Bekalu Molla Agegnehu Consultant & Attorney at Law

Bekalu Molla Agegnehu Consultant & Attorney at Law Well come to the official page of Bekalu Molla.

08/01/2024

ወደ ስራ ስሄድ አንድ የስልክ እንጨት ላይ የተለጠፈ ወረቀት አየሁኝ: ጽሁፉ እንዲህ ይላል

"እዚህ መንገድ ላይ 50 ብር ጠፍቶብኛል: ያገኘ ሰው ካለ እባካችህን አድራሻዬ በሚቀጥለው መንገድ በቀኝ በኩል ስትታጠፉ ያለው አሮጌ ቤት ነው:: አይኔ እንደፈለግኩኝ አያይም: እድሜዬም ገፍቷል: ልጆችም የሉኝም"
ይህንኑ ጽሁፍ ተከትዬ ወደ አሮጌው ቤት ስሄድ አንዲት ሴትዮ ደጃፍ ላይ ተቀምጠዋል: የእግር ኮቴየን ሰምተው "ማነው? ማን ልበል?" አሉኝ

"እዚህ መንገድ ላይ 50 ብር አግኝቼ ነው: እሱን ልሰጥ ነው የመጣሁት" ብዬ መለስኩላቸው

አሮጊቷ እንባ ቀደማቸው - "ልጄ! እስካሁን ድረስ ከ40 በላይ ሰዎች 50 ብር መንገድ ላይ ወድቆ አገኘን ብለውኝ መጥተዋል"

ቀጠሉ እማማ - "እኔ ይህንን ጽሁፍ አልጻፍኩኝም: ጽሁፍ ለመጻፍም ሆነ ለማንበብም አይኔ እሺ አይለኝም"
50 ብሩን በእጃቸው አስጨበጥኳቸው

ጽሁፉን ከስልክ እንጨቱ ላይ እንድቀደው ቢነግሩኝም አላደረግኩም: የመጣውን ሰው ሁሉ ይህንኑ ነበር የሚሉት

ይህንን ጽሁፍ የጻፈውን ሰው እንዴት እንዳደነቅኩት : እኚህን ሴትዮ ለመርዳት የሄደበት ርቀት በጣም ነው ያደነቅኩት!

ከሴትዮዋ ቤት ስወጣ አንዲት ወጣት ልጅ አስቆመቺኝ
"ወንድሜ! እዚህ መንገድ ላይ 50 ብር አግኝቼ ነበር: የቤቱ አቅጣጫ በየት በኩል እንደሆነ ታውቃለህ እንዴ?"
በልቤ እየሳቅኩኝ ቤቱን ጠቆምኳት😍
❤️🙌🏼
Zemelak Endrias

26/07/2023

ምክረ ሕግ- የሕንፃ አዋጅ፣ ደንብና መመሪያ መሰረታዊ መብትና ግዴታዎች

ለመላው የክርስትና እምእነት ተከታዬቻችንና ደንበኞቻችን እንኳን ለፋሲካ በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ በዓሉ የደስታ እና የፍቅር እንዲሆንላችሁ ከልብ እንመኛለን! በቃሉ ሞላ የህግ አማካሪና ጠበቃ...
16/04/2023

ለመላው የክርስትና እምእነት ተከታዬቻችንና ደንበኞቻችን እንኳን ለፋሲካ በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ በዓሉ የደስታ እና የፍቅር እንዲሆንላችሁ ከልብ እንመኛለን! በቃሉ ሞላ የህግ አማካሪና ጠበቃ።

Its hard to negotiate and come up with the best resolution when you don't know what you are negotiating for.
11/11/2022

Its hard to negotiate and come up with the best resolution when you don't know what you are negotiating for.

አድዋ የጥቁር ህዝቦች የነጻነት አርማ
01/03/2022

አድዋ የጥቁር ህዝቦች የነጻነት አርማ

06/06/2019

በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፑብሊክ
የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ምክር ቤት
ዝክረ-ሕግ
ZIKRE-HIG
OF THE COUNCIL OF THE AMHARA NATIONAL REGIONAL STATE IN THE FEDERAL DEMOCRATIC REPUBLIC OF ETHIOPIA

