26/08/2026
የካፍቾ ዘመን መለወጫ "ማሽቃሮ" በዓል የእስካሁን የስራ አፈፃፀምና በቀር ስራዎች ዙሪያ ከበዓሉ ኮሚቴዎች ጋር ውይይት ተደረገ።
በካፋ ዞን ጨታ ወረዳ ባህል ቱሪዝምና ስፖርት ጽ/ቤት 2019 ዓ/ም በሚከበረው የካፍቾ ዘመን መለወጫ "ማሽቃሮ" በዓል የእስካሁን ቅድመ ዝግጅት ዙሪያ ከኮሚቴዎች ጋር ውይይት ተደርጓል።
ውይይቱን የመሩት የወረዳ ምክትል አስተዳደርና ሥራ ክህሎት ጽ/ቤት ኃላፍ አቶ ከተማ ከፍያለው የሳምንታት ዕድሜ ብቻ ለቀረው የካፍቾ ዘመን መለወጫ "ማሽቃሮ" በዓል ኮሚቴዎች በትኩረትና በፍጥነት መስራት ይጠበቅባቸዋል ብለዋል።
በዓሉን በዩኔስኮ ዓለም አቀፍ ቅርስነት ለማስመዝገብ የተለያዩ ጥናታዊ ጹሑፎችን በማቅረብ በርካታ ስራዎች እየተሰሩ ነው በማለት ለውጤታማነቱ የባለድርሻ አካላቶች ርብርብ እንዲጠናከር ጠይቀዋል።
አቶ ከተማ የሀብት አሰባሰብ ስራን ለማጠናከር በተሰራው ስራ ከወረዳ አመራር ጀምሮ ሁሉም መሳተፋቸውን ጠቁመው በማመስገን ያልተሳተፉ አካላቶችም የበኩላቸውን እንዲወጡ ጠይቀዋል።
የወረዳ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የህዝብ ግንኙነት ዘርፍ ኃላፍ ወ/ሮ አበባሽ አበበ ባህል የአንድ አካባቢን ማህበረሰብ ማንነትና የአኗኗር ሂደትን አጉልቶ ከማሳየት እረገድ የማይተካ ሚና የሚጫወት ነው በማለት በየግዜው ይህ ማንነት ደምቆ እንዲታይ ባለመታከት ለትውልድ የሚያስተላልፉ ኮሚቴዎች ልመሰገኑ ይገባል ብለዋል።
በዓሉ ባህላዊ ይዘቱን ጠብቆ በድምቀት እንዲከበርና የተሟላ የእንግዳ አቀባበል እንዲኖር የደመቀ የፌስቲቫልና የካርኒቫል ቅድመ ዝግጅት እንዲኖር አሳስበዋል።
የወረዳ ባህል ቱሪዝምና ስፖርት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ መሸሻ መኩሪያ የእስካሁን የስራ አፈፃፀም ባቀረቡበት ወቅት የመንግስት ስራተኞችን ጨምሮ ሁሉንም ማህበራዊ መሰረት በማሳተፍ 1ሚልዮን 1መቶ 29ሽህ 5መቶ 70ብር መሰብሰብ ተችሏል ብልዋል።
በሀብት አሰባሰብ ስራ ላይ የሀይማኖት ተቋማቶችን ጨምሮ ሁሉም አካላቶች መሳተፋቸውን በማስታወስ የባለቤትነትና የእኔነት ስሜት በማህበረሰቡ ውስጥ መኖሩን የሚያሳይ ነው ብለዋል።
የበዓሉ አብይና ቴክኒክ ኮሚቴዎችም በቀረቡ የእስካሁን የስራ አፈፃፀሞች ላይ በመነጋገር በአጭር ግዜ ውስጥ ቀሩ የተባሉ ስራዎችን ቆጥረው በመስራት ስኬታማ በዓል ለማክበር የድርሻውን እንደሚወጡ አሳውቀዋል።
በኤልያስ ጋሎ
የጨታ ወረዳ መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት፦ወቅታዊ፣ ተዓማኒ፣ ትኩስና ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ፌስቡክና ቴሌግራም ገፆቻችን ይከታተላሉ ፣ይወዳጁ👇👇👇👇👇????
በፌስቡክ፦https://www.facebook.com/profile.php?id=100091368031356
በቴሌግራም፦https://t.me/C12g6/1057?single
በቲክቶክ፦https://vm.tiktok.com/ZMHtnCGMKnVKa-Th2vR/