Beteህግ

Beteህግ ህግ ፅሁፎችን ማጋራት

ህዳሴ ዘመኑ ትባላለች!!የተወለደችው በ2000ዓ.ም ነው።በእንጅባራ/ኮሶበር/ከተማ አገው ምድር ትምህርት ቤት በዘንድሮው የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና  583/600 በማምጣት በሀገሪቱ 2ኛው...
23/08/2026

ህዳሴ ዘመኑ ትባላለች!!የተወለደችው በ2000ዓ.ም ነው።በእንጅባራ/ኮሶበር/ከተማ አገው ምድር ትምህርት ቤት በዘንድሮው የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና 583/600 በማምጣት በሀገሪቱ 2ኛውን ከፍተኛ ውጤት አስመዝግባለች።
ይህ ውጤት ይፋ ከመሆኑ በፊትም በትምህርት ቤቱ የ11ኛ ክፍል አማካይ99.67በማምጣቷ ''ህዳሴ ቤተመፃህፍት'' በሚል ተሰይሞላታል።
እንኳን ደስ አለሽ!!!!መምህራኖቿ እና ቤተሰቧቿም ክብር ይገባችኋል!!!

21/08/2026

አዲስ አበባ ሁሉም ኢትዮጵያውያን የምንገናኝበት: ማንነትን የምንጋራበት: ውህደት የምንፈጥርበት: ከአፍሪካውያን ጋር የምንተሳሰርበት - ብቸኛ የጋራ ሀብታችን ናት: አአ ከመሬትነት በላይ ናት: ድርድር የለም!!!!!

18/08/2026

እንኳን አደረሳችሁ!!!ቅዱስ ሚካኤል በድንገት ወጥቶ ከመቅረት ይጠብቃችሁ!!

12/08/2026

አዲስ አበባ የሁሉም ኢትዬጵያውያን ከተማ እንጂ የአንድ ብሔር ከተማ ለማድረግ ማሰብ ስግብግብነት ነው።በመሆኑም በምክክር ኮሚሽን ስም ይህን የአንድ ቡድን ፍላጎት ህጋዊ መሰረት እንዲኖረው ለማድረግ የምትሰሩ ወገኖች የታሪክ ተወቃሽ እንዳትሆኑ ጥንቃቄ እንድታደርጉ በጥብቅ እናሳስባለን።
ሠላም ለሀገራችን!

06/08/2026

በአገራዊ ምክክር ጉባኤው አመካካሪዎችና ምሁራን ሐሳብ እንዲቀይሩ ለማድረግ ያልተገባ ተፅዕኖ እያሳደሩ መሆኑ ተነገረ

: - "የዘመሙ አካሄዶች ሲታዩ በጊዜውና በወቅቱ ዕርምት ይደረግባቸዋል"
የኢትዮጵያ አገራዊ ምክክር ኮሚሽን
- 250ው ስልታዊ ቡድን አዲስ አበባና ድሬዳዋ የፌዴራል አካል ሆነው እንዲቀጥሉ መግባባት ላይ መደረሱ ተገልጿል
የአገራዊ የምክክር ጉባዔ በአጀንዳ ጭብጦች ላይ ገለጻና ማብራሪያ እንዲሰጡ የተመደቡ አመካካሪዎች፣ምሁራንና ቃለ ጉባዔ ያዦች፣ ተመካካሪዎች የሚያነሱትን ሃሳብ ባለመቀበልና በተለይ የመጡበትን ተቋም መሠረት ያደረገ አቋም በመያዝ፣ ተመካካሪዎች ሐሳብ እንዲቀይሩና የምክክር ሒደቱ እንዲዘገይ ተፅዕኖ እያሳደሩ መሆኑን ስማቸው እንዲገለጽ ያልፈለጉ ተመካካሪዎች ገለጹ
በተለይ መንግሥትን ወክለው የመጡ አመካካሪዎች እንደ የመንግሥት አደረጃጀትና አገር ግንባታ ያሉ አጀንዳዎችን በተመለከተ ከምክክሩ ሒደት ባፈነገጠ መልኩ የራሳቸውን ሐሳብ ማንፀባረቃቸውን ምንጮች ተናግረዋል።
የመንግሥት አደረጃደት አጀንዳን በተመለከተ እንዲያወያዩ በኮሚሽኑ የተመደቡ አመካካሪዎች በዚህ የተነሳ ለቀናቶች ውይይት እንዳይመሩና ማይክ ብቻ እንዲያቀብሉ በማድረግ፣ በእነርሱ ምትክ ደግሞ ከቡድን መሪዎች ተመርጠው ውይይት እንዲመሩ መደረጉን ገልጸዋል።
ከዚህ አልፎ የኮሚሽኑ አመካካሪዎች ውይይት እንዲመሩ የተደረገበት ሁኔታ መኖሩን ጨምረው ተናግረዋል። በዚህ የአጀንዳ ሐሳብ በተለይ የተለያዩ የፓርቲዎችን ወክለው የተገኙ ተመካካሪዎች የአመካካሪዎች አካሄድ በተመለከተ ቅሬታ አቅርበው ሁኔታው ከላይ በተገለጸው መንገድ እንዲመራ መደረጉን ተመካካሪዎቹ ተናግረዋል።

