Quarit woreda female league office

Quarit woreda female league office Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Quarit woreda female league office, Legal, West gojjam Quarit woreda, Bahir Dar.

08/10/2024
 #የብልጽግና ፓርቲ የፖለቲካ ፕሮግራምየፓርቲያችን የፖለቲካ ፕሮግራም ዋነኛ ዓላማ ጠንካራና ቅቡልነት ያለው፣ የብሔር ማንነትን እና የሀገራዊ አንድነትን ሚዛን የጠበቀ ሀገረ-መንግስት መገንባት...
26/07/2023

#የብልጽግና ፓርቲ የፖለቲካ ፕሮግራም

የፓርቲያችን የፖለቲካ ፕሮግራም ዋነኛ ዓላማ ጠንካራና ቅቡልነት ያለው፣ የብሔር ማንነትን እና የሀገራዊ አንድነትን ሚዛን የጠበቀ ሀገረ-መንግስት መገንባት ነው፡፡ ከጠንካራ ሀገረ-መንግስት ግንባታ አንፃር ፓርቲያችን ህዝብ ከቀጥተኛ የህልውና አደጋ ተጠብቆ የልማት፣ የእኩልነት እና የነፃነት ፍላጎቶቹ እንዲሟላለት የሚያስችል ነፃ፣ ገለልተኛና ብቃትን መሰረት ያደረገ ሀገራዊ ተቋማዊ አደረጃጀት መገንባት ያስፈልጋል ብሎ ያምናል፡፡

በመሆኑም የሀገረ-መንግስት ግንባታ ጅምራችን ጠንካራና የማይናወጥ ተቋማዊ መሰረት ያለው እንዲሆን የብልጽግና ፓርቲ ግቡ አድርጎ ይንቀሳቀሳል፡፡ የብልጽግና ፓርቲ ዴሞክራሲን በተቋማዊና ህዝባዊ ባህል ላይ መገንባት አስፈላጊ እንደሆነ ይገነዘባል፡፡

በሌላ በኩል ከሀገረ-መንግስት ቅቡልነት አንፃር የብልጽግና ፓርቲ የኢትዮጵያ ሀገረ-መንግስት ጥንካሬን ለማሳደግ በህገ-መንግስት የተቀመጠውን አንድ የፖለቲካና የኢኮኖሚ ማህበረሰብ የመፍጠር ግብ ለማሳካት ይሰራል፡፡ በመሆኑም የሀገረ-መንግስቱን ቅቡልነት በሚጨምሩና ሀገራዊ መግባባትን በሚያመጡ፣ የህዝቦችን ግንኙነት በሚያሳልጡ እና የእውነተኛ እርቅ መንፈስን በሚያጎለብቱ ፖለቲካዊ እርምጃዎች ላይ ትኩረት አድርጎ ይንቀሳቀሳል፡፡ ፓርቲያችን የሀገረ-መንግስት ግንባታችን ህብረ-ብሔራዊ ማንነትን የተላበሰና ብዝሃነትን የሚያንፀባርቅ መሆን እንዳለበት በጽኑ ያምናል፡፡

የብልጽግና ፓርቲ የፖለቲካ ፕሮግራም ግቦች!!
1. ጠንካራና ቅቡል ሀገረ-መንግስት በጽኑ መሰረት ላይ ለመገንባት የሚያስችል ሀገራዊ መግባባት መፍጠር
2. በተቋማዊና ህዝባዊ ባህል ላይ የቆመ የዴሞክራሲ ስርዓት መገንባት
3. ዘላቂና አዎንታዊ ሰላምን ማረጋገጥ ናቸው፡፡

“ማንኛውም ስኬት የሚገኘው ፈተናን ተጋፍጦ በማለፍ ብቻ ነው”  ይልቃል ከፋለ (ዶ.ር) የባሕርዳር ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችን እያስመረቀ ነው፡፡ በምረቃ ሥነ  ሥርዓቱ ላይ የአማራ ክልል ርእሰ መሥ...
22/07/2023

“ማንኛውም ስኬት የሚገኘው ፈተናን ተጋፍጦ በማለፍ ብቻ ነው” ይልቃል ከፋለ (ዶ.ር)