ማውጫ
ደንብ ቁጥር 150/2009 ዓ/ም
በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የመምህራን የመኖሪያ ቤት መስሪያ ቦታ አሰጣጥና የተገነቡ ቤቶች ድልድል ማስፈፀሚያ ክልል መስተዳድር ምክር ቤት ደንብ CONTENTS
Regulation No. 150/2017
The Amhara National Regional State Teachers’ Dwelling Houses’ Construction Land Provision and the Distribution of Constructed Houses Ex*****on, Council of Regional Government Regulation
ደንብ ቁጥር 150/2009 ዓ/ም
በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የመምህራን የመኖሪያ ቤት መስሪያ ቦታ አሰጣጥና የተገነቡ ቤቶች ድልድልን ለማስፈፀም የወጣ ክልል መስተዳድር ምክር ቤት ደንብ Regulation No. 150/2017
A COUNCIL OF REGIONAL GOVERNMENT REGULATION ISSUED TO PROVIDE FOR THE EX*****ON OF THE TEACHERS’ DWELLING HOUSES’ CONSTRUCTION LAND DELIVERY AND THE DISTRIBUTION OF CONSTRUCTED HOUSES IN THE AMHARA NATIONAL REGIONAL STATE
የመምህርነት ሙያ ዜጎችን በተገቢው እውቀት፣ ክህሎት፣ ቀና አመለካከትና በጎ እሴት የመቅረጽ ሀላፊነት ያለበት ከመሆኑም በላይ ለሀገራችን ሁለንተናዊ እድገት ቁልፍ ሚና የሚጫወትና የህዳሴውን ጉዞ ለማሳካት የበኩሉን ጉልህ አስተዋጽኦ የሚያበረክት እንደሆነ በመታመኑ Whereas, it is believed that the teaching profession would, far from entailing a responsibility to shape citizens with the appropriate knowledge, skills, fair attitude and good values, play a pivotal role for the multi-faceted development of our country and henceforth contribute its significant share to the successful accomplishment of the renaissance voyage;
የየደረጃውን መምህራን የመኖሪያና የመስሪያ አካባቢ የተመቻቸ በማድረግ ለአገር እድገት የሚጠበቅባቸውን ሙያዊ ግዴታ በተነቃቃ መንፈስ መወጣት ይቻላቸው ዘንድ በሁሉም የክልሉ አካባቢዎች የተረጋጋ ስምሪት የሚኖርበትንና በዚህም አማካኝነት ጥራት ያለው ትምህርት የሚሰጥበትን እድል መፍጠር አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፤ Whereas, it has been found necessary to create an opportunity in which the stabilized deployment of teachers shall exist and hence quality education shall be provided in all the localities of the region by facilitating their residential and working environment at all levels so that they would be able to discharge their professional duties in an activated spirit for the country’s development;
በሙያው የሰለጠኑና ብቃት ያላቸው የክልሉ መምህራን ከጊዜ ወደጊዜ ሙያቸውን እየተዉ ወደ ሌሎች የስራ መስኮች የሚያደርጉትን ፍልሰት ለመቀነስ ይቻል ዘንድ የመጠለያ ችግር በግል ሂወታቸው ላይ የሚፈጥረውን አሉታዊ ተጽእኖ በማስቀረትና ማህበራዊም ሆኑ ኢኮኖሚያዊ ችግሮቻቸውን ከወዲሁ በማቃለል ቤተሰቦቻቸውና መላው ህብረተሰብ ለሙያው አዎንታዊ አመለካከት ኖሯቸው የየበኩላቸውን ድጋፍና እንክብካቤ እንዲያደርጉላቸው የሚያበረታታ ራሱን የቻለ የህግ ማእቀፍ አውጥቶ ገቢራዊ ማድረግ በማስፈለጉ፤ Whereas, in order that it might be possible to minimize the turn-over of those professionally trained and competent teachers in the region fleeing from their respective fields of profession in favor of other sectoral occupations from time to time, it is essential to enact and implement an autonomous legal framework that would somehow encourage their families and the society as a whole to provide them with their own support and care having thus developed a positive attitude for the profession in question, by getting rid of the problem which the lack of shelter happens to create in respect of their private lives and thereby alleviating their social and economic difficulties therewith;
የአማራ ክልል መስተዳድር ምክር ቤት በተሻሻለው የብሔራዊ ክልሉ ህገ-መንግስት አንቀጽ 58 ንዑስ አንቀፅ (7)ና በክልሉ አስፈጻሚ አካላት እንደገና ማቋቋሚያ፣ ማደራጃና ስልጣንና ተግባራት መወሰኛ አዋጅ ቁጥር 230/2008 ዓ.ም አንቀጽ 37 ድንጋጌዎች ስር በተሰጠው ስልጣን መሰረት ይህንን ደንብ አውጥቷል፡፡ NOW, THEREFORE, the Council of the Amhara Regional Government, in accordance with the powers vested in it under the provisions of Art. 58 Sub-Art. (7) of the Revised National Regional Constitution and Art. 37 of the Revised Regional Executive Organs’ Re-establishment, Organization and Definition of their Powers and Duties Proclamation No. 230/2015, hereby issues this regulation.
ክፍል አንድ PART ONE
ጠቅላላ ድንጋጌዎች GENERAL PROVISIONS
1. አጭር ርዕስ 1. Short title
ይህ ደንብ “የመምህራን መኖሪያ ቤት መስሪያ ቦታ አሰጣጥና የተገነቡ ቤቶች ድልድል ማስፈጸሚያ ክልል መስተዳድር ምክር ቤት ደንብ ቁጥር 150/2009 ዓ.ም” ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል፡፡ This Regulation may be cited as “The Teachers’ Dwelling Houses’ Construction Land Delivery and the Distribution of Constructed Houses Ex*****on, Council of Regional Government Regulation No. 150/2017”.
2. ትርጓሜ 2. Definitions
1. የቃሉ አገባብ ሌላ ትርጉም የሚያሰጠው ካልሆነ በስተቀር በዚህ ደንብ ውስጥ፡- 1. Unless the context requires otherwise, in this regulation:-
ሀ. “መምህር” ማለት በክልሉ ውስጥ በሚገኝና ንብረትነቱ የመንግስት በሆነ ከቅድመ-መደበኛ እስከመሰናዶ 2ኛ ደረጃ ባለ ትምህርት ቤት፣ የመምህራን ትምህርት፣ የቴክኒክና ሙያ ትምህርት፣ የግብርና፣ የጤና ሳይንስ ኮሌጅ ወይም የአካል ተሃድሶ ማሰልጠኛ ወይም የአገልግሎት መስጫ ማእከል አስተማሪ ወይም አሰልጣኝ በመሆን በቋሚነት ተቀጥሮ በሙያው የሚያገለግል ማንኛውም ሰው ሲሆን፤ ርእሳነ-መምህራንን፣ ምክትል ርዕሳነ-መምህራንን፣ ሱፐርቫይዘሮችን፣ የየኮሌጆቹን ወይም የየማእከላቱን ዲኖች፣ ዳይሬክተሮችና ምክትሎቻቸውን ይጨምራል፡፡ A. “Teacher” shall mean any person who has been permanently recruited and serves in his profession as a teacher or trainer from pre-school through preparatory secondary level school, teachers’ education, technical and vocational education, agriculture or health science college or physical rehabilitation training or service delivery center found in the regional state and belongs to the government and may include principals, deputy principals, supervisors of such schools, deans, directors and their deputies of each and every college or center thereof.
ለ. “ትምህርት ቤት” ማለት በክልሉ ውስጥ ተቋቁሞ በመንግስት ይዞታ ስር የሚተዳደር ከቅድመ-መደበኛ እስከ መሰናዶ 2ኛ ደረጃ ያለ ማናቸውም ትምህርት ቤት ሲሆን የመምህራን ትምህርት፣ የቴክኒክ ሙያ ትምህርትና ስልጠና፣ እንዲሁም የግብርና፣ የጤና ሳይንስ ኮሌጆችንና የአካል ተሃድሶ ማሰልጠኛ ወይም የአገልግሎት መስጫ ማእከላትን ይጨምራል፡፡ B. “School” shall mean any school set up in the Regional State and managed under the government ownership from preschool through preparatory secondary-level and include teachers’ education, technical-vocational education and training, agriculture and health science colleges as well as physical rehabilitation training or service delivery centers.
ሐ. “የመምህራን መኖሪያ መንደር” ማለት ህጋዊ ባለቤትነቱ የክልሉ መንግስትና ህዝብ የሆነና የመምህራንን የመጠለያ ችግር ለመፍታት ታስቦ በመንግስት ወይም በመንግስትና በህብረተ-ሰቡ የጋራ ተሳትፎ የሚገነቡ ሆነው መምህራን በማስተማር ስራቸው ላይ እስካሉ ድረስ የሚጠቀሙባቸው የጋራ መኖሪያ ቤቶች ያረፉበት ስፍራ ነው፡፡ C. “Teachers’ Residential Village” shall mean a place whose lawful ownership is to the Regional Government and people and wherein condominiums to be constructed either by the government or through the joint participation of the government and the community with the intention of resolving teachers’ shelter problem and used by teachers as long as they stay in their teaching career, are situated.

