Hurso cadet school

Hurso cadet school መኮንን የሰራዊቱ ብሬን ነዉ

22/09/2025
19/09/2025
በሁርሶ እጩ መኮንን ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት ሲካሄድ የቆየው ስፖርታዊ ውድድር ተጠናቀቀ።  በማሰልጠኛ ትምህርት ቤቱ የ26ኛ ዙር ንስር ኮርስ እጩ መኮንን ሰልጣኞች ከስልጠና ጎን ለጎን ሲያካሂ...
19/09/2025

በሁርሶ እጩ መኮንን ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት ሲካሄድ የቆየው ስፖርታዊ ውድድር ተጠናቀቀ።



በማሰልጠኛ ትምህርት ቤቱ የ26ኛ ዙር ንስር ኮርስ እጩ መኮንን ሰልጣኞች ከስልጠና ጎን ለጎን ሲያካሂዱት የነበረው ስፖርታዊ ውድድር አሸናፊዎች ዋንጫ በማንሳት ተጠናቋል።

በዚህ ጨዋታ ማጠቃለያ ላይ ተገኝተው ለአሸናፊዎች ዋንጫ የሰጡት የሁርሶ እጩ መኮንን ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት አዛዥ ኮሎኔል ከድር ጫጮ ናቸው።

የውድድሩ አስተባባሪ የማሰልጠኛ ትምህርት ቤቱ የሠራዊት ሥነ-ልቦና ግንባታ ቡድን መሪ ሌተናል ኮሎኔል ገመቹ አሰፋ ውድድሩ ስፖርታዊ ጨዋነትን በተላበሰ መልኩ ሲካሄድ እንደቆየ ተናግረዋል።

ውድድሩ በሴቶች መረብ ኳስ ፣በወንዶች መረብ ኳስ፣ በሴቶች እግር ኳስ፣ በወንዶች እግር ኳስ ሲካሄድ ቆይቷል።

በእለቱ ከዋንጫ ሽልማት ውጭ በስልጠና ቆይታው ለማሰልጠኛ ትምህርት ቤቱ ሙያዊ አበርክቶት ሲያደርጉ ለነበሩ አመራሮች አሰልጣኞችና እጩ መኮንን ሰልጣኞች የእውቅናና የምስጋና ሰርተ-ፊኬት ተሰጥቷል።

ዘጋቢ ሜሮን ጌታነህ
ፎቶ ግራፍ ሩሚያ ዩሱፍ

📌📌Telegram channel
👇👇👇👇
https://t.me/officer26R
📌📌 website
👇🌐🌐🌐🌐
https://www.hursoocts.com
📌📌You tube channel
👇👇🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
https://www.youtube.com📡
📌 📌page
👇👇👇🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
https://web.facebook.com/profile.php?id=61579221754852
መኮንን የሰራዊቱብሬን ነው።
Cadet26‼️

ተተኪ መኮንኖች የአባቶቻችሁን ታሪክ በመውረስ የኢትዮጵያ መለያና አርማ መሆን ይገባችኋል፡፡    ሌተናል ጄኔራል ይመር መኮነን  የመከላከያ ትምህርትና ስልጠና ዋና መምሪያ ሀላፊ ሌተናል ጄኔራ...
19/09/2025

ተተኪ መኮንኖች የአባቶቻችሁን ታሪክ በመውረስ የኢትዮጵያ መለያና አርማ መሆን ይገባችኋል፡፡

ሌተናል ጄኔራል ይመር መኮነን


የመከላከያ ትምህርትና ስልጠና ዋና መምሪያ ሀላፊ ሌተናል ጄኔራል ይመር መኮነን በሁርሶ ዕጩ መኮንን ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት ለ26ኛ ዙር ንስር ኮርስ ዕጩ መኮንኖች የአውደ ውጊያ ተሞክሮ አስተላልፈዋል፡፡
ጠንካራ እና ዘመናዊ ሠራዊት ለመገንባት ብቁ መኮንኖች መኖር አለባቸው እነዚህ መኮንኖች የሚገኙት ደግሞ ከብቁ ማሰልጠኛ ማዕከል ነው፤ እናንተ ልክ እንደ ጥቁር አንበሳ ኮርስ ሀገር በፈለገቻቸው ሰዓት ተገኝተው ደማቅ ታሪክ እንደፃፉት ሁሉ የነሱን ፈለግ መከተል አለባችሁ ብለዋል

የጀግንነትና አልደፈር ባይነታችን ሲነሳ ሁሌም አርበኞቻችንና ጀግኖቻችን እናስታውሳለን አሁንም በዚህ ትውልድ ጀግኖች እየተፈጠሩ ነው፤በፈተናዎች ተፈትነው ድል በማድረግ ፈንጥቀው የወጡ በከፍተኛ ጀብዱነት ሀገርን ያዳኑ የሀገር ባለውለታዎች ተፈጥረዋል ሲሉም ተናግረዋል፡፡

ሌተናል ጄኔራል ይመር መኮንን እናንተ ተኪ መኮንኖች የባንዳነት ተግባር የምትጠየፉና የኢትዮጵያ መለያ፤ አርማና አምባሳደር ናችሁ ሲሉም ገልፀዋል፡፡
የትምህርትና ስልጠና ዋና መምሪያ ምክትል ሀላፊ ለአመራር ስልጠና ሜጄር ጄኔራል ሰለሞን ቦጋለ