የባሕርዳር ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችን እያስመረቀ ነው፡፡ በምረቃ ሥነ ሥርዓቱ ላይ የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር ይልቃል ከፋለ (ዶ.ር)፣ የባሕርዳር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ፍሬው ተገኘ (ዶ.ር) እና ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡

የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳደር ይልቃል ከፋለ (ዶ.ር) ተመራቂ ተማሪዎች እና ለተመራቂ ተማሪ ወላጆች የእንኳን ደስ አላችሁ መልእክት አስተላልፈዋል፡፡ ርእሰ መሥተዳድሩ በመልእክታቸው ባሕርዳር ዮኒቨርሲቱ ላፉት 60 ዓመታት ለሀገር ብቻ ሳይኾን ለዓለም እውቀትን ለማስፋት የሚተጉ፣ ልማትን ለማሳደግ የሚሠሩ፣ የሰውን ሕይወት ለማሻሻል የተጉ ብቃት ያላቸው ሰዎችን በማፍራት አስተዋጽዖ አበርክቷል ብለዋል፡፡

ዩኒቨርሲቲው በማስተማር፣ በምርምር እና በማኅበረሰብ አገልግሎት ተልዕኮን ለመወጣት እየሠራ የሚገኝ አንጋፋና ተመራጭ ተቋም ኾኗል ነው ያሉት፡፡ የዩኒቨርሲቲው ተልእኮ የሚሳከው በትጋት በሚተጉ መምህራን፣ ተማሪዎች ትጋትና ተቋርቋሪነት ነውም ብለዋል፡፡ ዮኒቨርሲቲው ለሀገር እያደረገው ያለው አስተዋጽዖ የሚደነቅና የሚበረታታ መኾኑንም ገልጸዋል፡፡

ዩኒቨርሲቲው እውቀትን እያሰፋ፣ ምርምርን እያሳደገ፣ ቴክኖሎጂውን እያስተዋወቀ መኾኑንም ገልጸዋል፡፡ ዩኒቨርሲቲው እስካሁን ተመራጭ ኾኖ የቆየበትን እንደ ስንቅ በመውሰድ በቀጣይም ጠንክሮና አስፍቶ መሥራት አለበት ነው ያሉት፡፡ ዩኒቨርሲቲው ተመራጭ እንዲኾን የሠሩ ሁሉ ወደፊትም በትጋት እንዲሠሩም አሳስበዋል፡፡

እውቀት ለመሸመት፣ ክህሎት ለማሳደግ የራስን ጥረት ይጠይቃል ነው ያሉት፡፡ ተማሪዎች በራሳቸው የሚተማመኑ፣ እውቀት ያላቸው፣ በሰለጠኑበት ሙያ ሁሉ ሲሰለፉ የሚፈለገውን አስተዋጽዖ ለማድረግ የራስ ተነሳሽነታቸውን ማሳደግ ይጠበቅባቸዋል ብለዋል፡፡

በራስ የመተማመን ስሜትን ለመፍጠር የራስን አቅም ማሻሻል እንደሚገባም አንስተዋል፡፡ ተማሪዎች ለመመረቅ የበቁት ከፍተኛ ውጣ ወረዶችም በማለፍ እንደኾነ ያነሱት ርእሰ መሥተዳድሩ የኮሮና ቫይረስን እና በሰሜን ኢትዮጵያ የነበረውን ጦርነት ተቋቁመው ለመመረቅ መብቃታቸውን ነው የገለጸት፡፡ ፈተናዎችን ተቋቁመው የተመረቁ ተማሪዎች ፈተናን በትዕግሥት፣ በጽናት እና በጥበብ የማለፍን ልምደ እንዳገኙም አንስተዋል፡፡

ተማሪዎች የመጀመሪያውን የሕይወት ምዕራፍ አጠናቀው ቀጣዩ የሕይወታቸው ምዕራፍ መጀመሪያ ላይ መኾናቸውንም ተናግረዋል፡፡ ተማሪዎች ከትምህርት ሕይወታቸው የበለጠ ፈተና ሊገጥማቸው እንደሚችልም አስገንዝበዋል፡፡ ዩኒቨርሲቲው የቀጣይ ሕይወታቸው ያመረ እንዲኾን ጥበብና ስልት ያስተምራችኋል እንጂ በቀጣይነት ያለው ሕይወታቸው በራሳቸው ብርታት ላይ የተመሠረተ ነው ብለዋቸዋል፡፡