መ. “መኖሪያ ቦታ” ማለት በራሳቸው ምርጫ ገንብተው የሚጠቀሙበትን ቤት ለመስራት የሚያስችላቸውና በክልሉ መንግስት አማካኝነት በምደባ፣ በነፃ ወይም ካሳ ተከፍሎበትና በይፋ ተፈቅዶ ለመምህራን የተሰጠ ቦታነው፡፡ D. “Dwelling land” shall mean that plot of land which has been granted to teachers by the Regional Government, upon its official approval, through allotment, free of charge or payment of compensation thereon and enables teachers to construct a house they would use, having built it with their own preference.
ሠ. “ልዩ ድጋፍ የሚያስፈልገው መምህር“ ማለት በፌደራሉ መንግስት የአካል ጉዳተኞች የስራ ስምሪት አዋጅ ቁጥር 568/2000 ዓ.ም አንቀጽ 2 ንኡስ አንቀፅ (1) ድንጋጌ ስር የሚሸፈንና በሜዲካል ቦርድ የተረጋገጠለት አካል ጉዳተኛ ሆኖ የጉዳቱ ደረጃ በእኩል የስራ እድል ተጠቃሚነት መብቱ ላይ ተጽእኖ የሚያስከትልበት መሆኑ በአስፈጻሚ ኮሚቴው የታመነበት ማንኛውም መምህር ነው፡፡ E. “Teacher Needing Special Support” shall mean any teacher who is physically disabled and covered under the provision of Art. 2, Sub-Art. (1) of the Federal Government Physically Disabled Persons’ Right to Employment Proclamation No.568/2008 and whose status has been established by a medical board and henceforth believed by the executive committee that the extent of his disability would cause an impact on his right to benefit from equal opportunity for employment. .
ረ. (ንዑስ ማዘጋጃ-ቤት) ወይም (ታዳጊ ከተማ) ማለት እንደቅደም ተከተላቸው በአንድ መሪ ማዘጋጃ-ቤት ስር የተዋቀረ ከባቢያዊ የከተማ ማህበረ-ሰብ ወይም ማዘጋጃ-ቤት ያልተቋቋመበት ሆኖ ወደ ከተማነት በመሸጋገር ላይ ያለ ማናቸውም የማህበረ-ሰብ ስብስብ ነው፡፡ F. (Sub-municipality) or (Emerging town) shall mean a local urban community structured under a certain lead municipality or any communal group that is found in a condition of emergence into a status of a town, wherein no municipality has not been established, in order of their priorities.
ሰ. “መሪ ማዘጋጃ-ቤት” ማለት በአንድ ወረዳ ውስጥ የሚገኙትን ንዑሳን ማዘጋጃ-ቤቶችና ታዳጊ ከተሞች በማእከልነት ይዞ ስራቸውን እንዲያስተባብርና በበላይነት እንዲመራ ሀላፊነት የተሰጠው ማዘጋጃ-ቤት ነው፡፡ G. “Lead Municipality” shall mean a municipality which embraces those sub-municipalities and emerging towns found in a Woreda and is thus vested with the responsibility of coordinating and directing over their respective duties thereof.
ሸ. “አነስተኛ የከተማ አስተዳደር” ማለት በቀበሌዎች የተከፋፈለ ሆኖ ከወረዳ ተለይቶ የራሱ ውስጣዊ አስተዳደር ያለው ማናቸውም ከተማ ነው፡፡ H. “Smaller City Administration” shall mean any city which has been categorized into Kebeles and acquired its own internal administration, having broken away from the Woreda thereof.
ቀ. “መካከለኛ የከተማ አስተዳደር” ማለት በአነስተኛና በሜትሮፖሊታን የከተማ አስተዳደሮች መካከል ያለ ማናቸውም የከተማ አስተዳደር ሲሆን የዞን አስተዳደር ማዕከላትን ይጨምራል፡፡ I. “Medium City Administration” shall mean any city administration which is found between small and metropolitan city administrations and include the centers of zonal administrations.
በ. “ሜትሮፖሊታን የከተማ አስተዳደር” የሚለው ሀረግ የባህርዳር፣ የጎንደርና የደሴ ከተሞችን ይገልፃል፡፡ J. The term “Metropolitan City Administration” shall refer to those cities of Bahir Dar, Gondar and Dessie.
ተ. “ቢሮ” እና “የቢሮ ኃላፊ” ማለት እንዳግባብነቱ የክልሉ ትምህርት፣ ጤና፣ ከተማ ልማት፣ ቤቶችና ኮንስትራክሽን፣ የገጠር መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም፣ ግብርና ወይም ሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮና የዚሁ ቢሮ ኃላፊ ነው፡፡ K. “Bureau and Bureau Head” shall be the Regional Education, Health, Urban Development, Housing and Construction or Rural Land Administration and Use, Agriculture, and Labor and Social Affairs Bureau and the head of such Bureau, as appropriate. .
ቸ. “ሰው” ማለት የተፈጥሮ ሰው ወይም በህግ የሰውነት መብት የተሰጠው አካል ነው፡፡ L. “Person” shall mean any natural or juridical person.
2. በዚህ ደንብ ውስጥ በወንድ ፆታ የተገለፀው ማናቸውም ጉዳይ የሴትንም ፆታ ይጨምራል፡፡ 2. All provisions of this regulation set out in the masculine gender shall also apply to the feminine gender.
3. የተፈጻሚነት ወሰን 3. Scope of Application
ይህ ደንብ ከዚህ በላይ በአንቀጽ (2) ንኡስ አንቀፅ (1) ፊደል ተራ ቁጥሮች ሀ.ና ለ. ስር የተጠቀሱትን የክልሉን መምህራን፣ ትምህርት ቤቶችና ኮሌጆች በሚመለከት ተፈጻሚ ይሆናል፡፡ 1. This regulation shall apply with regard to the region’s teachers, schools and colleges specified under Art. 2 Sub-Art. (1) letter numbers A. and B. herein above.
4. አላማዎች 4. Objectives
ደንቡ የሚከተሉት አላማዎች ይኖሩታል፡- The Regulation shall have the following objectives:
1. መምህራን የተመቻቸ የመኖሪያ አካባቢ ተፈጥሮላቸው ሙያዊ ብቃታቸውንም ሆነ ስነ-ምግባራቸውን እያሳደጉ በስራቸው ላይ በመቆየት የተማሪዎችን ውጤታማነት በቀጣይነት በማሻሻል በክልሉ ውስጥ ጥራት ያለው ትምህርት እንዲረጋገጥ ማድረግ፤ 1. Following the creation of favorable living environment for teachers as well as improvement of their professional competence and ethical conduct and retain them in their career, cause the realization of quality education throughout the region by continuously enhancing the performance results of students;
2. መምህራን በተሰማሩበት የስራ መስክ ተረጋግተው በመቆየት የማስተማር ፍላጎታቸውም ሆነ ተነሳሽነታቸው እንዲጨምርና ለመማር-ማስተማሩ ሂደት የበኩላቸውን ገንቢ አስተዋፅኦ እንዲያበረክቱ ማበረታታት፤ 2. By having them maintained in the career they have engaged themselves in, to encourage teachers so that their interest and initiation would be boosted and thereby contribute their own constructive share for the learning-teaching process per’se;
3. ለመምህርነት ሙያ ተገቢውን ክብር በመስጠት ይኸው በተማሪዎችና በህብረተ-ሰቡ ዘንድ ያለውን ተቀባይነት በማሳደግ የተሻለ እውቀት ያላቸው ዜጎች ወደሙያው እንዲሳቡ ማድረግ፤ 3. To cause those citizens having better knowledge to be attracted into the field by giving appropriate respect to the teaching profession and increasing the acceptance of such by students and the community;
4. የትምህርት ጊዜን በአግባቡ ተጠቅሞ የመምህራንና ተማሪዎችን ስነ-ምግባር በማሻሻል በትምህርት ውጤታማነት ላይ አዎንታዊ ለውጥ እንዲመጣ ማድረግ፤ 4. To cause the bringing about of positive change with regard to the success in education by having properly used the academic duration and improving the ethical conduct of both teachers and students alike;
5. የልዩ ድጋፍ ተጠቃሚ የሆኑ አካል ጉዳተኛ መምህራን በህገ-መንግስቱ አንቀጽ 41 ንኡስ አንቀፅ (5) ስር የሰፈረውን አላማ በሚያሳካ መንገድ መደገፍ፡፡ 5. To back up those teachers with physical disabilities benefiting from special support in a way as to achieve the objective laid down under Art. 41 Sub-Art. (5) of the Constitution.