(ሪፖርተር)

🔗

በቃ አታልቅስ!!!
20/07/2026

በቃ አታልቅስ!!!

ይታያል ዛሬ!!!!
19/07/2026

ይታያል ዛሬ!!!!

19/07/2026

የ2026 የአለም ዋንጫ ማን ያሸንፋል??ቀድሞ በትክክል ለገመተ የሶስት ሰው ለእንዳንዱ 500ብር የሞባይል ካርድ ይሞላል።

17/07/2026

በክልሉ ፍርድ ቤቶች የ2018 ስትራቴጂክ እቅድ እና የሶስት ዓመት ትራንስፎርሜሽን ትግበራ አፈጻጸም ውይይት ላይ የተገኙ የጎንደር ከተማ ተሳታፊዎች ለክቡር አቶ አለምአንተ አግደው ስጦታ አበረከቱ

ባሕር ዳር፣ ሐምሌ 10/2018 (የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት)

የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በክልሉ ፍርድ ቤቶች የ2018 በጀት ዓመት ስትራቴጂክ እቅድና በሶስት ዓመቱ የትራንስፎርሜሽን ትግበራ ላይ ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች እና ተቋማት ከተወጣጡ ተሳታፊዎች ጋር መወያየቱ ይታወቃል።

በውይይቱ ወቅት ከተገኙ ተሳታፊዎች መካከልም ከጎንደር ከተማ የመጡ ተሳታፊዎች ተጠቃሾች ናቸው።

የጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ፕሬዝደንት ክቡር አቶ አለምአንተ አግደው የክልሉን የዳኝነት እና የፍትሕ ስርዓት በመሰረታዊነት ለመለወጥ የጀመሯቸው የለውጥና የማሻሻያ ስራዎች በአጭር ጊዜ ውስጥ አበረታች ውጤቶችን አስመዝግበዋል ያሉት ተወካዮቹ፣ ክቡር ፕሬዝደንቱ ለሌሎች ተቋማት እና የክልሉ ከተሞች አመራሮች መነቃቃትን የፈጠረ ስራ እየሰሩ ነው ብለዋል።

ክቡር ፕሬዝደንቱ ከራሳቸው ተቋም አልፈው ታሪካዊቷ የጎንደር ከተማ ምቹ የመኖሪያና የቱሪዝም መዳረሻ እንድትሆን ከተማ አስተዳደሩና የከተማዋ ነዋሪዎች እያደረጉት ላለው እንቅስቃሴ የበኩላቸውን አስተዋጽኦ ተወጠዋል ያሉት የጎንደር ከተማ ተሳታፊዎች፣ ለክቡር ፕሬዝደንቱ ስጦታ አበርክተውላቸዋል።

Address

Bahir Dar

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Beteህግ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share

Category