ሕይዎት ዘርፈ ብዙ ነው ያሉት ርእሰ መሥተዳድሩ ሕይወታችሁን የምትመሩበት የተለያየ አጋጣሚ ይኖራል፣ ራሳችሁን፣ ቤተሰባችሁን እና ሀገራችሁን የሚጠቅም ስራ እንደምትሠሩም እናምናለን ነው ያሏቸው፡፡ ሀገር የሚገነባው ትውልዱ በሚያበረክተው የተቀናጀና የተናበበ አስተዋጽዖ ድምር ውጤት ነውም ብለዋል፡፡

ሀገር የሚገነባው በትውልድ ነው፣ ተመራቂ ተማሪዎችም ሀገራቸውን በማገልገል ስኬታማ እንደሚኾኑም ያላቸውን እምነት ገልጸዋል፡፡ በቀጣይ ሕይወታችሁ የሚያጋጥማችሁን ፈተና በስሜት ሳይኾን በስክነት፣ በጉልበት ሳይኾን በጥበብ እና እውቀት እንደምትሻገሩ እናምናለንም ብለዋል፡፡ በስክነት እና በብስለት ከሄዱ ሀገር የገጠማትን ውስብስብ ችግር በመግታት እና በመፍታት ወደ ተሻለ ሰላምና ልማት እንደሚያሻግሯትም ገልጸዋል፡፡

የነገ

ነገን ዛሬ እንትከል በሚል መሪ ቃል የአረንጓዴ አሻራ የአንድ ቀን ጀንበር ችግኝ ተከላ ፕሮግራም ተጀመረ።በዛሬው እለት በምዕራብ ጎጃም ዞን በቋሪት ወረዳ የአንድ ቀን ጀንበር ችግኝ ተከላ  በ...
17/07/2023

ነገን ዛሬ እንትከል በሚል መሪ ቃል የአረንጓዴ አሻራ የአንድ ቀን ጀንበር ችግኝ ተከላ ፕሮግራም ተጀመረ።
በዛሬው እለት በምዕራብ ጎጃም ዞን በቋሪት ወረዳ የአንድ ቀን ጀንበር ችግኝ ተከላ በሁሉም ቀበሌዎች እየተካሄደ ይገኛል።

ብልጽግና ፓርቲ አዳጊና ተራማጅ ለሆነ አዳዲስ አስተሳሰብ የተዘጋጀ ተለማጭ የፖለቲካ ፍልስፍና የሚከተል ፓርቲ ነው፡፡✓ ተራማጅ የዴሞክራሲ ስርዓት በሚፈልግ መሰረታዊ የፖለቲካ ኢኮኖሚ አመክንዮ...
13/07/2023

ብልጽግና ፓርቲ አዳጊና ተራማጅ ለሆነ አዳዲስ አስተሳሰብ የተዘጋጀ ተለማጭ የፖለቲካ ፍልስፍና የሚከተል ፓርቲ ነው፡፡

✓ ተራማጅ የዴሞክራሲ ስርዓት በሚፈልግ መሰረታዊ የፖለቲካ ኢኮኖሚ አመክንዮ መፈታት ያለባቸው ውስጣዊ ችግሮች እልፍ በሆነበት አገርና ማህበራዊ መስተጋብር ውስጥ የብልፅግና ተራማጅ እሴቶች በእርግጥም ወቅታዊና አስፈላጊ ናቸው፡፡

✓ ብልጽግና ገና ከመነሻው የአገሩን ሰርዶ በአገሩ በሬ እንደሚባለው ለአገር በቀል ችግሮች አገር በቀል መፍትሄ ያስፈልጋቸዋል ብሎ የተነሳ ፓርቲ ነው፡፡ በዚህም ምክንያት ለአገር በቀል አስተሳሰብና የመፍትሄ አማራጮች ተገቢውን ትርጉም መስጠት ችሏል፡፡

✓ ሁሉም ፖለቲካዊ ችግሮቻችን ከውጪ በሚቀዱ የፖለቲካ አስተሳሰቦች አይፈቱም የተባለ ይመስል የግድ ከአገር በቀል የመፍትሄ አማራጮች ውጭ ሙሉ ለሙሉ ከውጭ በተቀዱ ርዕዮተ አለማዊ ፍልስፍናዎች መጠመድ የለብንም ብሎ የሚያስብ ፓርቲ ነው፡፡