ባህር ዳር
የካቲት 17 ቀን 2009 ዓ.ም
ገዱ አንዳርጋቸው
የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት
ርእሰ-መስተዳድር Done at Bahir
Dar This 24th day of February, 2017
Gedu Andargachew
Head of Government of the Amhara National Regional State

05/06/2019

የመንግስት ግንባታ ጨረታ ወይም የግዥ ሂደት መነሻ ስለሚቀርቡ ቅሬታዎች እና በግዥ ሂደቱ ላይ ስለሚሰጡ የእግድ ትዛዞች
By Bekalu Molla,
LLB, LLM in Land and Environmental Law at
Bahir Dar University, School of Law

አንድ ግዥ ፈጻሚ መስርያ ቤት የህንጻ ግንባታ ጨረታ ማስታወቂያ በማውጣቱ ምክንያት የተለያዩ የኮንስትራክሽን ድርጅቶች የጨረታውን ሰነድ በመግዛት በጨረታ ማስታወቂያው እና በጨረታ ሰነዱ ውስጥ በተቀመጡት የመወዳደርያ ሃሳቦች ወይም መስፈርቶች መሰረት Technical እና Financial Proposal አዘጋጅተው የሚያቀርቡ ሲሆን ግዥ ፈጻሚው መስርያ ቤትም በተጫራቾች የቀረቡትን ዶክመንቶች በጨረታ ኮሚቴው ከመረመረ በኋላ በመጀመርያ ደረጃ ተጫራቾች የሚፈለግባቸውን Technical መመዘኛዎች አሟልተው የቀረቡ ስለመሆኑ እና አለመሆኑ ተረጋግጦ Technical መመዘኛውን አሟልተው በመገኘታቸው ወደ ቀጣዩ ዙር ያለፉት ተጫራቾች ዝርዝር በማስታወቂያ ይገለጥላቸዋል፡፡
በመቀጠልም ቴክኒካል(Technical) መመዘኛውን ያለፉ ተጫራቾች ብቻ በሞሉት የግንባታ ዋጋ ወይም (Financial Proposal) መሰረት በጨረታ ኮሚቴው ማጣራት ተደርጎበት ዝቅተኛ የግንባታ ዋጋ ያቀረበው ወይም least bidder በመሆን ያሸነፈው ድርጅት ከተለየ በኋላ ለአሸናፊው ድርጅት ውል እንዲይዝ ጥሪ ይደረግለታል፡፡
ይሁን እንጅ በአብክመ የግዥ መመርያ ቁጥር 1/2003 መሰረት ማንኛውም ተጫራች በጨራታው ሂደት አና በጨረታው ውጤት ላይ ቅሬታ ካለው የግንባታ ውል ከመያዙ በፊት በመጀመርያ ደረጃ ለግዥ ፈጻሚው መስርያ ቤት ቅሬታቸውን ማቅረብ የሚችሉ ሲሆን ግዥ ፈጻሚው መስርያ ቤት በሰጣቸው ምላሽ ያልረኩ ከሆነ ወይም በመመርያው በተቀመጠው የጊዜ ገደብ ውስጥ ምላሽ ማግኘት ካልቻሉ ደግሞ በየደረጃው ላሉ የገንዘብ እና ኢኮነሚ ትብብር ቢሮዎች ቅሬታቸውን በማቅረብ ሊስተናገዱ የሚችሉ ሲሆን ቅሬታው የቀረበለት የገንዘብ እና ኢኮነሚ ትብብር ቢሮ ወይም መምርያ ወይም ጽ/ቤት የውል ሂደቱን ቅሬታው ተጣርቶ ምላሽ አስከሚሰጥበት ጊዜ ድረስ በማገድ የቀረበለትን ቅሬታ የክልሉ መንግስት ንብረትን እና ግዥን ለማስተዳደር ያወጣውን አዋጅ ቁጥር 179/2003፣ መመርያ ቁጥር 1/2003 እንዲሁም የጨረታ ሰነዱን እና የጨረታ ማስታወቂያውን መሰረት በማድረግ ቅሬታው በቀረበለት በ10 ቀናት ጊዜ ውስጥ ምላሽ ይሰጣል፡፡ በዚሁ አግባብ የገንዘብ እና ኢኮነሚ ትብብር ቢሮ የሚሰጠው ምላሽ የመጨረሻ አስተዳደራዊ ውሳኔ ቢሆነም በዚሁ የገንዘብ እና ኢኮነሚ ትብብር ቢሮ በሰጠው ምላሽ ላይ ቅር የተሰኘ ተጫራች ጉዳዩን ወደ መደበኛ ፍርድ ቤት በማቅረብ መብቱን ማረጋገጥ እንደሚችል መመርያ ቁጥር 1/2003 አንቀጽ 45 በግልጽ ይደነግጋል፡፡
የግንባታ የጨረታ ሂደትን አስመልክቶ በየደረጃው ላሉ የመንግስት ግዥ ፈጻሚ አካላት ቅሬታ በሚቀርብበት ጊዜ ሁለት ተነጻጻሪ መብቶችን በእኩልነት ማየት እና በተገቢው ጊዜ ማስተናገድ በየገረጃው ላሉ የመንግስት ግዥ የሚመለከታቸው አካላት በህግ የተጣለ ግዴታ ነው፡፡ እነዚህ ተነጻጻሪ መብት ያላቸው አካላት በጨረታው አሸናፊ ሁኖ ውል እንዲይዝ ጥሪ የተደረገለት ድርጅት ወይም ግለሰብ እና የዚህን ድርጅት የጨረታ አሸናፊነት በመቃወም ለገንዘብ እና ኢኮነሚ ትብብር ቢሮ ቅሬታ በማቅረብ የውል ሂደቱ እንዲታገድ የጠየቀው ድርጅት ወይም ግለሰብ ናቸው፡፡ ስለሆነም ቅሬታው የቀረበለት የገንዘብ እና ኢኮነሚ ትብብር ቢሮ የቀረበለትን ቅሬታ በህግ በተሰጠው የ 10 ቀን የጊዜ ገደብ ውስጥ መርምሮ እና አጣርቶ ምላሽ መስጠት ያለበት ስለመሆኑ በግዥ መመርያው ቁጥር 1/2003 አንቀጽ 40(5) በአስገዳጅነት ተደንግጓል፡፡
