ደምባ ጎፋ ወረዳ ፍትህ ጽ/ቤት Demba Gofa woreda justice office

ደምባ ጎፋ ወረዳ ፍትህ ጽ/ቤት Demba Gofa woreda justice office comprehensive legal service for our communities

03/03/2026
27/02/2026
የደምባ ጎፋ ወረዳ ፍትህ ጽ/ቤት የ2018 በጀት ዓመት 1ኛ መንፈቅ ዓመት የ6 ወር ተግባር አፈፃፀም ከባለ ድርሻ አካላት ጋር የግምገማና የቀጣይ ስራዎች የትኩረት አቅጣጫ ዉይይት አካሂዷል።የ...
23/02/2026

የደምባ ጎፋ ወረዳ ፍትህ ጽ/ቤት የ2018 በጀት ዓመት 1ኛ መንፈቅ ዓመት የ6 ወር ተግባር አፈፃፀም ከባለ ድርሻ አካላት ጋር የግምገማና የቀጣይ ስራዎች የትኩረት አቅጣጫ ዉይይት አካሂዷል።
የካቲት 16/2018 ዓ/ም
የደምባ ጎፋ ወረዳ ፍትህ ጽ/ቤት የ2018 በጀት ዓመት የ1ኛ መንፈቀ ዓመት 6 ወራት የዕቅድ አፈፃፀም ከባለድርሻ አካላት ጋር የግምገማና የቀጣይ ሥራዎች የትኩረት አቅጣጫ የማስቀመጥ መድረክ አካሂዷል።
በውይይት መድረኩ የደምባ ጎፋ ወረዳ ፍትህ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ የንገሬ የዴና እንደተናገሩት ጽ/ቤቱ የተጣለበትን ተግባርና ኃላፊነት ለመወጣት የ5 ዓመት መሪ ዕቅዶችን ከልሶ ተግባራትን እየሰራ እንደሚገኝና ለታቀደው ዕቅድ አፈፃፀም የባለድርሻ አካላት የተቀናጀ ሥራ ለላቀ ውጤት ጉልህ ሚና እንዳለው ገልፀዋል።
እንዲሁም ዕቅድን መነሻ በማድረግ የህግ የበላይነትን በወረዳችን ለማረጋገጥ ሕገ-መንግስቱንና ሕገ-መንግስታዊ ስርዓቱን ለማስጠበቅ፣ የዜጎችን ሰብዓዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶችን ለማክበርና ለማስከበር እንዲሁም መብትና ግዴታውን ጠንቅቆ የሚያቅ ህብረተሰብ ለመፍጠር በወረዳችን በሚገኙ ሁሉም ቀበሌያት በትኩረት እየተሰራ ይገኛል ብለዋል።
በመቀጠልም በዋና ዋና ሥራ ሂደቶች ማለትም:- በልዩ ልዩ ወንጀል ጉዳዩች፣ የሴቶችና ህፃናት ልዩ ምርመራና ክስ ጉዳዮች፣ የህግ ማርቀቅና ማስረጽ ዋና ሥራ ሂደትና የፍትሐብሄር ጉዳዮችን ዋና ስራ ሂደት ውጤታማና ችግር ፈቺ ስራዎች ተሰርተው የተሻለ አፈጻጸም ተመዝግቧል ብለዋል።
በፍርድ ቤቶች በኩልም እየተደረጉ በሚገኙ መደበኛ ክስና ክርክሮች የሚቀርቡ ክሶችን መርምሮ ቀልጣፋና አፋጣኝና ተገማች ውሳኔዎችን በመስጠት አርኪ አገልግሎት እየተሰጠ እንደሚገኝም ጭምር በውይይቱ ተገልጿል።
በተጨማሪም በአንዳንድ አካባቢዎች እጅግ ጫፍ የወጡ የመሬት ወረራዎችን በተመለከተ በጣም ፈታኝና የመሬት አስተዳደርን መሰረት አድርጎ አሰጣጡም ሆነ አወሳሰዱም ህጋዊ እንዲሆኑ ከግንዛቤ መፍጠር ጀምሮ መሬትን የማስመለስ ስራ ተሰርቷል ብለዋል።
የደምባ ጎፋ ወረዳ ፍርድ ቤት ፕረዚዳንት የሆኑት አቶ ድልነሳው ዲዶም በውይይቱ ፍርድ ቤቶች ለሚሰጧቸው ማናቸውም ውሳኔዎች የሁሉም ባለድርሻ አካላት ሚና የጎላ በመሆኑ ምቹ ባልሆነ ጂኦግራፊክ አቀማመጥና በሰፊ የቆዳ ስፋት ከፍትህ ቋሙ ርቆ ለሚገኘው ህዝባችን ፍትህን ተደራሽ ከማድረግ አንኳያ ሁሉም ባለድርሻ አካላት ትኩረት እንዲሰጥ አሳስበዋል።
በመጨረሻም የተግባር አፈፃፀም ሰነድ ቀርቦ የጋራ ውይይት የተደረገበት ሲሆን ተሳታፊ ባለድርሻ አካላት ሃሳብና አስተያዬት ሰጥተውበት የውይይት መድረኩ ተጠናቋል።

የካቲት 16/2018 ዓ.ም

👏👏👏
23/02/2026

👏👏👏

16/01/2026
Justice matters!⚖️⚖️⚖️
27/11/2025

Justice matters!⚖️⚖️⚖️

27/11/2025

#ማስታወቂያ
ለዳኝነት በወጣው ማስታወቂያ መሠረት ለጽሁፍ ፈተና የተመረጣችሁ ዕጩዎች የወጣ ማስታወቂያ
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ጠቅላይ ፍርድ ቤት The South Ethiopia Supreme Court

25/11/2025
15/10/2025

Address

Gofa Zone
Felege Niway

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ደምባ ጎፋ ወረዳ ፍትህ ጽ/ቤት Demba Gofa woreda justice office posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share