✓ ስለሆነም የውስጥ ችግራችንን ለመቅረፍ የምንዋሰው ሌላ ባዕድ አስተሳሰብ ሳያስፈልገን እንደነገሩ ድንበር ተሻጋሪ መልካም ተሞክሮዎችን እየቀላቀልን ከችግሮች መላቀቅ እንችላለን፡፡ በዚህም አገር በቀል ብልሀት ችግሮቻችንን መፍታት ጀምረናል፡፡

የብልፅግና ፓርቲ መለያ እሴቶች ፦👉 ህብረ ብሔራዊ አንድነት፦አንድ የፖለቲካና ኢኮኖሚ ማህበረሰብ መገንባት ነው፡፡ ህብረ ብሔራዊ ስንል የብሔር፣ የሐይማኖት ወይም ሌላ ማንነቶችን ያቀፈና ማንን...
13/07/2023

የብልፅግና ፓርቲ መለያ እሴቶች ፦
👉 ህብረ ብሔራዊ አንድነት፦
አንድ የፖለቲካና ኢኮኖሚ ማህበረሰብ መገንባት ነው፡፡ ህብረ ብሔራዊ ስንል የብሔር፣ የሐይማኖት ወይም ሌላ ማንነቶችን ያቀፈና ማንንም ያላገለለ ማህበረሰብ ማለታችን ነው፡፡

👉 የዜጎች ክብር፦
ኢትዮጵያዊያንን በእኩል ዓይን የሚያይና የሚዳኝ፣ ፍትሃዊ ተጠቃሚነታቸውን የሚያረጋግጥ፣ የብሔር ብሔረሰቦች መብትና ነጻነት የሚረጋገጥበት፣ እውነተኛ ህብረ ብሔራዊነት የሚረጋገጥበት፣ በዋና ዋና የሀገሪቱ ጉዳዮች ላይ ሁሉም ዜጋ ውሳኔ ላይ ተሳታፊ የሚሆንበት፣ የሀብት ስልጣንና የመብት ክፍፍሉ ፍትሃዊ የሚሆንበት የፖለቲካዊ ኢኮኖሚ ስርዓት መፍጠር፣ አንድ የፖለቲካና ኢኮኖሚ ማህበረሰብ መገንባት፡፡

👉 ነጻነት፦
ዜጎች የራሳቸውን ህይወት ርዕይ የመምረጥ፣ በመረጡት መንገድ የመኖር መብት እንዲረጋገጥ ማድረግ፡፡ የዜጎችን ሁለንተናዊ ተሳትፎ በማሳደግ የሀገራችንን ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች በዘላቂነት መፍታት፡፡ የዜጎችን የመሰብሰብ፣ የመደራጀት፣ የመጻፍና ሀሳብን በነጻነት የመግለጽ፣ የመምረጥና የመመረጥ መብቶችን ማረጋገጥ፡፡

LidLideta woreda 7 prosperity party-ብልጽግናrLideta woreda 7 prosperity party-ብልጽግናpLideta woreda 7 prosperity party-ብልጽግናoLideta woreda 7 prosperity party-ብልጽግናrLideta woreda 7 prosperity party-ብልጽግና

የመደመር ትውልድ ባህሪዎች ፦👉  አንድነትን የሚወድና ለአንድነት የሚሰራ👉 ብልጽግናን የሚሻ፣ ለመለወጥና ለማደግ የሚጓጓ👉 በሃሳብ ልዕልና የሚያምን👉 መስጠትንና በነጻ ማገልገልን እንደ ክብር ...
13/07/2023

የመደመር ትውልድ ባህሪዎች ፦
👉 አንድነትን የሚወድና ለአንድነት የሚሰራ
👉 ብልጽግናን የሚሻ፣ ለመለወጥና ለማደግ የሚጓጓ
👉 በሃሳብ ልዕልና የሚያምን
👉 መስጠትንና በነጻ ማገልገልን እንደ ክብር የሚያይ
👉 ድህነትንና ቆሻሻን የሚጸየፍ ትውልድ ነው።