ከዚህም ባሻገር ቢሮው የመንግስት ግዥን በሚመለከት ህግን ከማውጣት ጀምሮ የማስፈጸም እና የመፈጸም እንዲሁም ለሚቀርቡ ቅሬታዎች ህጋዊ ምላሽ የመስጠት ህጋዊ ሃላፊነት የተሰጠው በመሆኑ በህግ መሰረት የተሰጠውን ስልጣን መጠቀም ያለበት በህግ በተሰጠው የጊዜ ገደብ ውስጥ ብቻ ነው፡፡ በዚህ ረገድ ቢሮው በህጉ በተቀመጠው ጊዜ ለቀረበው ቅሬታ ምላሽ ሳይሰጥ ቢቀር ወይም በህግ ከተሰጠው የ10 ቀን የጊዜ ገደብ በኋላ በቅሬታው ላይ ምላሽ ቢሰጥ የተሰጠው ውሳኔ እንዳልተሰጠ የሚቆጠር ወይም ተግባራዊ ሊሆን የማይችል ውሳኔ እንደሆነ ከጠቅላላው የይርጋ ህግ መርህ መገንዘብ ይቻላል፡፡ የአብክመ የግዥ መመርያ ግዥ ፈጻሚው መስርያ ቤት በግዥ ሂደቱ ላይ የሚቀርብለትን ቅሬታ መርምሮ በ3 ቀናት ምላሽ እንዲሰጥ እንዲሁም በየደረጃው የሚገኙ የገንዘብና ኢኮነሚ ቢሮዎች ደግሞ ቅሬታው በቀረበላቸው በ10 ቀን ጊዜ ውስጥ ቅሬታውን ተመልክተው ውሳኔ እንዲሰጡ በጊዜ የተገደቡበት ምክንያት የመንግስት ግዥ ወጭ ቆጣቢ እንዲሆን እና በተያዘለት የግዥ እቅድ መሰረት እንዲከናወን ለማስቻል እና በዚሁ ቅሬታ በቀረበበት የግዥ ሂደት ላይ ላሉ ሁለት ተነጻጻሪ የመብት ጥያቄዎች ምክንያታዊ ነው ተብሎ በተቀመጠው ጊዜ ውስጥ ፍትህ ለመስጠት ሲባል መሆኑን መገንዘብ ይቻላል፡፡
ነገር ግን የህጉን ተግባራዊነት ስንመለከት ግዥ ፈጻሚ የመንግስት መስርያቤቶችም ሆኑ የገንዘብ እና ኢኮነሚ ቢሮ የክልሉን የግዥ ሂደት በሚመለከት ቅሬታ ሲቀርብለት ቅሬታውን መርምሮ የግዥ ፈጻሚውን መስርያቤት የጨረታ ኮሚቴ ውሳኔ በማጽናት ወይም በማሻሻል ወይም በመሻር ውሳኔ የሚሰጥ ቢሆነም ይህንን ውሳኔ ግን በመመርያው በተቀመጠው የጊዜ ገደብ ውስጥ ሲሰጡ አይታይም ወይም ይህ ያልሆነበትን አሳማኝ እና ህጋዊ ምክንያትም በውሳኔው ላይ ሲገልፁ አይታይም፡፡
ለምሳሌ የገንዘብ እና ኢኮነሚ ትብብር ቢሮ በአንድ የመንግስት ግዥ ሂደት ላይ የተነሳን ቅሬታ መርምሮ ለመወሰን በህግ የተፈቀደለት ጊዜ 10 ቀን ብቻ ሁኖ ሳላ ያለበቂ ህጋዊ ምክንያት ውሳኔውን ከ10 ቀን በኋላ ቢሰጥ እና ይህ ውሳኔ ደግሞ የግዥ ፈጻሚው መስርያቤት በግዥ ሂደቱ ላይ የሰጠውን ውሳኔ የሚሽር ቢሆን ይህ ውሳኔ በህጉ በተቀመጠው የጊዜ ገደብ ያልተሰጠ ውሳኔ በመሆኑ ተፈጻሚነት ሊኖረው አይችልም፡፡ ስለሆነም ግዥ ፈጻሚው መስርያ ቤት አስቀድሞ የግዥ ሂደቱን የፈጸምሁት ህግን ተከትየ ነው ብሎ ካሰበ እና በቅሬታ አቅራቢው የቀረበለትን ቅሬታ ሳይቀበለው የቀረ እንደሆነ በዚሁ ውሳኔው ላይ ቅሬታ አቅራቢው ተጫራች ለአብክመ ገንዘብ እና ኢኮነሚ ትብብር ቢሮ ሊያቀርብ ይችላል፡፡ ይሁን እንጅ የአብክመ ገንዘብ እና ኢኮነሚ ትብብር ቢሮ ለቀረበው ቅሬታ በህጉ በተቀመጠው 10 ቀን ጊዜ ውስጥ ምላሽ አለመስጠቱን በራሱ ካረጋገጠ ቢሮው የሰጠው የእግድ ትዛዝም ሆነ በቅሬታው ላይ አጣርቶ የመወሰን መብቱ በይርጋ ቀሪ የሚሆን በመሆኑ ማንኛውም ከ10 ቀን በኋላ የሚሰጥ ውሳኔ ሁሉ እናዳልተሰጠ የሚቆጠር እና ግዥ ፈጻሚውን መስርያ ቤት የሚያስገድድ ባለመሆኑ ወይም ቅሬታው ምላሽ እንዳላገኘ በመቁጠር ከአሸናፊው ድርጅት ጋር ውል በመያዝ የግዥ ሂደቱን መፈጸም ይኖርበታል፡፡ ይሁን እና ግዥ ፈጻሚው መስርያ ቤት የግዥ ሂደቱ ህግን ተከትሎ የተፈጸመ ስለመሆኑ ሙሉ እምነት እያለው እንዲሁም ቅሬታ አቅራቢው ለገንዘብ እና ኢኮነሚ ትብብር ቢሮ ያቀረበው ቅሬታ በህጉ በተቀመጠው የጊዜ ገደብ ምላሽ ያላገኘ መሆኑን እየተረዳ ከአሸናፊው ድርጅት ጋር ውል አልይዝም ወይም ውል ለመያዝ አልገደድም ለማለት የሚያስችለው ህጋዊ ምክንያት የለም፡፡ ውል ሳይዝ ቢቀር ጨረታው የተሰረዘው ህጋዊ ባልሆነ ምክንያት መሆኑን በፍርድ ቤት ክስ በመመስረት እና በማስረጃ በማረጋገጥ ጨረታው ሊሰረዝ የማይገባው ስለመሆኑ ወይም አሸናፊው ድርጅት ውል ይዞ ቢሰራ ኑሮ ሊያገኝ የሚችለውን የተጣራ ትርፍ(net profit) እና በጨረታው መሰረዝ ምክንያት የደረሰበትን የወጭ ዝርዝር በማቅረብ ካሳ (liquidated damage) በግዥ ፈጻሚው መስርያቤት ላይ ለማስወሰን ይችላል፡፡
ይህም በመንግስት እና ህዝብ ገንዘብ ላይ የሚያደርሰው ጉዳት ከፍ ያለ ከመሆኑ ባሻገር በግዥ ሂደቱ ላይ ተሳታፊ የሆኑ የንግድ ድርጅቶችም ከጨረታ ጀምሮ አስከ መረጣ እና እነዚህ ቅሬታዎች አስከሚስተናገዱበት ጊዜ ድረስ የሚደርስባቸው መጉላላት እና ወጭና ከፍተኛ ከመሆኑ ባሻገር የመልካም አስተዳደር ችግር በመሆኑ የሚመለከተው የግዥ ፈጻሚ አካል ሁሉ ሊያስብበት የሚገባ ጉዳይ መሆኑ የጸሃፊው ምክረ ሃሳብ ነው፡፡
28/9/2011

