Bruck Admass / ብሩክ አድማስ ጌጤ/

Bruck Admass / ብሩክ አድማስ ጌጤ/ Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Bruck Admass / ብሩክ አድማስ ጌጤ/, Legal, Amhara region, Gonder.

13/05/2023

✍️✍️✍️✍️ የአማራ ክልል ፍርድ ቤቶች ከፍርድ ቤትነት ወደ የሕግ ማሰልጠኛ ማዕከልነት እንዳይቀየሩ ያሰጋኛል

በዚህ አመት በ 9 ወሩ ብቻ በአማራ ክልል ከ 103 በላይ ዳኞች የዳኝነት ስራቸውን መልቀቃቸውን የጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዘደንት በክልሉ ምክር ቤት ስብሰባ ላይ ንግግር ማድረጋቸው ይታወቃል ። በቅርቡ ለመልቀቅ ያመለከቱት ቁጥርም ብዛት እንዳለው ይነገራል ።

የዳኝነት ሙያ ከጊዜ ወደ ጊዜ ልምድ በያዝን ቁጥር ከቅልጥፍና÷ከጥራትና ከስነ ምግባር አኳያ የሚሻሻል የሙያ ዘርፍ ነው ።
ዳኞች ተሹመው ሰራ ሲጀምሩ የመሰረታዊ ሕጎች / substantive laws / ችግር ብዙም ባይገጥማቸውም የስነ ስርዓት ሕጎች / procedural laws / እና የአስተዳደራዊ ስራዎች ላይ አዲስ እንደሚሆንባቸው አያጠራጥርም ።
ዳኞች አዲስ ተመድበው ሲሰሩ የአሰራር የቅልጥፍና መሰል ተግዳሮቶች ማጋጠሙ አይቀሬ ነው ።
ዳኞች 3 አመት ከሰሩ በኃላ በልምድ የዳበሩ ስለሚሆኑ በአሰራር ቀልጣፋ ወጭ ቆጣቢ ተደራሽ ስራን ይሰራሉ ተብሎ ይታመናል ። ዳኞች በቆይታ ብዛት በእውቀት ÷ክህሎትና ስነ ምግባር የተሻሉ ተቋሙንና ሕዝቡን ከበፊቱ በተሻለ ሁኔታ ያገለግላሉ ተብሎ ይታመናል ።
አሁን ባለው ሁኔታ ግን ዳኞች ይሾማሉ 3 አመት ሲሞላቸው በዚህ ወቅትም የተሻለ እውቀትና ክህሎት ልምድ ይዘው ተቋሙንና ሕዝቡን ያገለግላሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ብቃትና ጥራት ያሉት ዳኞች አሉት የሚል ስም ሊያገኝ ሲል በሌላ ሙያ መሰማራቱ ከዳኝነት ስራው የተሻለ ሁኖ ስለተገኘ የዳኝነት ሙያውን እየለቀቁ ይገኛሉ ።

ስለሆነም የአማራ ክልል ፍርድ ቤቶች ልምድ እውቀትና ክህሎት ያለቸው ዳኞች በየ ፍርድ ቤቱ እንዲኖሩ ፍርድ ቤቶች የማሰልጠኛ ማዕከል እንዳይሆኑ ከወዲሁ ለሚለቁ ዳኞች መፍትሔ ያስፈልጋል ።

በማዕከላዊ ጎንደር ዞን የማዕከላዊ አርማጭሆ ወረዳ ፍርድ ቤት ፕሬዘደንት
ቀን 05/09/2015 ዓ.ም

Address

Amhara Region
Gonder

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Bruck Admass / ብሩክ አድማስ ጌጤ/ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share

Category