አያት ቅድመ አያቶቻችን ዳር ደንበሯ ሳትደፈር ከነ ሙሉ ክብሯ ያስረከቡን ሀገር አያሌ መስዋዕቶችን በመክፈል መሆኑን ገልፀው በተለያዩ ጊዚያት የተካሄዱት አውደ ውጊያዎች በኢትዮጵያ አሸናፊነት የተጠናቀቁ ቢሆንም ባንዳዎች ግን ነበሩ ብለዋል።
አሁንም እዚህም እዚያም የጠላት ተልዕኮ በመቀበልና ፍርፋሪ ለማግኘት ከታሪካዊ ጠላቶቻችን ጭምር በማበር የባንዳነት ስራ እየሰሩ ያሉትን የሀገራችን ልጆች የታሪክ ተወቃሽ አትሁኑ ሀገራችን ኢትዮጵያ ሁሌም አሸናፊ ነች ሲሉም ተናግረዋል።

ዘጋቢ ፊሊሞን ገብረእግዚሀብሔር
ፎቶግራፍ ሩሚያ ዮሱፍ

📌📌Telegram channel
👇👇👇👇
https://t.me/officer26R
📌📌 website
👇🌐🌐🌐🌐
https://www.hursoocts.com
📌📌You tube channel
👇👇🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
https://www.youtube.com📡
📌 📌page
👇👇👇🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
https://web.facebook.com/profile.php?id=61579221754852
መኮንን የሰራዊቱብሬን ነው።
Cadet26‼️

የ54ኛ ዙር ተመራቂ መኮንኖች የሁርሶ ዕጩ መኮንን ማሠልጠኛን ጎበኙ የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ሃምሌ 30 ቀን 2017 ዓ.ም በቀድሞ አጠራሩ ሁርሶ ጦር ትምህርት ቤት የ54ኛ ዙር ተመራቂ መኮ...
19/09/2025

የ54ኛ ዙር ተመራቂ መኮንኖች የሁርሶ ዕጩ መኮንን ማሠልጠኛን ጎበኙ
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ሃምሌ 30 ቀን 2017 ዓ.ም

በቀድሞ አጠራሩ ሁርሶ ጦር ትምህርት ቤት የ54ኛ ዙር ተመራቂ መኮንኖች የሁርሶ እጩ መኮንን ማሰልጠኛ ትምህርት ቤትን በመጎብኘት ማሰልጠኛው እንደ አዲስ ማሰልጠን ከጀመረ ለ26ኛ ዙር ተቀብሎ ንስር ኮርስ በሚል መጠሪያ ለሚያሰለጥናቸው ዕጩ መኮንን ሰልጣኞች ተሞክሯቸውን አጋርተዋል።

የቀድሞ ተመራቂዎቹ በ1982 ዓ.ም በጀማሪ መኮነንነት ተመራቂ መሆናቸውን ገልጸው አሁን ላይ በተለያየ የግል ስራ ላይ ቢሆኑም ሀገር በፈለገቻቸው በየትኛውም ወቅት አዎንታዊ ምላሽ ሲሰጡ መቆየታቸውን በማስታወስ ለቀጣይም ዝግጁ መሆናቸውን አረጋግጠዋል።

ያለችን አንዲት ሀገር ናት ለእሷ ደግሞ የትኛውንም አይነት ዋጋ ለመክፈል ዝግጁ ነን ያሉት የቀድሞ ተመራቂ መኮንኖቹ የአሁኑ ትውልድም በኢትዮጵያ ጉዳይ በምንም አይነት ነገር ሳይታለል ምትክ አልባ ሀገሩን በቅንነት እና በታማኝነት ማገልገል እንዳለበት ጠቁመው የ26ኛ ዙር ንስር አጭር ኮርስ አባላትንም የአመራርነት ስልጠናቸውን ጨርሰው ወደ አሃድ ሲቀላቀሉ ሀገራቸውን በታማኝነት እና በቅንነት ማገልገል እንዳለባቸው አሥገንዝበዋል።

የሁርሶ ዕጩ መኮንን ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት አዛዥ ኮሎኔል ከድር ጫጮ 54ኛ ዙር ተመራቂ መኮንኖች ከ34 አመታት በኋላ በተመረቁበት ትምህርት ቤት ተገኝተው ያደረጉት ጉብኝትና ተሞክሮ ልውውጥ የውትድርና ሙያ በተቋሙ እስካሉ ብቻ የሚሰራበት ሳይሆን ከተቋሙ ከተለዩ በኋላም ሀገር እና ህዝብን በተለያዬ የሙያ መስክ ለማገልገል መሰረት መሆኑን ከማሳየቱም በላይ ፍጹም ኢትዮጵያዊነት የተንጸባረቀበት እንደሆነ ገልፀዋል።

ዘጋቢ በፊሊሞን ገብረእግዚሃብሔር
ፎቶ ግራፍ ሩሚያ ዮሱፍ

📌📌Telegram channel
👇👇👇👇
https://t.me/officer26R
📌📌 website
👇🌐🌐🌐🌐
https://www.hursoocts.com
📌📌You tube channel
👇👇🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
https://www.youtube.com📡
📌 📌page
👇👇👇🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
https://web.facebook.com/profile.php?id=61579221754852
መኮንን የሰራዊቱብሬን ነው።
Cadet26‼️

Address

Hurso
Dire Dawa
1001

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Hurso cadet school posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share

Category