04/06/2019

አሁን ባለው የኢትዮጵያ የንብረት መብት ህግ የመሬት ይዞታ መብት እና የቤት ባለቤትነት መብት መካከል ያለው መሰረታዊ አንድነት እና ልዩነት
By
Bekalu Molla, LLB, LLM in land and Environmental Law at
Bahir Dar University, School of Law
የንብርት መብት በጠቅላላው፡
ማንኛውም የኢትዮጵያ ዜጋ የግል ንብረት የማፍራት መብት እንዳለው፣ ይህ መብትም ንብረትን የመያዝ፣ በንብረቱ የመጠቀም፣ ንብረቱን በስጦታ፣ በውርስ ወይም በሽያጭ ወይም በሌላ ማኛውም መንገድ የማስተላለፍ መብቶችን የሚያጎናጽፍ ሰፊ መብት ሲሆን በህግም ጥበቃ የሚደረግለት መብት ነው፡፡
ይሁን እንጅ ይህ በህግ ጥበቃ የሚደረግለት ንብረት የማፍራት መብት የአብዛኛውን ህዝብ መብት ወይም ጥቅም ለማስጠበቅ ሲባል በህግ ሊገደብ አንደሚችል ከህገመንግስቱ አንቀጽ 40 በግልጽ መረዳት ይቻላል፡፡ የግል ንብረት ባለቤትነት መብት የሚመነጨው ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ዜጋ ወይም ህጋው ሰውነት ያላቸው ድርጅቶች በጉልበታቸው፣ በመፍጠር ችሎታቸው ወይም በካፒታላቸው ያፈሩት ሲሆን የንብረት መብት ይኖራቸዋል፡፡ ንበረት ግዙፍነት ያለው ሁኖ የሚንቀሳቀስና፣ የማይንቀሳቀስ ተብሎ ሊከፈል ይችላል(የፍ/ህ/ቁ 1127)፡፡
የመሬት ይዞታ መብት እና የቤት ባለቤትነት የንብረት መብቶች ግዙፍነት ያላቸው የንብረት መብቶች ሲሆኑ ከማይነቀሳቀሱ የንብረት መብቶች ውስጥ የሚመደቡ ናቸው (የፍ/ህ/ቁ 1030)፡፡ ይህም ሁለቱን መብቶች አንድ የሚያደርጋቸው የመጀመርያው ጉዳይ ነው፡፡
የገጠርም ሆነ የከተማ መሬት ባለቤት መንግስት እና ህዘብ ብቻ እንደሆነ እና መሬትን መሸጥ በህግ የተከለከለ ስለመሆኑ በህገመንግስቱ ተደነግጓል፡፡ ዜጎች በመሬት ላይ ያላቸው መብት የመሬት ይዞታ መብት ሲሆን ከሽያጭ በስተቀር በመሬቱ ላይ የመጠቀም፣ የይዞታ መብታቸውን በስጦታ፣ በውርስና በኪራይ ለማስተላለፍ ይችላሉ፡፡ ይህ የመሬት ይዞታ መብትም እንደማንኛውም ግዙፍነት ያለው የንብረት መብት በህግ ጥበቃ የሚደረግለት ሰፊ መብት ነው፡፡
በሌላ በኩል የግል የቤት ባለቤትነት መብት ደግሞ ለሁሉም ዜጎች እና ህጋዊ ሰውነት ላላቸው ድርጅቶች በእኩልነት የተሰጠ መብት ሲሆን የቤት በለንብረት የሆነ ግለሰቦች ወይም ህጋዊ ሰውነት ያላቸው ድርጅቶች በቤቱ ላይ የመጠቀም፣ በስጦታ ወይም በውርስ የማስተላለፍ፣ የመሸጥ እና በሌላ ማንኛውም መንገድ ንብረቱን ለሌላ ወገን የማስተላለፍ መብት የሚሰጥ ነው፡፡
የመሬት ይዞታ መብት እና የቤት ባለቤትነት መብቶች መካከል ምን አይነት ግንኙነት ሊኖር ይችላል? ቤት የሚገነባው በመሬት ላይ ነው፡፡ መሬት ደግሞ የመንግስት እና የህዝብ ነው፡፡ መንግስት እና ህዝብ ባለቤት በሆኑበት መሬት ላይ የተገነባ ቤት እንዴት ዜጎችን የግል የንብረት መብት ሊያጎናጽፋቸው ይችላል የሚሉት ነጥቦች በዚህ ጽሁፍ ውስጥ የሚዳሰሱ ነጥቦች በመሆናቸው እንደሚከተለው ለማብራራት እሞክራለሁ፡፡
በመሬት ይዞታ መብት እና በቤት ባለቤትነት መብቶች መካከል ምን አይነት ግንኙነት ሊኖር ይችላል?
የኢትዮጵያ አርሶ አደሮች እና ዘላኖች መሬትን ለግጦሽም ሆነ ለእርሻ በነጻ የማግኘት እና ከርስታቸው ያለመነቀል ወይም ያለመፈናቀል መብት እናዳለቸው እንዲሁም የግል ባለሃብቶች በህግ በሚወሰን ክፍያ ከመንግስት መሬት ማግኘት እንደሚችሉ በህገመንግስቱ ተደንግጓል (አንቀጽ 40(4፣5፣6))፡፡ የኢትዮጵያ አርሶ አደሮች እና ዘላኖች መሬትን በነጻ ከመንግስት የሚያገኙ ስሆን ሌላው ዘጋ ወይም ህዝብ ግን የመሬት ይዞታ መብቱን የሚያገኘው በክፍያ ነው፡፡ ይህ የህገመንግስቱ ክፍል ከአርሶአደሮች እና ዘላኖች በስተቀር ያሉትን ዜጎች በሃገሪቱ ማንኛውም የኢኮነሚ እንቅስቃሴ ውስጥ የመሳተፍን እና በሃገሪቱ ሃብት እኩል የመጠቀም እና በእኩልነት የመልማት ህገመንግስታዊ መባታቸውን የሚገድብ መሆኑን ማስተዋል ይቻላል፡፡