መልካም ዜና!🙏 #በቡሬ ከተማ አስተዳደርና አካባቢው ለምትገኙ ትምህርት ለተጠማችሁ ትምህርት ፈላጊዎች በሙሉ እንሆ መልካም ዜና!!!በሃገር አቀፍ ደረጃ በአዲስ ተጠንቶ የቀጣዩን የኢትዮጵያ ሁኔ...
07/07/2023

መልካም ዜና!🙏

#በቡሬ ከተማ አስተዳደርና አካባቢው ለምትገኙ ትምህርት ለተጠማችሁ ትምህርት ፈላጊዎች በሙሉ እንሆ መልካም ዜና!!!

በሃገር አቀፍ ደረጃ በአዲስ ተጠንቶ የቀጣዩን የኢትዮጵያ ሁኔታ ባገናዘበ መልኩ ሚዲያው ከፍተኛ ቦታን የሚሰጠው በመሆኑ የሃገሪቱ የልህቀት ማዕከል በጥናትና ምርምር መርምሮ በማስተርስ ሁለተኛ ዲግሪ በCommunication and Media Studies (MA) የትምህርት ክፍል በደብረ ማርቆስ ዩኒቨርስቲ እና ሌሎች በተመረጡ የሃገሪቱ የዩኒቨርስቲዎች እንዲሰጥ ተወስኖ ወደ ተግባር መገባቱ ይታወቃል።

በመሆኑም በደብረ ማርቆስ ዩኒቨርስቲ በቡሬ ካምፓስ መማር እንፈልጋለን እና ጠይቅልን ብላች በውስጥ እና በውጭ መስመር እንዲሁም በአካል ለጠየቃችሁኝ መምህራንና ሌሎች ግለሰቦች ሁሉ በኮሙኒኬሽን እና የሚዲያ ጥናት የትምህርት ክፍል መማር የምትችሉ መሆኑን ዩኒቨርስቲው ማስታወቂያ ስላወጣ በማስታወቂያው መሰረት ከነገ (01/11/2015 ዓ/ም) ጀምራችሁ በኤከስቴንሽን መርሃ ግብሩ መሰረት መማር የምትችሉ መሆኑን አበስራለሁ።

ሚዲያ ለአንዲት ሃገር ህልውና ወሳኝ በመሆኑ ሁሉም አካል ለሚዲያ እና ኮሙኒኬሽን ዘርፍ ትኩረት ሊሰጠው ይገባል።

መረጃውን በቅንነት ሼር ሼር በማድረግ ለሌሎቹ አጋሩልን!

መልካም ጊዜ!

እንደ ሀገር እያገጠሙን ያሉ  ውስጣዊና ውጫዊ  ውስብስብ ችግሮችን በፍጥነት ለመፍታት የሚያስችል ብቁ  አመራር ለመፍጠር እየተሰራ ነው፡-አቶ አባይ አለሙ -  የምዕራብ  ጎጃም ዞን ብልጽግና ...
27/06/2023

እንደ ሀገር እያገጠሙን ያሉ ውስጣዊና ውጫዊ ውስብስብ ችግሮችን በፍጥነት ለመፍታት የሚያስችል ብቁ አመራር ለመፍጠር እየተሰራ ነው፡-አቶ አባይ አለሙ - የምዕራብ ጎጃም ዞን ብልጽግና ፓርቲ የፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ፡፡

