Butajira Area Justice Coordination

Butajira Area Justice Coordination This page is created for the purpose of contacting with the public at large via internet. At this pa

የጉራጌ ዞን ፍትህ መምሪያ ቡታጅራ አካባቢ ፍትህ ማስተባበሪያ በ 2008 ዓ.ም በጉራጌ ዞን የተለዩየ ፍትህ ጽ/ቤቶች ለተመደቡ ጀማሪ ዐቃብያነ ህግ በክስ አመሰራረት እና በቅጣት አወሳሰን መመ...
16/09/2016

የጉራጌ ዞን ፍትህ መምሪያ ቡታጅራ አካባቢ ፍትህ ማስተባበሪያ በ 2008 ዓ.ም በጉራጌ ዞን የተለዩየ ፍትህ ጽ/ቤቶች ለተመደቡ ጀማሪ ዐቃብያነ ህግ በክስ አመሰራረት እና በቅጣት አወሳሰን መመሪያ ላይ ከመስከረም 6-9/2009ዓ.ም ድረስ ስልጠና በመሰጠት ላይ ይገኛል።

15/09/2016

የቡታጅራ አካባቢ ፍትህ ማስተባበሪያ ከፍተኛ ዐ/ህግ የሚሰጣቸው አገልግሎቶች
1.የዜጎችን ሰብአዊ መብቶች እንዲከበር እና እንዲረጋገጡ በሕግ አግባብ ክትትልና ቁጥጥር አድርጎ የህግ የበላይነትን ማረጋገጥ፡፡
2.ከባድና ውስብስብ ወንጀሎችን በማጣራት ሂደት ከፖሊስ ጋር በቅንጅት መስራት፣ ተጣርተው በመጡ የምርመራ መዝገቦች ላይ በችሎት በሕግ አግባብ ክርክር አድርጎ ውሳኔ እንዲሰጥባቸው በማድረግ የሕግ የበላይነት ማረጋገጥ፡፡
3.ከስር የሚወጡ የወንጀልና የፍታብሔር የይግባኝ ቅሬታዎችን ተቀብሎ ክርክር ማድረግ፣ ይግባኝ መጠየቅና አፈጻጸም መከታተል፡፡
4.ልዩ ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው የህብረተሰብ ክፍሎች የሕግ ድጋፍና የምክር አገልግሎት መስጠት፡፡
5.የመንግስትና የህዝብ ጥቅም ያለባቸው የፍ/ሔር ጉዳዮችን ለይቶ በመከታተል በድርድርና በክስ ገቢ እንዲሆን በማድረግ የመንግስትና የሕዝብ ተጠቃሚነትን ማረጋገጥ፡፡
6.ፍትህ ነክ አቤቱታዎችንና ቅሬታዎችን ተቀብሎ ምላሽ በመስጠት የተገልጋይ እርካታን ማሳደግ፡፡

የጠበቆች ሲቪል ማኅበራት ፈቃድ ውል ምዝገባ ዋና የስራ ሂደት የሚሰጣቸው አገልግሎቶች
1.የተለያዩ ውልና ውክልናዎችን ህጋዊነታቸውን መርምሮ በማጽደቅ የተገልጋይ ህብረተሰብ ተጠቃሚነትን ማረጋገጥ፡፡
2.የተለያዩ የውል ይፍረስልኝ እና የውክልና ይሻርልኝ ጥያቄዎችን በመቀበል ህጋዊነታቸውን መርምሮ ማጽደቅ
3.ጠበቆች ሕግንና የስነ-ምግባር መመሪያውን አክብረው መስራታቸውን ድጋፍ ፣ ክትትልና ቁጥጥር ማድረግ
4.ጠበቆች ለአቅመ ደካማ የህብረተሰብ ክፍሎች የ50 ሰዓት ነጻ የህግ ድጋፍ አገልግሎት እንዲሰጡ ማድረግ
5.ጠበቆች ላይ የሚቀርቡ የስነ-ምግባር አቤቱታዎችን አጣርቶ ለክልሉ እና ለዞኑ የጠበቆች የሥነ-ምግባር ጉባኤ ማቅረብ፡፡
6.የስራ ሂደቱ የሚሰጣቸውን አገልግሎቶች ህበረተሰቡ እንዲያውቃቸውን እንዲገነዘባቸው ለስር መዋቅር ድጋፍ ማድረግ፡፡

Address

Butajira

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Butajira Area Justice Coordination posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Butajira Area Justice Coordination:

Share