ሆኖም ግን የመሬት ይዞታ መብት በነጻ ወይም በህግ በሚወሰን ክፍያ ከመንግስት የሚገኝ ሲሆን የቤት ባለቤትነት መብት ግን በግዥ፣ በስጦታ፣ በውርስ፣ ወይም በሌላ መንኛውም መንገድ የሚገኘ ሊሆን ይችላል፡፡ እዚህ ላይ ሊተኮርበት የሚገባው ጉዳይ ቤቱ የተገነባው መንግስት እና ህዝብ ባለቤት በሆኑበት መሬት ላይ መሆኑ እና የተገነባውን ቤት ከመሬቱ ተነጥሎ ሊታይ የሚችል ንብረት አለመሆኑ ነው፡፡ ግንባታው ከመሬቱ ተነጥሎ ሊታይ የሚችል ካልሆነ ደግሞ የመሬት ይዞታ መብትን በህግ በተወሰነ ክፍያ ከመንግስት ተረክቦ ቤት የገነባ የቤት ባለቤት ባለቤት ያልሆነበትን መሬት ወይም በመሬቱ ጨምሮ በሽያጭ ማስተላለፍ እንደሚችል ለመገንዘብ የሚከብድ ጉዳይ አይደለም፡፡ ስለሆነም የመሬት ይዞታ መብትን እና የቤት ባለቤትነትን አንድ የሚያደርጋቸው ሁለተኛው ምክንያት የመሬት ይዞታ መብት ቤት ከተገነባበት በኋላ በሽያጭ ለሌላ ወገን ሊተላለፍ መቻሉ ነው፡፡ እዚህ ላይ መሬትን በሽያጭ ማስተላለፍ እና የመሬት ይዞታ መብትን በሽያጭ ማስተላለፍ ግን ተመሳሳይ ትርጉም ሊሰጣቸው እንደማይችል ልብ ሊሉ ይገባል፡፡
መንግስት እና ህዝብ ባለቤት በሆኑበት መሬት ላይ የተገነባ ቤት እንዴት ዜጎችን የግል የንብረት መብት ሊያጎናጽፋቸው ይችላል
ከፍ ሲል እንደገለጽሁት መሬት የማይሸጥ የማይለወጥ የመንግስት እና የኢትዮጵያ ህዝቦች ንብረት ነው፡፡ ይህም ማለት መንግስት ከሽያጭ በስተቀር መሬትን በሌላ ማንኛውም መንገድ ማስተላለፍ የሚችል ስለመሆኑ መገንዘብ ይቻላል፡፡ ስለሆነም ዜጎች መሬትን ከመንግስት በነጻ ወይም በክፍያ የሚያገኙት ቢሆነም በዚሁ መሬት ላይ ያላቸው መብት ግን የመሬት ይዞታ መብት ብቻ ነው፡፡ ይህም ማለት ማንኛውም የመሬት ይዞታ መብት ያለው (Possessor) ሁሉ መሬቱን ከመሸጥ በስተቀር መሬቱን የመያዝ፣ በመሬቱ የመጠቀም፣ መሬቱን በስጦታ፣ በውርስ ወይም በኪራይ የማስተላለፍ መብቶች ሁሉ የሚያጠቃልል ነው፡፡
አንድ የመሬት ይዞታ መብት ያለው ባለይዞታ (Possessor) በመሬቱ ላይ ቤት ቢገነባ ወይም አትክልት ተክሎ መሬቱን ቢያለማው ይህ ባለይዞታ ለገነባው ቤት ወይም ለተከለው አትክልት ባለሃብት (owner) ይሆናል፡፡ ስለሆነም መንግስት እና ህዝብ ባለቤት በሆኑበት መሬት ላይ የተገነባ ቤት እንዴት ዜጎችን የግል የንብረት መብት ሊያጎናጽፋቸው ይችላል የሚለው ጥያቄም ሊመለስ የሚገባው ከዚሁ አንጻር ሊሆን ይገባል፡፡ የቤት የግል ንብረት ባለቤትነት ባለቤቱ ቤቱን በሽያጭ ማስተላለፍን ጨምሮ ሌሎች የንብረት መብቶችን የሚሰጥ ሰፊ መብት ነው፡፡ እዚህ ላይ ልንመለከተው የሚገባው ጉዳይ አንድ የቤት ባለቤት የሆነ ሰው ሁለት መብቶችን አጣምሮ የያዘ ስለመሆኑ ነው፡፡ የመጀመርያው ቤቱን የገነባበት የመሬት ይዞታ መብቱ ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ በመሬቱ ላይ የተገነባው ቤት ባለቤትነት መብቶች ናቸው፡፡ እነዚህን ሁለት የንብረት መብቶች ለየብቻ ተነጣጥለው ሊታዩ የሚችሉ ባይሆንም የመሬቱ ባለቤት መንግስት እና ህዝብ ሲሆን የቤቱ ባለቤት ደግሞ ቤቱን የገነባው የመሬት ባለይዞታ ግለሰብ ወይም ድርጅት ነው፡፡ ስለሆነም አንድ የቤት ባለቤት በይዞታ መሬቱ ላይ ቤት ሰርቶ ሲሸጥ ቤቱ እና ቤቱ የተሰራበት ይዞታ ተነጣጥለው ሊታዩ የሚችሉ ባለመሆናቸው (intrinsic element) በመሆናቸው የይዞታ መብቱንም ጭምር በሽያጭ እንዳስተላለፈ ይቆጣራል፡፡
አሁን ባለው የኢትዮጵያ የንብረት መብት ህግ የመሬት ይዞታ መብት የሚገኝባቸው መንገዶች መሬት የማይሸጥ እና የማይለወጥ የመንግስት እና የኢትዮጵያ ህዝቦች ንብረት ነው የሚለውን መርህ የጣሰ ስለመሆኑ፡፡
ሁሉም የኢትዮጵያ ህዝቦች እና ብሄረሰቦች (አርሶ አደሮች፣ ዘላኖች እና የከተማ ኗሪዎች) በእኩልነት የመሬት ባለቤቶች እንደሆኑ ህገመንግስቱ በማያሻማ ሁኔታ ደንግጓል፡፡ ስለሆነም ሁሉም ዜጋ እኩል የሆነ የመሬት ባለቤትነት እና ተጠቃሚነት መብት ያለው ስለመሆኑ ተረጋግቷል ማለት ነው፡፡ ይህ ከሆነ ደግሞ የመሬት ስሪት በገጠር እና በከተማ በልዩነት ሊታይ የሚችል አይደለም፡፡ በገጠር እና በከተማ የመሬት ስሪት ልዩነት አለው ከተባለም ልዩነቱ መምጣት ያለበት አርሶ አደሩ ወይም ዘላኑ የገጠር የእርሻ መሬትና የግጦሽ መሬት ፍላጎት ያለው መሆኑ ሲሆን የከተማው ነዋሪ ደግሞ የመኖርያ ቤት መስርያ ወይም ለተሰማረበት የንግድ ስራ የሚመጥን የድርጅት ቤት መገንቢያ መሬት የማግኘት ፍላጎት ያላቸው መሆኑ ብቻ ነው፡፡