በምዕራብ ጎጃም ዞን ‹‹መፍጠርና መፍጠን፣የወል እውነቶችን የማፅናት ቀጣይ የትግል ምዕራፍ›› በሚል መሪ ሀሳብ በፍኖተ ሰላም ከተማ ለ3 ተከታታይ ቀናት ሲሰጥ የቆየው የከፍተኛና መካከለኛ አመራሮች ስልጠና ተጠናቋል፡፡የምዕራብ ጎጃም ዞን ብልጽግና ፓርቲ የፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ አቶ አባይ አለሙ እንደገለጹት እየገጠሙን ያሉ አሁናዊ ውስብስብ የፖለቲካና የልማት ፈተናዎችን በብቃት ለመሻገር ብቃት ያለው አመራር መፍጠር አስፈላጊ ነው ብለዋል፡፡ ስልጠናው አመራሩ ራሱን በፍጥነት እየተለዋወጠ ካለው አለም አቀፋዊና ከባቢያዊ ነባራዊ ሁኔታዎችን ፈጥኖ በማዋሀድ ህዝቡን እያማረሩ ያሉ የአገልግሎት አሰጣጥና የመልካም አስተዳደር መጓደሎች ለመፍታት የሚያሥችል የአመራር ጥበብን ተከትሎ እንዲመራ ተደማሪ አቅም የሚፈጥር መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ወቅቱ እየገጠሙን ያሉ ውስጣዊና ውጫዊ ችግሮችን ለመሻገር የሚያስችሉ የአመራር ጥበቦችን በመተግበር የሕዝቡን ሰላምና ደህንነት ለማረጋገጥ የሚሰራበት ነው ያሉት የፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊው አመራሩ ያገኘውን ስልጠና በተግባር በማሳየት የሕዝቡን አሁናዊና ያደሩ ተደማሪ ችግሮችን በፍጥነት መፍታት ይጠበቅበታል ብለዋል፡፡ ስልጠናው የአመራር አንድነትን በመፍጠር የተጀመሩ የልማት ስራዎችን ወደ ላቀ ደረጃ በማሻገር በኑሮ ውድነትና በሰላም እጦት እየተፈተነ ያለው ህዝብ እፎይታ እንዲያገኝ የሚሰራበት ወሳኝ ጊዜ ስለመሆኑም ነው አቶ አባይ የገለፁት፡፡

ከስልጠና ተሳታፊዎቹ መካከል የሰከላ ወረዳ ባህልና ቱሪዝም ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ አገሬ አናጋውና የባህር ዳር ዙሪያ ወረዳ ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ዳዊት ጌታነህ በበኩላቸው ስልጠናው መሰረታዊ የህዝብ ጥያቄ የሆኑትን የኑሮ ውድነትና የሰላምና ደህንነት ይረጋገጥልን ጥያቄዎችን በፍጥነት ለመፍታት የሚያስችል ዝግኙነትን እንዲያዳብሩ እገዛ እንዳደረገላቸውም ተሳታፊዎቹ ተናግረዋል፡፡ እያጋጠሙ ያሉ አሁናዊ ችግሮችን ከህዝብ ጋር እየተመካከሩ መፍታትወቅቱ የሚጠይቀው ተግባር መሆኑንም ነው አስተያየት ሰጭዎቹ የተናገሩት፡፡ ስልጠናው በአመራር ዘመናቸው የነበሩባቸውን ክፍተቶች እንደሞላላቸውም ገልፀዋል፡፡ አስተያየት ሰጭዎቹ ወደ ህዝቡ ሲወርዱ ከስልጠናው ያገኛቸውን አሻጋሪ ሀሳቦች በመያዝ እያገለገሉ ያሉትን ህዝብ በቅንነት በማገልገል ለሚያጋጥሙ ችግሮች በፍጥነት ምላሽ በመስጠት ኃላፊነታቸውን ለመወጣት መዘጋጀታውን ገልፀዋል፡፡

27/06/2023

እንደ ሀገር እያገጠሙን ያሉ ውስጣዊና ውጫዊ ውስብስብ ችግሮችን በፍጥነት ለመፍታት የሚያስችል ብቁ አመራር ለመፍጠር እየተሰራ ነው፡-አቶ አባይ አለሙ - የምዕራብ ጎጃም ዞን ብልጽግና ፓርቲ የፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ፡፡

