በመጀመሪያ እግራቸው የረገጠውና ያን ሁሉ ጥበብ የገለጠላቸው የድሮው ባህርዳር ፓሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ነበር።ጠፈር ሁሉ ለመቆጣጠር የቻሉት ታድያ ከዚህ የምንረዳው ኮንስትራክሽንና ኢንድስትሪያል ኮሌጆች ናፓሊ ቴክኒክ ኮሌጆች በቴክኖሎጂ ለመምጠቅ ድርሻቸው እጅግ የጉላ በመሆኑ እነዚህ ኮሌጆች በተማላ ወርክ ሾፕ ተግባር ተኮር የሆነ ትውልድ እንዲቀርጡ ወርክሾፖች እንዲማሉ ሁሉም ኢትዮጵያዊ መረባረብ አለበት።ውጮች መጥተው ሀገራችን ሊያሳድጓት አይችሉም እኛ ነን ማሳደግ ያለብን ወገኔ ስማኝ በየአካባቢህ እንዚህን ኮሌጆች አጠናክር ነገ ድህነት ታሪክ ይሆናል

19/09/2024

የደቡብ ኢትዮጲያ ክልል መንግስት ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ቢሮ በቀን 9/1/2017 አ/ም በኮሌጆችና ከዞን መምሪያ ባለሙያዎች ጋር በአርባምንጭ ከተማ በጋሞ በሃል አዳራሽ በጋሞ ባህል ጨዋታዎች ታዳሚው ሲዝናና ከቆየ በሃላ የ2016 አ/ም እቅድ አፈፃፀምና የ2017 አ/ም እቅድ ገለፃ ተደርጓል።ከዚያም ከተሰብሳቢዎች ገንቢ ገንቢ ሀሳቦች ና ጥያቄዎች ተነስተው በክልሉ ቴክኒክና ሙያ ቢሮ ሃላፊ ና ባለሙያዎች ለተነሱ ጥያቄዎች መልስ ሰጠው በሌሎች ወቅታዊ ጉዳይ ገለፃ ካደረጉ በሃላ ጥሩ አፈፃፀም ላሳዮ ኮሌጆች የሽልማት መርሃ ግብር የከናዎነ ሲሆን በዚህም መሠረት በደቡብ ኦሞ ዞን የሚገኘው የሊሞ ጌንቶ ኮንስትራክሽንና ኢንድስተሪያል ኮሌጂ በዞን ደረጃ ሁለት እስከ አምስት ድረስ ኢንድስትሪያልና ኮንስትራክሽን ካላቸው ኮሌጆች 1ኛ በመውጣት ተሸልሟል።።

19/09/2024

የደቡብ ኢትዮጲያ ክልል መንግስት ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ቢሮ በቀን 9/1/2017 አ/ም በኮሌጆችና ከዞን መምሪያ ባለሙያዎች ጋር በአርባምንጭ ከተማ በጋሞ በሃል አዳራሽ በጋሞ ባህል ጨዋታዎች ታዳሚው ሲዝናና ከቆየ በሃላ የ2016 አ/ም እቅድ አፈፃፀምና የ2017 አ/ም እቅድ ገለፃ ተደርጓል።ከዚያም ከተሰብሳቢዎች ገንቢ ገንቢ ሀሳቦች ና ጥያቄዎች ተነስተው በክልሉ ቴክኒክና ሙያ ቢሮ ሃላፊ ና ባለሙያዎች ለተነሱ ጥያቄዎች መልስ ሰጠው በሌሎች ወቅታዊ ጉዳይ ገለፃ ካደረጉ በሃላ ጥሩ አፈፃፀም ላሳዮ ኮሌጆች የሽልማት መርሃ ግብር የከናዎነ ሲሆን በዚህም መሠረት በደቡብ ኦሞ ዞን የሚገኘው የሊሞ ጌንቶ ኮንስትራክሽንና ኢንድስተሪያል ኮሌጂ በዞን ደረጃ ሁለት እስከ አምስት ድረስ ኢንድስትሪያልና ኮንስትራክሽን ካላቸው ኮሌጆች 2ኛ በመውጣት ተሸልሟል።።

Address

Demeka
Hamer

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when SOUTH OMO TVET Department posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share

Category