ስለሆነም ከፍ ሲል እንደገለጽነው ህገመንግስቱ በመርህ ደረጃ መሬት የህዝብ እና የመንግስት ነው ካለ በገጠር ያለውን የእርሻ መሬት እና የግጦሽ መሬት ለአርሶ አደሩ እና ለዘላኑ በነጻ እንዲተላለፍ ከፈቀደ በከተማ ለሚኖረው ነዋሪ እና ነጋዴም የቤት መስርያ ቦታ እና ለንግድ ድርጅቱ የሚያስፈልገውን የመስርያ ቦታ በነጻ ወይም ያለክፍያ ሊያገኝ ይገባው ነበር፡፡
እዚህ ላይ በአትኩሮት ልንመለከተው የሚገባው ጉዳይ በአሁኑ ስዓት በሃገራችን በተለይም በከተሞች አካባቢ የኗሪዎች ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ እና አዳዲስ ከተሞች ሳይቀር እየተፈጠሩ የመጡበት ጊዜ ላይ የምንገኝ በመሆኑ ከፍተኛ የሆነ የመኖርያ ቤት እጥረት አለ፡፡ ይህንን ችግር በመገንዘብ መንግስት በተለያዩ ጊዚያት የተለያዩ ፖሊሲዎችን እና የከተማ የመሬት ስሪት አዋጆችን በማውጣት ወደስራ ገብቶ የነበር ቢሆነም የመኖርያ ቤት ችግሩን ለመቅረፍ አልቻለም፡፡ መጠለያ የማግኘት መብት ደግሞ መሰረታዊ መብት በመሆኑ በማንኛውም ምክንያት ሊገደብ የሚችል አይደለም፡፡ በመሆኑም ሁሉም ዜጋ በሃገሪቱ ሁሉም ክልሎች ተዘዋውሮ የመስራት እና በሚሰራበት አካባቢ የመኖርያ ቤት መስርረያ ቦታ የማግኘት መብቱ ሊከበርለት ይገባ ነበር፡፡
ነገር ግን አሁን ባለው ነባራዊ ሁኔታ የገጠር ኗሪው አርሶ አደር ወይም ዘላን መሬትን በነጻ የማግኘት እና በዚሁ መሬቱ ላይ የመኖርያ ቤት የመገንባት እና የቤት ባለቤት የመሆን እንዲሁም በመሬቱ ላይ የግብርና ስራዎችን የማከናወን ኢኮነሚያዊ መብቱ የተረጋገጠለት ሲሆን የከተማው ነዋሪ በተቃራኒው ግን መሬትን ለመኖርያ ቤት መስርያም ይሁን ለንግድ ስራው ማካሄጃ የሚያገኘው በክፍያ ነው፡፡ እዚህ ላይ ልብ ሊሉት የሚገባው ጉዳይ የገጠሩ ኗሪ መሬትን በነጻ የሚያገኘው ቢሆነም ከዚህ ይዞታው ሲነሳም መንግስት ወይም የከተማው ነዋሪ ተገቢው ካሳ የሚከፈለው መሆኑ ሲሆን በመሬቱ ላይ እኩል መብት ያለው የከተማው ነዋሪ በገጠር ለሚኖርው ካሳ እንዲከፍል መደረጉ የፍትሃዊነት ጥያቄን ከማስነሳቱ ባሻገር በከተማ የሚኖሩ ዜጎችን በሃገሪቱ ኢኮነሚ እኩል ተጠቃሚ የመሆንን እና ንብረት የማፍራት መብታቸውን የሚገድብ መሆኑን መገንዘብ ይቻላል፡፡ ከዚህም ባሻገር አሁን ያለው የገጠር መሬትን ለማስተዳደር የወጡ አዋጆች በከተማ ገቢ በሚያስገኝ ስራ ላይ የተሰማራ ማንኛውም የከተማ ነዋሪ ስራውን ትቶ አርሶ አደር ስካልሆነ ድረስ የገጠር መሬት ተጠቃሚ መሆን እንደማይችል የሚደነግግ ሲሆን ከዚህ በተቃራኒ በገጠር የመኖርያ ቤት ሰርቶ የቤት ባለቤት የሆነው እና በእርሻ ስራ የሚተዳደረው አርሶ አደር ግን እንደከተማው ኗሪ በከተማ የመኖርያም ይሁን የንግድ ድርጅት መስርያ ቦታን በህግ በተወሰነ ክፍያ በእኩልነት የማግኘት መብቱ ተረጋግቷል፡፡
ባጠቃላይ አሁን ባለው የኢትዮጵያ የንብረት መብት ህግ የመሬት ይዞታ መብት እና የቤት ባለቤትነት መብት በከተማ እና በገጠር በሚኖረው ህዝብ መካከል ያለው ልዩ ተጠቃሚነት በቀላሉ የሚታይ ባለመሆኑ እና የዜጎችን ፍትሃዊ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥ ባለመሆኑ የሚመለከታቸው ሁሉ ሊያስቡበት ይገባል እያልሁ ማንኛውንም አስተያየታችሁን በስልክ ቁጥር 0918781244/0913380418 እንዲሁም በኦፊሽያል የፌስክ ፔጃችን ኮመንት ላይክ እና ሸር በማድረግ ብትገልጹልን ምስጋናችን ከፍ ያለ ነው፡፡

እኛ የአባቶቻችን ልጆች ነን::
28/02/2019

እኛ የአባቶቻችን ልጆች ነን::

I Respect and Treat Every One In The First Class Way.
20/02/2019

I Respect and Treat Every One In The First Class Way.

Address

Bahar Dar Ghiorghis
BAHIRDAR

Telephone

+251918781244

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Bekalu Molla Agegnehu Consultant & Attorney at Law posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Bekalu Molla Agegnehu Consultant & Attorney at Law:

Share