በምዕራብ ጎጃም ዞን ‹‹መፍጠርና መፍጠን፣የወል እውነቶችን የማፅናት ቀጣይ የትግል ምዕራፍ›› በሚል መሪ ሀሳብ በፍኖተ ሰላም ከተማ ለ3 ተከታታይ ቀናት ሲሰጥ የቆየው የከፍተኛና መካከለኛ አመራሮች ስልጠና ተጠናቋል፡፡የምዕራብ ጎጃም ዞን ብልጽግና ፓርቲ የፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ አቶ አባይ አለሙ እንደገለጹት እየገጠሙን ያሉ አሁናዊ ውስብስብ የፖለቲካና የልማት ፈተናዎችን በብቃት ለመሻገር ብቃት ያለው አመራር መፍጠር አስፈላጊ ነው ብለዋል፡፡ ስልጠናው አመራሩ ራሱን በፍጥነት እየተለዋወጠ ካለው አለም አቀፋዊና ከባቢያዊ ነባራዊ ሁኔታዎችን ፈጥኖ በማዋሀድ ህዝቡን እያማረሩ ያሉ የአገልግሎት አሰጣጥና የመልካም አስተዳደር መጓደሎች ለመፍታት የሚያሥችል የአመራር ጥበብን ተከትሎ እንዲመራ ተደማሪ አቅም የሚፈጥር መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ወቅቱ እየገጠሙን ያሉ ውስጣዊና ውጫዊ ችግሮችን ለመሻገር የሚያስችሉ የአመራር ጥበቦችን በመተግበር የሕዝቡን ሰላምና ደህንነት ለማረጋገጥ የሚሰራበት ነው ያሉት የፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊው አመራሩ ያገኘውን ስልጠና በተግባር በማሳየት የሕዝቡን አሁናዊና ያደሩ ተደማሪ ችግሮችን በፍጥነት መፍታት ይጠበቅበታል ብለዋል፡፡ ስልጠናው የአመራር አንድነትን በመፍጠር የተጀመሩ የልማት ስራዎችን ወደ ላቀ ደረጃ በማሻገር በኑሮ ውድነትና በሰላም እጦት እየተፈተነ ያለው ህዝብ እፎይታ እንዲያገኝ የሚሰራበት ወሳኝ ጊዜ ስለመሆኑም ነው አቶ አባይ የገለፁት፡፡

ከስልጠና ተሳታፊዎቹ መካከል የሰከላ ወረዳ ባህልና ቱሪዝም ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ አገሬ አናጋውና የባህር ዳር ዙሪያ ወረዳ ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ዳዊት ጌታነህ በበኩላቸው ስልጠናው መሰረታዊ የህዝብ ጥያቄ የሆኑትን የኑሮ ውድነትና የሰላምና ደህንነት ይረጋገጥልን ጥያቄዎችን በፍጥነት ለመፍታት የሚያስችል ዝግኙነትን እንዲያዳብሩ እገዛ እንዳደረገላቸውም ተሳታፊዎቹ ተናግረዋል፡፡ እያጋጠሙ ያሉ አሁናዊ ችግሮችን ከህዝብ ጋር እየተመካከሩ መፍታትወቅቱ የሚጠይቀው ተግባር መሆኑንም ነው አስተያየት ሰጭዎቹ የተናገሩት፡፡ ስልጠናው በአመራር ዘመናቸው የነበሩባቸውን ክፍተቶች እንደሞላላቸውም ገልፀዋል፡፡ አስተያየት ሰጭዎቹ ወደ ህዝቡ ሲወርዱ ከስልጠናው ያገኛቸውን አሻጋሪ ሀሳቦች በመያዝ እያገለገሉ ያሉትን ህዝብ በቅንነት በማገልገል ለሚያጋጥሙ ችግሮች በፍጥነት ምላሽ በመስጠት ኃላፊነታቸውን ለመወጣት መዘጋጀታውን ገልፀዋል፡፡

ማሕበራዊ ሚዲያን ለበጎ ዓላማ እንጠቀምበት! ከቴክኖሎጂ እድገትና መዘመን ጋር ተያይዞ ዘርፍን የሚጠቀሙ ዜጎች ቁጥር ከጊዜ ወደጊዜ ጨምሯል። የኢንተርኔት አገልግሎት ተደራሽነትን ተከትሎ ማሕበራ...
27/06/2023

ማሕበራዊ ሚዲያን ለበጎ ዓላማ እንጠቀምበት!

