ሕጉ ምን ይላል/Seeri Maa Hiya'ne

ሕጉ ምን ይላል/Seeri Maa Hiya'ne Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from ሕጉ ምን ይላል/Seeri Maa Hiya'ne, Lawyer & Law Firm, Dillaa, Dilla.

    📝📝 በፍትሐብሔር ክስ 📝📝📝  #ተከሳሾች የክስ ጉዳይ ከመታየቱ  በፊት የምከተሉ ነጥቦች ላይ ቅሬታ ካላቸው መቃወሚያ ማቅረብ አለባችው 👉ፍርድ ቤቱ ሥልጣን የለውም በማለት  መቃወሚያ 👉...
01/06/2025


📝📝 በፍትሐብሔር ክስ 📝📝📝

#ተከሳሾች የክስ ጉዳይ ከመታየቱ በፊት የምከተሉ ነጥቦች ላይ ቅሬታ ካላቸው መቃወሚያ ማቅረብ አለባችው

👉ፍርድ ቤቱ ሥልጣን የለውም በማለት መቃወሚያ
👉ክስ የቀረበበት ጉዳይ አስቀድሞ በፍርድ የተወሰነ ነው
👉ጉዳዩ ' በሌላ ' ፍርድ ቤት በክርክር ፡ ላይ ፡ ያለ ከሆነ
👉አንደኛው ተከራካሪ ወገን በነገሩ ፡ የማያገባው በመሆ ኑ ' በመግለጽ ክስ ዉስጥ ገብቶ ፡ መከራከር ፡ አይገባውም የሚል መቃወሚያ :
👉 ክሱ' በይርጋ' የታገደ መሆኑን የሚገልጽ ፡ መቃወሚያ
👉ጉዳዩ በእርቅ ያለቀ ወይም ለእርቅ የተቀጠረ፡ መሆኑን የሚገልጽ ፡ መቃወሚያ

👉የክሱ አቀራረብ ትክክለኛውን ፎርም አልተከተለም በማለት መቃወሚያ ለማቅረብ ግን #አይቻልም ።
"""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""
በሳሙኤል ተሰማ (LLB,LLM)
Attorney

28/05/2025

ሕጋዊ የመኪና ሽያጭ ውል ለመፈፀም መሟላት ያለባቸው ሰነዶች ያውቃሉ?
"""""""""""""""""""""""""""'''"""""""""""""
::
👉በሕግ አግባብ የተዘጋጀ የሽያጭ ውል ሰነድ/ፎርም/
👉እዳና እንዳ ስላለመኖሩ የተጣራ መሆኑን ማረጋገጥ፤
👉የባለቤትነት ማስረጃ ሊብሬ፤
👉የሻጭና የ7ዥ መታወቂያ
👉ሻጭ ከህግ ወይም ከውል የመነጨ የመሸጥ ስልጣንን የሚያረጋግጥ ህጋዊ ሰነድ
👉ንብረቱ የንግድ ማህበር ከሆነ የማህበሩ መመስረቻና መተዳደሪያ ደንብ፣ ዋና የንግድ ምዝገባ፣ እንዳስፈላጊነቱ ቃለፖባኤ!
👉የሻጭ ያላ7ባ ማስረጃ ወደም ያ7ባ ከሆነ የጋብቻ ማስረጃ እና የትዳር አጋር የፈቃድ ስምምነት፣
👉ከትራንስፖርት ባለስልጣን የሚሰጥ የመኪና ዋጋ ግምት
👉ለኮድ 1 እና 3 ከትራንስፖርት ባለስልጣን እና ከ7ቢዎች የሚሰጥ ከሊራንስ፤
👉ለኮድ 1 እና 3 አስር ዓመት ቢሞላውም ከቀረጥ ነፃ ከሆነ ከገቢዎችና ጉምሩክ ከቀረጥ ነፃ መብት ማስተላለፍ ባለሥልጣን የተፃፈ ደብዳቤ ወደም ይህን መነሻ በማድረግ መንገድ ትራንስፖርት የሚሰጠው የማረጋገጫ ሰነድ!

ሕጉ ምን ይላል ?
በሳሙኤል ተሰማ (LLB,LLM)
Attorney

27/05/2025


📝📝📝📝📝📝📝📝📝

1👉ማንኛውም ሰው እያወቀ ወይም ማወቅ ሲገባው የጉምሩክ ህጎችን በመተላለፍ የተከለከሉ፣ ገደብ የተደረገባቸው ወይም የንግድ መጠን ያላቸውና የጉምሩክ ሥነ-ሥርዓት ያልተፈጸመባቸው ዕቃዎችን
📝በድብቅ ወይም ከህጋዊ መተላለፊያ መስመሩ ውጪ ወደ አገር ካስገባ፣
📝ከሀገር ካስወጣ ወይም
📝ከአገር ለማስወጣት ወይም ለማስገባት ከሞከረ ወይም
📝በህጋዊ መንገድ የወጡ ዕቃዎችን በህገወጥ መንገድ መልሶ ካስገባ በማያንስና #ከአሥር ዓመት በማይበልጥ 200ሺ መቀጮ ይቀጣል፡፡

2👉ከላይ በተመለከተው ሕገወጥ መንገድ የተገኙ ዕቃዎች መሆናቸውን እያወቀ ወይም ማወቅ ሲገባው ዕቃዎቹን
📝 ያጓጓዘ፣
📝ያከማቸ፣
📝 የያዘ፣
📝ለሽያጭ ያቀረበ ወይም
📝 የገዛ ማንኛውም ሰው
በማያንስና በማይበልጥ እና ከብር 50ሺ እስከ ብር 100ሺ በምሚሆን መቀጮ ይቀጣል፡፡

3👉 በመጀመሪያ ነጥብ የተመለከተው ወንጀል የተፈፀመው ወይም ከሆነ የፅነ- እስራት ቅጣቱ ከ10 ዓመት እስከ 15 ዓመት ከፍ ይደረጋል፡፡

📖የፌደራል ጉምሩክ አዋጅ ቁ.859/2006📖
📝📝📝📝📝📝📝📝📝

በሳሙኤል ተሰማ (LLB,LLM)
Attorney

27/05/2025

" " የfacebook ገፅ
ከዚህ በፍት ለ 5ተከታታይ አመታት የሕግ ግንዛቤ ለማስፋት በስፋትና በጥልቀት የሕግ ትንተና እየሰጠ ለጥያቀዎቻችሁ ተገቢውን ምላሽ እያቀረበ ከእናንተ ጋር የቆዬ ሲሆን በቅርብ ጊዜ group የተመሰረተበትን የsamuel tesema account hack በማድረግ ከጥቅም ውጭ በማድረጋቸው ከእናንተ ጋር ለመገናኘት ባለመቻሉ ይህን አድስ group ለመክፈት ተገድጃለሁ::
ስለሆነም ውድ የገፁ ተከታዮች ሌሎችንም ወደዝህ በመጋበዝ/invite በማድረግ ሕግን ባለማወቅ ከሚገጥማችሁ የመብት ጥሰትና የጥቅም ጉዳት ራሳችሁን እንድትታደጉ እጠይቃለሁ 🙏🙏

Address

Dillaa
Dilla

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ሕጉ ምን ይላል/Seeri Maa Hiya'ne posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share