ከቴክኖሎጂ እድገትና መዘመን ጋር ተያይዞ ዘርፍን የሚጠቀሙ ዜጎች ቁጥር ከጊዜ ወደጊዜ ጨምሯል። የኢንተርኔት አገልግሎት ተደራሽነትን ተከትሎ ማሕበራዊ ሚዲያው ተጽዕኖ ፈጣሪና ቀዳሚ የሕዝብ የመገናኛ አማራጭ ሆኗል። ይህም በመሆኑ ተፈላጊ መረጃዎችን በፍጥነት በማድረስ በሕዝብ ሕልውና ውስጥ የሚያበረክተው አስተዋጽኦ ከፍ ያለ ነው።

የሰዎችን ግንኙት ቀላልና ቀልጣፋ አድርጓል። ጊዜ፣ ጉልበትና ሃብታቸውን ሳያባክኑ በየአሉበት ሁነው በፍጥነት እንዲገናኙ አድርጓል። ይህ እድገት አንዱ የስልጣኔ መገለጫ ነው። ለኢኮኖሚያችን እድገትም ትልቅ አቅም ነው። ይህንን መልካም እድል ለሰላም፣ ለልማትና ለሀገር ግንባታ መጠቀም ያስፈልጋል።

ይሁን እንጅ ማሕበራዊ ሚዲያው ለሁለንተናዊ እድገት ሚናው የጎላ ቢሆንም በአግባቡና በሰለጠነ መንገድ መጠቀም ካልተቻለ ደግሞ እጅግ የከፋ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ቀውስ ያስከትላል፡፡

በሰለጠነ መንገድ መጠቀም ካልቻልነ ሰላማችን ያናጋል፤ ጥላቻን ያስፋፋል፡፡ የሕዝብን አብሮነት ይሸረሽራል፡፡ መጠራጠርና ልዩነትን በማስፋት ሕዝብን ከሕዝብ በማጋጨት ለሰዎች ሕይወት እልፈት፣ ለሀብትና ንብረት ውድመት ምክንያት ይሆናል፡፡

በተለይም አሁን አሁን ኃላፊነት በጎደለው መንገድ በመጠቀም የተዛቡ፣ በጥላቻና በልዩነት የተሞሉ፣ መሰረት ቢስ ወሬዎችን በማሰራጨት በሕዝብ መካከል ልዩነት በመፍጠር የግጭትና ሁከት መቀስቀሻ መሳሪያ በሆነበት ወቅት ላይ እንገኛለን፡፡

ከልዩነት እና ጥላቻ ደግሞ ጥፋት እንጅ የሚገኝ ትርፍ የለም። ሊኖርም አይችልም። ማህበራዊ ሚዲያውን ለበጎ ዓላማ በማዋል የህዝባችን አብሮነት፣ ወንድማማችነት፣ ተቻችሎና ተከባብሮ የመኖር የቆየ ባህልንና እሴት ይበልጣል ማጠናከሪያና ማቀራረቢያ መሳሪያ ማድረግ ይኖርብናል።

በክልላችንም ዘርፉን ለበጎ ዓላማ በመጠቀም በጋራ የተንቀሳቀሱ ወጣቶችና የበጎ ሃሳብ ባለቤቶች መልካም ስራዎችን ለአካባቢያቸው ሕዝብ አበርክተዋል። በተለያዩ አካባቢዎች ትምህርት ቤትና ጤና ተቋም ሰርተዋል፤ የህዝብ አገልግሎት መስጫ ተቋማት ገንብተዋል፣ ሰብአዊ ድጋፍ ለሚሹ ዜጎች ድጋፍ አሰባስበው ዜጎችን ከጉስቁልና አውጥተዋል፣ የፈረሱ ተቋማትን ጠግነዋል።

ባሕል፣ ታሪክና እሴቶቻቸውን አስተዋውቀዋል፤ ትልልቅ የፋይናንስ ተቋማትን መስርተዋል። በዚህ መልኩ ሚዲያውን ለበጎ ተግባር በመጠቀም አርአያ ለሆናችሁ ሁሉ ምስጋናችን ላቅ ያለ ነው።

በቀጣይም ይሔንን በጎ ዓላማችሁን አጠናክራችሁ እንድትቀጥሉ እያልኩ፥ የክልላችን ምሁራን፣ ወጣቶች፣ የዘርፍ ተጠቃሚዎችና የሚዲያ ተቋማት ለሀገር ሰላምና እድገት ጉልህ አስተዋጽኦ ያለውን ዘመናዊ ሚዲያ ለበጎ ዓላማ በማዋል የበኩላችሁን ድርሻ እንድትወጡ በራሴና በክልሉ መንግሥት ስም አደራ ለማለት እወዳለሁ።

Address

West Gojjam Quarit Woreda
Bahir Dar

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Quarit woreda female league office posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share

Category